fredag 26. januar 2018

የወልድያው ግጭት፤ የአቶ ዘርዓይ አስገዶም ንግግር፤ ቴዲ አፍሮ —ዶቼቬሌ አማርኛ

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚዎች ሳምንቱን ያሳለፉት በወቅታዊ ጉዳዮች ተጠምደው ነው፡፡ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የነበሩ ተቃውሞዎች ከፍተኛ ትኩረት ስቧል፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ዋና ኃላፊ በአንድ ስብሰባ ላይ ያደረጉት ንግግርም መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ዝግጅት የብዙዎች መወያያ ነበር፡፡
የእስረኞች ፍቺ፣ የጥምቀት በዓል፣ የቴዲ አፍሮ የሙዘቃ ዝግጅት በማህበራዊ መገናኛ ተጠቃሚዎች ዘንድ የመደሰት እና የመዝናናት ስሜትን አረብቦ ነበር የከረመው፡፡ ይህ ስሜት ሳይቀዘቅዝ ነበር ከወደ ወልድያ የተለመደው አሳዛኝ የተቃውሞ እና ሞት ዜና የተሰማው፡፡ ቅዳሜ ጥቅምት 12 ቀን 2010 ዓ.ም በጥምቀት ማግስት የሚውለውን የቃና ዘገሊላ በዓልን ለማክበር አደባባይ በወጡ የወልድያ ከተማ ነዋሪዎች እና በጸጥታ ኃይሎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት ሰዎች መሞታቸው እና መቁሰላቸው በአጭር ጊዜ ከዳር ዳር ተዳረሰ፡፡
Agazi force (Credit: DW)
ግጭቱ የተቀሰቀሰው በዓል አክባሪዎቹ እንዳይጨፍሩ በጸጥታ ኃይሎች ከተከለከሉ በኋላ መሆኑ ተነገረ፡፡ ከአዲስ አበባ ውጭ የኢንተርኔት ግንኙነት በመቋረጡ ምክንያት በግጭቱ ምን ያህል ሰው እንደሞተ እና እንደቆሰለ ትክክለኛ መረጃ ማግኘት አዳጋች ቢሆንም ብዙዎች ሀዘናቸውን እና ቁጣቸውን ገለጹ፡፡ በማግስቱ የጸጥታ ኃይሎች ለቀብር ከወጡ ሰዎች ጋር መጋጨታቸው ብዙዎችን «የሰው ግድያ ማብቂያው የት እንደሆነ?» እንዲጠይቁ አድርጓቸዋል፡፡ 
በተለይ የሰሜን ወሎ ዞን የፖሊስ ኃላፊ በክልሉ እና ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ቀርበው የሰጡት ገለጻ ለብዙዎች ዋነኛ መነጋገሪያ ነው የሆነው፡፡ «ሰዎች መንግሥት ላይ ተቃውሞ ሲያሰሙ እንዴት በጥይት ለመቆጣጠር ይሞከራል?» ሲሉ የሞገቱ በርካቶች ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል አንዱ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ነው፡፡ ዲያቆን ዳንኤል «ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት ስንት ወልድያ ያስፈልገናል?” ሲል ረቡዕ ዕለት በፌስ ቡክ ገጹ ባስነበበው ጽሑፉ ጠይቋል፡፡ 
“የጸጥታ ኃይሎች በወልድያ ነዋሪዎች ላይ የፈጸሙት ግድያ በምንም ዓይነቱ መመዘኛ ከውግዘት የሚያመልጥ አይደለም፡፡ በኃይል የሚፈታ ችግር እንደሌለ መንግሥት ራሱ ከማናችንም በላይ የሚያውቀው ነገር ነው፡፡ የዛሬውን መንግሥት የመሠረተው ኢሕአዴግ ወደ በረሓ እንዲገባ ያደረገው ደርግ ችግሮችን ሁሉ በውይይት ሳይሆን በኃይልና በኃይል ብቻ ለመፍታት በመፈለጉ መሆኑን በየግንቦት ሃያ በዓሉ ስንሰማው ኖረናል፡፡ ለሰው የሚጠላውን ኃጢአት ራሱ ከመሥራት በላይ ውድቀት የለም፡፡ በዓሉ የአንድ ቀን በዓል ነው፡፡ ቢታገሡት ያልፍ ነበር፡፡ ሌላ ችግር ይከሰታል ተብሎ ከተጠረጠረና መረጃ ከተሰበሰበ እንኳን አያሌ የችግር መፍቻ አማራጮች ነበሩ፡፡ ‹የጸጥታ ችግርም› ‹የጸጥታ ኃይሎች›ም እኛ ሀገር ብቻ አይደለም ያሉት፡፡ ባለ ሥልጣኖቻችንም ለልምድ ልውውጥ በየሀገሩ ሲሄዱ ነው የሚኖሩት፡፡ ምነው ታድያ የተሻለ አማራጭ መማር አቃታቸው?
እንዲህ ላሉ ችግሮችስ ጥይት መፍትሔ አለመሆኑን ባለፉት ሁለት ዓመታት ሀገሪቱ ያለፈችበት ሁኔታ ብቻ እንዴት አያስተምረንም? ይልቅ ለምን የችግሩን ምንጭ ለማድረቅ አንሠራም? ‹የሚያስለቅስ ነገር ነግሮ አታልቅስ ይለኛል› የሚል የትግርኛ አባባል አለ፡፡ ሕዝቡ ለምን ሆድ ባሰው? ወጣቶቹ ለምን ተቃወሙ? የዚህ ሁሉ ችግር ምንጩስ ምንድን ነው? ብሎ መሥራት አይሻልም፡፡ ለምን ሕዝብን ከሕዝብ ወገንን ከወገን የሚያጋጭና ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ቂም እንዲቋጠር ይፈለጋል? ለምንስ የዘርና የጎሳ መልክ እንዲይዝ ይፈለጋል? ወንጀለኞችስ ለምንድን ነው በጎሳ ካባ ውስጥ እንዲደበቁ ሁኔታዎች የሚመቻቹት? ከመሬት መንቀጥቀጡ (shock) በላይ ድኅረ መንቀጥቀጡ (aftershock) ውጤቱ የከፋ መሆኑን አናውቅምን? ችግሩንስ ከመሠረቱ ለመፍታት ስንት ወልድያ ያስፈልገናል?”
የማነ ምትኩ የተባሉ የፌስ ቡክ ተጠቃሚም ተመሳሳይ ይዘት ያለው አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ “በዓል ነው። በዓሉ በየቤትህ ተቀምጠህ የምትፈስክበት ዓይነት አይደለም። ማህበራዊ በዓል ነው። ሰው ተሰብስቦ ያከብረዋል። አጋጣሚውን ተጠቅመው የታፈኑ ድምፆች ይደመጡበታ። የግድ ነው። አፈና በበዛበት ስርዓት ህዝብ እነዚህን አጋጣሚዎች ይጠቀማል። አጋጣሚውን ተጠቅሞ ህዝብ ብሶቱን ሲገልፅ መሰማት ነበረበት። ለመሆኑ [ኢህአዴግ]፥ ህገመንግስታዊ መብታቸውን ማክበርስ ተወው፡፡ የተሰበሰብን ሁሉ በጥይት በትነህ እስከመቼ ትዘልቀዋለህ? አስለቃሽ ጭስ፥ ውሃ፥ ወዘተ የሚባሉ ሰልፍ በታኝ ነገሮችን መጠቀም የምትጀምረው መቼ ነው? ጥይትስ ቢሆን ለማስፈራራት ወደ ሰማይ ይተኮሳል እኮ? አስር የተኩስ እሩምታ ከተሰማ ዘጠኝ የሚወድቀው እስከመቼ ድረስ ነው? ይህ እኮ ጦር ሜዳ አይደለም፡፡ ከዜጎች ህይወት ይልቅ ጥይት እንዳይባክን መጨነቅህ ለምን ይሆን?” ሲሉ ጠይቀዋል።
ዮናስ ሐጎስ በበኩላቸው “በወልድያው ተቃውሞ እንደታየው አይነት በአንድ ብሔር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መዘዙ ብዙ ነው” የሚል መልዕክት ያዘለ ጽሁፍ በፌስ ቡክ ገጻቸው አስፍረዋል፡፡ “መንግስትንና ስርዓትን መቃወም አንድ ነገር ነው። ተቃዋሚዎች ፖሊስ ጣቢያ ሊያጠቁ፣ የመንግስት ተቋማትን ሊያጠቁ ይችላሉ። ይሄ በየትኛውም ዓለም ላይ በሚካሄድ ተቃውሞ የተለመደው አሰራር ነው። ግን የሰውን ስም እየለዩ በብሔር ብቻ ተንተርሰው የግለሰብ መኖርያዎችንና የንግድ ተቋማትን ማጥቃት ሲጀመር መንገዳችን ወዴት እንደሆነ በግልፅ እያሰመርን መሆኑ ይታወቅ። በሕዝብ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የመንግስት አሊያም የስርዓት ተቃውሞ ሳይሆን የእርስ በርስ ጦርነት መነሻ ደወል ነው። ይሄ ፍጥጥ ያለ ሐቅ ነው” ብለዋል፡፡ 
ጉደታ ገለልቻም “ነገሮች እንዳይወሳሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልገናል” በሚል ርዕስ ተከታዩን ማሳሰቢያ ረቡዕ ዕለት በፌስ ቡክ አስተላልፈዋል፡፡ “ሰሞኑን በአማራ ክልል ወልዲያ አካባቢ በደረሰው አሰቃቂ ግድያዎች ምክኒያት ከደረሰብን ጥልቅ አዘን ሳናገግም ሌላ ግድያ በኦሮሚያ ክልል መቂ አካባቢ መፈፀሙን ሰማን! በጣም ያሳዝናል በጣምም አዝነናል! ጎበዝ ምን ይሻላል? ነገሮቻችን አንድ እርከን ወደ ፊት ይጎዙና ሁለት እርከን ወደ ኋላ ይመለሳሉ! የትግላችን አቅጣጫ ጠራ ብለን ሰናበቃ ነገሮቹ ተመልሰው ይወሳሰቡብናል! ለማንኛውም ማንም ሆነ ማን ከፌዴራልም ሆነ ከክልል ውድ የሰው ልጅ ላይ አነጣጥሮ በመተኮስ የሕይወት መጥፋት እና የአካል ጉዳት ያደረሱት አካላት ጉዳያቸው ተጣርቶ በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ ለመሳሰብ እንወዳለን!”
