tirsdag 28. mai 2013

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በገንዘብ የአለማችን ሀብታም ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን የበቁ መሆናቸው ተዘገበ



“ዘ ሪቸስት ዳት ኦርግ” የተሰኘው ድረ-ገፅ ይፋ እንዳደረገው፤ የቀድሞው ጠ/ ሚ/ር መለስ ዜናዊ የ3 ቢሊዮን ዶላር ባለቤት በመሆን ነው ከዓለማችን ፖለቲከኞች የሁለተኛ ደረጃን የያዙት።

“ዘ ሪቸስት” የተሰኘው ይህ ድረ-ገፅ፤ በአንደኛ ደረጃ ባለፀጋ ሲል ያሰፈራቸው የቀድሞውን የጣሊያን ጠ/ሚ/ር ሲልቪዮ በርሎስኮኒን ሲሆን አንደኛ ደረጃ ያስቀመጣቸውን የ5.9 ቢሊዮን ዶላር ያፈሩት ከፖለቲካው መድረክ ሳይሆን በሜዲያው መስክ ከተሰማሩበት ሥራ ነው።

የጣሊያኑ ሴሪአ የእግር ኳስ ክለብ የሆነው የኤ.ሲ. ሚላንና የቴሌሚላኖ የቴሌቪዥን ጣቢያ ባለቤት የቀድሞው የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ በርሎስኮኒ አሁንም የተንደላቀቀ ሕይወትን በመምራትና ዳንኪራ በመጨፈር የጣሊያንን ሜዲያዎች የፊት ገፅ የያዘ ፣ ርዕሰ-ዜና የሚሰራላቸው ታላቅ ሰው ናቸው ብሏቸዋል – ዘ ሪቸስት ዳት ኦርድ።

ከፍተኛ የገዘብ ምንጫቸው እንደሆነ የሚነገርለትና ላለፉት 25 ዓመታት በባለቤትነት የያዙት የአውሮፓው ታዋቂ የግር ኳስ ክለብ ኤሲ ሚላን ሲሆን፤ የ76 ዓመቱ በርሎስኮኒ በኢጣሊያ ቁጥር አንድ የሆነ የኢንተርቴይንመንት እንዲሁም የኢንሹራንስ፣ የባንክና የፊልም ፕሮዳክሽን ኩባንያዎች ባለቤት ጭምር ናቸው።

በግላቸው ከነዚህ ዓይነት የንግድ ዘርፎች ጭራሽ የሌሉበት የቀድሞው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ከሊባኖሱ ጠ/ሚኒስትርና የንግድ ሰው ነጀብ ሚካቲ የ3 ቢሊዮን ዶላር ባለቤት በመሆን የዓለማችን ሁለተኛ ባለፀጋ ፖለቲከኛ የተሰኙ ሲሆን የሀብት ምንጫቸው ፖለቲካ የተባለላቸው ሆነዋል።

በ3 ቢሊዮን ዶላር ጎን ለጎን ሆነው የተቀመጡት የቀድሞው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊንና የሊባኖሱን ጠ/ሚ/ር ነጂብ ሚካቲ የሚለያቸው የሀብት ምንጫቸው በአፍሪካ ያንሰራፉትና ያስፋፉት የቴሌኮም ኩባንያና ሌሎች የንግድ ሥራዎቻቸው ሲሆን የአቶ መለስ ዜናዊ ግን ፖለቲካ ብቻ መሆኑ ነው።

በዚህ የሀብታሞች ተርታ ሦስተኛ የተቀመጡት የሊባኖስ ጠ/ሚ/ር ሳድ አድን ራፊቅ አል ሐሪሪ ሲሆን የሀብት ልካቸውም 1.9 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ነው።

ታዋቂ የንግድ ሰው፣ ባለኩባንያና ፖለቲከኛው ራፊቅ አል ሐሪሪ የሃብት ምንጮቻቸውንም ቢዝነስ ነው ተብሏል በ ዘ ሪቸስት ዳት ኦርግ ዘገባ።

ከሴት ጠ/ሚ/ሮች የፓኪስታኗ ቤናዚር ቡቶ የ850 ሚሊዮን ዶላር ባለቤት ሆነው ከሴት ፖለቲከኞች በብቸኝነት ተጠቅሰዋል።

ያአቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ባለቤታቸው በ6000 ብር ደመወዝ ሲተዳደሩ ቆይተው በድህነት ኖረው በድህነት የሞቱ መሆኑን በመግለፅ ሲከራከሩላቸው፣ እንዲያውም የዓለማችን ደሃና ጠንካራ መሪ ተብለው ሊፃፍላቸው ይገባል በማለት ሲከራከሩ እንደነበር ይታወሳል።

mandag 27. mai 2013

Ethiopia: Asking ‘Why’ in the Land of ‘No why’


Only Boethius – that Roman philosopher of fickle fate and the vicissitudes of fortune – could have consoled a puny man in Ethiopia, who woke up to the malignancy of fate on the first week of May 2013.

