fredag 29. august 2014

በጥፍሩም በጥርሱም ለስልጣን የሚተጋ መንግሰት …… እንዴት እንታገለው!! – ከግርማ ሰይፉ ማሩ

በጥፍሩም በጥርሱም ለስልጣኑ የሚተጋን መንግስት በሁሉን አቀፍ ትግል መጣል አለብን ብለው ጠብ መንጃ ቢያነሱ ክፋቱ ምን ላይ እንደሆነ አልታይህም እያለኝ ነው፡፡ ለምን በጠብ መንጃ ፍልሚያ ስልጣን መያዝ እንዳለብኝ በግሌ ባይገባኝም አሁን ግን የኢህአዴግ ዓይነት መንግሰት ከደርግ እንዴት እንደሚሻል ማሰብ እያቃተኝ ነው፡፡ የሰላማዊ ትግል ሰራዊት እንዴት እንገንባ ለሚለው ጥያቄ አፋጣኝ ምለሽ ካልሰጠን በስተቀር መንግሰት በግልፅ እየደገፈ ያለው በጠብ መንጃ ሊገዳደሩ የፈለጉት ነው፡፡ በሰላም ያልነውን ሰላም እየነሳን ይገኛል፡፡ መንግሰት ሆይ ሰላም እንድትሆን ሰላም ሰላም ለምንል ዜጎች ሰላም ሰጠን የምር የቀረበ ጥያቄ ነው፡፡
በፍትሕ አደባባይ የፈለገውን ማድረግ የወሰነ መንግሰት በእጅ አዙር ደግሞ በየማተሚያ ቤቱ እየሄደ መፅሄትና ጋዜጣ ታትሙና ወዮላችሁ ማለት ተያይዞታል፡፡ ይህ ከህግ ሰርዓት ውጭ በየማተሚያ ቤቱ በግንባር እና በስልክ የሚደረገው ማሰፈራሪያ ከወሮበላነት ውጭ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡ መንግሰት ለህዝብ ጥቅም ሲባል ክስ መስርቻለሁ ብሎዋል፡፡ ህዝቡ የሚለው ግን ሌላ ነው፡፡ መፅሄት መቼ ነው የሚወጣው ነው፡፡ በቃ!!! ፍርድ ቤት በመፅሔትና ጋዜጦች ላይ ቢፊልግ እግድ ቢፈልግ ይዘጉ እሰኪል ድረስ ምን የሚያጣድፍ ነገር መጥቶ እንደሆነ ባናውቅም የመንግሰት አሽከሮች በየጉራንጉሩ ባሉ ማተሚያ ቤቶች ደጃፍ እየዞሩ ማሰፈራራት ተያይዘውታል፡፡ ሹሞቻችን ይህን አላደረግንም ብለው እንደሚክዱ ባውቅም ይህን ዓይነት ወሮበላነት ማስቆም ካልቻሉ ተጠያቂ እንደሚሆኑ መርሳት የለባቸውም፡፡ ስህተታችውን በአደባባይ ተችተን እንዲታረሙ የሚሰጣቸው ምክር ካንገሸገቸው የመጨረሻው ቀን ሲመጣ እንደሚጠየቁ ግን ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ የወሮበላ አለቃነት ከወሮበላነት በላይ የሚያስጠይቅ ነው፡፡ እነዚህን ወሮበላዎች አስቁሙልን ግልፅ አቤቱታ ነው፡፡ በየሳምንት ብዙ መቶ ሺ ብር ገቢ ያገኙ የነበሩ ማተሚያ ቤቶች በህጋዊ መስመር ሳይሆን በስልክና በቃል ከወሮበሎች በሚሰጥ ማሰፈራሪያ አጅ መስጠት እና ገበያ ማባረር ደግሞ የሚያስመሰግን ፍርሃት እንዳልሆነ ልብ ሊሉት ይገባል፡፡ የእያንዳንዳችን ፍርሃት ተደምሮ ነው እነርሱም ያለምንም ይሉኝታ ሊያሰፈራሩን ቤታቸውን ድረስ የሚመጡት፡፡ በወረቀት ትዕዛዝ ይድረሰኝ ለማለት ወኔ የሌለው ማተሚያ ቤት የሙት ዓመትና ተዝካር ወረቀት ሲያትም ይኖራታል፡፡
መንግሰት በሚዲያዎች ላይ በዶክመንተሪ ጀምሮት የነበረውን ወደ ፍትህ አደባባይ ያመጣውን የግል ሚዲያ አሁንም ገና አልበቃውም፡፡ በጥፍርም በጥርስም ሊዘለዝል እየባተተ ይገኛል፡፡ ኢትቪ ቤታችን ድረስ መጥቶ ለሆዳቸው ባደሩ ምሁራን ተብዬዎች እና ሹመኞች ሲሳደብ ያመሻል፡፡ የኮሚኒኬሸን ጉዳዮች መስሪያ ቤት ውስጥ ዳይሬክተር ናቸው የተባሉ ታምራት ደጀኔ የሚባሉ ኃላፊ መሰሪያ ቤቱ የመንግሰት ደሞዝ የሚከፈላቸው እኔ ጭምር በምከፍለው ግብር መሆኑን ዘንግተው የግል ፕሬስ ከተቃዋሚዎች ጋር ወግኖ እየሰራ ነው ብለው ከገዢው ፓርቲ ጎን ቆመው ሲከሱን አምሽተዋል፡፡ እኚህ ግለስብ ከተቃዋሚ ጎን መሰለፍ ማን ሀጥያት ነው እንዳላቸው አላውቅም፡፡ ተቃዋሚዎች በህግ ተመዝግበው የሚሰሩ ተቋማት እንደሆኑ እና የሚደግፋቸውም የሚቃወማቸውም ሰዎቸ መኖራቸው የሚጠበቅ መሆኑን ዘንግተውታል፡፡ ለነገሩ እርሳቸው የሚደግፉት ፓርቲ ነገ ተቃዋሚ የሚባል ወንበር ላይ ሊኖር እንደሚችል በተሰፋ ደረጃ ማሰብ አልቻሉም፡፡ ለነገሩ ኢህአዴግ በጥቅም የተገዙ አባላቶቹ ስልጣን ሲያጣ አብረውት እንደማይቆዩ ይረዳዋል- እርሳቸውንም ጨምሮ ማለቴ ነው፡፡ ለዚህም ነው ኢህአዴግ በጥርስም በጥፍርም ፍልሚያ ውስጥ የሚገባው፡፡ አቶ ታምራት ደጀኔ እንዲረዱ የምፈልገው የግሉ ፕሬስ ተቃዋሚን ቢደግፍ አንድም ነውር እንደሌለው ይልቁንም ገዢውን ፓርቲ ለመደገፍ ገዢው ፓርቲ ብቁ እንዳልሆነ ማሳያ ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ በገንዘብ የሚደግፋቸው ነገር ግን ተደግፈው መቆም የማይችሉ “የግል” ተብዬ ሚዲያዎች እንደነበሩ መርሳት የለባቸውም፡፡ ለምሳሌ ኢፍቲን፣ ዛሚ፣ ወዘተ
ሰኞ ነሃሴ 19/2006 በቀረበው ዶክመንተሪ ተብዬ ዘባተሎ ላይ ከለየላቸው የመንግሰት ሹሞኞች እስከ ዩኒቨርሲት መምህራን አልፎ ተርፎም አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴን ያሳተፈ ነበር፡፡ እርገጠኛ ነኝ ሀይሌ በሚዲያ ላይ ስለሚታዩ ግድፈቶች አጠቃላይ ሁኔታ ነበር የሚናገረው እንጂ አሁን ክስ ስለተመሰረተባቸው የግል ሚዲያዎች አልነበረም፡፡ ቆርጦ ቀጥሉ ኢቲቪ ግን ከህዝብ ጋር ሊያጋጨው ፍላጎቱን አሳይቶዋል፡፡ ሌላው ተዋናይ ዶክትረ አሸብር ወልደጊዮርጊስ ነበሩ፡፡ ከብዙ ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ነበር መልስ አሰጣጣቸው፣ የከሰሱትም ሪፖርተርን ነው፡፡ መንግሰት ደግሞ ከሪፖርተር ጋር ጉዳይ የለውም፡፡ እንዲከሱ ሲጠበቅ የነበረው ሌላ ነበር፡፡ ይቅር ብያለሁ ብለው አልፈውታል፡፡ የእርሳቸው ይቅር ባይነት ከመንግሰት ሰፈር ሊገኝ አልቻለም፡፡ ተበቃይ መንግሰት ለስልጣኑ ሲል በጥፍሩም በጥርሱም ከግል ሚዲያው ጋር ግብ ግብ ገጥሞዋል፡፡ ማን ያሸንፋል አና መቼ ወደፊት የሚታይ ነው፡፡
የቀረበውን ዘጋቢ ፊልም ማስታወሻ ይዜ ለሁሉም በስማቸው አንፃር ለመፃፍ ነበር የፈለኩት ይህን ዘባተሎ የበዛበት ድሪቷም ዘጋቢ ተብዬ ከዚህ በላይ ማለት ተገቢ ሆኖ ስለአልተመቸኝ ተውኩት …. ይህ ዘጋቢ ፊልም ተብዬ የተሰራበት ሙሉ ዶክመንት ለታሪክ እንደሚቀር ተሰፋ አለኝ፡፡ የዛን ጊዜ እንወቃቀሳለን፡፡ ምሁራን ተብዬዎች በእናንተ ተሰፋ ቆርጠናል ….. በእናንተ መምህርነት አንድም የተሻለ ጋዜጠኛ እንደማናገኝ፡፡ ለነገሩ ልጆቹ የአስተማሪዎች ብቻ ሳይሆን የእኛም ናቸው እና በቤታችን ይማራሉ፡፡ ሀገር ማለት ልጄ ብለን እናስተምራለን፡፡