አቶ ጉደታ እንደጠቀሱትም በመቂ አቅራቢያ ባለችው የዓለም ጤና ከተማ ማክሰኞ ዕለት ሰዎች መገደላቸው በማኅበራዊ መገናኛዎች መረጃው ተሰራጭቷል፡፡ የዓለም ጤናው ክስተት መነሾ በከተማይቱ ያሉ ተማሪዎች በወልድያ እና ሰኞ ዕለት በሞያሌ የሞቱ ሰዎችን ለመዘከር ሲሞክሩ ነው ተብሏል፡፡ በቆቦ ከተማም እንዲሁ በወልድያ ሰዎች መገደላቸውን የተቃወሙ ሰዎች ህይወት መጥፋቱ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴ ተጠቃሚዎች ዘንድ ሀዘንን አስከትሏል፡፡ በቆቦ ረቡዕ የተጋጋለው ተቃውሞ እና ግድያው ሐሙስም ቀጥሎ እንደዋለ በቪዲዮ እና ፎቶ ጭምር ተደግፈው በማህበራዊ ድገጾች የተሰራጩ መረጃዎች አሳይተዋል፡፡ 
በኢትዮጵያ አልበርድ ያለው የተቃውሞ እና የሰዎች ሞት በሀገሪቱ ያሉ መገናኛ ብዙሃንን እና ባለስልጣናትንም ለውይይት በአዳራሽ አሰባስቦ ነበር፡፡ «በወቅታዊ ሃገራዊ ሁኔታ የብሮድካስት ሚዲያ አዝማሚያ» በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ይሄው ውይይት የተካሄደው ጥር 12 ቀን 2010 ዓ.ም ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ኃላፊ አቶ ዘርዓይ አስገዶም በውይይቱ ወቅት የሰነዘሩት ሀሳብ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ አቶ ዘርዓይ በውይይቱ መገናኛ ብዙሃንን በስም እየጠሩ እንዲህ ወርፈዋል፡፡ 
“ከቴሌቪዥን ሁሉም ሞኒተር ያደረግናቸውን እዚህ ማቅረቡ ሌላ ትርጉም እንዳይሰጠው ስጋት አለኝ፡፡ አንዳንዶቹን ላቅርብ፡፡ ከሚሊኒየም አዳራሽ በቅርቡ የተላለፈው የኦሮሞ ወጣት ተነስ እና አዲስ አበባ አራት ኪሎ ግባ የሚለው የሃጫሉ [ሁንዴሳ] ዘፈን እንዴት በቀጥታ በህዝብ መገናኛ ብዙሃን ይተላለፋል? ጸረ- ህዝብ የሆነ ዘፈን ነው፣ የኦሮሞን ህዝብ ከሌላው ህዝብ ጋር የሚያጋጭ ነው፡፡ ዘፈኑ ፈረስህን ቀልብ፣ ተዘጋጅ፣ ታጠቅ፣ አራት ኪሎ ግባ ነው፡፡ የኦሮሚያ ቴሌቪዥን ቀጥታ ለቀቀው፡፡ በነጋታውም ደገመው፡፡ ያ ዘፈን ሲለቀቅ ከፍተኛ ስጋት ነው የፈጠረው፡፡ 
አማራ ቴሌቪዥን የወልቃይት እና የጎንደርን ጉዳይ እንዴት ነው የዘገበው? ምን ያህል ጊዜ ነው የዘገበው? ጎንደሬዎች መቀሌ ሄደው [ትግሬዎችን] መልሱልን ሲሉ ለምንድነው ያልዘገበው? ተዘጋጅቶ ተልኮለት እያለ፡፡ ባንዲራ ሲቃጠል ምን ሰራ የአማራ ቴሌቪዥን ?ህገመንግስት ሲቃጠል ማለት ነው በሌላ አነጋገር፡፡ በትልቁ ኢቢሲ ሞኒተር አድርገን የተረዳነው ኢቢሲ ሀገር ስትበጣበጥ የዳር ተመልካች ሆኖ ነው የሰነበተው፡፡ መረጃ አይሰጥ፣ ወይ አይተነትን፡፡ ሁነቶችን ብቻ ነበር ሲዘግብ የነበረው” ሲሉ አቶ ዘርዓይ ለተሰብሳቢዎቹ ተናግረዋል።
ይህን አመልክተው በማኅበራዊ መገናኛዎች ከተሰጡ አስተያየቶች፤ ኡቱባ ጋዲሳ በፌስ ቡክ “የሃጫሉን ዘፈን ለማስተርጎም የወጣችው በጀት መቶ ሺህ ትሆናለች” በማለት በቀልድ ይንደረደራሉ፡፡ “ወጣቱ የተመከረው አራት ኪሎ ዩኒቨርስቲ እንዲገባም ነው፡፡ ቄሮ ተምሮ ሀገሩን እንዲያሻሽል ነው” ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ አሞን ግርማ በበኩላቸው “አቶ ዘርዓይ አስገዶም በእኛ ግምገማ ሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ የድሮዋን ኢትዮጵያ፣ የጠፋችውን ነው የሚመስለው፡፡ ያሁኗ ኢትዮጵያ እንዳልጣማቸው በግልጽ ነው የሚታየው ብለዋል፡፡ እኔ ደግሞ ያሁኗ ኢትዮጵያ እንዳልጣመችን ስላወቁልን ብቻ ደስታችን የላቀ ነው” ሲል ተሳልቋል፡፡ የጋዜጠኝነት መምህሩ ዳግም አፈወርቅ “የሸገር ጥፋቱ ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን አብዝቶ መጨነቁ ነው” ብሏል፡፡ ስለ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እና ኃላፊው ደግሞ በፌስ ቡክ ገጹ ተከታዩን ጽፏል፡፡
“በቅርቡ በባለስልጣኑ የሚሰጡ መግለጫዎች የሚዲያ ህጎችን እየጠቀሱ የሚዲያዎችን ጥፋት ከመዘርዘር ይልቅ ማስፈራሪያ ይበዛባቸዋል፡፡ ይሄ ደግሞ የተለመደውን አይነት ህጋዊ ሳይሆን አስተዳደራዊ እርምጃ (administrative measures) ለመውሰድ እያኮበኮቡ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ጋዜጠኛ በስራው በሚታሰርባት እና በሚሰደድባት ሀገር፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ሀላፊዎች የህዝቡን የማወቅ መብት (the public’s right to know) ከቁብ ሳይቆጥሩ ጋዜጠኞችን መረጃ በሚከለክሉባት ሀገር፣ ነፃ ድምፆች እየጠፉ የመንግስት ሚዲያ እና የመንግስት ተቆርቋሪ ሚዲያ በበዛባት ሀገር ባለስልጣኑን የሚያስጨንቀው ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ችግር በሚዲያዎች መዘገቡ ነው፡፡ ያሳዝናል!!! በፖለቲከኛ ሳይሆን በባለሙያ የሚመራ፣ ለፓርቲ ወይም ለመንግስት ጥቅም ሳይሆን የህዝብን የማወቅ መብት ለማስከበር የቆመ፣ በሚዲያ ላይ ያለው የመንግስት ጠቅልሎ የመያዝ (government monopoly) ቀንሶ ወይም ጠፍቶ ነፃ ድምፆች እንዲበዙ የሚሰራ የሚዲያ ተቆጣጣሪ ተቋም እንዲኖር እመኛለሁ” ሲል ደምድሟል፡፡ 
የሕግ ባለሙያው በትሩ ዲባባ በሕገ መንግስቱ የፌደራል መንግሥት ስልጣን እና ተግባር በተዘረዘረበት አንቀጽ 51 የብሮድካስቲንግ ባለስልጣን በግልጽ አለመጠቀሱን በፌስ ቡክ ጽሁፉ አንስቷል፡፡ “ከህዝብ የተሰረቀ ስልጣን፣ የግለሰብ ስልጣን ነው” ሲል የሚከራከረው በትሩ ስለ ባለስልጣኑ እንዲህ ይላል፡፡ “የብሮድካስቲንግ ስልጣን የክልሎች ስልጣን ነው። ታዲያ በፌዴራል ደረጃ እራሱን ‘ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን’ ብሎ የሚጠራው አመጣጡና አመሰራረቱ ሕገ መንግስታዊ መሰረት የለውም። ከክልሎች የተሰረቀ ስልጣን ነው። የተሰረቀ ስልጣን ብቻም ሳይሆን ክልሎች ላይ ስልጣን አለኝ ይላል፡፡ ‘እንዲህ ብለህ ፃፍ፤ እንዲህ ካልተናገርህ’ ይላል። ከባዶ ተነስተው ወቃሽ!” ሲል ይተቻል፡፡
Teddy Afro
የዛሬው መሰናዷችንን የምንቋጨው በድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጉዳይ ይሆናል፡፡ አዲሱን አልበሙን ካወጣ ወዲህም ሆነ ላለፉት አራት ዓመታት በሀገር ውስጥ የሙዚቃ ዝግጅት እንዳያካሂድ ተከልክሎ የነበረው ቴዲ አፍሮ ባለፈው እሁድ በባህር ዳር ከተማ አድናቂዎቹን በሥራው አዝናንቷል፡፡ የሙዚቃ ዝግጅቱ በዋዜማው በወልድያ የተከሰተው ግጭት እና ሞት ጥላ አጥልቶበታል፡፡ የተወሰኑ የማኅበራዊ መገናኛ ተጠቃሚዎች እንደውም ቴዲ በሀዘኑ ምክንያት የሙዚቃ ዝግጅቱን እንዲሰርዝ እስከመጠየቅ ተጉዘዋል፡፡ ይህን የታዘበ የመሰለው ጸሀፌ ተውኔቱ ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ ሁኔታውን በራሱ በድምጻዊ እውቅ ዘፈን ርዕስ “እያነቡ እስክስታ” ሲል ገልጾታል፡፡ 
ብዙ የተባለለት የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ዝግጅት በሰላም ቢጠናቀቅም በማኅበራዊ ድረገጾች የመነታረኪያ አጀንዳ ሆኖ ቆይቷል፡፡ የንትርኩ ማጠንጠኛ ደግሞ ፖለቲካዊ ይዘት ያለውን “ጃ ያስተስርያል የሚለውን ዘፈኑን ለምን በመድረክ ሳይጫወት ቀረ” የሚል ነው፡፡ ብሌን መስፍን ይህን ስሜት የሚያንጸባርቅ ጽሁፏን በፌስ ቡክ አካፍላለች፡፡ 
“ቴዲን ከሌሎች ዘፋኞች ልዩ ያደረገው በድፍረት ይሄንን ስርዓት መናገር መቻሉና ታሪክን ማውሳቱ ነው። ደፍሮ ይሄንን ስርዓት በዋናነት የነቀፈበት ዘፈኑ ደግሞ ‘ጃ ያስተሰርያል’ ነበር፡፡ የታወቀበትን፣ የተገፋና የታፈነ ሕዝብ ልብ ውስጥ ዙፋን ያሰጠውን ይሄን ዘፈን በልመና እንኳ መዝፈን የተሳነው ለምን ይሆን? “የሕዝብ” ልጅ ቴዲ፣ ልቡ ለደማው ሕዝብ፣ በአንድ ዘፈን ሊያውም በራሱ ዘፈን የእናንተው ነኝ ቢል ምን ነበረበት? ለ‘ማራኪዬ’ እና ለ‘ሳማት ሳማት አለኝ’ ሚሊኒየም አዳራሽ ጥጋብ ልባቸውን ያሳበጣቸውን ባለጊዜዎች ማስጨፈር ማን ከልክሎት፡፡ ወገኑ እየረገፈ ዳንኪራ አምሮት የሄደ የለ፤ የልቤን ይናገርልኛል ብሎ