Boethius sat at the pinnacles of power in Rome before treachery brought him down. Accused of treason, he was imprisoned and horrifically executed within a year of his downfall. But, not before he wrote “The Consolation of Philosophy”, a monologue between himself and “Lady Philosophy” in which he recounts his experience. The allegorical Lady consoles the fallen consul of the Ostrogothic king – the Master of Italy – by “discussing the transitory nature of fame and fortune, and the ultimate superiority of things of the mind”; the gist of her counsel being do good when you can, never trust fate.

I will answer for the crimes I have committed. … But, why my family? … Why? What have they done? …what kind of a country are we turning out to be?”
The words of a man with a name difficult to pronounce: Gabrewahid Wolde-Giorgis.
Gabrewahid was the feared the DEPUTY Director General of Ethiopian Revenue and Customs Authority. He was also something more relevant to this discussion. Gabrewahid was the political “advisor” of successive Presidents of Somali Regional State of Ethiopia in late 1990s and early 2000s, before he was given more enriching portfolios in the Federal Government. An advisor in name, a decider indeed, Gabrewahid was the mentor and the political God-father of many of today’s young stooges in the region.

Gabrewahid was arrested on 12 May 2013 in Addis Ababa, as part of a highly publicized crackdown on corruption. A week later, Ethiopian TV reported that Gabrewahid’s wife – a certain Colonel Haimanot – was arrested for obstruction of justice. The TV alleged that she was apprehended while trying to hide or destroy incriminating evidence. It displayed caches of local and foreign currencies and bags full of land title deeds and ownership certificates of building complexes, which it said were exhibits on the move to safe houses.

As the rotating wheels of fate indifferently pushed Gabrewahid from the cliffs of absolute power – acquired on account of affinity and lineage association to the Palace and the ruling tribe – and threw him down headlong to the forbidding prisons of Addis Ababa, the tumbling man rediscovered vocabulary which he has not known nor used for decades. He asks ‘why’! He remembers ‘why’, in a land that has long suspended the use of this word; among people who have long erased questions of reason from their daily language.

This immanent amnesia of abusers of power invokes the words of the thoughtful George Steiner.
In “Grammars of Creation”, Steiner posits that “when barbarism becomes so domesticated, it can only change our language for the worse”. Steiner highlights the example of a thirsty prisoner in one of the death-camps of Nazi Germany, who having watched his torturer pouring water on the floor asks, “ why are you doing this?”, only to be told “ there is no ‘why’ here’.

There is no ‘why’ in Ethiopia. There has not been ‘why’ for a long, a long time. Enveloping and erratic fate has finally woken Gabrewahid – a mere rider of this malignant wayfarer – to the real master of life’s ebb and flow. It is not Ethiopia that changed. It is Gabrewahid’s circumstances that changed irreversibly. Fate has uncaringly turned its wheels, in the process taking one more man down, lifting some others up.

Otherwise, Ethiopia is the same country. The rules of the game are intact. The status quo has not vanished. TPLF’s Ethiopia is not evolving into a monster that is has not been before. It remains a land where injustice and oppression reign. It is a country where the proverbial enigma of “suffering good men and successful bad men, ironically in a world overseen by God” is lived every day. It is not a different Ethiopia. We are living in the same Ethiopia Gabrewahid’s TPLF built. We are living in the same Ethiopia where the medieval rule of vicarious liability applies in the 21st century; a country where one is hanged for the real or perceived crimes of his kin.

Only a series of equally poignant ‘whys’ can answer Gabrewahid’s tragic ‘why’, and his subsequent question ‘what kind of a country are we turning out to be’.