አወዛጋቢው የአወልያ ት/ቤት እና የልማት ድርጅት በቦርድ እንዲተዳደር ተወሰነ

ላለፉት ሶስት ዓመታት እያወዛገበ ያለው የአወልያን ትምህርት ቤት እና ልማት ድርጅት ማን ያስተዳድረው የሚለው ጥያቄ መፍትሄ እንደተገኘለት ትላንት ለጋዜጠኞች በተሰጠ መግለጫ ተገለጸ:: ከዚህ በፊት በቀድሞ የእስልምና ምክር ቤት ውሳኔ የአወልያን የልማት ድርጅት ያስተደደር የነበረው አለም ዓቀፉ የእስልምና ድርጅት ሲታገድ የልማት ድርጅቱ በምክር ቤት እንዲተዳደር መደረጉ የሚታወስ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙ ይህንን ውሳኔ በመቃወም ከፍተኛ የሆነና ሰላማዊ ተቃዉሞውን ላለፉት ሶስት ዓመታት ሲያሳዩ ቆይተዋል፡፡
Addis_august8_2013_11
ከተቃውሞው በተጨማሪ ኮሚቴዎች በመምረጥ በአወልያ ጉዳይ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊ ጋርም ውይይቶችን ጀምረው እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይህም ባለመሳካቱ እና በህዝበ ሙስሊሙ የተመረጡት የሰላም አፈላላጊ ኮሚቴዎች በመንግስት ቁጥጥር ሲውሉ ተቃወሞ በከፍተኛ ሁኔታ እንደተባበሰ እና የአውልያ ትምህርት ቤት በእስልምና ምክር ቤት መተዳደር የለበትም፣ የአወልያን የልማት ድርጅት ነፃ የሆነ ገለልተኛ ወገን ሊመራው ይገባል፣መጂሊሶቹ አይወክሉንም፣ የታሰሩት የሰላም አፈላላጊ ኮሚቴዎች ይፈቱ የሚል የተቃውሞ ድምጾችን ላለፉት ሶስት ዓመታት እያሰሙ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በቅርቡም በታላቁ የአኑዋር መስጊድ ህዝበ ሙሰሊሙ ከጸሎት(ሶላት) ቦኃላ ተቃውሞቻውን እያሰሙ ባለበት ወቅት በመንግስት ሀይሎች ከፍተኛ የሆነ ድብደባ እና እስር እንደተፈጸመባቸው በተለያዩ የዜና ዘገባዎች እና ማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የወጡት ምስሎች ያሳያሉ፡፡
Addis_august8_2013_22
በትላንትናው ዕለት የእስልምና ምክር ቤቱ ፕረዝዳንት የሆኑት ሼክ ኪያር መሀመድ አማን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የአወልያ ጉዳይ መፍትሔ ማግኘቱን ገልጸዋል፡፡ የአወልያ ጉዳይ ተቃውሞ ያስነሳው የቀድሞ የምክር ቤቱ አመራሮች በአወልያ ትምህርት ቤት መምህራን እና ተማሪዎች ላይ የህዝቡን ስሜት ባለመረዳት በወሰዱት ተገቢ ያልሆነ እርምጃ ምክንያት ተቃውሞ ሊነሳ ችሏል ብለዋል፡፡ አያይዘውም በአሁን ጊዜ ግን በህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ መሠረት አወልያ በቦርድ እንዲተዳደር ሆኗዋል ብለዋል፡፡ ቦርዱም የእስልምና እውቀታቸውን እና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ባላቸው ምሁራን፣ ባለሀብቶች እንዲሁም ከክልል እና ከፌዴራል የእስልምና ምክር ቤቶች በተወጣጡ ሰዎች ቦርዱ መመሥረቱን ገልጸዋል፡፡
የእስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት በዓመት ከ7 ሚሊዮን ብር እሰከ 10 ሚሊዮን ብር መድቦ ለመምህራን ደሞዝ እና ለትምህርት ቤት ወጪ እንደሚያደርግ ሲገለጽ በአሁኑ ውቅትም የአወልያ ልማት ድርጅት ዓመታዊ በጀቱ 20 ሚሊዮን ብር እንደተደረገ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የአወልያ የልማት ድርጅት በውስጡ ጤና ጣቢያ ፣ትምህርት ቤት እና ሌሎች ተቋማት ያሉት ሲሆን በትምህርት ቤቱም 2500 ለሚሆኑ ተማሪዎቸ ትምህርት ይሰጣል፡፡ ከነዚህም ተማሪዎች 500 የሚሆኑትን በነፃ የሚያስተምር ሲሆን ከ125 ተማሪዎቹ ደግሞ ግማሽ ክፍያን ሲቀበል ከቀሩት ተማሪዎች ግን ሙሉ ክፍያውን ይቀበላል፡፡
የአወልያ የልማት ድርጅት በቦርድ እንዲተደደር ከእስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት መወሰኑን እንዴት እንደተመለከተው ጥያቄ ያቀረብኩለት የቀድሞ የአውልያ ትምህርት ቤት ተማሪ የነበረው ሰኢድ “መጅሊሱ/ምክር ቤቱ ይህን ውሳኔ ለመወሰን በጣም ዘግይቷል ቢሆንም አውልያ በቦርድ እንዲተደደር መወሰኑ እንዳስደሰተው ተናግሯል፡”፡ ሌላው አሰተያየቱን የሰጠኝ የአወልያ ተማሪ የነበረና በረብሻው ምክንያት ትምህርቱ እንዳቆም የነገረኝ መኑር የተባለ አሰተያየት ሰጪ “ይሕ ውሳኔ የመጀሊሱ ሳይሆን የመንግስት ነው፡፡ ምክንያቱም መጀመሪያም መንግስት ነው ይህ ሁሉ እንዲፈጠር ያደረገው አሁንም ሁኔታዎችን መቆጣጠር ሲያቅተው ለማረጋጋት እና ህዝበ ሙስሊሙ ለጥያቄያቸው መልስ አግኝተዋል ብሎ ለማውራት እንዲመቸው ያደረገው ነው ፡፡” ሲል የግል አሰተያየቱን ለአዲስኒውስ ሰጥቷል፡፡
የሆነው ሆኖ ከህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች መካከል አንዱ የሆነው የአወልያ ጉዳይ በቦርድ እንዲተዳደር ተወስኗል፡፡ በእርግጥ ህዝብ ሙስሊሙ ይህን ውሳኔ ተቀብሎታል? ተቃዎሞንስ በዚህው ያበቃል? እርስዎስ ይህ ውሳኔ የሙስሊሙን ጥያቄ ይፈታል ወይስ ሌላ የመንግስት ማረጋጊያ ዘዴ ነው ብለው ያስባሉ? እነዚህ ጥያቄዎች በሚመጡት የጁማዓ ቀናት መልስ የምናገኝላቸው ይሆናሉ፡፡

mandag 25. august 2014

ኦህዴድ በየደረጃው ያሉ አመራሪዎችን ለአስቸኳይ ስብሰባ ጠራ

በሁሉም የኦሮምያ ክልሎች  በሚገኙ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች፣ የግብርና ዋና እና ምክትል
ሃላፊዎች፣ የሴቶች ጽ/ቤት ፣ መሬት ጥበቃ ፣ ሲቪል ሰርቪስ እና መልካም አስተዳደር ፣ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፣ ውሃና ማእድን፣ ገጠር መንገድ ፣ ጥቃቅንና
አነስተኛ ጽ/ቤት ፣ ገንዘብና ኢኮኖሚ ፣  ትምህርት/ጽ/ቤት፣ እና  የወጣቶችና ስፖርት ሃላፊዎች ከነገ ጀምሮ ለአስቸኳይ ስብሰባ እንዲከቱ ተደርጓል። አስቸኳይ
ስበሰባው ለምን እንዳስፈለገ ባይታወቅም፣ ሰሞኑን ኢህአዴግ እያደረገ ካለው ግምገማ እንዲሁም በድርጅቱ ውስጥ የሚታዩትን ችግሮች ከመገምገም ጋር ሊያያዝ
እንደሚችል ምንጮች ጠቁመዋል።

የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ራሳቸውን እያገለሉ ነው

የኮንዶምኒየም ቤቶች በወቅቱ ዕጣ ወጥቶ ለሕብረሰቡ ማስተላለፍ ካለመቻሉ ጋር ተያይዞ ቆጣቢዎች
በመሰላቸትና ተስፋ በመቁረጥ ከፕሮግራሙ ራሳቸውን እያገለሉ መሆኑ ተሰምቷል።
የአዲስአበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ዋና ስራአስኪያጅ አቶ መስፍን መንግሥቱ ሰዎች በተለያየ ምክንያት እየለቀቁ መሆኑን አምነው ነገር ግን ከተስፋ መቀረጥ
ጋር እንደማይገናኝ ለመንግሥት መገናኝ ብዙሃን አረጋግጠዋል፡፡ እንደእሳቸው ገለጻ በድጋሚ ከተመዘገቡ 993ሺህ የኮንዶምኒየም ፈላጊዎች መካከል 7ሺ ያህሉ
በገዛ ፈቃዳቸው ፕሮግራሙን በማቋረጥ የንግድ ባንክን የቁጠባ ደብተር መልሰዋል፡፡
የፌዴራል መንግሥት ከቁጠባ የተሻለ ገንዘብ ለመሰብሰብ ከያዛቸው ፕሮግራሞች አንዱ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ቁጠባ ሲሆን ይህንኑ ተከትሎም የአዲስአበባ ከተማ
አስተዳደር ከአንድ ዓመት በፊት በድጋሚ ባካሄደው የመኖሪያ ቤት ፈላጊዎች ምዝገባ መሠረት ተመዝጋቢው በየወሩ የተወሰነለትን ገንዘብ በንግድ ባንክ በኩል
እንዲቆጥቡ፣ ይህን መቆጠብ ያልቻሉ የቤት ባለቤት መሆን እንደማይችሉ በደነገገው መሠረት በርካታ ነዋሪዎች ገንዘብ ማስቀመጥ ጀምረው ነበር፡፡ ነገር ግን ቤቶቹ
መቼ እንደሚተላለፉ አለመታወቁ፣ ከዚህም በተጨማሪ መንግሥት ቀድሞ የገባውን ቃል ማለትም ቤቶቹ የሚተላለፉት በዕጣ ብቻ ነው የሚለውን በሚሸረሽር መልኩ
ለፖለቲካ ዓላማው ሲል ቤቶቹን አንዴ ለመንግሥት ሠራተኛች  ሌላ ጊዜ ለሹማምንቱ ቅድሚያ እሰጣለሁ በማለት በፈለገው ጊዜ እያነሳ የሚሰጥበት አሰራር መስፈኑ
ቆጥቤ የቤት ባለቤት እሆናለሁ የሚለው ተስፋ እንዲጨልም ማድረጉን ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ብዙ ሰዎች ቤቱን ላላገኝ የመንግሥት ፕሮፖጋንዳ መሳሪያ አልሆንም በሚል ከቁጠባው በመሸሽ ላይ ሲሆኑ የተወሰኑት ደግሞ ጨርሶ ከፕሮግራሙ
ራሳቸውን ማግለል መጀመራቸው ታውቋል፡