mandag 22. januar 2018

ህወሃት ለአገርና ለህዝብ ጥቅም ብሎ መታደስ የሚችል ድርጅት አይደለም። ትግሉ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል (የአርበኞች ግንቦት 7 ርዕስ አንቀጽ)

የአርበኞች ግንቦት 7 ርዕስ አንቀጽ
Patriotic Ginbot 7 logoህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የመንግሥት በትረ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት 1983 ጀምሮ ጠባብ አላማውን ለማሳካት ሲል በርካታ ወንጀሎችንና ክህደቶችን በአገርና በወገን ላይ ሲፈጽም የኖረ ድርጅት ነው። ከነዚህ ወንጀሎች አንዱና ምናልባትም ለረጅም ጊዜ ተንሰራፍቶ ሥልጣን ላይ ለመቆየት ያስቻለው እርስ በራሳችን እንዳንተማመን በመካከላችን የዘራው የጥላቻ ፖለቲካ ነው። በህወሃት የጥላቻ ፖለቲካ መሠረት ኢትዮጵያችን አያት ቅድሜ አያቶቻችን በጋራ በከፈሉት መስዋዕትነት የተመሠረተችና ከተከታታይ የባዕድ ወረራ ነጻነቷን ጠብቃ የኖረች አገር ሳትሆን አንድ ማህበረሰብ ሌለውን ቅኝ በመግዛት የፈጠራት አገር ነች። ይህ ቅኝ ገዥ ሃይል ደግሞ ሥልጣን ላይ የተፈራረቁ መንግሥታት እስከዛሬ አገራችን ውስጥ ላደረሱት የአስተዳደር በደሎች ሁሉ ተጠያቂ ነው። ላለፉት 26 አመታት የመንግሥት ተቋማትና ሚዲያዎች በቅንጅት ሲያስተምሩና ሲቀሰቅሱ የኖሩት እንዲህ አይነት መሠረት የሌለውን መርዘኛና ከፋፋይ ቅስቀሳ ህብረተሰቡ ውስጥ ለማሰረጽ እና በአገራችን ላይ የጋራ ኩራት እንዳይኖረን የማድረግ ደባ ነው። በዚህ አፍራሽ ፕሮፖጋንዳ ምክንያት በኢትዮጵያዊነታቸው እንዲሸማቀቁ ተደርገው ያደጉ ፤ በደረሰባቸው የማንነት ቀውስ አዲስ ማንነት ፍለጋ የህገመንግሥቱን አንቀጽ 39 ተስፋ የሚያደርጉ ዜጎች ቁጥር በቀላሉ የሚገመት አልሆነም። ሌላው ቀርቶ በጥቁር ህዝቦች ሁሉ ዘንድ እንደ ነጻነት አርማ ተደርጎ የሚታየው አረንጓደ ብጫ ቀይ ባንድራችን የኩራታችን ምልክት ሳይሆን የባርነት ምልክት ተደርጎ እንዲታይ ያልተሠራ ሻጥር የለም። ለአንድነታችንና ለሉአላዊነታችን ከፍተኛ ዋጋ የከፈሉ ጀግኖች አባቶቻችን ታሪክ ተንቋሾ እንዲናፍርባቸው ተደርጎአል። በአመታት ጥረት የተገነቡ ብሄራዊ ተቋሞቻችን እንዲፈርሱና አገራቸውን በቅንነት ሲያገለግሉ የነበሩ ብዙ ሺዎች እንዲባረሩ ተፈርዶባቸዋል። ብሄራዊ መከታችን የነበረው የቀድሞ ጦር በፋሽስትነት ተፈርጆ እንዲፈርስና ከአምስት መቶ ሺ በላይ አባላቱ ለልመናና ለጎዳና ተዳዳሪነት እንዲዳረጉ ተደርገዋል። ኢትዮጵያዊ ሪህራሄና ወገንተኝነት በጎደለው ጭካኔ በብዙ መቶ ሺ የሚቆጠሩ ዜጎች ተወልደው ካደጉበት ቄያቸው እንዲፈናቀሉና መሬታቸው ለባዕዳንና ለሥርዓቱ አገልጋዮች እንዲከፋፈል በማድረግ ከፍተኛ ሃብት ተካብቶበታል። ይሉኝታና ሃፍረት በሌለው ጋጥ ወጥነት አብዛኛውን የመንግሥት ሠራተኛና የግል ንግድ ባለቤቶችን ከሥራቸው በማፈናቀል በምትኩ የአንድ ቡድን አባላት በበላይነት የሚቆጣጠሩት የኢኮኖሚና የፖለቲካ ሥልጣን ተፈጥሮአል። ይህንን ግፍና ኢፍትሃዊ አሠራር የተቃወሙትን ዜጎች ሁሉ በገቡበት ገብቶ ለማጥፋት በተወሰደው እርምጃ በጠራራ ጸሃይ በርካታ ዜጎች በየአደባባዩ ተገድለዋል ፤ ታስረዋል ፤ ተገርፈዋል ፤ አገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ተደርጎዋል። ከግዲያ ተርፈው ዛሬ ድረስ በየ እስር ቤቱ የሚማቅቁና ፤ እዚያ እስር ቤት ውስጥ በተፈጸመባቸው ድብደባ አካል ጉዳተኛ ሆነው የሚሰቃዩ ዜጎች ቁጥር ስፍር የለውም።
ላለፉት ሶስት አመታት አገራችን ውስጥ እየተቀጣጠለ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ ዋና አላማ ህወሃት የማእከላዊውን የመንግሥት ሥልጣን በመቆጣጠር ላለፉት 26 አመታት በህዝባችንና በአገራችን ላይ ሲፈጽማቸው የኖሩትን ወንጀሎችና ግፎች ሁሉ በማስቆም ነጻና ገለልተኛ በሆነ የምርጫ ሥርዓት ህግ ህዝብ በሚመርጠው መንግሥት እንዲተዳደር ለማድረግ ነው። እንዲህ አይነት የመንግሥት ሥርዓት አገራችን ውስጥ ከተመሠረተ ሂልውናው እንደሚያከትም የተረዳውና እስከዛሬ ከህዝብና ከአገር ስለዘረፈው ሃብት ብቻ የሚጨነቀው የህወሃት አመራር ይህንን የህዝብ ትግል ከተቻለ ለማስቆም ካልሆነ ደግሞ አቅጣጫ ለማስቀየር ይጠቅመኛል ብሎ ያሰበውን ሁሉ ስትራቴጂ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ነው። አዲስ አበባ ላይ በቅርቡ ተካሂዶ ከነበረው የኢህአደግ ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ቦኋላ “ለመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታና ለብሄራዊ መግባባት ሲባል የፖለቲካ እስረኞችን እፈታለሁ፤ ከተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ጋር እነጋገራለሁ” የሚለው ሁሉ ለፈፋ የዚያ ስትራቴጂ አካል ነው።
በአርበኞች ግንቦት 7 እመነት ህወሃት ስለ ፖለቲካ እስረኞች መፈታት ጉዳይ የሚያወራው አገራችንን ከከተታት ቀውስ ለማውጣት ፈቅዶና ተጨንቆ ሳይሆን ከውስጥና ከውጪ የተቀሰቀሰበትን ተቃውሞ ደፍጥጦ በአሸናፊነት ለመውጣት የሚያስፈልገውን ጊዜ ለመግዛት ያስችለኛል ብሎ አስልቶ ነው። ጠባብ አላማውን ለማሳካት ህወሃት እንዲህ አይነት ዜደ ሲጠቀም የመጀመሪያው አይደለም የመጨረሻውም ሊሆን አይችልም። ምርጫ 97 ላይ ደርሶበት ከነበረው ተመሳሳይ ውጥረት በአቸናፊነት ለመውጣት ምዕራባዊያን ወዳጆቹ ፊት ከጸሃይ በታች ከምድር በላይ ባሉ ነገሮች ሁሉ እደራደራለሁ ብሎ ምሎ ተገዝቶ በአገር አቀፍ ደረጃ ተጠርቶ የነበረውን ተቃውሞ ሰልፍ እንዲሰረዝ ካስደረገ ቦኋላ እንዴት አድርጎ ስጋት የሆኑበትን የቅንጅት መሪዎችና ደጋፊዎች እንዳጠፋ እናውቃለን። ህዝብ ለማዘናጋትና የተቀሰቀሰበትን ተቃውሞ ለማርገብ ሲባል ይፋ በሆነው የፖለቲካ እስረኞች መፈታት ጉዳይ የአገዛዙ ባለሥልጣናት የሰጡት እርስ በርሱ የሚጣለዝ መግለጫ በጉዳዩ ላይ በመካከላቸው ምንም መግባባት እንደሌለ አሳብቆባቸዋል።
በአገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ማንኛውም ሰው በፖለቲካ እምነቱና አመለካከቱ እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ መታሰሩ ህገወጥ እርምጃ እንደሆነ ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 ያምናል። በዚህም ምክንያት ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱና ዜጎችን ያለጥፋታቸው በማሰር የሚያሰቃዩ ወንጀለኞች ሁሉ ለህግ እንዲቀርቡ ሲጠይቅና ሲታገል ቆይቶአል። አሁንም ይታገላል። አርበኞች ግንቦት 7 የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ በተደጋጋሚ የሚጠይቀው የነርሱ መፈታትና አላማቸውን በነጻነት ማራመድ መቻል ለሚታገልለት የዲሞክራሲ ሥርዓት ከፍተኛ አስተዋጾ ስላለው እንጂ ግቡ ስለሆነ አይደለም። ህወሃት በዚህ ጉዳይ እንደማይስማማ ግልጽ ነው። ስለዚህ በአንድ በኩል እስረኞችን ነጣጥሎ በመፍታት የተነሳበትን ህዝባዊ ተቃውሞ አከሽፋለሁ ብሎ ያስባል በሌላ በኩል ደግሞ በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን ጸጥታ ሃይሎችን በሙሉ በአንድ ኮማንድ ሥር በማስገባት የተነሳበትን ህዝባዊ ተቃውሞ እጨፈልቃለሁ ብሎ እንቅስቃሴ ጀምሮአል። ሁለቱም ስልቶች ካልተሳኩ ደግሞ ያለ የሌለ ሃይሉን ይዞ ትግራይ ውስጥ በመመሸግ የተቀረውን ህዝብ እርስ በርሱ አባላለሁ ብሎ ያስባል።
አርበኞች ግንቦት 7 ከአሁን ቦኋላ የትግራይ ምድርም ሆነ የአዲስ አበባው ሚኒልክ ቤተመንግሥት የህወሃት ዋሻ ሆኖ የህዝባችን መከራና ስቃይ የሚቀጥልበት ሁኔታ እንዳይኖር አቅም በፈቀደለት ሁሉ አጥብቆ ይታገላል። ያታግላል። አማራና ኦሮሞን እሳትና ጭድ በማድረግ ኢትዮጵያን እስከወዲያኛው ለመግዛት የነበረው የአመታት ምኞት ዳግም ላያንሰራራ ተንኮታኩቶ ወድቆአል። የእስረኞቻችን በከፊልም ሆነ በሙሉ መለቀቅ ህዝባችን ለሥር ዓት ለውጥ የጀመረውን ሁለገብ ትግል ለአፍትም ቢሆን አያስቆምም።
በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በኢህአደግ ስብሰብ ውስጥ ሆናችሁ የወያኔን ጠባብ አጀንዳ ስታስፈጽሙ የኖራችሁ የህዝብ ወገኖች ሁሉ! እየታሰርን ፤ እየተገረፍንና ፤ እየተገደልን ለዚህ ያደረስነውን የህዝብ ትግል በመቀላቀል ፍትህ እኩልነትና ነጻነት የሰፈነባት ዲሞክራሲያዊት ኢገር በጋራ እንድንመሠርት ወገናዊ ጥሪ ቀርቦላችኋል ። ከህዝብ አብራክ የወጣህ የአገሪቱ መከላኪያ ሠራዊት ፤ የፖሊስና ደህንነት አባላት ሆይ! ለሥርዓት ለውጥ እየተካሄደ ያለው ትግል አንተን ከአንድ አናሳ ቡድን መጠቀሚያነት አውጥቶ በህገመንግሥቱ የተሰጠህን አገራዊ አንድነት የማስጠበቅ ሃላፊነትህን በነጻነት እንድትወጣ እንጂ አንተን በበቀልና በጥላቻ የመበተን አይደለም። ስለዚህ ወያኔ እኔ ከሌለሁ የሚመጣው መንግሥት ይበትነሃል ፤ እንደ ቀድሞ ጦር ልብስህን አንጥፈህ ለልመና ትዳረጋለህ የሚለውን መሰሪ ቅስቀሳና ፕሮፖጋንዳ ሰምተህ በገዛ ወገንህ ላይ አትተኩስ፤ አትግደል ፤ አትሰር። ይልቁንም የያዝከውን መሣሪያ በቡድን ተቧድነው አጥንትህንና ደምህን በመጋጥ በከበሩ የህወሃት አለቆችህ ላይ አዙርና የአገዛዝ ዕድሜውን አሳጥር። ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 ምን ጊዜም ከጎንህ ይቆማልና ዛሬውኑ ትግላችንን ተቀላቀል።
ድል ለኢትዮጵይ ህዝብ!

ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ ኦስሎ በደማቅ ተከናወነ

የዲሞክራሲያዊ ስርዓት  ምስረታን በሀገራችን እውን ለማድረግ በሚደረገው ርብርብ ትግሉ የሚፈልጋቸውን የድጋፍ ዘርፎች እያጠና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ላይ ያለው እና መቀመጫ ዋና ፅህፈት ቤት በኦስሎ ኖርዌይ  በማድረግ  እየሰራ የሚገኝው  የድሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጭ ድርጅት በኖርወይ  በትናትናው ዕለት ማለትም በ19.01.2018 እኤአ የጠራው ሰላማዊ በደማቅ ሁኔታ ተከናዉኗል።
በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሶስት መሰረታዊ ነጥቦችን በማንሳት መልእክት ተላልፏል ፡
  1. የሃገራችን ህዝብ ለነፃነቱ እና የዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲኖረው ከዘረኛው አገዛዝ ጋር የሞት ሽረት ትንቅንቅ ላይ ባለበት በዚህ ወቅት የኖርዌይ መንግሥት ከኢትዮጵያ አምባ ገነን ገዥዎች ጋር እያደረገ ያለው የዲፕሎማቲክ ግንኙነት እና የገንዘብ ድጋፍ በማቆም ከህዝብ ጎን እንዲቆም ለማሳሰብ :
  2. በሊቢያ እና በመካከለኛዉ ምስራቅ ሃገራት የሚደረገውን የባሪያ ንግድ ለማስቆም የኖርዌይ  መንግስት የበኩሉን ስራ እየስራ ያለመሆኑን ለመቃወም ;
  3. በኖርዌይ የምገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የሚደረገውን የማዋከብ እና ያለ ምንም የመጉዋጉዋዣ ሰነድ እና ፍቃደኝነት የሚደረገውን ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ  ተግባር አጥብቆ ለመቃወም ሲሆን ::
ሰልፉም ከመሃላ ከተማ ያረባነቶርጌት ተጀምሮ  የኖርዌይ ፓርላማ ፊትለፊት ተሰላፊው ድምፁን በማሰማት ወደ ውጭ ጉዳይ ቢሮ በማምራት በዚያ ተቃውሞን በከፍተኛ ድምፅ ካሰማ በሁኋላ የተዘጋጀውን  ደብዳቤ በድርጅታችን ፅሃፊ ወይዘሪት ኤልሳቤጥ ግርማ አማካኝነት  በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  የአፍሪካ ቀንድ  እና ምእራብ  አፍሪካ ከፍተኛ አማካሪ  ማራታ ዲሩድ ተረክበዋል።  ተወካይዋ ጉዳያችንን በጥልቀት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  በኩል እደሚመልከቱት እና መልሳቸውን በደብዳቤ እንደሚያሳውቁን ገልፅውልናል ::
በሰልፉ መዝጊያ የሰልፉ አስተባብስሪ አቶ ፍቅሬ አሰፋ ለታዳሚው ባደረጉት ንግግር በሃገራችን እና በመላው አለም በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለው መከራ እና በደል ምንጩ  በሃገራችን የሚገኝው አገዛዝ ሲሆን ይንን ጠባብ ገዥ መደብ በውስጥም በውጭም በሚደረግ ትግል አዳክሞ ማፍረስ እና በሁሉም የሁሉ የሆነ የዲሞክራሲያዊ ስርዓት በመስረት ዛሬ ነጌ የማይባልበት ጉዳይ በመሆኑ ተናግረዋል :: ድርጅታቸው ለዝሁ ኢትዮጵያን የመታደግ አላም ከሚታገሉ ሃይላት ጋር በትብብር  በፅናት እየሰራ መሆኑንም አክለው ተናግረዋል ::
አቶ ፍቅሬ  በተጨማሪ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ ቀጥታ ወደ ኦስሎ መብረር  መጀመሩን ተከትሎ የኖርዌይ መንግስት ኢትዮጵያ ካለው አገዛዝ ጋር ከአለም አቀፍ ህግ ጋር በተቃረነ መልኩ የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቁ ኢትዮጵያውያንን ያለ ፓስፖርት እና ከስደተኞቹ እውቅና ውጭ በሌሊት እያፈኑ አውሮፕላን ውስጥ በማስገባት ቦሌ አየር ማረፊያ  እየወሰዱ መጣል መጀመራቸው እንደ ኢትዮጵያዊ በጣም የሚያሳዝን ተግባር ነው ብለዋል :: ይህ  ተግባር የኢትዮጵያን ክብር የሚነካ ውርደትም ነው ብለዋል።  በዚያች ሃገር ማንነቱ እንኩዋን ሳይጠየቅ የተላከ መረጃ ሳይኖራቸው ጭምር የወያኔ ደህንነቶች ጋር ተመሳጥረው በራሳችን አየር መንገድ መታፈን አሳዛኝ ተግባር ስለሆነ  በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ በቀጣይነት በአለም አቅፍ ደርጃ የሚሰሩ ስራዎች  እንደሚኖሩ ተናግረዋል ::
በመጨረሻም ታዳሚው ያለውን ከፍተኛ የኖርዌይ ቅዝቃዜ ተቋቁሞ  በሃገሬ ጉዳይ ያገባኛል  በማለት ስለተገኘ በዲሞክራስያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጭ ድርጅት በኖርዌይ ስም አመስግነው ሰልፉ በተሳካ መልኩ ተፈጽፏል።

ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ

tirsdag 16. januar 2018

Leaked: Let’s go back 17 years | by Hadush Kassu

Let’s go back 17 years.

by Hadush Kassu | Director General at Federal Government Communication Affairs Office of Ethiopia
Debretsion was second in command to then Intelligence Chief Kinfe Gebremedhin. He was also his close confidant who knew about Kinfe’s offshore account where he had kept large sums of money siphoned off from public coffers.
When Kinfe was assasinated, Debretsion tried to find a way to transfer these funds from Kinfe’s account in National Westminister Bank, UK, to his own without the knowledge of Kinfe’s son, Leul.
However, a Malaysia based consultant advised him that the only viable course of action to get the funds is to ask the bank to transfer the money to Kinfe’s son and ‘collect it from him.’ He was also advised to withhold information from the bank about where the money would end up.
Whether he succeeded or not is a different matter but their exchanges (including others) show Debretsion tried to hoodwink Kinfe’s family and transfer the funds directly to his own account. Most importantly this is evidence that TPLF officials have offshore accounts where they keep money stolen from the Ethiopian people. The money belongs neither to Kinfe’s son nor to Debretsion.
Kylian Mbappe 

መያዧ መጨበጫ ጠፍቶባቸዋል! (በጌታቸው ሺፈራው)

~ ለብሔራዊ መግባባት ሲባል የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ስምምነት ላይ ተደርሷል ተባል!
~ ትንሽ ቆይተው ስምንት ጊዜ ደልዘው አንድንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትንና ሌሎች ግለሰቦችን እንፈታለን አሉ!
~ ይህም ቆጫቸው፣ ሽንፈት መሰላቸውና የፖለቲካ እስረኛ የለም አሉ!
~ቆይተውም ተጠቃሚ የነበረ፣ ተገፋፍቶ ወንጀል የፈፀመ፣ ሕገ መንግስቱን ያልናደ ብለው ቀባጠሩ፣
~ ካጎሩት ሁሉ እስረኛ 115 እንፈታለን አሉ። ከእነዚህ መካከል ወደ እስር ቤት የሚመልሱት እንዳለ ታወቀ!
~ የህዝብን ቀልብ ይስብላቸው ዘንድ የእነ ዶክተር መረራን ስም ጠቅሰው በሁለት ቀን ውስጥ እንደሚፈቷቸው በዜና ለፈለፉ!
~ ዜናውን ሰምተን ሳንጨርስ እነ ዶክተር መረራን ለመፍታትም ሁለት ወር ጠብቁ እያሉ ነው። ለብሔራዊ መግባባት እንፈታቸዋለን ያሉትን አሁን ደግሞ የይቅርታ ኮሚቴ ይመረምረዋል ማለታቸው እየተነገረ ነው!
~ቢጨንቃቸው እስር ቤት ውስጥ ተኩሰው የገደሏቸውን እነ አብዲሳ ቦካን ከተፈች ዝርዝር ውስጥ አጠቃለሉ! ሟቾችን በምህረት ፈታን ሊሉን!
~ ትንሽ ቆይተው “እስረኛ የለም” ሊሉም ይችላሉ። አይ ኤስ ያረዳቸውን ወንድሞቻችን “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አላረጋገጥንም” እንዳሉት “እስረኛ መኖሩን አላረጋገጥንም፣ እናጣራ” ሊሉንም ይችላሉ።
~ የሚይዙትን የሚጨብጡትን በማጣታቸው፣ ባለመስማማታቸው ነው። አንድ እስረኛ ሲፈታ ስልጣናቸው ላይ የሚያመጣውን በማሰብ ነው። በዚህ ሁሉ መቀባጠር ኃይል እንደከዳቸው አላወቁም፣ አሊያም ማወቅ አልፈለጉም።
~ ይህ ሁሉ ያዙኝ ልቀቁኝ እስረኞች ያለውድ በግድ የሚፈቱበት ቀን ሩቅ አለመሆኑን በግልፅ የሚያሳይ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ለአሳሪዎቹ ይቅርታ ያደርጋል ወይ በሚለው ላይ ግን እርግጠኛ መሆን አይቻልም።

mandag 15. januar 2018

Ethiopia to free opposition leader, others jailed for involvement in unrest

Aaron Maasho/  Reuters
ADDIS ABABA (Reuters) – Ethiopian authorities have dropped charges against a senior opposition leader and hundreds of others who had been jailed for involvement in unrest that gripped the country in 2015 and 2016, the country’s attorney general said on Monday.
Hundreds have been killed in violence in the Horn of Africa country since protests first erupted in its central Oromiya province over allegations of land grabs.
Several dissident politicians have since been jailed having been charged with involvement in terrorism and collusion with the secessionist Oromo Liberation Front, which the government has branded a terrorist group.
Facing mounting unrest, Prime Minister Hailemariam Desalegn announced earlier this month that jailed politicians would be released and those facing trial would have their cases dismissed in a bid to foster reconciliation.
On Monday, Attorney General Getachew Ambaye told journalists that 528 people had so far been selected for clemency, including Merera Gudina – leader of the opposition group Oromo Federalist Congress who was arrested in late 2015.
Getachew said criteria for their selection involved taking into account proof that the suspects did not take part in actions that led to killings and severe injury, damaging infrastructure, and “conspiracy to dismantle the constitutional order by force”.
“All 528 will be released within two months,” he said.
Merera was arrested after a trip to Brussels to meet members of the European Parliament, and formally charged with attempting to “dismantle or disrupt social, economic and political activity”.
He was also accused of backing a secessionist group Addis Ababa labels a terrorist movement, as well as flouting guidelines on a state of emergency that was imposed for nine months during his trip to Belgium.
Nearly 700 people died in one bout of unrest during months of protests in 2015 and 2016, according to a parliament-mandated investigation.
Rallies over land rights broadened into demonstrations over political restrictions and perceived rights abuses, before spreading into the northern Amhara region and – to a smaller extent – in its SNNP province in the south.
In recent months, a spate of ethnic clashes have also taken place. Dozens of people were killed in several bouts of violence between ethnic Oromos and Somalis in the Oromiya region last year.
Hailemariam made his announcement after the ruling EPRDF coalition concluded a weeks-long meeting meant to thrash out policies to address grievances.
The unrest had triggered growing friction within the party. Some high-ranking members had subsequently submitted their resignation, while officials have openly squabbled with each other over the cause of clashes.
Getachew said more pardons and releases are set to follow.
Ethiopia, sandwiched between volatile Somalia and Sudan, is often accused by rights groups of using security concerns as an excuse to stifle dissent and media freedoms. It denies the charge

søndag 14. januar 2018

ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎችን በአዲስ አበባ ዙሪያ ለማስፈር በተደረገ ጥረት በተነሳ አለመግባባት የሰው ህይወት መጥፋቱ ተሰማ

ዋዜማ ራዲዮ- በቅርቡ ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎችን በአዲስ አበባ ዙሪያ ለማስፈር በተደረገ ጥረት በተነሳ አለመግባባት የሰው ህይወት መጥፋቱን በቦታው የተገኙ እማኞች ገለፁ።
እማኞች እንደነገሩና የዋዜማ ሪፖርተር እንዳጣራችው በአዲስ አበባ በኮልፌ አቅጣጫ አዲስ አበባና ኦሮምያ በሚዋሰኑበትና በኦሮምያ ክልል በሚገኘው አሸዋ ዴዳ በተባለው አካባቢ ከዚህ ቀደም ከገበሬዎች ላይ መሬት በመግዛት መኖሪያ ቤት ገንብተው በአካባቢው የሚኖሩና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን ለማስነሳት የተደረገው ሙከራ ደም አፋሳሽ ሆኗል።
“ህጋዊ አይደላችሁም” በሚል ከአካባቢው እንዲለቁ የተነገራቸው ነዋሪዎች ከደንብ አስከባሪዎች ጋር አርብ ዕለት በፈጠሩት ግጭት የአንድ ሰው ህይወት መጥፋቱንና በርካቶች መጎዳታቸውን ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያመልክታል።
ግማሽ ሚሊየን ያህል ዜጎች ከሶማሌ ክልል ከተፈናቀሉ በኋላ በተለያዩ አካባቢዎች እንዲሰፍሩ ለማድረግ እየተሞከረ ሲሆን አብዛኞቹ ተፈናቃዮች ቀድሞ ወደ ነበሩበት ሶማሌ ክልል የመመለስ ፍላጎት እንደሌላቸው ገልፀዋል።
ተፈናቃዮቹን በአዲስ አበባ ዙሪያ ለማስፈር የኦሮምያ ክልል እንቅስቃሴ እያደረገ ሲሆን ቀደም ሲል ከገበሬዎች መሬት በመግዛትም ሆነ በተለያየ መንገድ የመኖሪያ ቤት የገነቡ ነዋሪዎች መሬቱን እንነጠቃለን በሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ለዋዜማ ተናግረዋል።
በተለይ ከዛሬ ነገ “ህጋዊ ት ሆናላችሁ”  ተብለው ከአስር አመታት በላይ ግብር እየከፈሉ መቆየታቸውን ገልፀው አሁን ግን የኦሮምያ ክልል የመሬት አስተዳደር ስራተኞች በየኣአካባቢው እየተዘዋወሩ ቅኝት በማድረግና መረጃ በማሰባሰብ ላይ እንደሆኑ ተናግረዋል።
የኦሮምያ ክልል ተፈናቃዮችን በተለያዩ አካባቢዎች የማስፈር እቅድ እንዳለው ገልፆ መልሶ ማስፈሩ የተፈናቃዮችን ፍላጎትና የኑሮ ሁኔታ ያገናዘበ እንደሚሆንና ሁሉንም በአዲስ አበባ ዙሪያ የማስፈር እቅድ አለመኖሩን ገልጿል።
በርካታ ተፈናቃዮች ከአዲስ አበባ ርቀው ባህላቸውና ወጋቸው ወደሚመሳሰልበት አካባቢ ለመስፈር ፍላጎት እንዳላቸው እንደነገሩት የኦሮምያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ባልደረባ ነግሮናል።

fredag 12. januar 2018

Ethiopia court jails members of outlawed group Ginbot 7

wire-1533201-1508011668-945_634x421
People protest against the Ethiopian government during Irreecha, the annual Oromo festival to celebrates the end of the rainy season, in Bishoftu on October 1, 2017
A court in Ethiopia has sentenced more than 30 people to long prison terms for belonging to an outlawed group.
They were allegedly members of Ginbot 7, a group the authorities say is committed to overthrowing the government.
The Ethiopian government designated it a terrorist group in 2011.
The move comes just two weeks after the government announced it would free some politicians who have been convicted or facing various charges in court.
Members of the Ginbot 7 group, founded by an Ethiopian-born British citizen, Andargachew Tsege, will now serve sentences of between 15 and 18 years.
Dozens more have been jailed by the courts over the past weeks due to their association with the group.
Meanwhile, a leading opposition figure and his co-accused have been sentenced to six months in prison for contempt of court.
Bekele Gerba, an official of the Oromo Federalist Congress, was jailed after he protested against the non-appearance of defence witnesses in the court trying his case.
The judge was angered after he reportedly sang a protest song in court.
He is among politicians who would have charges against him dropped following the announcement by Prime Minister Hailemariam Desalegn, many Ethiopians believe.