Why were students who protested election results in Addis Ababa massacred on a broad daylight in 2005? Why did Professor Asrat Woldeys die in prison for speaking his mind? Why are Ethiopian journalists languishing in prisons for writing stories? Why are Birhanu Nega and many intellectual clairvoyants banished for winning elections? Why are Bekele Garba and Olbana Lelisa in jail?
Why were and are Ethiopian Somalis, mainly from the Ogaden clan, killed? Why were and are Ogaden women raped? Why were the dreams of many young girls dashed through rape and torture? Why have young boys fled their homes and are living in the squalid refugee camps of neighbouring countries? Why is Sultan Fozi Ali Abdi rotting in detention? Why is Bashir Dool suffering in a prison in a lifeless village? Why is Abdi Bakool not seeing his children for once? Why did the elderly Nadiir die in prison? Why have you, Gabrewahid, fired from their jobs through shoddy ‘evaluation sessions’ and ordered the arrest of men and women – whose only crime was to be brothers or relatives of perceived political opponents of the regime you served – in your prime days in Somali Regional State of Ethiopia?

These and many other ‘whys’ will lead the distressed Gabrewahid, and the wider terrified Ethiopian public, to the answers of the ostensibly esoteric ‘whys’. These answers, will hopefully help us to solve more substantive ‘Whys?’, which we – the oppressed people of Somali Regional State – grapple with every day.

Why is Abdi Iley, a psychopathic clown, anointed as our ‘leader’ and ‘President’, and is arresting and killing our elders and intellectuals? Why are mad men controlling the means of mental production through their control of material production (resources), thereby sowing the seeds of moral degeneration in our youth? What kind of a society will emerge when social rejects shape society’s values? Why are rowdy children in Palaces and the mature men in prisons?

Why are abusers of own people hailed as great leaders by some sections of the international community, while those who speak for the weak are labeled malcontents and extremists? Why this inexplicable transposition of fates?

Why is every small road that gives a veneer of progress and economic development being broadcasted, blown out of value and touted for phenomenal notice, while the rampant atrocities and violations of human rights in Ethiopia are not adequately covered by the international media and is not causing a global outcry?

Why what is wrong in Darfur is right in Somali (Ogaden) region? Why what is good for the goose is bad for the gander?

Why do only guests – foreigners – see good things in a house whose hosts – Ethiopians – swear is a hell? Why are some of our elders and intellectuals turning into a modern-day Coriolanus – the vengeful Roman warrior who vowed to destroy the same Rome which nurtured and revered him, out of hubris, out of foolhardy conceit? Why are they unable to unite for the noble ideal of democracy, justice and freedom? Why prolong the life of a totalitarian regime through schismatic politics? Why forfeit national aspirations to “address” sectarian agendas?

Why do domineering global powers glorify petty thieves and market them to their victims through enforced endearment? Why speak loudly about the roads built but remain silent about the violations of human rights? Why erase the language of justice and dignity from our daily use and affectedly recite grammars of ‘development’? Why give new and opposite meaning to old words? Why make ‘peace’ a subterfuge for continued oppression? Why make ‘struggle’ synonymous with anarchy and delusion?

Even more frustrating, why does the Ethiopia opposition cling to doctrinite politics – a politics dictated by inert conviction, not by realism and attendant flexibility and adjustment in policy and strategy?

We, too, have many unanswered ‘whys’.
We are equally confused, Gabre.

fredag 24. mai 2013

ሰማያዊ ፓርቲ በማንኛውም መልኩ ሰልፉን ለማካሄድ መወሰኑን አስታወቀ


የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጀነር ይልቃል ጌትነት ትናንት ለኢሳት ሬዲዮ እንደገለጹት የፓርቲው አመራሮች የፈቃድ ደብዳቤ ለማስገባት ወደ አዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት የሰላማዊ ሰልፍና የህዝባዊ ስብሰባ ማስታወቂያ ቢሮ ቢሄዱም ሃላፊዎቹ ደብዳቤውን ለመቀበል ፈቀደኛ አልሆኑም።

ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የቢሮ ሀላፊ ደብዳቤ አልቀበልም በማለታቸው የፓርቲው አመራሮች ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉ ከከንቲባው ጽህፈት ቤት ሀላፊ እሰከ ካቢኔ ጉዳዮች ምክትል ሀላፊ ድረስ ላሉ ሰዎች ለመስጠት ቢሞክሩም ” ደብዳቤ እንዳንቀበል ከበላይ ታዘናል” የሚል መልስ እንዳገኙ ገልጿል።

ከፓርቲው በኩል ሶስት ሰዎች ከማዘጋጃ ቤቱም እንዲሁ ሶስት ሰዎች በተገኙበት ደብዳቤውን ለሰላማዊ ሰልፍና ለህዝባዊ ስብሰባ ማስታወቂያ ቢሮ ሀላፊ ጠረጴዛ ላይ ማስቀመጣቸውን መግለጫው አመልክቷል።