fredag 22. august 2014

የጠ/ሚንስትር ጽ/ቤት በሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ

ኢህአዴግ ምንጮች እንደገለጹት በሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሃመድ ኡመር እና
በክልሉ የካቢኔ አባሎች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ተከትሎ በጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጽ/ቤት በተካሄደው አስቸኳይ ግምገማ ፣ ፕሬዚዳንቱ
ፈጸሟቸው የተባሉ በርካታ ወንጀሎች ተዘርዝረው ቀርበዋል።
አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በሰብሳቢነት በመሩት ግምገማ ላይ ም/ል ጠ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የጠ/ሚኒስትሩ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ አለቃ ጸጋየ በርሄ፣
የደህንነት ምክትል ሹሙ ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ፣ የምስራቅ እዝ ዋና አዛዥ ጄኔራል አብርሃ በቅጽል ስማቸው ኳታር፣ የፌደራልፖሊስ ወንጀል መከላከል ሃላፊ
ጄ/ል ግርማየ መንጁስ፣  አቶ አዲሱ ለገሰ፣ አቶ አብዲ መሃመድና የተለያዩ የክልሉ የካቢኔ አባላት እንዲሁም ሌሎች 2 የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮችም
ተገኝተዋል። አቶ አብዲ ስልጣን ከያዙ ጀምሮ  እሳቸው በሚመሩት ሚሊሺያ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች  በተለያዩ ምክንያቶች መገደላቸውን፣ በርካታ
ሲቪሎች ታስረው ህክምና ሳይገኙ በቀላፎ፣ በፌርፌርና በሌሎችም እስር ቤቶች እንዲሞቱ ማድረጋቸው፣ ከመንግስት የተመደበውን ግዙፍ  በጀት ለአንዳንድ
የፌደራል ባለስልጣናት በተለይም ለጄ/ል አብርሃ ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ ወቅቶች እንዲሰጣቸው በማድረግና በተለያዩ መንገዶች በብዙ መቶ
ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እንዲዘርፍ ማድረጋቸው እንዲሁም ከ20 ቀናት በፊት የአገር ሽማግሌዎችን በመሰብሰብ በአንቀጽ 39 መሰረት የራሳችንን  መንግስት
ስለምናውጅ ለዚህ ታሪካዊ ክስተት ራሳችሁን አዘጋጁ፣ ፌደራል መንግስትም በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ መግባት አይችልም ብለው መናገራቸው፣ የልዩ ፖሊስና የጎሳ
አባላቱ ከፍተኛ ገንዘብ እንዲዘርፉ ማሰማራታቸው፣ በክልሉ የሚካሄዱትን ትላልቅ ፕሮጀክቶች ያለ ጫራታ በመስጠት ሆን ብለው ለብዝበዛ አዘጋጅተዋል የሚል
ግምገማ ቀርቦባቸዋል።
በግምገማው ወቅት ጄ/ል አብርሃ በአቶ አብዲ ላይ የቀረበውን ግምገማ አጥብቀው ተቃውመዋል። አቶ አብዲ ” ምነው መለስ በኖረ” የሚል ቃል ከመናገራቸው
ውጭ ምንም አይነት መልስ ሳይሰጡ ግምገማው ተጠናቋል። አቶ ሃይለማርያም የአቶ የአብዲን ተቀናቃኞች ሰብስበው ያነጋገሩ ቢሆንም፣ ስለሚወሰደው እርምጃ
ምንም ሳይሉ ቀርተዋል።
አቶ አብዲ ከደህንነቱ ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋና ከአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ  ጋር ውዝግብ ውስጥ የገቡ ሲሆን፣ አቶ ሃይለማርያም እርሳቸውን ለመገምገም ስልጣን
እንደሌላቸው በተደጋጋሚ ሲነጋሩ ይሰማል። የአቶ አብዲ ጉዳይ የህወሃት ባለስልጣናትን ለሁለት መክፈሉ  ታውቋል።

በባቲ ኦሮሞዎች እና የአጎራባች አፋር ክልል ነዋሪዎች ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉ ተሰማ

በባቲ ወረዳ ልዩ ስሙ ቡርቃ በተባለ ቀበሌ አካባቢ የሚኖሩ የሁለቱ አጎራባች ክልሎች
ነዋሪዎች በተለያዩ ጊዜያት በተኩስ እየተጋጩ በሁለቱም ወገን ሰዎች እየሞቱ ቢሆንም ፤የሁለቱ ክልል መሪዎች ጉዳዩን ለመፍታት ምንም ዓይነት
ጥረት አለማድረጋቸው እንዳሳዘናቸው የባቲ ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
በቡርቃ  ቀበሌ  የተቀበረ ወርቅ አለ ተብሎ መነገሩ ለግጭቱ መባባስ ምክንያት መሆኑን የሚናገሩት የአይን እማኞች፣ የኦሮምያ ዞን መሬቱን
ለባላሀብቶች ሰጥቶ በማስቆፈርላይእያለበአካባቢውየሚኖሩትየአፋርተወላጆችድርጊቱንበመቃወምበቁፋሮበተሰማሩትሰራተኞችላይተኩስ ከፍተው
ጉዳት ማድረሳቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በተኩስልውውጡምቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ከመገደላቸውም በተጨማሪበንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን አክለው ተናግረዋል።
አካባቢውን በግል የተደራጁ የአፋር ታጣቂዎች የተቆጣጠሩት ሲሆን የባቲ ወረዳ የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊዎች ችግሩን ለመፍታት ቦታውን ከተቆጣጠሩ
ታጣቂዎች ጋር ቢነጋገሩም ታጣቂዎች ማንኛውንም ትእዛዝ ከአፋር መንግስት እስካልመጣ ድረስ  አንነጋገር ምበማለታቸው በአጎራባች ክልሎቹ
የጠረፍ ከተሞች መካከል ሊካሄድ የነበረው የሰላም ውይይት በተደጋጋሚከሽፏል።
የሁለቱ ክልል መንግስታት አመራሮች ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው ለመፍታት ባለመፈለጋቸው ነዋሪዎቹ ወቀሳ አቅርበዋል።
በሁለቱ ክልል ድንበር ያለው ውጥረት ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ እንደቀጠለ መሆኑን የአይን እማኞች ለዘጋቢችን ገልፀዋል፡፡

torsdag 21. august 2014

ሰማያዊ ፓርቲ “ለተማሪዎች በግዳጅ የሚሰጠውን ካድሬያዊ ስልጠና እና ትውልድን የማኮላሸት ሴራ አጥብቀን እናወግዛለን!” አለ

ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ ባወጣው መግለጫው ለተማሪዎች በግዳጅ እየተሰጠ ያለውን ካድሬያዊ ስልጠና በማውገዝ ኢሕአዴግ እየሰራ ያለውን ትውልድን የማኮላሸት ሴራ አጥብቀን እናወግዛለን አለ። መግለጫው እንደወረደ እነሆ፦
blue partyላለፉት 23 ዓመታት ህወሓት/ኢህአዴግ ስራዬ ብሎ ካዳከማቸውና ጉዳዬ ከማይላቸው ዘርፎች ውስጥ የሚመደበው የትምህርት ስርዓቱ ሲሆን ይህም ከኢህአዴግ ስህተቶች ሁሉ ዋነኛው እና አሳፋሪ ተግባሩ ነው፡፡ ለሁለት አስርት አመታት ትውልዱን በማምከን በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ከገፉት ጉዳዮችም ግንባር ቀደሙ የህወሓት/ኢህአዴግ የተምታታበት የትምህርት ፖሊሲ መሆኑም ይታወቃል፡፡ ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገት የጀርባ አጥንት መሆኑ እየታመነ የትምህርት ስርዓቱ ሆን ተብሎ በንቀት እና በዝርክር አሰራር እንዳያድግና ጥራት እንዳይኖረው ኢህአዴግ እየተጋ አሁን ድረስ ዘልቋል፡፡
በዚህ አይነቱ አጥፊ አካሄድ ምክንያትም ሀገራችን በዓለም ደሃ ሀገራት ተርታ ቀዳሚዋ ሆናለች፡፡ የተማረ እየተገፋ በስራ አጥነት ሲንከራተት እና ለስደት ሲዳረግ በካድሬነት የስርዓቱ አገልጋይ መሆን ደግሞ በተቃራኒው ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡ በተለይም ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው የገዢው ፓርቲ አባል እንዲሆኑ ሲገደዱ መቆየታቸውና የኢህአዲግ አባል ካልሆኑም ስራ ሊያገኙ እንደማይችሉ እየተነገራቸው በፍራቻ ለአባልነት የተመዘገቡ ብዙዎች እንደሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ በዚህ ሳያበቃ አሁን አሁን ደግሞ የገዢውን ፓርቲ ያረጀና ያፈጀ ኋላቀር አስተሳሰብና ርዕዮተ-ዓለም በተማሪዎች ላይ ለመጫን በየዓመቱ መጀመሪያ ‹ስልጠና› በሚል ፈሊጥ በጀት በጅቶ በግድ ሊግታቸው እየሞከረ ይገኛል፡፡
በዚሁ በያዝነው ወርም በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች እንዲሰበሰቡና ስልጠና እንዲወስዱ ጥሪ የተላለፈ ሲሆን ስልጠናውን ያልተከታተለም መደበኛ ትምህርቱን እንደማይቀጥል ማስፈራሪያ አይሉት ማሳሰቢያ በገዢው ፓርቲ በኩል ተላልፏል፡፡ ሌላው አስገራሚ ዜና ደግሞ ተማሪዎቹ በግድ ስልጠናውን እንዲወስዱ መገደዳቸው ሳያንስ ወደ ግቢ ከገቡ በኋላ ተመልሰው መውጣት እንደማይችሉ መሰማቱ ነው፡፡ ይህም ኢህአዴግ ካድሬዎቹን የሚያሰለጥንበት ዝግ የስብሰባ ስልት መሆኑ ጉዳዩን የበለጠ አስገራሚ ያደርገዋል፡፡
ህወሓት/ኢህአዴግ ይህንን ስልጠና ሲያካሂድም፡-
1. ህግን በጣሰ መልኩ የትምህርት ማዕከላትን የፖለቲካ ማራመጃ እና የአንድ ፓርቲ ርዕዮተ-ዓለም ማስፈፀሚያ አድርጓል፡፡
2. ይህን ፋይዳ ቢስ ስልጠና በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎችና ከ800.000 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች በሚሰጥበት ወቅት ከፍተኛ የህዝብ ሀብት እያባከነ ይገኛል፡፡
3. ተማሪዎች የእረፍት ጊዜያቸውን በነፃነት ማሳለፍ ሳይችሉ በአስቸኳይ ወደ ዩኒቨርስቲዎች እንዲመለሱ ተገድደዋል፡፡
4. በሚሰጠው ስልጠናም ላይ በአክራሪነት በብሔርተኝነትና በመሳሰሉት ጉዳዩች ሽፋን በተማሪዎች ዘንድ መርዛማ ጥላቻን እየረጨ ይገኛል፡፡
5. በአጠቃላይ በስልጠናው ወቅት ርካሽ የፕሮፖጋንዳ ስልትን በመጠቀም መጪውን ምርጫ በማምታታት ለማለፍ እየሞከረ ሲሆን ይህም በአምባገነንነቱ ቀጥሎ ህብረተሰቡን አማራጭ ለማሳጣትና ሀገሪቷን ወዳልተፈለገ አለመረጋጋት ሊወስድ እየሞከረ መሆኑን ያሳያል፡፡
በመሆኑም ሰማያዊ ፓርቲ ይህን የገዢው ፓርቲ ህገ ወጥ አድራጎት አጥብቆ እያወገዘ ጉዳዩን እየተከታተለም አቋሙን ይፋ የሚያደርግ መሆኑንን ይገልፃል፡፡ ተማሪዎችም በዚህ ህገ ወጥ ተግባር ሳይደናገጡ ያለምንም ፍርሃት ህጋዊ በሆነ መንገድ ይህን ካድሬያዊ ስልጠና በማውገዝ፣ የገዢውን ፓርቲ ድብቅ ሴራ በማጋለጥ እና ለህወሓት/ኢህአዴግ የተለመደ አጥፊ ፕሮፖጋንዳ ባለመታለል ተማሪዎች በአንድነት እንዲቆሙ ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ነሀሴ 15/2006 ዓ.ም ሰማያዊ ፓርቲ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