Terrorists or activists?

By Emmanuel Igunza, BBC Africa, Addis Ababa
The government would say there is no contradiction between its recent statement on freeing prisoners and these sentences.
Although their supporters are hoping they will be released, the authorities here see Ginbot 7 members as terrorists, not political activists.
Both its current leader Berhanu Nega and its founder Andargachew Tsege have been sentenced to death in absentia by an Ethiopian court for trying to overthrow the government. They both deny the charges.
Andargachew was arrested in Yemen and taken to Ethiopia in 2014 while Berhanu’s whereabouts are unknown.
Berhanu, a former university professor in the US, has previously threatened to march to Addis Ababa to remove the current government from power.
The government says the US-based group is sponsored by Eritrea and accuses it of trying to infiltrate the country.
Most of its members live in exile but authorities says some are active – but in hiding in Ethiopia.
It is highly unlikely that if any prisoners are released, Andergachew would be one of them as the government has previously taken a very strong stand against his release, despite pressure from human rights groups.

Up until now, the government has not followed up on its promise or issued a clear timeline on when those politicians jailed would be set free, reports BBC Ethiopia correspondent Emmanuel Igunza.
Ethiopia has always denied that there were any political prisoners in the country, as alleged by human rights and opposition groups.
The country has been hit by a wave of political unrest in recent years.
In December, social media users staged a day of action to remember those held behind bars.
Correction: This story has been updated to remove the suggestion that the UK government has campaigned for Andargachew’s release

የአገራችሁ የወደፊት እጣ ፋንታ ለሚያሳስባችሁ እና የህዝባችን የመከራ ጊዜ እንዲያጥር ለምትፈልጉ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ

አለም አቀፍ የኢትዮጵያዊያን የጋራ ግብረ-ሃይል
አለም አቀፍ የኢትዮጵያዊያን የጋራ ግብረ-ሃይል ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያን ዘመዶቻቸዉን ለመርዳት፣ ለንግደና ለግንባታ ወደ አገር ቤት የሚልኩት የዉጭ ምንዛሬ (ዶላር፣ ዩሮና፣ ፓዉንድ) የህወሓት አገዛዝ እጅ እንዳይገባ በማድረግ ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ መጀመሩ ይታወቃል።

ግብረ-ሃይሉ የህወሓት አገዛዝ በእጁ የሚገባዉን የዉጭ ምንዛሬ ባንድ በኩል ኢትዮጵያዊያንን ለማፈንና ለመግደል የሚጠቀምባቸዉን መሳሪያዎች ከዉጭ ለመግዣና በሌላ በኩል ከአገሪቱ የሚዘርፈዉን ሃብት ወደዉጭ ለማሸሺያ እንደሚጠቀምበት ጠቅሶ፣ የዚህን አገዛዝ እድሜ ለማሳጠር በርካታ ኢትዮጵያዊያን የህይወት ዋጋ እስከመክፈል በደረሰ ቆራጥነት በሚታገሉበት ባሁኑ ወቅት፣ ካገራቸዉ ወጥተዉ በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የህዝባቸዉን የነጻነት ትግል ለማገዝ የአገዛዙን የዉጭ ምንዛሬ አቅም ማመናመን ቀላሉ፣ ቀጥተኛዉና ባጭር ጊዜ ዉስጥ ዉጤት ሊያስገኝ የሚያስችል ተግባር እንደሆነ ማስገንዘቡ የሚታወስ ነዉ።
ግብረ-ሃይሉ፣ ስለዚህ ዘመቻ ለአሜሪካ ድምጽ የአማርኛ ፕሮግራም የሰጠዉን ቃለ-መጠይቅ ተከትሎ የህወሓት አገዛዝ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሰሞኑን በዉሸት የተሞላ፣ ተራና አጭበርባሪ ምላሽ ሰጥቷል።
በተለይ ቃል አቀባዩ የሬምታንስ ዘመቻዉ የሚጎዳዉ ከዉጭ በሚመጣ ሬሚታንስ ላይ የሚደገፉ ወገኖቻችንንና እርሳስና እስክርቢቶ መግዣ የሚሆን ገንዘብ የሌላቸዉን ተማሪዎች ነዉ ሲል ከተለመደዉ የህወሓት-ወያኔ የቅጥፈት መጽሃፍ የተወሰደ፣ ጊዜዉ ያለፈበት ማደናገገሪያ አስተላልፏል። በተለይ ግን ዘመቻዉ ኢትዮጵያዊነት የሚጎድለዉ ድርጊት ማለቱ ለአገዛዙ ያለዉን ህሊና ቢስ ታማኝነትና ለኢትዮጵያዊያን የማመዛዘን ችሎታ ያለዉን ንቀት የሚያሳይ ስላቅ ነዉ። ከደቂቅ ህጻናት እስከ አረጋዉያን ድረስ አዉሬአዊ በሆነ ጭካኔ የሚገድል ዘረኛና ወንጀለኛ አገዛዝ እያገለገሉ የአገራቸዉና የወገናቸዉ ሰቆቃ ጧት ማታ የሚያብሰለስላቸዉን ኢትዮጵያዊያን በጸረ-አገራዊነት እና በጸረ-ኢትዮጵያዊነት ለመዉቀስ የሚያስችል ሞራላዊ መሰረት ሊኖር አይችልም።  ኤፈርትን የመሳሰሉ የዝርፊያ እና የጎሰኝነት ተቋማት አደራጅቶ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የኢትዮጵያን ህዝብ ከሚመዘብር ስርአት ጋር በሎሌነት አብሮ እየሰሩ ለኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮጵያዊነት ወገንተኛ መሆን ፍጹም አይቻልም።
የሬምታንስ እቀባ ዘመቻዉ ኢላማ አንድና አንድ ብቻ ነዉ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ለሃያ ሰባት አመታት በጫማዉ ስር ረግጦ የያዘዉ የህወሓት-ወያኔ አገዛዝ ነዉ።
የኢኮኖሚ ጫናዎች በደቡብ አፍሪካ (አፓርታይድ ላይ በተደረገ ትግል)፣ በአሜሪካ (የጥቁሮች የእኩልነት ትግል)፣ በህንድ (የነጻነት ትግል) አፋኛና ግፈኛ ስርአቶችን ለማንበርክ ከፍተኛ ሚና ተጫዉተዋል። ስለዚህም፣ በአገራችሁ ፍትህ፣ እኩልነትና ሰብአዊ መብቶች ተከብረዉ ለማዬት የምትሹ ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ለዘመድ፣ ወዳጅ፣ ንግድና ግንባታ ብላችሁ ወደ አገር ቤት የምትልኩት የዉጭ ምንዛሬ በዚህ አፋኝና ገዳይ አገዛዝ እጅ  እንዳይገባ በማድረግ የበኩላችሁን ወገናዊና አገራዊ ግዴታ እንድትወጡ ግብረ-ሃይሉ  በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል።  ይህም ማለት፦
ሀ)አገር ቤት ለሚኖሩ ዘመዶቻችሁ ገንዘብ በምትልኩበት ወቅት፣ እንደ ዌስተርን ዩንየንና መኒ ግራም የመሳሰሉትን መደበኛ የባንክ መስመሮችን እንዳትጠቀሙና በምትኩ በየአካባቢያችሁ የሚገኙ፣ ከህወሓት አገዛዝ ጋር ንኪኪ የሌላቸዉና ከባንክ ዉጭ ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት የሚሰጡ ነጋዴዎችንና ግለሰቦችን እንድትጠቀሙ፤ በባንክ መላክ ብቸኛዉ አማራጭ ለሚሆንባችሁ ደግሞ የምትልኩትን የገንዘብ መጠን ወይም የጊዜ ፍጥነት እንደሁኔታዉ እንድትቀንሱ፤
ለ)የአገሪቱ ሰላም በታወከበትና ያገዘዙ ባለሟሎች ሳይቀሩ ገንዘባቸዉን ወደዉጭ በሚያሸሹበት በአሁኑ ወቅት፣ የትዉልድ አገራችሁ ቤት ለመስራትም ሆነ በንግድ ወይም ሌላ ቢዝነስ ላይ ኢንቨስት ለማድረግ የምታስቡ ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያን፣ እቅዳችሁን ለጊዜዉ እንድታዘገዩት ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን።
በመጨረሻም፣ ለወትሮዉ በዉጭ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን ለምናሰማዉ ስሞታ መልስ ለመስጠት ደንታ ያልነበረዉ የህወሓት-ወያኔ አገዛዝ፣ ባሁኑ ጊዜ ፈጥኖ ምላሽ መስጠቱ ከሚገኝበት ከፍተኛ የፖለቲካና የኢኮኖሚ አጣብቂኝ ጎን፣ የዉጭ ምንዛሬ እቀባዉ ሊፈጥር የሚችለዉ ፈጣንና ወሳኝ ጫና እንዳስደነገጠዉ የሚያሳይ ስለሆነ ላልሰሙት እያሰማችሁ ትግሉን እንድትቀጥሉበት አደራ እንላለን።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
አለም አቀፍ የኢትዮጵያዊያን የጋራ ግብረ-ሃይል

torsdag 11. januar 2018

የክልላችን መንግስት እና የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የቴዲ አፍሮን ጥያቄ ተቀብሎ ፈቃድ ሰጥቶታል ” አቶ ንጉሱ ጥላሁን

አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን/ቴዲ አፍሮ/በባህር ዳር ከተማ የሙዚቃ ኮንሰርት ሊያዘጋጅ ነው፡፡ቴዲ አፍሮ ከአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ጋር ልዩ ቃለ-መጠይቅ ዝግጅት ይኖረዋል፡፡
አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን/ቴዲ አፍሮ/ በባህር ዳር ከተማ የሙዚቃ ኮንሰርት ለማቅረብ ያቀረበው ጥያቄ በክልሉ መንግስትና በከተማ አስተዳደሩ ፍቃድ አግኝቷል፡፡ስለሆነም ጥር 12/2010 ዓ/ም ‹‹ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር››የሚለው የፍቅር ጉዞ ኮንሰርት በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ከተማ ይካሄዳል፡፡
የአርቲስት ቴዲ አፍሮ ማኔጀር አቶ ጌታቸው ማንጉዳይ ጥር 12 በዉቢቷ ባህር ዳር አርቲስቱ የሙዚቃ ኮንሰርቱን እንዲያቀርብ የአማራ ክልል መንግስት እና የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ፍቃድ የሰጠዉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኮንሰርቱም በተያዘለት ጊዜ በባህር ዳር ከተማ ይካሄዳል ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ‹‹ኮንሰርቱ ስለ ሰላም ፣ስለ ፍቅር፣ስለአንድነት ፣ስለ አብሮነት እና ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚቀነቀንበት ነዉ፡፡ የክልላችን መንግስት እና የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የአርቲስቱን ጥያቄ ተቀብሎ ፈቃድ ሰጥቶታል ›› ብለዋል።
አርቲስት ቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያ የሚለውን አልበም ከለቀቀ በኋላ የሚያቀርበዉ የመጀመሪያ የሙዚቃ ኮንሰርቱ ነው፡፡