ፓርቲው አክሎም ” ሰልፉን ለማድረግ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ በህግ በኩል የጎደለ አንድም ቅንጣት ነገር ባለመኖሩ ሰልፉ በታቀደው ቦታና ሰአት የሚካሄድ መሆኑን ” አስታውቋል።

onsdag 22. mai 2013

በገላሺ ከተማ የኢትዮጵያ ወታደሮች 10 ሰዎችን መግደላቸውን ኦብነግ አስታወቀ


የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ( ኦብነግ) ለኢሳት በላከው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ትናንት ግንቦት 13 ቀን 2005 ዓም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከልዩ ሚሊሺያ ጋር በመተባበር በወሰደው እርምጃ አቶ ማካሊ ሙስጠፋ ሀሰን፣ አቶ ሻፊ አው ካሊፍ፣ አቶ አብዱላሂ አብዲ፣ አቶ ሻኩል አብዲ፣ አቶ ፋራህ ሙሀመድ፣ አቶ አብዲሀይ ሼክ አህመድኑር እና አቶ አብድራሺ ሻፊቺች የተባሉትን ነዋሪዎች ገድለዋል።

የግድያው ምክንያት በጋላሺ የጦር ምድብ የሚገኙ 70 የልዩ ሚሊሺያ አባላት ከድተው እጃቸውን ለግንባሩ መስጠታቸውን ተከትሎ ፣ ነዋሪዎቹ የጠፉትን ወታደሮች አድራሻ እንዲያወጡ ከተጠየቁ በሁዋላ ነው። ወታደሮቹ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 7 ሰዎችን እጆቻቸውን ካሰሩ በሁዋላ እንደረሹኑዋቸው፣ 3ቱን ደግሞ ከከተማዋ 3 ማይል ርቅት በሚገኝ ቦታ ላይ እንደገደሉዋቸው ግንባሩ አስታውቋል።

ግንባሩ እንዳለው በዚህ አመት ብቻ ከ300 ያላነሱ የአካባቢው ተወላጆች በመከላከያ ሰራዊት እና በልዩ ፖሊስ አባላት ተገድለዋል።

 ጉዳዩን በማስመልከት ቃለምልልስ ያደረግንላቸው የግንባሩ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሀሰን አብዱላሂ፣ የከዱት ወታደሮች ግንባሩን መቀላቀላቸው እውነት ቢሆንም፣ የተገደሉት ነዋሪዎች ግን ድርጅቱ አባላት አለመሆናቸውን ገልጸዋል።

የግንባሩ የውጭ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ሀሰን አብዱላሂ በመከከላከያ ሰራዊት እና ልዩ ሚሊሺያ የሚፈጸመው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል
በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስትን መልስ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

የባለራእይ ወጣቶች ማህበር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ታሰረ



የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ ግንቦት14፣ 2005 ጧት ላይ በደህንነቶች ተይዞ መወሰዱን የማህበሩ ሊቀመንበር ወጣት ሀብታሙ አያሌው ለኢሳት ገልጿል።

ወጣት ብርሀኑ ሰማያዊ ፓርቲ ከጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ መታሰሩን ወጣት ሀብታሙ ገልጿል።

ወጣት ሀብታሙ ከሌሎች የማህበሩ አባላት ጋር በመሆን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ቢሄዱም፣ እስረኛውን ሊያገኙት እንዳልቻሉ ይሁን እንጅ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከቀኑ 9 ሰአት ላይ የወጣት ብርሀኑ ቤት እየተፈተሸ መሆኑን መረጃ እንደደረሳቸው ገልጿል።

ምሽት 12 ሰአት ላይ ያነጋገርነው የማህበሩ ቦሌ ክፍለከተማ ምክትል ሀላፊ ወጣት ጥላየ ታረቀኝ እንደገለጸው ደግሞ ከዚህ ቀደም ታስረው በነበረበት ወቅት ሲዝትባቸው የነበረው ሳምሶን የተባለ የደህንነት ሰራተኛ ወጣት ብርሀኑን እንዳስያዘው ገልጿል።