መለስን ቅበሩት! – ተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

ከኢትዮጵያ ሀገሬ የደቀቀ ኢኮኖሚ ላይ በማን አህሎኝነት ወጪ ተደርጎ፣ ቅጥ ባጣ መልኩ በመላ አገሪቱ እየተከበረ ስላለው የቀድሞ አምባገነን ጠ/ሚኒስትር ሁለተኛ ሙት ዓመት ዝክርም ሆነ ሰውየውን ዛሬም በአፀደ-ህይወት ያለ ለማስመሰል እየሞከሩ ላሉት ጓዶቹ አንዲት ምክር ብጤ ጣል ማድረጉ ተገቢ ነው ብዬ ስለማስብ በአዲስ መስመር እንዲህ እላለሁ፡-
yemeles amelekoአብዮታዊው ገዥ-ግንባር ግንቦት ሃያ፣ የህወሓት ምስረታ፣ የብአዴን አፈጣጠር፣ የኦህዴድና የደኢህዴን ውልደት፣ የብሔር ብሔረሰቦች በዓል፣ የባንዲራ ቀን፣ የመከላከያ ሳምንት፣ የፍትሕ ሳምንት፣ የሕዳሴ ግድብ መሰረት ድንጋይ የተጣለበት… ጅኒ-ቁልቋል እያለ ዓመቱን ሙሉ በማይጨበጥ ተራ ፕሮፓጋንዳ ማሰልቸትን መንግስታዊ ኃላፊነት አድርጎታል፡፡ ይህ እንግዲህ ለቁጥር የሚያታክቱ፣ በነጭ ውሸት የታጨቁ እና በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ቅኝት የተንሸዋረሩ ‹ዶክመንተሪ ፊልሞቹ›ን ረስተንለት ነው፡፡
ይህ ሁሉ ያልበቃው ‹‹ጀግናው›› ኢህአዴግ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈት ወዲህ፣ ወርሃ-ነሐሴንም እንደ ግንቦት ሃያው ሁሉ የሟቹን ታጋይነትና አብዮታዊነት፤ ሕዝባዊነትና አርቆ አስተዋይነት፤ የርዕዮተ-ዓለም ተራቃቂነትና የአየር ንብረት ተካራካሪነት፤ በፖለቲካ ቢሉ በኢኮኖሚ ቁጥር አንድ ጠቢብነትና ባለራዕይነት፤ ፍፁም ፃድቅነትና ሰማዕትነት…. የሚተረክበት ሲያደርገው ቅንጣት ታህል ሀፍረት አልተሰማውም፡፡ ሰሞኑን በ‹‹ኢትዮጵያ›› ቴሌቪዥን ግድ ሆኖብን ተመልክተንና ሰምተን በትዝብት ካሳለፍናቸው ‹‹መለስ፣ መለስ›› ከሚሉ የከንቱ ውዳሴ አደንቋሪ ድምፆች በተጨማሪ፣ የኦሮሞን ባሕላዊ ልብስ ሲያለብሱት፣ ሐረሪዎች ጋቢ ሲደርቡለት፤ በደቡብ የሚገኙ ብሔሮች የየራሳቸውን ባሕል የሚወክሉ አልባሳት ሲሸልሙት፣ ስለወላይታነቱ ሲመሰክሩለት… ደጋግመን ለመመልከት ተገደናል፤ ይሁንና ድርጅቱ ስለ ቀድሞ ሊቀ-መንበሩ አልፋና ኦሜጋነት ለመስበክ ዙሪያ ጥምዝ ከዳከረለት ከእንዲህ አይነቱ የተንዛዛ ፕሮፓጋንዳ ይልቅ፣ በዚሁ የቴሌቪዥን መስኮት የቀረበ አንድ ጎልማሳ ‹‹መለስ ሁሉም ማለት ነው›› ሲል የሰጠው አስተያየት፣ ቅልብጭ አድርጎ ይገልፅለት ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ የዚህ አይነቱ ምጥን አስተያየትም በጥራዝ ነጠቅነት ዘላብዶ የኋላ ኋላ በሀፍረት ከማቀርቀር ያድናል፡፡ ለምሳሌ እናንተ የግንባሩ ካድሬዎች ስለመለስ ምሁርነት ለመናገር ስትዳዱ ሁሌ የምትደጋግሙት፣ ያንኑ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ አርቃቂነቱ እና የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ኀልዮት አዋቃሪነቱ ነው፡፡ ግና፣ ይህ ‹‹ንድፈ-ሃሳብ›› ተብዬ ራሱ በርዕዮተ-ዓለምነት ለመጠራት የማይበቃ የተውሸለሸለ ጭብጥ ስለመሆኑ በርካታ ምሁራን በጥናቶቻቸው ከማስረገጣቸው ባሻገር፣ አገሪቷን ለከባድ ኢኮኖሚያዊ ድቀት፣ ሕዝቧን ደግሞ ለጥልቅ ድህነት መዳረጉን ብቻ ማስታወሱ በቂ ይሆናል፡፡ ስለልማታዊ መንግስት አዋጭነት በብቸኝነት እንደተከራከረ ተደርጎ የሚለፈፈውን እንኳን ንቆ መተው ሳይሻል አይቀርም፡፡ ከታንዲካ ማካንደዋሬና መሰል የፅንሰ-ሃሳቡ አበጂዎች የዘረፋቸውን መከራከሪያዎች ማን ዘርዝሮ ይዘልቀውና፡፡ ‹መለስን ቅበሩት› የምለውም፣ እንዲህ ያሉ አስነዋሪ ማንነቶቹን ማስታወስ ስለሚያም ነው፡፡
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

እናም እውነት እውነት እላችኋለሁ፡- ስለሰውዬው የምትነግሩን እና የምታስቀጥሉት ‹ሌጋሲ›ም ሆነ የምትተገብሩት ረብ ያለው አንድም ራዕይ የለምና ዝም፣ ፀጥ ብላችሁ የምራችሁን ቅበሩት፡፡ እስቲ! ኦጋዴንን ተመልከቱ፤ ካሻችሁም ወደ አኝዋኮች ተሻገሩ፤ ያን ጊዜ እናንተ በአርያም የሰቀላችሁት ሰው፣ ለነዚህ ሁለት ብሔሮች የቀትር ደም የጠማው ጨካኝ መሪ እንደነበር፣ በክፋት ትዕዛዞቹ ጥፋት ከተረፈ ጠባሳ ትረዱታላችሁ፡፡ ለአቅመ-ሔዋን ያልደረሱ ህፃናት በሰልፍ የሚደፈሩባት፣ ወጣቶች እንጀራ ፍለጋ በተስፋ-ቢስነት ጥልቁን ውቅያኖስ ሰንጥቀው ለመሰደድ የማያመነቱባት፣ የጤና ኬላ ማግኘት ተስኗቸው በልምሻ የሚባትቱ ብላቴኖችን በአቅም-የለሽነትና በቁጭት የምናስተውልባት ደካማ አገር አስረክቦን እንዳለፈ ከወዴት ተሰወረባችሁ? ከቀዬዎቻቸው በጉልበት ለተፈናቀሉ ወገኖች በመቆርቆር ‹‹ሕግ ይከበር!›› ባሉ በየጉራንጉሩ ወድቀው እንዲቀሩ የተፈረደባቸው ጎበዛዝትን ሬሳ እንድንቆጠር ያደረገን ደመ-ቀዝቃዛ ‹መሪ› እንደነበረስ ስንት ጊዜ እያስታወስን እንቆዝም? ቀደምት አባቶች ወራሪውን ፋሽስት ለማንበርከክ የተዋደቁባቸው ጢሻና ኮረብቶች በዚህ ዘመን የዜጎች ወደሞት አገራት መሸጋገሪያ ጽልማሞቶች የሆኑት በማን ሆነና ነው? ከሕግ ተጠያቂነት ቢያመልጥ፣ ከታሪክ ተወቃሽነት ልትታደጉት የምትችሉ ይመስላችኋልን?
…ይልቅ እመኑኝ! ፀጥ ብላችሁ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጥልቅ ጉድጓድ ቆፍራችሁ ቅበሩት! ላይመለስ በመሄዱም እንደ ግልግል ቆጥራችሁት እርሱት!! መቼም በገዛ ራሱ ሕዝብ ላይ ትውልዶች ይቅር ሊሉት የሚሳናቸውን ይህን መሰሉ መከራ ላዘነበ ሰው በአፀደ-ስጋ ሳለም ሆነ በበድን የሙት መንፈሱ ስር በየዓመቱ ለአምላኪነት መንበርከክ፣ የናንተን አልቦ ማንነት እንጂ ሌላ አንዳች የሚነገረን ቁም ነገር ጠብ ሊለው አይችልም፡፡ ይህም ሆኖ ለመለስ አምልኮ እጅ መስጠት አሳፋሪነቱ፣ ለካዳሚዎቹ ብቻ መሆኑን መስክሮ ማለፉ የቀሪዎቻችን ዕዳ እንደሆነ መገንዘብ አለብን፡፡

tirsdag 19. august 2014

የአዲስ አበባ ፖሊሶች ለስልጠና እንዲከቱ ተደረገ

ለፖሊስ ከፍተኛ አዛዦች በኮልፌ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ከተጠናቀቀ በሁዋላ መደበኛ ፖሊሶች ደግሞ
በተለያዩ የማሰልጠኛ ቦታዎች በግዳጅ ገብተው ስለመንግስት ፖሊሲና እቅድ ስልጠና እየተሰጣቸው ነው።
በኮልፌ በአዛዥ ፖሊሶች ሲጠየቁ የነበሩት ጥያቄዎች በመደበኛ ፖሊሶች ተጠናክረው መቅረባቸው ታውቋል። ከትናንት ጀምሮ በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ
ግንቦት 20 እየተባለ በሚጠራው ትምህርት ቤት ውስጥ 500 የሚደርሱ ፖሊሶች ገብተዋል። እያንዳንዱ ፖሊስ ለ12 ቀናት ስልጠና የሚሰጠው ሲሆን፣
ለእያንዳንዱ ፖሊስ ለ12 ቀናት 800 ብር በጀት ተመድቦላቸዋል። ይህ ገንዘብ ለምግብ፣ ለምኝታ እና ለሌሎችም ወጪዎች ሲሆን፣ ፖሊሶቹ ከስልጠና
ቦታው መውጣት፣ ምግብ ከውጭ አስመጥቶ መብላት እና ለሻሂ እረፍት በሚል ወደ ውጭ መውጣት አይፈቀድላቸውም። 46 የሚሆኑ ነፍሰ ጡር ሴት
ፖሊሶች ቤታቸው እየሄዱ እንዲያድሩ ቢጠይቁም የተፈቀደላቸው ግን 15 ብቻ ናቸው። ፈቃድ ከተከለከሉት መካከል የ3 ወር አራሶችም እንደሚጘኙበት
ታውቋል። በዚሁ መሰረት ከስልጠናው በሁዋላ ቤታቸው እንዲያድሩ ሲፈቀድላቸው ሌሎች ፖሎሶች ግን በስልጠናው ቦታ ማደርና መዋል ግድ ይላቸዋል።
የተመደበላቸው በጀት አነስተኛ መሆኑና ለቁርስ፣ ለምሳና ለእራት የሚቀርብላቸው ምግብ ደረጃውን ያልጠበቀ ነው በማለት ቢቃወሙትም፣ አሰልጣኞቹ
ግን ይህ ተደረገው ፖሊሱ ለመንግስት ያለውን ታማንነት ለመፈተን ተብሎ ነው የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡
በንፋስ ስልክ በተካሄደው የመጀመሪያ ቀን ውይይት ላይ የመንግስት ባለስልጣናት ይህ መንግስት ለህዝቡና ለእናንተ ምን ያላደረገው ነገር አለ? ምን ጉድለት
አለበት? የሚል ጥያቄ የቀረበ ሲሆን፣ ፖሊሶች መንግስት እያደረገው ያለው ነገር እዚህ ግባ የማይባል መሆኑን፣  የአስተዳደሩም ሁኔታ ልክ አለመሆኑን እና
ለውጥ እንደሚያሻው በድፍረት ገልጸዋል። የመንግስት ባለስልጣናት ለህዝቡ ተሰሩ ያሏቸውን ስራዎች ዘርዝረው ቢያቀርቡም ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ
ሁኔታ ፖሊሶች አጣጥለዋቸዋል። መንግስት ለአዲስ አበባ ፖሊሶች የኮንዶሚኒየም ቤት እንዲያገኙ ቅድሚያ እንደሚሰጣቸውና የቤት ችግራቸው እንደሚፈታላቸው
ቢናገርም፣ ፖሊሶች ግን ከዚህ ቀደም የተገቡትም ቃል ኪዳኖች ተግባራዊ አልሆኑም በሚል በባለስልጣኖች በድጋሜ የተገቡትን ቃል ኪዳኖች አልተቀበሉዋቸውም።
ፖሊሶቹ የመንግስትን ስትራቴጂንና ፖሊስን እንዲያውቁ፣ በመጭው ምርጫ ላይ ፖሊሶች መንግስት እንዲያሸንፍ ጥረት እንዲያድርጉ ተነግሯቸዋል። ተቃዋሚዎች
የሚናገሩት የማይረባ መሆኑንና መንግስትን መደገፍ አማራጭ የሌለው ነገር መሆኑን ገልጸዋል።
ሰልጣኝ ፖሊሶች የስልክ ጥሪ ቢደርሳቸው ስልክ ማንሳት እንደማይችሉና የተደወለላቸውን ስልክ ለተቆጣጠሪዎች የማስመዘገብ ግዴታ ተጥሎባቸዋል። የስልክ ጥሪ
የተቀበለና ጥሪውን ያላስመዘገበ ፖሊስ የዲሲፒሊን እርምጃ የሚወሰድበት መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
በአዲስ አበባ የወጣቶች ስፖርት ማእከልም እንዲሁ 600 የሚሆኑ ፖሊሶች ለስልጠና እንዲገቡ ተደርጓል።