ትግላችን የችግሩ ስር የሆነዉን ስርዓቱን ማስወገድ ላይ ያትኩር

ዶ/ር አበራ ቱጂ
በእራቱ የኢህአዲግ ድርጅት መሪዎች የተሰጠዉን ረጂም መግለጫ በጥሞና ተከታተልኩ። አራቱም ባለስልጣኖች አሁን ኢትዮጵያ ለገባችበት የፖለቲካ ቀዉስ ዋናዉ ምክንያት ራሳቸዉ የኢህአዲግ ባላስልጣናትና የነሱም የአመራር ዉድቀት ያመጣዉ መሆኑን ገልጸዋል።  እንዲሁም በኢህአዲግ አመራሮች ዉስጥ ዲሞክራሲያዊ አሰራ እንዳልነበረ፤ በዚያም የተነሳ በህዝቡና ተቃዋሚ ድርጅቶች ላይ ላይ በተለያየ መንገድ አፈናና ማኮላሽት ጭምር ይፈጽሙ እንደነበረ ገልጸዉልናል።  ለህዝቡ የሚገልጹት ጉዳይ ታአማኝነት እንዳልነበረውም አቶ ሃይለማሪያም የአሰፋንና የእናቱን ታሪክ በመጥቀስ ነግረዉናል። በዉስጣቸው ያለው ችግር፣ ከግል ከስልጣን ጥም የተነሳ እንደሆነ፣ በዚህም በመቧደን አንዱ አንዱን ለማጥፋት ይሰሩ እንደነበር፣ የግል ሃብት ለማከበትም ሲሉ ኮንትሮባንድ አንዳስፋፉ የመሳሰሉትን ሁሉ ዘርዝረዋል። ባለስልጣኖች፣ ያሚመሩበት ስርዓትና የፈጠሩት የጎሳ ፈደራሊዝም ግን ምንም ችግር አላመጣም፤ ችግሩ እኛው ራሳችን ብቻ ነን፣ የምንከተለው መርህና ስርዓት ፍጹም ትክክል ነዉ ይሉናል። ይህ ሁሉ ቀዉስና የሰዉ እልቂት የመጣዉ በነሱ መሆኑን ቢገልጹም አንድም ሰዉ እንኳ ተጠያቂ ሁኖ ለፍርድ ሲቀርብ አላየንም።  የችግሩን ዋና ምንጭ በትክክል  ለመመርመርና ለመለወጥ ፍላጎቱ የላቸዉም። ጉዳዩ ጊዜ ለመግዛት የተደረገ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ነው።
የችግሩ ምንጭ ራሳቸው መሆናቸዉን ማመልከታቸው ባልከፋ፤ ነገር ግን አሁንም ከኛ ዉጭ ለኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ የለም እያሉን ነው። የህዉሃት-ኢህአዲግ ባለስልጣናት ብዙ ጊዜ እንደሚናገሩት ድርጅቱ እንደእባብ ነው።  እባብ ቆዳዉ ሲያረጅ፣ ያረጀዉን ቆዳ ገልፍፎ ጥሎ፣ ለተመልካች አዲስ መስሎ ብቅ ይላል። አሁን በኢትዮጵያ ላይ ለሃያ ስድስት ዓመታት ይህን ሁሉ ግፍ ከፈጸሙ በኋላ አሁንም እንግዛችሁ፣ እንጋልባችሁ ይሉናል።  የህዉሃት-ኢህአዲግ መሪወች አሁንም ከአንድ መቶ ሚሊዮኑ ኢትዮጵያዊ ዉስጥ ከኛ ዉጭ አገር መሪ ሊኖር አይችልም እያሉን ነዉ። ከኛ የተሻለ አዋቂና ለአገር አሳቢ የለም ማለታቸዉ ነው። ይህም ህሊና ከማጣትም ያለፈ፣ በህዝብ ሰቆቃ መሳለቅ ነው። መግለጫቸው ከምንም ነገር በላይ የሚያሳየው ለአገሪቱና ለህዝቡ ያላቸዉን ጭንቀት ሳይሆን፣ ይፋ የወጣዉንና ያስፈራቸዉን፣ በዉስጣቸው ያለዉን ልዩነት እንዴት አጥፍተው አሁንም የተለመደዉን የግፍ ስራቸዉን ለመቀጠል መዘጋጀታቸዉን ነው።
ኢትዮጵያዊያን ልንጠይቀዉ ያሚገባ አንድ ዋና ጥያቄ አለ። ለመሆኑ ህዉሃት-ኢህአዲግ አገር አስገንጥሎ፣ የኢትዮጵያን የባህር በር ዘግቶ፣ ንጹህ ዜጎችን ፍትህን ስለጠየቁ በአነጣጣሪ ተኳሾች እየገደለና፣ የተለየ ሃሳብ ያላቸዉንና የመንግስትን ስህተት ያሳዩትን ሁሉ አስሮ እያሰቃየ፣ እያኮላሸ፣ ሊወራ የማይገባው ነዉር በፖለቲካ እስረኞች ላይ እየፈጸመ፣ አዉሮጳዊያን ቅኝ ገዢወች በፈጠሩት ዘመን ያለፈበት ስልት፣ ዜጎችን በጎሳና ቋንቋ ከፋፍሎ እያጫረሰ፣ ይህን ሁሉ ስቃይ በህዝብና በአገር ላይ እያደረሰ፣ እንዴት ከእሩብ ምዕተ ዓመታት በላይ አገሪቱንና ህዝቡን መግዝት ቻለ? አሁንስ እንዴት በዚሁ የግፍ አገዛዙ ለመቀጠል ድፍረት አገኘ?  የተማመነው በመሰረተው መሰሪ ስርዓት በመሆኑ ነው።
በኢትዮጵያችን አሁን የተፈጠረው ቀዉስ ዋናው መንስዓኤ የህዉሃት-ኢህአዲግ መሪወች እንደሚሉት የነሱ የአመራር ዉድቀት ሳይሆን፣ ለህዉሃት-ኢህአዲግ ደም፣ አጥንትና ህይወት የሆነዉና የተመሰረተበት ጨካኝ ስርዓት ነው።  የችግሮቹ ዋናው መንስዓኤው ከሰወቹ በላይ የሆነው ስርዓቱ ነው።
በስርዓቱ ላይ ያላነጣጠር የመፍትሄ ሃሳብ፣ ችግሩን ከስር መሰረቱ ለመንቀልና ችግሩ ተመልሶ እንዳይመጣ ለማድረግ አይችልም። ወያኔ ኢህአዲግ፣ የችግሩን ዋና ስር ወይም መሰረት፣ የተወሰኑ ባለስልጣኖች የፈጠሩት ነው በማለት ብቻ፣ የተወሰኑ ባለስልጣኖችን በማተካካት የጥገና ለውጥ በማድረግ አሁንም አረመኒያዊ አገዛዙን አጠናክሮ ለመቀጠል እየተዘጋጀ ነው።
ችግርን ለማስወገድ፣ የችግሩን ስር (root cause) በዘዴ መመርመርና በትክክል መለየት ያስፈልጋል። የዚህም ጽሁፍ ዓላማ ይህ ነው። አሁን አገራችን የገባችበትን ችግር ምን አመጣዉ የሚለውን ጥያቄ በትክክል መመለስ ይገባል። የችግሩ ዋና ስር፣ የችግሮች ሁሉ መሰረት ሆኖ፣ ችግሮች ወይንም ችግሮችን የሚያስከትሉ ሰንሰለታዊ ሁነቶችን የሚቀሰቅስና፣ ልናስውግደው የሚገባው የችግሮችን ስርዎ-መንሴ ነው። ይህን የችግር መንስዔ በአግባቡ ካስወገድነው የፈጠራቸው ችግሮችና፣ ችግሮቹን ተከትለው የሚመጡ መጥፎ ወይም የማይፈለጉ ሁነቶች ለዘለቄታው ይጠፋሉ ወይም ተመልሰው አይመጡም።  የችግሩን ዋና ስር ሳናጠፋ ሰበብ (triggering event) ወይንም ከላይ ከላይ ያሉ ችግሮች ወይንም የዋናዉን ችግር ምልክቶች ወይም መገለጫወች (manifestations or symptoms) ላይ ብናተኩር፣ ችግሩ ተመልሶ መምጣቱ ወይንም ሌላ መልክ ይዞ ተጠናክሮ መከሰቱ አይቀርም።
በሌላ በኩል፣ ይህ አገራችን የገባችበትን ችግር፣ ኢትዮጵያ በተሻለ አቅጣጫና አስተዳደር ለመመራት የምትዘጋጅበት ጥሩ እድልም ይዞልን እንደመጣ በመቁጠር፣ ይህን የቁጣና የቁጭት ሃይል ወደ አዎንታዊ ጉልበት በመቀየር፣ ከችግሩ አዙሪት መውጣት እንድንችል የአገራችንን የፖለቲካ ስርዎ-ችግር በማስወገድና፣ አገራችን የህግ የበላይነት የሰፈነባትና የቂም-በቀል ፖለቲካ የማይኖርባት፣ ሁሉም ዜጋ በእኩልነት አስተዋጾዖ የሚያደርግባት፣ ሆና እንድትቀጥል መስራት አለብን።
አሁን ያለውን ችግር ከስፋቱና ጥልቀቱ የተነሳ በተወሰኑ ዓርፍተ ነገሮች መግለጽ ያስቸግራል።  ዋናው ችግር ግን ኢትዮጲያዊያን እንደ አንድ በአገሩ በነጻነት ሰርቶ የመኖር መብት እንዳለው ሰብዓዊ ፍጡር ሳይሆን፣ የወያኔ መንግስትና የፈጠረው ስርዓት፣ ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ ያለፍርድ ይገድሏቸዋል፣ አስነዋሪ ሰቆቃ ይፈጽሙቧቸዋል፣ ንብረታቸውን ይቀማሉ፣ እንዳይናገሩና አንዳይደራጁ ያፍኗቸዋል፣ የወያኔን ብልሹ መርህ፣ ‘ፖሊሲ’ ወይም ‘ዶክትሪን’ እንዲቀበሉ ያስገዲዷቸዋል።  ሰወች በሰብዓዊ ሃይላቸው ተጠቅመው በነጻነት ማሰብ፣ መስራትና ማደግና ይከለከላሉ። በአጭሩ የኢትዮጲያ ዜጎች በወያኔወችና  ወያኔወች በፈጠሩት ስርዓት ተፈጥሯዊና ህጋዊ መብታቸው ተገፎ እንደእንሰሳ ተቆጥረው ወንጀል እየተፈጸመባቸው ነው።
የዚህን የአገራችንን ዘርፈ-ብዙ ችግር ምንጩን ለማወቅ “ችግሩ ለምን ተፈጠረ ወይም ምን አመጣው’ በማለት የችግሩን ስር እስከምናገኝ ተከታታይ ጥያቄወችን ማንሳት ያስፈልጋል። ለምሳሌ ያህል አንድ የችግሩን ሁነት (event) እንመልከት።  በሰላም የመብት ጥያቄ ያቀረቡ ሰለማዊ ሰልፈኞች ለምን በመንግስት አነጣጥሮ ተኳሾች ይገደላሉ?  ለዚህ የሚጠበቀው መልስ የመንግስት ባላስልጣን የግድያ ትዕዛዝ ስለሰጠ ነው እንበል። ይህን የግድያ ትዕዛዝ የሰጠ የመንግስት ባላስልጣን ከቦታው ቢነሳ፣ ሰለማዊ ሰልፈኞችን መግደል ያቆማል ወይ? ለዚህ ምሳሌ ማየት ያለብን፣ አቶ መለስ ዜናዊ የ1997 ምርጫ ተክትሎ ግድያ አዘው ወደ ሁለት መቶ የሚሆኑ ሰለማዊ ሰልፈኞችን አዲስ አበባ ዉስጥ ብቻ በግፍ አስገድለዋል። እሳቸው በሞት ሲለዩ የተኳቸውና እግዚአብሄርን ይፈራሉ ይባል የነበሩት አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ ህዉሃትን ለማስደሰት፣ ተመሳሳይ ትዕዛዝ በመስጠት በመቶወች የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎችን እያስገደሉ ነው።
የክልል መሪወችም ሆነ የተውሰኑ የጦር ጄኔራሎች የወያኔን አጥፊ ተልዕኮ ከፈጸሙ በኋላ ተተክተው አይተናል።  የህዝብ ሃብት ዘረፉ የተባሉና፣ በዘረኛ ቅስቅሳ ህዝቡን በጠላትነት ያነሳሱ የነበረው ጠቅላይ ሚኒስተር፣ ተተክተው አይተናል።  ሰወቹን በመቀያየር መንግስት የበለጠ ችግር ሲፈጥር እንጂ ሲያሻሽል አልታየም። የይምሰል ህግም ማውጣት ችግሩን አልፈታም።  ሰወችን በመቀየር፣ የማሰቃያንና የማኮላሻን ቦታ በመቀየር ብቻ ችግሩን ማጥፋት ወይም ተመልሶ እንዳይከሰት ማድረግ አይቻልም። በመሆኑም የችግሩ ምንጭ የተወሰኑ ስልጣን ላይ ያሉት ሰወች ወይንም የህግና፣የብልሹ አስተዳደር፣ የሙስና፣ የህዝብ ንብረት ምዝበራ፣የችሎታ ማነስ ወይም የአፈጻጸም ጉድለት አይደለም። እንዚህ ስርዎ-ችግሩ ያመጣቸው የችግሩ ምልክቶች ወይም ሁነቶች ብቻ ናቸው።
ዛሬ የሚገድሉትና የሚያስገድሉት የወያኔ ባለስልጣኖች ከስልጣን ቢወገዱና የመሰረቱት ዘረኛ፣ አድሏዊና አፋኝ ስርዓት (system) እስካለ ድረስ፣ ሌሎች በቦታዉ ተተክተዉ፣ ችግሩ ይቀጥላል፣ ወይንም መልኩንና ሰወችን እየቀያየረ በድጋሜ ይመጣል። ስርዓቱ የወያኔን መሰሪና በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ተልዕኮ ለመፈጸም ሲባል በልዩ ሴራ የረቀቀ መዋቅር ተዘጋጅቶለታል። ስርዓቱን እንዳይወድቅ ደግፈው የያዙ፣ የተሳሰሩና እርስ በርሳቸው የሚደጋገፉ፣ ተደጋግፈዉም የከፋ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያመጡ ብዙ ምሶሶወች አሉት።  ስርዓቱን ቀጥ አድርገው የያዙት፣ እያደሱና እየጠገኑ ያቆሙት የሚከተሉት የስርዓቱ ዋልታወች ናቸው።
  1. በዘርና ቋንቋ ከፋፋይ መርህ፤ የዚህ ስርዓት የመሃል ምሰሦ የሆነው አገሪቱን በዘርና ቋንቋ መከፋፈሉና የፈጠረውን የዘራው የዘር ወይም የጎሳ ጥላቻ ፖለቲካ ነው።  ይህ ወያኔወች የኢትዮጲያን ታሪክና አንድነት በማጥፋት፣ ህዝቡን ለመቆጣጠር ያመጡት የጎሳ ፖለቲካ ለወያኔው ስርዓት ከሁሉም በላይ መድህኑ ሁኗል። ኢትዮጵያዊያን የአገራቸውን ችግር በጋራና በሰለጠነ መንገድ ተወያይተው፣ መክረዉና ተቀራርበው እንዳይፈቱ፣ በአገር አቀፍ ጉዳይ ላይ ከማትኮር ይልቅ በመንደር ድንበርና በጥላቻ ፖለቲካ እንዲጠመዱ አድርጓቸዋል።
  2. አፋኝ ጦርና የስለላ ድርጅት፤ ስርዓቱን የሚቃወሙትን ሁሉ ለማፈን፣ በወያኔ ታማኞች በበላይነት የሚመራ አገርና ህዝብን ሳይሆን፣ ወያኔወችንና አፋኝ ስርዓቱን የሚጠብቅ የጦርና የፖሊስ ሃይል አለ። የዜጎችን ዕለት-ከዕለት ህይወት ለመቆጣጠርና ለመሰለል፣ የሃሳብ ልዩነት ያላቸዉን ተቃዋሚወች ለማጥፋት ወያኔወች ከሚመሩት የስለላ ድርጅት በተጨማሪ፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴሩና ቴሌኮሙኒኬሽን የመሳሰሉትን ለማፈኛነት ይጠቀማል ።