 የወጣት ብርሀኑ ቤተሰቦች ቤት ሲፈተሽም በአንድ መጽሀፍ ውስጥ ራሳቸው ደህንነቶች ያስገቡትን ጽሁፍ ” ይሀው አገኘነው በማለት” ብርሀኑን እንዲፈርም እንደጠየቁትና ከጠበቃየ ጋር ሳልማከር አልፈርምም እንዳለ ወጣት ጥላየ ተናግሯል።

በጉዳዩ ዙሪያ የጉለሌን ፖሊስ ጣቢያ ሀላፊዎች ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሰካም።

tirsdag 21. mai 2013

ሰሞኑን በደሴ ከተማ ሩቂያ እየተባለ በሚጠራው አዳራሽ በተደረገው ስብሰባ ህዝቡ ስሜቱን በድፍረት ሲገልጽ ዋለ


ስብሰባው ከማንኛውም የድምጽና የምስል ቀረጻ ነጻ እንዲሆን ቢደረግም ኢሳት በደሴ ከተማ ከሚኖሩ ወጣቶች ጋር በመተባበር ስብሰባውን ለመቅረጽ ችሎአል።

በዚህ ስብሰባ ላይ ከመልካም አስተዳዳር እና ከንግድ ጋር በተያያዘ የከተማዋ ታዋቂ ግለሰቦች እና የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች ትችቶችን እና ምስጋናዎችን አቅርበዋል። አብዛኞቹ ተናገሪዎች በከተማው ፖሊስ ላይ ከፍተኛ ነቀፌታ አሰምተዋል።

መንግስቱ ዘገየ የተባሉ የአማራ ክልል የጠበቆች ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት እና የህግ አማካሪ “ለዜጎች ለምን ጥብቅና ቆማችሁ ተብለን የእናቶቻችን ስም እየተጠራ በፖሊሶች ተሰድበናል” ብለዋል::

ሌላው ተናጋሪ አቶ ፈቃዱ አለነ ደግሞ ነዋሪዎች በጠራራ ጸሀይ እንደ ኬንያና ናይጀሪያ እየተዘረፉ መሆኑን ገልጸው የፖሊስ አመራሮች ራሳቸውን ማጥራት አለባቸው ሲሉ አክለዋል።

አቶ ቴዎድሮስ ታደሰ በበኩላቸው “ፖሊስና ህዝብ ከተራራቁ ቆይተዋል፣ ከፖሊስ አዛዡ እስከ ተራው መርማሪ ያለው መዋቅር ችግር አለው፣ ሀብታችን ዋስትና አጥቷል” ብለዋል።

አቶ ዮናስ ከበደ የተባሉ ተናጋሪ ደግሞ በምሽት የከተማው ህዝብ እንደልቡ መጓዝ በማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ገልጸዋል።

ገብረማርያም የተባሉ ነዋሪም እንዲሁ ሰው የገደለ ሰው 7 ቀን ታስሮ ሲፈታ ሰው ያልገደ ሰው ደግሞ ደሀ ስለሆነ ብቻ ለ2 ወራት ታስሮ ለመፈታቱ ማስረጃ አለኝ በማለት የፖሊስን አሰራር ነቅፈዋል።

ነዋሪዎቹ በንግዱ ማህበረሰብ ላይ እየደረሱ ያሉ በደሎችንም ዘርዝረው አቅርበዋል። እያሱ ጌታቸው የተባሉ ነዋሪ በከተማ ውስጥ አንድ የንግድ ፈቃድ ሰጪ መስሪያቤት ብቻ ቢኖርም፣ የሚያሽጉት ድርጅቶች ብዛት በርካታ መሆን በመንግስት በኩል የተቀናጀ ስራ አይሰራም ወይ? የሚል ጥያቄ እያስነሳ መሆኑን ገልጸዋል።

ህዝቡ ባነሳቸው ጥያቄዎች ዙሪያ ስብሰባውን የመሩትን የደሴን ከተማ ከንቲባ አቶ አለባቸውን ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም ስልካቸውን ባለማንሳታቸው ሊሳካልን አልቻለም።

የስብሰባውን ሂደት ለመቅረጽ የተባበሩንን የደሴ ከተማ ወጣቶች ለማመስገን እንወዳለን።

mandag 20. mai 2013

ሰበር ዜና..... ፋሲለደስ የተባለች ጀልባ በጣና ሀይቅ የመገልበጥ አደጋ በመድረሱ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች ህይወት ተቀጠፈ!!