mandag 18. august 2014

የወያኔው ኢንሳ በአዲስ መልክ የፌስቡክ ስም አጥፊ ፔጆችን/ገጾችን ሊያደራጅ ነው


facebook
ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነት እና ነጻነት ለመሸራረፍ ብሎም ለመበታተን ከሚጠቀምባቸው ዘዴዎች አንዱ በማህበራዊ ድህረገጹ ያሰማራቸውን ከተቃዋሚ ሃይላት ጋር ተመሳስለው የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት መስለው የተቃዋሚ ሃይሎችን ሎግ በመጠቀም እንዲሁም ለሽፋንነት በየመሃሉ የተቃዋሚ ድርጅቶችን መግለጫ እንደወሽመጥ በማስገባት በማታለል እና በማጭበርበር ላይ ተመስርተው ሲሰሩ የነበሩ ስም አጥፊ ገጾችን/ ፔጆችን በአዲስ መልክ ለማደራጀት በዚህ ሳምንት እረፍት እንዲወስዱ ያደረጋቸው መሆኑ ታውቋል።
ስም በማጥፋት ለውጥ ፈላጊ ሃይሎች በተለያዩ አክቲቪስቶች ላይ መጠራጠር እንዲያሳድሩ እና ጠቃሚ የተባሉ ጦማርያንን እንዲያጡ እና ትግሉ አቅጣጫውን እንዲስት በስፋት አዲስ የአሰራር ዘይቤ ለመቀየስ የተሳዳቢዎች የተዛልፊዎች እና የስም አጥፊዎች የማህበራዊ አካውንት እና ፔጆች እረፍት ላይ መሆናቸውን እና በተጠናከረ መልኩ ወደ ስራ እንደሚመለሱ በቅርብ የሚያውቋቸው ወዳጆቻቸው ተናግረዋል።
በዚሁም መሰረት በዜጎች መካከል ከባድ ጥርጣሬን ያጭራሉ የተባሉ የፈጠራ ጽሁፎች እና የሞቱ ሰዎች ፎቶዎችን በመጠቀም የተለያዩ የፌክ ወንጀሎችን በመጻፍ እንድሁም ከብልግና እና የሰውን ክብር ከሚያዋርዱ አዳዲስ ብካይ የሃሰት መረጃዎች ጋር ወዘተ ተያይዘው ወደ ማህበራዊ ድህረገጾች እርፍታቸውን ጨርሰው እንደሚመጡ ታውቋል።

fredag 15. august 2014

በመንግሥት ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ ያልሰለጠኑ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ መግባት ሊከለከሉ ነው

የትምህርት ሚኒስቴር ከ360 ሺህ በላይ ነባርና አዳዲስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመንግሥትን ፖሊሲና
ስትራቴጂን እንዲሰለጥኑ አስገዳጅ መመሪያ ያወጣ ሲሆን በሥልጠናው ላይ ተሳትፎ የምስክር ወረቀት ያልያዘ ተማሪ በዩኒቨርሲቲዎቹ ትምህርቱን
መቀጠል እንደማይችል በግልጽ አስጠንቅቋል፡፡ የትምህርትሚኒስትሩአቶሺፈራውሽጉጤሰሞኑንለጋዜጠኞችእንደገለጹትበመንግሥትፖሊሲዎችና
ስትራቴጂዎችላይ ከ250ሺህበላይነባርየዩኒቨርሲቲተማሪዎችእናከ116 ሺህበላይአዳዲስተማሪዎችለተከታታይ 15 ቀናት አበልበመክፈልባሉበት
አካባቢበፕላዝማሥልጠናእንደሚሰጥአስታውቀዋል፡፡ የሥልጠናውየመጀመሪያዙርከሳምንት በኃላእንደሚጀምርያስታወቁትሚኒስትሩሁለተኛው ዙር
በመስከረምወር 2007 ዓ.ምተሰጥቶለማጠናቀቅመታሰቡን ተናግረዋል፡፡ ሥልጠናውንየሚሰጡትከፍተኛየመንግሥትባለስልጣናትመሆናቸውን
የሥልጠናውዝርዝርእናየሚፈጀውወጪምንያህል እንደሆነተጠይቀውከመናገርተቆጥበዋል፡፡ሆኖምሌሎችምንጮችበሥልጠናውከተካተቱት ርዕሰ
ጉዳዮችመካከል ስለሃይማኖትአክራሪነት፣ስለሽብርተኝነት፣ስለልማታዊመንግሥትጉዳዮችእንደሚገኙበትጠቅሰዋል፡፡ ይህሥልጠና ኢህአዴግ በመንግሥት
ወጪለቀጣዩምርጫድጋፍለማግኘትእንዲሁም ነባር አባላቱን በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለመተካት ለዘረጋው መርሃ ግብር ማስፈጸሚያ ነው በሚል አስተያየቶች
ይሰጣሉ። ምንጮች እንደሚሉት ለፓርቲው ስራ ገንዘብ እንዲወጣ የሚደረገው ከመንግስት ካዝና ነው። በተመሳሳይ ዜና ደግሞ ባለፈውሰኞየተጀመረው
ለፌደራልዳኞች፣አቃቤያነ ህጎች፣ የፖሊስናየደህንነትሃላፊዎችየሚሰጠው የአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ስልጣና እንደቀጠለ ነው። በተወካዮች ምክር ቤት
እየተካሄደ ባለው ስልጣና  ተሳታፊዎቹበአይነትናበይዘትየተለያዩጥያቄዎችንአንስተዋል። አንድ ተሳታፊ “የዚህዓይነትስልጠናበዚህወቅትበተለይለኛለምንኣስፈለገ?የፍትሕኣካላትበተለይዳኞችከፖለቲካነጻናቸውበሚባልባትሃገርውስጥበተለይየስልጠናማንዋሉየኢሃዴግንአርማመያዙየዳኝነትን ገለልተኝነት
ጥያቄ ውስጥ አያስገም ወይ?” የሚል ጥያቄ አንስተዋል። ሌላ ተሳታፊ ደግሞ ” ኢሃዴግለ23አመታትየገዛፓርቲ ሆኖሳለለ10ዓመታትእድገትአመጣሁ ማለቱ
ድክመቱንከመግለጽ ይልቅ ስለ እድገትናስልጣኔብቻማዉራቱምንማለትነው? ” ሲሉ ጠይቀዋል። ከታሪክ ጋር በተያያዘ በተነሳው ገለጻ ላይ ደግሞ አንድ ጠያቂ

አጼሚኒሊክወራሪነውወይስሃገር አቅኚወይምተስፋፊ?በሚኒሊክዘመንየነበረው የመደብጭቆናነው ወይስየብሄርጭቆና ?” በማለት ጥያቄ አቅርበዋል። ቋንቋን
በተመለከተም ” ኣንድኢትዮጵያንለመፍጠር አንድቋንቋአያስፈልግምወይ?” የሚሉእናሌሎችተዛማጅ ጥያቄዎችም ተነስተዋል።  አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ገመዳለተነሱት
ጥያቄዎች መልስ የሰጡ ሲሆን፣ አጼ ሚኒሊክን በተመለከተ በሰጡት መልስ  አጼ ሚኒሊክ ወራሪ መሆናቸውን ገልጸዋል።  በሚኒሊክወቅትየነበርው ጭቆና
ሁለትገጽታነበረውያሉት አባ ዱላ “በአማራክልልየመደብጭቆና ፣በኦሮሚያናበደቡብክልሎች ደግሞ የብሄርጭቆና  ነበር ” ብለዋል። ስርዓቱየሚከተለዉን
ኣይዶሎጂበሚመለከት በሰጡት ገለጻ ደግሞ “ኢህአዴግ የታይዋንናየህንድን ልማታዊመንግስታትርእዮት አለምወይምአስተሳሰብእንደሚከተሉነገርግን የኢህአዴግ
ርእዮት አለም  እንደነሱልማትንበግድየሚጭን መንግስትሳይሆን፣ልማታዊና ዲሞክራሲያዊነው” ብለዋል።ተሰብሳቢዎቹም ” የነታይዋንአይነትልማትንበግድ
የሚጭንመንግስትእንዴትዲሞክራሲያዊይሆናል?” የሚል ጥያቄ አንስተዋል። ኢህአዴግ በመላ አገሪቱ የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮችን ፣ የመንግስት ሰራተኞችን፣
የህዝብ ተወካይ የሚባሉትንና የግንባሩን ካድሬዎች ሰብስቦ በወቅታዊ የአገሪቱ ሁኔታ እያነጋገረ ነው።