  3. በፖለቲካ ድርጅቱ ቁጥጥር ስር ያለምጣኔ ሃብትና የዕምነት ተቋማት፤ስርዓቱን በገንዘብ ሃይል ለመደገፍና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በመስጠት፣ ደጋፊውችን ለማብዛትና፣ ተቃዋሚወችን ለማዳከም፣ የኢኮኖሚ አውታር የሆኑትን የአገሪቱን መሬት፣ ማአድን፣ ባንክ፣ የንግድ ተቋማትን እንደ አየር መንገድ፣ ኤፈርት፣ ሜቴክ፣ ቴሌኮሙኒኬሽን፣ መብራት ሃይልና የመሳሰሉትን በቁጥጥሩ ስር አስገብቷል። የመንግስት መስሪያ ቤቶችን በደካሞችና በወያኔ ደጋፊወች ብቻ በመሙላት፣ ዜጎችን በህዉሃት ላይ ጥገኛ እንዲሆኑ በማድረግ፣ የስርዓቱን እድሜ ለማራዘምና የዜጎችን ዕለት ከዕለት ኑሮ ለመቆጣጠር ይጠቀምባቸዋል። የዕምነት ድርጅቶችንም እንደዚሁ በወያኔ ታማኞች እንዲመሩ በማድረግ ህዝብ ሲበደል አንዳይነሱና፣ ግፍ ሲፈጸም እዉነትን እንዳይናገሩ አድርጓል።
  4. ተቃዋሚወችን የሚያጠፋየይስሙላ የፍትህና የምርጫድርጅቶች፤ ወያኔ ካለው የአንድ-ድምፅ ፓርላማ በተጨማሪ ለይስሙላ ያሉ የፍትህ መስሪያ ቤቶች፣ የወያኔን ስርዓት “ህጋዊ” ጠለላ ይሰጣሉ። አፋኝ ህጎችን እንደ ጸረ-ሽብርና፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ህግ በማውጣት፣ መንግስትን የሚቃወሙትንና የመብት ጥያቄ ያነሱትን በእስር ያሰቃያል፣ ሰቆቃ ይፈጽማል። ዜጎችን የመናገር፣ የመሰብሰብ፣ የመደራጀት መብታቸውን ይነፍጋል። ለይምሰል ያክል ምርጫ ያካሂዳል፣ ከወያኔ በስተቀር ተመራጭ እንዳይኖር ያደርጋል። ምርጫን ያጭበረብራል።
  5. አማርጭ ሃሳብ የሚዘጋና ጥላቻየሚነዛ የመገናኛ ብዙሃን፤ወያኔወች የሚመሩዋቸዉን በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ የመገናኛ ብዙሃንን፣ በህዝቡ መሃል ጥላቻን ለመዝራት፣ ውሸትን ለማሰራጨት፣ ህዝቡን የመንግስትን አቋም ብቻ እንዲከተል ለማድረግ፣ አማራጭ ሃስቦችን ዝግ ለማድረግ ይጠቀምባቸዋል። የግል መገናኛ ብዙሃንን፣ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችን፣ የዝቡን ችግርና በደል እንዳያሳውቁ ፣ህዝቡን እንዳያነቁ ያጠፋል። የትምህርት ተቋማትን ወጣቱን በዘር ለመከፋፈል፣ ሰላዮችንና ጆሮ-ጠቢወችን በመሰግሰግ፣ የጎሳ ጥላቻ ማስተማሪያ በማድረግ፣ የአዕምሮ ነጻነት እንዳይኖር በማፈን፣ የወያኔ ካድሬ መፈልፈያ አድርጓቸውል።
እነዚህ እርስ በእርስ የሚደጋገፉናየተሳሰሩ ምሶሶወችና፣ ምሶሶወቹየቆሙለት መሰሪና አገር አጥፊተልዕኮና መርህ፣ ምሶሶወቹ የቆሙበት መዋቅሩና፣ ስርዓቱን የሚመሩትናየሚያገለግሉት ሰወች፣ በአንድተዋህደውና ተቀናጅተው ነው አሁንየደረስንበትን ችግር የፈጠሩት።ለዚህም ነው ችግሩ ስርዓታዊ(systemic) ነው፣ ወይም የችግሩ ዋና መንስዔ ስርዓቱ ነው የምንለው።  
ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት በአገራችን ያለው አደገኛ ሁኔታ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ድርጅት ማንፌስቶ እንደሚገልጸው ወያኔውች በደደቢት የጀመሩት በይበልጥ በአማራ ላይ በአላቸው ጥላቻ ላይ የተመረኮዘ በልዩ ተንኮል የተዘጋጀ፣ ከፋፋይ፣ አድሏዊና አፋኝ ስርዓት ነው። አሁን ያለው ችግሩ በተወሰኑ ግለሰቦች ብቻ የተፈጠረ ወይም በተናጠል የሚታይ አይደለም። በአገራችን ያለው ችግር ይህ ስርዓት እስካለ ድረስ ይቀጥላል። የችግሩ ስርዎ-መንስዔ (root cause) ይህ ወያኔ የፈጠረው ስርዓት ነው። የችግሩን ወቅታዊ ሁነቶች፣ ለምሳሌ ሰዎችን መቀየር፣ አንደ የአዲስ አበባ ድንበር መስፋፋት ችግር ወይም የወልቃይት ጉዳይ ለጊዜው መልስ በመስጠት ችግሩን ለዘለቄታው መፍታት አይቻልም።
ወያኔወች ዛሬ የፖለቲካ እስረኞችን፣ ምህረት ጠየቁ እያሉ፣ ካደነዘዙና የማይድን የአዕምሮ ሰቆቃ ከፈጸሙባቸው በኋላ ቢፈቷቸውም፣ ነገ ደግሞ ባለተራወችን ያስራሉ። ዛሬ ግድያቸውን  ለጊዜው ቢያቆሙ፣ ከተውሰነ ጊዜ በኋላ ይጀምራሉ። ወያኔወች በሃያ ስድስት ዓመታት አገዛዛቸው ያሳዩን ሃቅ ይህን በደል፣ ተራ በተራ፣ መርሃ-ግብር አውጥተዉለት፣ በተለያየ የህብረተሰቡና የአገሪቱ ክፍል ላይ መፈጸማቸውን ነው። ከሁሉም በላይ አገር ሊመሩ የሚችሉ ዜጎችንና ድርጅቶችን ገና ብቅ ሲሉ ያጠፋሉ። ዜጎችን ሰላማዊ አማራጮች ሁሉ እንዲዘጉባቸው በማድረግ ተስፋ በማስቆረጥ ወደጦርነትና ሃይል አማራጭ ይገፋሉ። በአገሪቱ የዘር ጥላቻን ይዘራሉ።  እኛ ካልገዘናችሁ ህዝቡም አገሪቱም ትጠፋለች በማለት ህዝቡን ያሸብራሉ። በመግደል፣ በመዝረፍና በማሸበር ረግጦ መያዝ ከአገዛዙ ስርዓት እምነትና ተልዕኮ የመጣ እንጂ የተወስኑ አምባገነኖች ብቻ ፍላጎት አይደለም።  ሰወቹ ቢቀያየሩም፣ ይህ ስር የሰደደና በተንኮል የተዘጋጀ አፋኝ ስርዓት እስካለ ድረስ፣ ባለው አጥፊና የማያፈናፍን የድርጅት ባህል (organizational culture)፣ በስፋት በተደራጀው የስለላ ድርጅትና ሌሎች ከላይ የተጠቀሱ ዋልታወቹ ጋር በመሆን፣ አዲስ የሚቀላቀሉትን ግለስቦች ባህሪ ስርዓቱ በተቃኘበት መንገድ ይቀርጸዋል።
ሰላማዊ ሰልፈኞችን ለመግደል ትዕዛዝ የሚያስተላልፉት ወያኔወች የተለመደ ድራማቸውን ይዘው ቀርበዋል። የታዘዙትም የክልል ባለስልጣኖች ትዕዛዙን ተቀብለዋል። ወያኔወች “በጥልቀት እንታደሳለን” እያሉ የሚያላዝኑት፣ ችግሩን የሚያዩበት መነጸራችው ያው ሃያ ስድስት ዓመታት የገዛን ወያኔ የዘረጋው ዘረኛዉና መሰሪዉ ስርዓት ነው። የሚመሩበትም ፍጹም የተማከለ፣ ሚስጥራዊና ከፋፋይ፣ የማያፈናፍንና፣ በተወሰኑ የህወሃት ሰወች የሚመራ፣ ስርዓት ነው።
ወያኔወች ፈታኝ ወቅት ሲያጋጥማቸው በሚስጥር በመወሰን፣ ከስራቸው ያስጠጓቸውን ተለጣፊወች ተጠያቂ ያደረጉ ይመስላሉ፤ ወይንም አንዳንዶቹን ሆዳሞች የመስዋዕት በግ ያደርጓቸዋል። በረከት ስምኦን ባለፈዉ ዓመት ይህን ነበር ያለው።  “በኢትዮጲያ ዉስጥ ፈደራል የሚባል ህዝብ የለም ክልላዊ ህዝብ ነው ያለው ኢህአዲግ ለብልሽት ብሄራዊ ካባ ልንደርብለት አይገባም የሚል በጣም ጠንካራ አቋም ነው ያለው፣ በጣም ጠንካራ፣እያንዳንዱ ክልል፣ እያንዳንዱ ብሄራዊ ድርጅት የራሱን ብልሽት ራሱ ይታገል።”  ይህም ወንጀሉን የሚፈፅመዉን የፌደራል መንግስትና ወያኔ ከደሙ ንጹህ እንደሆነ በማቅረብ፣ አፋኙን ስርዓት ለማዳንና ለማጠናከር የተወሰኑ የአማራና የኦሮሞ ተለጣፊ መሪወችን፣ ህዝባቸውን ካስጨፈጨፉ በኋላ ሊወረዉሯቸው መሆኑን ሲገልጽ ነበር። የአሁንም ድራማ ከዚያ የተለየ አይደለም።
የወያኔ ኢህአዲግ ሰወች ማሰብና መጓዝ የሚችሉት ይህ ስርዓት ባሰመራላቸው ቀጭን መስመር ብቻ ነው።  አንዳንድ የሚባንኑ የኢህአዲግ ሰወች ቢኖሩም እንኳ፣ ከዚህ ከተሰጣቸው፣ ነገሮችን የመመልከቻ ዘይቤ (paradigm) ዉጭ ሊያስቡ አይችሉም። ሌላ አዲስ ነገር እንዳያስቡ ይህ ስርዓት አፍኖና አስሮ ይዟቸዋል። በወያኔ የአዕምሮ ማደንዘዣና አስገዲዶ ማሳመን (indoctrination and brainwash) ያልተረቱ እንደ አቶ ለማ መገርሳ ያሉ አንዳንድ የስርዓቱ አባላት ቢኖሩም እንኳን፣ ከዚህ ወጭ ማሰብ ከጀመሩ ስርዓቱ በተለያየ ተንኮል ያጠፋቸዋል። ይህ የችግሮቹ ሁሉ ዋና ምንጭ የሆነ ስርዓትና፣ የችግሩን ሁነቶች የፈጠሩት ግለስቦች፣ ችግሩን በፈጠሩበት አስተሳሰባቸው፣ አገራችንን አሁን ከገባችበት የፖለቲካ ምስቅልቅል ሊያወጧት አይችሉም።  እንዲያውም የህወሃት መንግስት ተጠናክሮ ለመቀጠል ይህን አጋጣሚ ይጠቀምበታል።
መቶ ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ በአለባት ኢትዮጵያ ይህን እየገደለ፣ በሰቆቃ የገዛንን ስርዓት ተጭኖብን እንድንቀጥል የሚያስገድደን ምን ሁኔታ አለ?  ወያኔ ለህዝብ ባለው ንቀት፣ ይህን ሁሉ ወንጀልና ግፍ በረቀቀ ዘዴ አቀነባብሮ እየፈጸመ፣ አሁንም ለኢትዮጵያ ከኔ በላይ አሳቢ የለም፣ መፍትሄዉም እኔዉ ነኝ ይለናል። ከዘረፉት በተረፋቸው የብድርና እርዳታ ገንዘብ መንገድ ሰርተናል ከሆነ የሚሉን፣ ፋሺስት ጣሊያንም እየጨፈጨፈን በአምስት ዓመታት የበለጠና እስካሁን እያገለገለ ያለ መንገድ ሰርቷል።
የበደለ ቢረሳ የተበደለ አይረሳም። የኢትዮጲያ ህዝብ በዚህ ስርዓትና በወያኔ የደርሰበትን ግፍ ህሊና ያለዉ ሰዉ ፍጹም አይረሳዉም።  አገር ለመገንጠልና ለማስገንጠል አቅዶ የተነሳው የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር (ህዉሃት)፣ ብዙ ሺህወችን ጨፍጭፎና አስጨፍጭፎ ስልጣን ላይ ወጥቶ፣ በኢትዮጲያ ላይ ያደረሰውን በደል በዚህ አጭር ጽሁፍ ጨርሶ መዘርዘር አይቻልም። በመሃል አዲስ አበባ የተገደሉት እነ አሰፋ ማሩ፣ የእነ ሽብሬ ህይወት በግፍ የተጨፈጨፉት የጋምቤላ፣ ኦሮምያ፣ሲዳሞ፣ ኡጋዴን፣ አዲስ አበባ፣ ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወገኖቻችን ደም አሁንም ወደሰማይ ይጣራል።  በገደሉት ልጇ አስከሬን ላይ አንድትቀመጥ አስገድደው የደበደቧትን የወለጋዋን እናት ሰቆቃ እግዚአብሄር ያያል። በወያኔ እስር ቤት የሚሰቃዩና የተገደሉ በሺወች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን፣ የፖለቲካ እስረኞችና ጋዜጠኞች እምባ ወደአምላካቸው ይፈሳል። ይህንና ሌሎች ተዘርዝረው የማያልቁ በደሎችን የፈጸመብንን ስርዓት ተሸክመን የምንጓዝበት ምን ምክንያት ሊኖር ይችላል? የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ ስርዓትና፣ ከህዉሃት-ኢህአዲግጋር አልቆረበም። በቃ።
አሁን ለደረስንበት የፖለቲካ ችግርና ዋናዉ መንስዔዉ ይህ የወያኔ አፋኝና ጨፍጫፊ ስርዓት ነው። ይህ ስርዓት በኢትዮጲያ ህዝብ ላይ የፈጸመው ወንጀል ራሱን ገፍቶ ሊያጠፋው ተቃርቧል። ስለዚህ ሁሉም ኢትዮጲያው በዘር በሃይማኖት ሳይከፋፈል በአንድ ላይ ተባብሮና ተነስቶ ይህን ግፈኛ ስርዓት ያስውግድ። ከዛ ዉጭ በችግሩ ምልክት ወይም እዚህም-እዛም ያሉ ግለሰቦች ላይ ያተኮረ፣ ያዝ-ለቀቅ የሆነ ትግል ወያኔወች የመሰረቱትን ስርዓት ዕድሜ ያራዝማል። ወያኔና ስርዓቱ አንገፍግፎናል። ይህ መሰሪ ስርዓት ፈርሶ በህግ የበላይነት የሚመራና፣ ለሁሉም ዜጎች መብት የቆመ ስርዓት መመስረት አለበት። ትግላችን የጥላቻንና የመከፋፈልን ፖለቲካ የሚዘጋና፣ የችግሩ ስርዎ-መንሰዔ ላይ ያተኮረ ይሁን። የኢትዮጲያ ህዝብ የአጋዚን ‘ስናይፐር’ ሳይፈራ መስዋዕትነት እየከፈለ ያለው፣ የተወሰኑ ትንንሽ ሌቦችን ከስልጣን ለማባረር ሳይሆን፣ ሃያ ስድስት ዓመታት እየጨፈጨፈ የገዛንን ስርዓትና በላዩ ላይ የሰፈሩትን ወንጀለኞች እስከመጨረሻዉ ለማስወገድ ነው። ይህን ስርዓት ለመጣልና ትግሉን ከግብ ለማድረስ፣ ኢትዮጵያዊያን በመተባበርና፣ ጥቃቅን ልዩነታቸውን ወደጎን በመተው፣ በአንድ ላይ ተነስተን የችግሩ ስርዎ-መንሰዔ  ላይ የተቀነባበረና ዘርፈ-ብዙና ስልታዊ እርምጃወችን ልንወስድ ይገባል። ይህ ህዉሃት የመሰረተዉ አፋኝና ከፋፋይ ስርዓት መወገድ አለበት። የኢትዮጵያ ህዝብ ክዚህ አስከፊ ስርዓት እስር ነፃ መዉጣት አለበት።
አንድነት ሃይል ነው