በሎሚ መጽሄት ስራ አስኪያጅ ላይ የተከፈተውን ክስ ለማየት ቀጠሮ ተሰጠ

የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ህገመንግስታዊ ስርአቱን በሃይል ለማፍረስ ተንቀሳቅሰዋል
በሚል ከከሰሳቸው አምስት የግል ሚዲያ ተቋማት መካከል የሎሚ መጽሄትን ክስ የተመለከተ ሲሆን፣ ስራ አስኪያጁ አቶ ግዛው ታየ ከጠበቃቸው ጋር ተማክረው
መልስ እስከሚሰጡ ድረስ ሌላ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱም የምክር ጊዜውን የፈቀደ ሲሆን፣ ተከሳሹ የ50 ሺ ብር ዋስ አስይዘው ለነሃሴ
14 እንዲቀርቡ አዟል። ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም የሮዝ አሳታሚ ድርጅትንና ከአገር ጥለው የተሰደዱትን የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ስራ አስኪያጅን ክሶች በሌሉበት አይቷል።
ገዢው ፓርቲ በመጪው ምርጫ ላይ ስጋት ይፈጥራሉ ብሎ የሚያስባቸውን የግል መጽሄቶችና አንድ ጋዜጣ ህገመንግስታዊ ስርአቱን በሃይል ለማፍረስ ይንቀሳቀሳሉ በሚል
ወንጀል መክሰሱ ይታወቃል። አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች መንግስት እየወሰደ ያለውን ነጻውን ፕሬስ የማጥፋት ዘመቻ አጥብቀው እየኮነኑት ነው።

ዓረና-መድረክ እሁድ በትግራይ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያካሂድ ነው

በመጪው እሁድ በመቀሌ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል። የመቀለ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ከዚህ በፊት በቂ የፖሊስ ሃይል የለንም በማለት ሰለማዊ ሰልፉ ለሌላ ቀን እንድናሸጋግረው ኣስታውቆ እንደነበር ኡእሚታወስ ነው።
የሰለማዊ ሰልፍ የሚያደርጉበትን ጎዳናዎችና የሚያርፉባቸው አደባባዮችን የሚያመላክት ደብዳቤ ትናንት 08 / 12 /2006 ዓ/ም ወደ መቐለ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ኣስገብተዋል። መድረክ ከዚህ በፊትም በኣዲስ ኣበባና በሃዋሳ ከተሞች የተሳኩ ሰለማዊ ሰልፎች ማድረጉ የሚታወስ ነው።
የአረና ቃል አቀባይ እንዳለው ከሆነ፤ ኣስተዳደሩ ያለበት የፖሊስ እጥረት በሚቀርፍ መንገድ(ዲያስፖራ ሲጠብቅ የሰነበተው በሺዎች የሚቆጠር የፌደራል ፖሊስ እያለ እንድናካሂድ የመረጥነው እጥረቱ ግምት ውስጥ ኣስገብተን ነው።) በዚህ መሰረት የሃገራችን፣ የክልላችንቻ የከተማችን ወቅታዊ ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች በማንገብ መንግስት ኣዳምጦ መፍትሄ እንዲያበጅላቸው እንጠይቃለን። እነ ኣብራሃ ደስታ፣ ኣልጋነሽ ገብሩና ሌሎች የዓረና ኣባላት፣ የመድረክ ኣባላት፣ በኣጠቃላይ በሰለማዊ መንገድ እየታገሉ ዘብጥያ የወረዱ ዜጎቻችን ፍትህ እንዲበጅላቸው ከመቐለና ኣከባቢው ህዝብና ሁነን ድምፃችን እናሰማለን ።
ነፃነታችን በእጃችን ነው…! …በማለት ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

torsdag 14. august 2014

እነ ወይንሸት ሞላ በዋስ እንዲፈቱ በድጋሚ ታዘዘ

ያለአግባብ ታስረው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲዋ ወይንሸት ሞላና ፎቶ አንሺ ጋዜጠኛዋ አዚዛ መሃመድ ከሁለት ሳምንታት በፊት በአንዋር መስጊድ ይካሄድ በነበረው የጁምአ በአል ላይ ተገኝተው ነበር። የፖሊስ እና ደህንነት ሃይሎች ሰላማዊውን ሰው ሲደበድቡ እና ሲያስሩ፤ እነ ወይንሸት ሞላም በስፍራው በመገኘታቸው ብቻ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸው ታስረዋል። በተለይም ወይንሸት ሞላ እጇ እስኪሰበር ድረስ ነበር የተደበደበችው። ባለፈው ሳምንት የዋለው የልደታ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለቱም እንዲፈቱ ቢያዝም፤ ፖሊስ ወዲያው ጉዳዩን ሰበር ችሎት ወስዶ ዋሳቸውን አሳግዶባቸው እንደነበር ይታወሳል።
ወይንሸት ሞላ
ወይንሸት ሞላ (የሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣቶች ሃላፊ)

አዚዛ መሃመድ - የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ፎቶ አንሺ።
አዚዛ መሃመድ – የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ፎቶ አንሺ።
በዛሬው ቀን የዋለው ችሎት ወይንሸት ሞላ፣ አዚዛ እና ኢብራሂም አብዱልሰላም በ5ሺህ ብር የመታወቂያ ዋስ እንዲፈቱ ውሳኔ ሰጥቷል። እንደከዚህ ቀደሙ መልሰው ካላሰሯቸው በቀር ሶስቱም በቅርቡ ከ እስር ይወጣሉ ተብሎ ይታወቃል።

በአፍሮ ታይም፣ ሎሚ፣ እንቁ እና ጃኖ ላይ ክስ ተመሰረተ (የሁሉም ክስ ቻርጅ ደርሶናል)

ባለፈው ሳምንት በአፍሮ ታይም፣ ሎሚ፣ እንቁ፣ ጃኖ እና አዲስ  ጉዳይ የፕሬስ ውጤቶች ላይ ክስ መመስረቱን በቴሌቪዥን እና ሬድዮ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በዚህ ክስ ምክንያት የአዲስ ጉዳይ ጋዜጠኞች ወደ ኬንያ ሲሰደዱ የተቀሩት አራቱ የፕሬስ ውጤቶች ግን አሁንም አፈናውን ተቋቁመው ለመስራት እየሞከሩ ናቸው። አዲስ ጉዳይ አዘጋጆች ከአገር ስለወጡ በነሱ ላይ የተመሰረተው የክስ ቻርጅ ዝርዝር የለንም። ሆኖም በቀሩት የፕሬስ ውጤቶች ላይ የተመሰረተውን ክስ በዚህ ዘገባ መጨረሻ ላይ ከዚህ በፎቶ አስቀምጠነዋል።
የአፍሮታይምስ ጋዜጣ ማኔጅንግ ዳይሬክተር
የአፍሮታይምስ ጋዜጣ ማኔጅንግ ዳይሬክተር
በነገርዎ ላይ ይህ “ህዝብን በመንግስት ላይ ማነሳሳት” የሚለው ክስ እኛም ኢትዮጵያ በነበርንበት ወቅት ይደርሱን ከነብሩ የክስ ቻርጆች ውስጥ አንደኛው ነው። አሁንም ድረስ ታድያ ይህ አንቀጽ እየተጠቀሰ ክስ መመስረቱ አልቆመም። የሚገርመው ነገር አቃቤ ህጉ ህዝቡ በመንግስት ላይ ስለመነሳሳቱ ወይም እምነት እንዲያጣ ስለመደረጉ አንድም የሰው ምስክር አቅርቦ አያውቅም። ይልቁንም እኛው ራሳችን ያሳተምነውን ጋዜጣ እና መጽሄት በመረጃነት መልሶ ያቀርበዋል። አሁንም እንደተመለክትነው አቃቤ ህጉ መረጃ ብሎ ያቀረበው የፕሬስ ውጤቶቹ ያሳተሙትን ጋዜጣ እና መጽሄት ነው።
የሎሚ መጽሄት አሳታሚ ግዛው ታዬ
የሎሚ መጽሄት አሳታሚ ግዛው ታዬ
“ህዝብ በመንግስት ላይ እንዲነሳሳ በማሰብ…” ብሎ ሰውን መክሰስ በራሱ ችግር አለው። ምክንያቱም ሰው በማሰቡ ብቻ ሊከሰስ አይገባውም። የኢትዮጵያ አቃቤ ህግ ግን እያንዳንዱን ዜና በራሱ መንግድ በመተርጎም ጋዜጠኛው ይህን የጻፈው ህዝብን ለማነሳሳት አስቦ ነው” በማለት ላለፉት ሃያ አመታት በጋዜጠኞች ላይ ክስ እየመሰረተ ነው የሚገኘው።
የእንቁ መጽሄት ስራ አስኪያጅ አለማየሁ ማህተመወር
የእንቁ መጽሄት ስራ አስኪያጅ አለማየሁ ማህተመወር
ዛሬ የሁሉንም ክስ ቻርጆች አንድ ላይ አንድ ቦታ ለማተም የፈለግነው ወደፊት ይህንን የክስ ቻርጅ ለተለያዩ ጉዳዮች ቢፈልጉት እንኳን በቀላሉ እንዲያገኙት በማሰብ ነው።
የጃኖ መፅሔት አሳታሚና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ አስናቀ
የጃኖ መፅሔት አሳታሚና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ አስናቀ
የሁሉንም ክስ ቻርጅ በፎቶ መልክ ከዚህ በታች አቅርበነዋል። እያንዳንዱን ፎቶ በማተለቅ ማንበብ ይችላሉ። በፌስ ቡክዎም ላይ ለሌሎች ያካፍሉ።

onsdag 13. august 2014

ፖሊሶች በአበል ጉዳይ እየተወዛገቡ ነው

በዳግማዊ ሚኒልክና በሌሎችም አካባቢዎች የሚሰለጥኑ ፖሊሶች በቀን የሚታሰብላቸው ገንዘብ በቂ ባለመሆኑ
ጥያቄ አንስተዋል። ፖሊሶቹ ለቁርስና ምሳ እንዲሁም ለሻሂና ቡና 24 ብር በቀን የሚታሰብላቸው ቢሆንም፣ ገንዘቡ አይበቃንም በሚል ጥያቄ አንስተዋል።
ፖሊሶቹ  ስልጣናውን ሳያቋርጡ ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ የኮሚሽኑ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ለማግባባት እየሞከሩ ነው።
በዳግማዊ ሚኒሊክ ት/ቤት ውስጥ ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ ከ500 በላይ ፖሊሶች እየሰለጡ ነው። ስልጣናው መጪውን ምርጫ ታሳቢ አድርጎ የሚሰጥ
ነው። በኮልፌ በነበረው  ስልጠና ላይ ፖሊሶች ከመብት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን አንስተው እንደነበር መዘገባችን ይታወቃል።

የአዲስ አበባ መስተዳድር በቤቶች ግንባታ ዙሪያ ለምርጫ እንዲደርስ በሚል አስቸኳይ ትእዛዝ ሰጠ

በ40 በ60 በሚባለው የቤቶች መርሃግብር የታቀፉ የዲያስፖራ አባላት  ከቀጣዩዓመት ምርጫበፊት ቤት
እንዲሰጣቸው የአዲስ አበባ መስተዳድር መመሪያመስጠቱ ታውቋል። ሆኖምየጠቅላላተመዝጋቢውንየቤትፍላጎትለመሸፈንበትንሹከ16 ዓመታትበላይጊዜን
እንደሚወስድ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ የአዲስ አበባቁጠባቤቶችኢንተርፕራይዝእስካሁን 13ሺህ 800 ቤቶችን  በሰንጋተራእና ቃሊቲ ክራውን
ሆቴልበመሳሰሉአካባቢዎችላይእየገነባመሆኑየታወቀሲሆን ፣ እነዚህን ቤቶችእስከሚቀጥለውዓመትአጋማሽድረስለዕድለኞችለማስተላለፍታቅዷል።
የአስተዳደሩምንጮችእንደገለጹትቤቶቹከቀጣይዓመትምርጫበፊትሙሉበሙሉ ተጠናቀውእንዲተላለፉከአስተዳደሩመመሪያተሰጥቷል። ሆኖም
ለ40 በ60 የቤቶች ፕሮግራምየተመዘገበውጠቅላላሕዝብቁጥር 164 ሺህ 779 ያህልሲሆንአስተዳደሩግን  በዓመትከ10 ሺህቤቶችበላይቤቶችን
የመገንባትአቅምባለመፍጠሩየተመዘገቡትንብቻ ለማዳረስከ16 ዓመታትበላይጊዜንእንደሚፈልግየአስተዳደሩምንጮችአስታውቀዋል፡፡ ይህደግሞ ከዛሬ
ነገየመኖሪያቤትባለቤትእሆናለሁብሎተስፋላደረገውሕዝብተስፋ አስቆራጭዜናነውብለዋል፡፡ በ20/80 በተለምዶኮንዶሚኒየምፕሮግራምየምርጫ 97
ንመቃረብታሳቢአድርጎ ሲጀመርከ350ሺበላይየአዲስአበባነዋሪመኖሪያቤትእፈልጋለሁብሎመመዝገቡን ያስታወሱትምንጮቹ ፣ ፕሮግራሙ 10 ዓመታት
ያህልቆይቶመመለስየቻለውግን 100 ሺበታችቤትፈላጊዎችንጥያቄነውብለዋል፡፡በዚህመረጃመሠረትየጠቅላላ ተመዝጋቢውንፍላጎትለሟሟላትተጨማሪ
ከ20 ዓመታትበላይጊዜንእንደሚወስድ  አፈጻጸሙበራሱየሚናገርነውሲሉአስረድተዋል፡፡ የአስተዳደሩምንጭእንደሚሉትመንግሥትበአዲስ አበባበዓመት
ለቤቶችግንባታብቻ ከ2 እስከ 3 ቢሊየንብርእያወጣመሆኑንአስታውሰውከዚህበላይለማውጣትየፋይናንስ አቅምችግርመኖሩን፣ገንዘቡቢገኝምበግንባታአፈጻጸም
በኩልየአቅምችግርበመኖሩ በአጭርጊዜየመኖሪያቤትፍላጎትንለመመለስየማይችልበትአጣብቂኝውስጥእንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር
ቴዎድሮስ አድሃኖም እንደገለጹት ደግሞ ዲያስፖራው በፈለገበት አካባቢ ቤት ለመስራት ይችል ዘንድ ክልሎች መመሪያ እንዲያወጡ መታዘዙን ገልጸዋል። ሁሉም
ክልሎች ተመሳሳይ የሆነ መመሪያ ባለማውጣታቸው ለዲያስፖራው ቤት ለማደል የታቀደው እቅድ የተፈለገውን ውጤት አለማምጣቱን ገልጸዋል። ይሁን እንጅ ኢሳት
የአዲስ አበባን አዲሱን ካርታ ዝግጅት አስመልክቶ ከወራት በፊት በሰራው ዘገባ፣ የቤት ግንባታ መርሃግብሩ የተሰናከለው በአዲስ አበባ የቤት መስሪያ ባዶ ቦታ
በመጥፋቱ ነው። ቀደም ብሎ የኦሮምያን ልዩ ዞኖች ወደ አዲስ አበባ በመጠቅለል የቤት መስሪያ ቦታዎችን ለማግኘት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ የኦሮምያ ክልል አንዳንድ
ባለስልጣናትና አብዛኛው የኦሮሞ ተወላጅ በመቃወሙ እቅዱን በቀላሉ ተግባራዊ ማድረግ አልተቻለም። ዲያስፖራው ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉ ቦታዎችን እንዲጠይቅ
ለማግባባት ኢምባሲዎች የስራ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ለአባይ ግድብ በቦንድ ስም ገንዘብ በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ ለማሰባሰብ
የታቀደው እቅድ አለመሳካቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምነዋል። ከፍተኛ ገንዘብ ይገኝበታል የተባለው የአሜሪካ የቦንድ ሽያጭ አምና ጭራሽ አልተካሄደም ብሎ መናገር
እንደሚቻል ሚኒስትሩ ገልጸዋል። በሁሉም አገሮች ያለው የቦንድ ሽያጭ ደካማ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ ፣ ለድክምቱ ዝርዝር ምክንያቶችን አላቀረቡም።
የዶ/ር ቴዎድሮስ ገለጻ፣ ኢሳት ከዚህ ቀደም የቦንድ ሽያጩ በውጭ አገር አለመሳካቱን ሲዘግብ የቆየውን ያረጋገጠ ሆኗል። በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ለአባይ ግድብ
ማሰሪያ ገንዘብ ለመሰብሰብ በገዢው ፓርቲ በኩል የሚዘጋጁትን ዝግጅቶች አጥብቆ ሲቃወም እንደነበር ይታወቃል። አቶ መለስ የአባይን ግድብ እቅድ ይፋ ሲያደርጉ
በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ 1 ቢሊዮን ዶላር ያዋጣል የሚል እምነት ነበራቸው፣ ይሁን እንጅ እስካሁን ባለው መረጃ በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ከ20 ሚሊዮን
ዶላር በላይ ሊያዋጣ አልቻለም።

tirsdag 12. august 2014

ኢህአዴግ በከፍተኛ ደረጃ ለሚገኙ አመራሮች ስልጠና መስጠት ጀመረ

የፌደራልአቃቢያነህጎችእናዳኞች፣የፈደራልማረሚያቤቶችባለስልጣናት፣የፌደራልናየአዲስአበባፖሊስ
አመራሮችናየደህንነትሃላፊዎችበአቶአባዱላገመዳአሰልጣኝነት  የኢትዮጵያህዝቦችትግልናሃገራዊሕዳሴያችንበሚልርእስስልጠናጀምረዋል።
ስልጠናው ምናልባትም በቅርቡበቀድሞውም/ል ጠ/ሚ  አዲሱለገሰ  በቀረበዉና የኢህአዴግን የአመራር ችግር በሚዘረዝረውን  ጥናት ላይ ለመወያየት
ሳይሆን እንደማይቀር ምንጮች ጠቁመዋል።
በዚህጥናትኢህኣዴግበከፍተኛየአመራርእጥረትእየተቸገረመሆኑን፣ኦሮሞየሆኑየኦህዴድኣባላትሙሉበሙሉወደኦነግእንዳደሉእንዲሁምደግሞ፣የአማራውክፍልየሆነውብሄረ
አማራዲሞክራሲያዊንቅናቄ ከግንቦት7 ጋር ሽርክና መፍጠሩን መግለጻቸው ይታወሳል። አቶ አዲሱ የትራንስፎርሜሽኑ እቅድ ሊሳካ ያልቻለው በአመራር ችግር ምክንያት መሆኑንም ተናግረዋል።
ስብሰባው ነሃሴ5የተጀመረሲሆንለ3 ሳምንት ያክል ይቆያል ተብሎ ይጠበቃል።

የ”ብርቱው ሰው” መልዕክት – ከቃሊቲ እስር ቤት (በኤሊያስ ገብሩ)