Ethiopia Is Falling Apart

Tepid reforms and halfhearted concessions won’t save the country’s authoritarian government from its existential crisis.

Mohammed Ademo and Jeffrey Smith
People protest against the Ethiopian government during Irreecha, the annual Oromo festival to celebrates the end of the rainy season, in Bishoftu on October 1, 2017.
An Ethiopian religious festival transformed into a rare moment of open defiance to the government one year after a stampede started by police killed dozens at the gathering. The Irreecha festival is held annually by the Oromos, Ethiopia’s largest ethnic group, which in late 2015 began months of anti-government protests over claims of marginalisation and unfair land seizures. / AFP PHOTO / Zacharias ABUBEKER (Photo credit should read ZACHARIAS ABUBEKER/AFP/Getty Images)
For a brief moment last week, Ethiopia seemed poised to shed its reputation as Africa’s Stasi state. At a press conference on Jan. 3, Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn vowed to free political prisoners and shutter the notorious Maekelawi prison, which has long served as a torture chamber for government critics, opposition leaders, journalists, and activists.
Desalegn’s announcement shocked Ethiopian citizens and observers alike. Initial reports indicated that the Ethiopian regime had finally accepted that mistakes had been made and serious abuses had been committed on its watch. Indeed, the stark admission would have marked the first time ever that Ethiopia had acknowledged holding political prisoners in the country. (Human rights groups have estimated that they number in the tens of thousands.)
The outpouring of optimism did not last long. Within hours, an aide to Desalegn clarified the prime minister’s remarks, saying that “mistranslation” by the media was to blame for the confusion. And indeed Desalegn’s actual comments in Amharic were less clear-cut. He spoke of the need to cultivate national reconciliation and to expand democratic freedoms, adding that “some political leaders and individuals whose crimes have resulted in court convictions or their ongoing trial” would be pardoned or have their cases withdrawn. A week after the press conference, it remains unclear how many people will be freed or when, if at all.
One fact remains clear, however. Following three years of escalating anti-government protests — mostly by the Oromo ethnic group and to an extent the Amhara, who together comprise two-thirds of the country’s 100 million people — Ethiopia can no longer afford to ignore demands for political reform. For years, the regime has sacrificed respect for basic political rights and civil liberties on the altar of economic growth. And its claims of a rapidly growing economy have always been dubious at best. The status quo can no longer hold.
A staunch U.S. ally in the war on terrorism, Ethiopia is seen as a stable oasis in the troubled Horn of Africa region, which is plagued by both extremist attacks and ruthless counterinsurgency operations. This image of stability has been cultivated by well-oiled lobbyists in Washington and by an army of social media trolls on the government payroll. However, despite the outward veneer of growth and stability, all is not well in Ethiopia.
In an effort to boost lagging exports, authorities devalued Ethiopia’s currency, the birr, by 15 percent last October. The country is also struggling to mitigate the effects of massive youth unemployment, high public debt, rising inflation, and a shortage of foreign currency. The economic woes that have beleaguered Ethiopia have fueled the increasing unrest. Amhara and Oromo protesters decry economic marginalization and systemic exclusion at the hands of powerful ethnic Tigrayan leaders. The economic dividends of the country’s modest growth are not broadly shared outside the wealthy business class and associates of the ruling party. To make matters worse, a long-simmering border disputebetween the Oromia and the Somali regions has left hundreds of people dead and more than 700,000, mostly from the Oromo ethnic group, internally displaced.
Taken together, these burgeoning crises have raised credible concerns about the risk of state collapse. And there are good reasons to be worried. Western donorsand foreign investors alike are increasingly jittery about the political uncertainty and growing popular unrest. In its annual Fragile States Index, which predicts risk of state failure, the Fund for Peace ranked Ethiopia 15th out of 178 countries surveyed, up from 24th in 2016.
Adding to the creeping sense of doom is an internal power struggle that is ripping apart the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF), which has been in power since 1991. The EPRDF is a coalition of four unequal partners, including the Amhara National Democratic Movement, the Oromo People’s Democratic Party (OPDO), and the Tigrayan People’s Liberation Front (TPLF). Ostensibly, each party is meant to represent the vested interests of its ethnic region within the EPRDF.
In theory, Ethiopia is a federation, based on decentralized ethnic representation. In practice, the federal system has for years enabled the domination of the country’s political space, economy, and security services by ethnic Tigrayans. The TPLF represents the Tigray region, home to only about 6 percent of the country’s population. Yet the party gets the same number of votes as the OPDO, which represents the roughly 40 percent of Ethiopians who are ethnic Oromos.
This inherent tension broke the surface in October 2016, when newly elected OPDO leaders began to openly embrace protesters’ grievances and calls for reform. This marked the first sign of a split within the EPRDF and set the stage for the ongoing power struggle over how to respond to the increasingly deadly and destabilizing Oromo protests.
The Oromo protest movement has amplified the OPDO’s voice within the EPRDF. At the press briefing held with Desalegn on Jan. 3, Lemma Megersa, the head of the OPDO and president of Oromia, accused TPLF officials of planting cronies inside his party and viewing political power as their own personal property. He made this claim in the presence of the TPLF chairman — a stunning public rebuke.
On the surface, the ruling coalition now appears open to correcting course. Instead of blaming its failures on terrorists, “anti-peace elements,” or diaspora-based opposition groups as the EPRDF has done in the past, Desalegn acknowledged the need for reform. To stop Ethiopia from falling apart, however, the government will need to go much further than the halfhearted concessions hinted at by the prime minister. It must undertake a host of long-overdue political and legal reforms, including dismantling the fusillade of draconian laws it has enacted over the last two decades to stifle dissent, decimate civil society, and muzzle the opposition.
A number of prominent Ethiopian opposition leaders, activists, and journalists — some of whom are expected to be freed after Desalegn’s remarks — have been unjustly detained and convicted under a noxious trio of laws, namely the Freedom of the Mass Media and Access to Information Proclamation, the Charities and Societies Proclamation, and the Anti-Terrorism Proclamation. To ensure that prisoners who are pardoned do not end up back behind bars, and to truly reckon with the abuses committed during the EPRDF’s 27-year rule, Ethiopia’s leaders should immediately begin dismantling the machinery of oppression by repealing and replacing those laws, which have been routinely condemned for failing to meet international standards.
In addition, to turn the page on its checkered past, the EPRDF regime — which now controls 100 percent of seats in parliament — must also implement a process of national reconciliation based on the principles of inclusivity and genuine political dialogue. In his Jan. 3 statement, Desalegn cited the need for social healing as a reason for the pardon of some prisoners. It was a historic moment. But for it to translate into real change, the country’s leaders must resolve to release all political prisoners without delay or preconditions; fully implement the country’s rarely applied but progressive constitution; ensure the independence and impartiality of the judiciary; end unchecked impunity for corrupt officeholders and security officials; and hold to account those responsible for the death and displacement of hundreds of Ethiopians.
No one expects change in Ethiopia to occur overnight. The reform process will undoubtedly be lengthy and fraught with potential obstacles. But to rescue the country from the undue weight of its own repression, EPRDF leaders have no choice but to change course.
Like this article? Read an unlimited number of articles, plus access to our entire 47-year printed archive, the FP App, and the Digital Magazine when you subscribe to FP Premium for just 99 cents!