ESKINDER.Eskinderfamily‹‹ለእውነት መቆም ካልተቻለ ስብዕና ይወርዳል፣ ሕሊናህም ይሞታል››
‹‹የክስ እና የእስር መብዛት … የድል ጊዜ እየቀረበ መሆኑን ያሳያል››
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ (ከቃሊቲ እስር ቤት)
‹‹እ… እስክንድር “The Iron man’’?››
የቃሊቲ ጠባቂ ፖሊስ
————————————–
ጥቁር ሰኞ (Black Monday) ከሚሉት ወገን አይደለሁም፤ በአባባሉም አላምንም፡፡ እያንዳንዱ ግለሰብ በሁሉም ቀናቶች ጥሩም ሆነ ጥሩ ያልሆነ ሁነቶችን ሊያስተናግድ ይችላል፡፡ ይህንን ማለት የወድድኩት ዛሬ ሰኞ በመሆኑ ነው፡፡ ብዙዎች ዕለተ ሰኞ እንደሚከብዳቸው እና እንደሚጫጫናቸው ይናገራሉ፡፡ በቀናት መጥቆር እና መንጻት ማመናችንን ትተን፣ እያንዳንዱ ቀናቶችን ለሥራ እና ለመልካም ነገሮች በአግባቡ ብንጠቀምባቸው መልካም እያልኩ ወደዋናው ርዕሰ ጉዳዬ ላምራ፡-
18 ዓመት ተፈርዶበት በቃሊቲ ወህኒ ቤት ታስሮ የሚገኘውንና እጅግ የማከብረውን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በቃሊቲ ከጠየኩት አንድ ወር ገደማ ሆኖኝ ነበር፡፡ ባለፈው ሳምንት ልጠይቄው አስቤ፣ በአዲስ የጋዜጣ ሥራ ተጠምቼ ስለነበር ሳልችል ቀረሁ፡፡ ዛሬ ግን፣ ከመኝታዬ እንደተነሳሁ የናፈቀኝን እስክንድርን ለመጠየቅ ወደቃሊቲ ማምራት እንዳብኝ ወሰንኩና ጉዞዬን ጀመርኩ፡፡
ሳሪስ አቦ አካባቢ የመኪና መንገድ ተጨናንቆ ተዘጋግቷል፡፡ ከአዝጋሚው የመኪና ጉዞ በኋላ ቃሊቲ ደረስኩ፡፡ ለመግቢያ ሰዓት (6፡00) የቀረው አስር ደቂቃ በመሆኑ ከታክሲ ወርጄ መሮጥ ግዴታዬ ሆነ፡፡ ቃሊቲ በታችኛ በር ከገባሁ በኋላ መዝጋቢ ፖሊስ እስኪመጣ ድረስ እስረኛ ጠይቀው የሚወጡ ጠያቂዎችን ማየት ጀመርኩ፡፡ የእስረኛ ቁጥር ብዙ፣ የጠያቂውም እንደዚያው! ‹‹መቼ ይሆን! የታሳሪ እና የጠያቂዎች ቁጥር በሀገራችን የሚቀንሰው?›› ስል ራሴን ጠየኩ፡፡ በወቅቱ ግን መልስ አላገኘሁለትም፡፡
የጥዋት ጠያቂዎች እየወጡ ሳለ የድምጻዊ ኤፍሬም ታምሩ የቀደምት ሥራዎቹ የሆኑ ለስላሳ ዘፈኖች በተከታታይ በትልቅ ስፒከር ሲንቆረቆሩ ነበር፡፡ ለስለስ ያሉ የሀገራችን ድምጻውያን የቀደምት ሥራዎች ከሚከፈትባቸው ቦታዎች መካከል አንዱ ቃሊቲ ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜያቶች እነእስክንደርን፣ ርዕዮት ዓለሙንና ውብሸት ታዬን ለማጠየቅ ስሄድ አድምጬ አውቃለሁ፡፡
****‹‹እ… እስክንድር “The Iron man’’››****
ከምዝገባ በኋላ የተለመደውን ፍተሻ አልፌ ጭር ወዳለው የቃሊቲ ግቢ ዘለኩኝ፡፡ አንድ ጠባቂ መጣና ‹‹ማንን ልጥራልህ?›› አለኝ፡፡ ‹‹እስክንድር ነጋን›› አልኩት፡፡ ወዲያው ፈገግ እያለ ‹‹እ… እስክንድር “The Iron Eskidner-NEgaaman’’ (ብርቱ ሰው)›› በማለት ሊጠራልኝ ሄደ፡፡ የጥበቃው ፖሊስ እንዲህ ማለቱ ትንሽ አግራሞትን ፈጥሮልኝ ነበር፡፡ ‹‹እስክንድር ብርቱ መሆኑን እነሱም ያውቃሉ ማለት ነው?›› በማለት ለራሴ ፈገግ አልኩ፡፡ [ብርቱ ሰው! በሚል ርዕስ ‹‹ፋክት›› መጽሔት ላይ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በአንድ ወቅት ስለእስክንድር ጽፉ ነበር፡፡ ኢቲቪም ባሳላፍነው ሳምንት የፍትህ ሚኒስቴር አምስት መጽሄቶችንና አንድ ጋዜጣን በወንጀል ክስ መከሰሱን ተከትሎ ባስተላለፈው ዜና እና በ‹‹ሕትመት ዳሳሳ›› ፕሮግራም ላይ ይህ ርዕስ እና የእስክንድር ፎቶግራፍ ያለበት የመጽሔቱን የፊት ገጽ በተደጋጋሚ ሲታይ ነበር] ፖሊሱም ይህን አይቶ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አደረብኝ፡፡
ወዲያው እውነተኛ ፈገግታ የማይለየው እስክንድር ፈገግ እያለ ወደእኔ መጣ፡፡ በአጋጣሚ በር ጋር ስለጠበኩት በአካል በደንብ ለመገናኘት ዕድሉን አገኘን፤ ጠባቂዎቹም ዝም ስላሉን ተቃቅፈን ሰላምታ ተለዋወጥን፡፡ ከሰላምታው በኋላም እስክንድር ትንሽ ጎንብስ ብሎ፣ አንገቴ ላይ የጠመጠምኩትን ስካርፍ ጫፍ ላይ የነበረውን የኢትዮጵያ ባንዲራ በሁለት እጆቹ ይዞ ሳመው፡፡ የእስክንድር ትህትና መቼም ተነግሮ አያልቅ ብዬ ዝም አልኩ፡፡
*****‹‹ሰርካለም እንዴት ነች?››******
ሁለት ጥበቃዎች ከግራና ከቀኝ ሆነው ማውራት ጀመርን፡፡ ‹‹ስለመጣህ ደስ ብሎኛል?›› አለኝ፡፡ ‹‹እስኬው እኔም ናፍቀኸኝ ነበር፤ ሥራ ስለበዛብኝ ነው መምጣት ያልቻልኩት›› አልኩት፡፡ ‹‹ከዚህ በፊት ቅድሚያ ለሥራ! ብዬሃለሁ›› አለኝና ‹‹አሁን ላይ ብዙ ነገሮች አሉ፤ ከየቱ እንጀምር? በኋላ ይሄንን ሳልጠይቀው? ይሄንን ሳልነግረው? ብዬ እንዳላስብ›› በማለት ጥያቄውን በፈገግታ አስከተለ፡፡
‹‹አንተ ደስ ካለህ ነገር ጀምር›› አልኩት፡፡ ፈጠን ብሎ ‹‹ሰርካለም እንዴት ነች? ታገኛታለህ?›› በማለት ጠየቀኝ፡፡ ‹‹ደህና ነች፡፡ አልፎ አልፎ በማኅበራዊ ሚዲያ አገኛታለሁ፡፡ ነፍቆትም ማደጉን በፎቶፍራፉ ተመልክቻለሁ፡፡ የእሷንም የቅርብ ጊዜ ፎቶፍራፍ ፌስ-ቡክ ላይ አይቼዋለሁ፤ ደህና ናቸው›› በማለት መለስኩለት፡፡
‹‹በጣም ናፍቀውኛል›› የእስክንድር ምላሽ ነበር፡፡ …በእሱ ቦታ ራሴን ሳስቀምጠው እጅግ የሚከብድ ነገር ነው፡፡ ግን የእስክንድር በጣም ጠንካራ ነው፤ መንፈሱም ጭምር፡፡ …
‹‹አቤል (ዓለማየሁ) ደህና ነው?›› ሲልም በድጋሚ ጠየቀኝ፡፡ ‹‹ደህና ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት ሊጠይቅህ መጥቶ በር ተዘግቶበት መመለሱን ነግሮኛል›› አልኩት፡፡ ‹‹አመሰግናለሁ›› በለው፡፡ [ጓደኛዬ ጋዜጠኛ እና መጽሐፍ ጸሐፊ አቤል አለማየሁ ያለ ማንም ቆስቋሽ፣ በራሱ ተነሳሽነት የታሰሩ ጋዜጠኞችን እና ፖለቲከኞችን ከሚጠይቁ የተወሰኑ ሰዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ በአሁን ወቅት በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙት በፍቃዱ ኃይሉ (በፍቄ) እና ተስፋለም ወልደየስ፣ እንዲሁም በቃሊቲ የምትገኘዋ ማህሌት ፋንታሁን (ማሂ) በራሳቸው ተነሳሽነት የታሰሩትን በመጠየቅ አውቃቸዋለሁ፡፡ ይህ እስከዳር ዓለሙ (ቹቹ)ን፣ መሳይ ከበደንና ኢዩኤል ፍስሐንም ይጨምራል]
ከሰሞኑ ፍትህ ሚኒስቴር በአምስት መጽሄቶችና በአንድ ጋዜጣን አቀረብኩት ስላለው ክስ እስክንድር ሰምቷል፡፡ ‹‹ክሱ ለሚዲያዎቹ ደረሳቸው እንዴ? ‹‹ዕንቁ›› መጽሄትም በክሱ ላይ ስላለበበት አንተን አስቤህ ነበር?›› አለኝ፡፡
‹‹ከፍቄ (የዕንቁ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር) ጋር ተደዋውለን ነበር፡፡ እስከአሁን ባለኝ መረጃ መሰረት ክሱ አልደረሳቸው …ሕግን አክብረን በሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ሰርተናል፤ አሁንም በሕግ ማዕቀፍ ውስጥ በመስራት አምናለሁ፤ ከዚህ ባለፈ ግን በግሌ የሚመጣብኝ ነገር ካለ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ፡፡ ጋዜጠኝነት ከፍርሃት ጋር አብሮ አይሄድም፡፡ እየፈሩ ጋዜጠኝነት የለም፤ ይህ የግል እምነቴ ነው›› በማለት ብዙ ጊዜ ለቅርብ ጓደኞቼ በጨዋታ አጋጣሚ የማካፍላቸውን ሀሳብ ለእስክንድርም ነገርኩት፡፡
‹‹ዴሞክራሲ እንዲሁ አይመጣም፡፡ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ሰዎች ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መሆን አለባቸው፡፡ አንተም ዋጋ መክፈል ካለብህ መክፍል አለብህ፡፡ ግን ጨካኝ አትበለኝ፡፡ ጨካኝ ሆኙም አይደለም፤ መሆን ያለበት ግን ይሄ ስለሆነ ነው፡፡ (እስክንድር ያመነበትን ፊት ለፊት ነው የሚናገረው) ….ለተከሰሰሱት ሚዲያዎች በሙሉ አንድ ከልቤ ውስጥ ያለ አንድ መልዕክት አስተላልፍልኝ? በማለትም ጥያቄውን አስከተለ፡፡
‹‹እሺ››
እስክንድር ቀጠለ፡- ‹‹በክሱ መምጣት ልትደነግጡ አይገባም፡፡ ኢህአዴግ ሊከስስና በፍ/ቤት እንድትቀጡም ሊያደርጋችሁ ይችላል፡፡ ይሄንን ከዚህ በፊትም አይተነዋል፡፡ እናንተ ግን በታሪክ፣ በሕዝብና በህሊናችሁ ፊት ነጻ ናችሁ፡፡ የክስ፣ የእስርና የስደት መብዛት ሰላማዊ ትግል መኖሩንና ትግሉም እየሰራ መሆኑን ያሳያል፡፡ ሰላማዊ ትግል እና የመብት ጥያቄዎች ሲኖሩ እስር እና ክስ ይኖራሉ፡፡ አንዳንዴም ሞት ይኖራል፡፡ ክሱን ተከትሎ እኔ በግሌ ሁለት ዓይነት ስሜት አለኝ፡፡ ሰዎች ሲከሰሱ እና ሲታሰሩ አዝናለሁ፣ ይሰማኛል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሰላማዊ ትግል እየተሰራ እና ውጤት እያመጣ አድርጌ እቆጥረዋለሁ፡፡ እስር እና ክስ በበዙ ቁጥር የድል እና እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚፈጠርበት ጊዜ እየቀረበ መሆኑን አመላካች ነው፡፡ አይዟችሁ! ኢህአዴግ ሊፈርድባችሁ ይችላል፡፡ ነገር ግን፣ በታሪክ ፊት ነጻ ናችሁ፡፡ መንግሥቱ ንዋይ እኮ ያለአግባብ ተፈርዶበታል፤ በታሪክ፣ ሕዝብና በህሊናው ፊት ግን ነጻ ነው፡፡››
አያይዞም፣ ስለማርቲን ሉተር ኪንግ አንድ የግል ታሪክን አስታውሶ አወጋኝና ‹‹ኤልያስ፣ ለእውነት መቆም አለብን፡፡ ለእውነት መቆም ካልተቻለ ስብዕና ይወርዳል፣ ሕሊናህም ይሞታል፡፡›› በማለት ምክሩን ለገሰኝ፡፡
ሁለቱ ፖሊሶች ‹‹በቃችሁ!›› የሚል ድምጻቸውን አሰሙ፡፡ ከእስክንድር ጋር በ30 ደቂቃ ውስጥ ብዙ ቁም-ነገሮችን ተለዋውጫለሁ፤ መቼም ሁሉም አይጻፍ? ከእስክንድር ጋር ልለያይ ስል ባለቤቱ ሰርካለም ፋሲል እስክንድር 18 ዓመት የተፈረደበት ዕለት ከፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፒያሳ ድረስ አብረን ስንሄድ ደጋግማ የነገረችኝ ቃል ይበልጥ በውስጤ አቃጨለ፡፡
‹‹እስክንድር ማለት ላይብረሪ ነው፡፡ እሱን ማሰር አንድ ቤተ-መጽሐፍት እንደመዝጋት ይቆጠራል››
ሰርኬ፣ እውነትሽን ነው፡፡ ይሄንን ትናንትም በማወቅ አምን ነበር፣ ዛሬም ይበልጥ አውቄያለሁ፡፡
በመጨረሻ እስክንድር ‹‹እገሌ እገሌ አልልህም፤ ሁሉንም አከብራችኋለሁ፣ እወዳችኋለሁ›› በልልኝ ብሎ ተሰናበተኝ! እንግዲህ የእስክንድርን ሰላምታ አድርሻለሁ፡፡