ይችን እና ሌሎች መሰሎቿን ጀልባዎች ፤ጣና ላይ ጥሏቸው የሄደው ጣልያን ነበር።ፋሲለደስ፣ታጠቅ፣ሊማሊሞ፣አንድነት ተብለው ተስመዋል።በአካባቢው ኗዋሪዎች የአሽዋ መርከብ ተብለውም ይጠራሉ።አብዛኛው ስራቸው ከደልጊ ባህርዳር አሸዋ ማጓጓዝ ነው።የጣና ሃይቅ ትራንስፖርት(ናቢጋ ጣና)፣'በመንግስት' የተረሳ ድርጅት በመሆኑ በአዲስ ሊተካቸው አልቻለም።

ይባስ ብሎ ለህዝብ ማጓጓዣነት ይጠቀምባቸዋል (የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንዲሉ)...አማራጭ የሌለው ወገኔ ነብሱን ሽጦ በነዚህ መርከቦች መጠቀም ግድ ይለዋል።

የአገሬ ሰው ከጎርጎራ-ደልጊ-እሰይደብር-ቁንዝላ-ደቅ(ጉረር)-ዘጌ-ባህርዳር በነዚህ ጥርሳቸውን በፈጁ የአሸዋ መርከቦች ሲቀዝፍ ባጅቷል። እስከ ዛሬ ድረስ ይህን ያህል የከፋ አደጋ ደርሶ አያውቅም ነበር፣መንግስት ቢጨክንበትም እሩህሩሁ ጣና እና ጀልባዎቹ ተስማምተው ይወስዱት ይመልሱት ነበር።

ዛሬ ግን አልሆነም። ጣናም በሞገድ ተናጠ ፤ከመርከቦቹ አንዷ የሆነችው ፋሲለደስም ሩጫዋን ጭረሰች እና ሰጠመች። አማራጭ የለሹ ድሃው ወገኔም አለቀ አሉኝ! ነብሱን ሽጦ የተሳፈረው ወገኔ የፈራው ደርሰበት። እህህህ.....ወገኔ መከራህ መከራዬ በዛ! ስቃይህ ስቃዬ አላልቅ አለ!...እህህህ.....

søndag 19. mai 2013

May 18, Tribute to Mr. Abebe Gelaw

18 May 2012 Abebe Gellaw's call for freedom
This day marks the 1st Anniversary of that unforgettable occasion on 18 May 2012 that your call for freedom at the Regan Memorial Building in Washington, at the meeting of world leaders and dignitaries chaired by President Obama. The man that you quite rightly labeled “Meles Zenawi is a dictator” was seen shaken, drooping, scared and demoralized in that Hall. He shamed his cohorts that are engaged in building his personality cult crowning him with the accolade: “Statesman leading Africa and a fearless commander of a fighting guerrilla force that shook the mountains”. To hide their utter embarrassment they even profusely disseminated the tyrant’s photograph sitting on a tank reading a book.
18 May 2012 Abebe Gellaw’s call for freedom at the Regan Memorial Building in Washington.
Your clear call reverberated in our global village of the age of information and promptly elevated the moral of Ethiopians; it instilled renewed hope and resolve to unite the forces of change in their struggle against the dictatorial TPLF/EPRDF regime well-armed to the teeth and supported by the Western powers.
In my opinion, unity of the Ethiopian people, opposition political forces, and independent civil societies is now on a steady march to eradicate tyrannical governance once and for all. The scattered anger has been gathering in the course of the year (since 18 May 2012) to the point of becoming a formidable force, which is able to deal with the atrocious legacy of Meles Zenawi who was publicly calling well-meaning opposition entities his enemies.

torsdag 16. mai 2013

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የተጀመረው ተቃውሞ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎአል




በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ጋሞ ካምፓስ ትናንት ከምሽቱ 4 ሰአት ላይ የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ያዋለ ሲሆን “ተማሪዎች መብታችን ይከበር፣ ድምጻችን ይሰማ፣ ጥያቄያችን ይመለሰ፣ ተምሮ ለኮብል ስቶን ” የሚሉ መፈክሮች አሰምተዋል።

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት ግቢውን የተቆጣጠሩት ሲሆን ተማሪዎች እርስ በርስ እንዳይገናኙ አድረገዋል።

ተማሪዎች የምግብ መበላሸትን ሰበብ አድርገው አድማውን ቢጀምሩም፣ ሌሎች ከትምህርት ጥራት እና ከአስተዳደር ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ማነንሳታቸውን አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የዩኒቨርስቲው ሰራተኛ ተናግረዋል።

 እስካሁን 9 ተማሪዎች ታስረዋል። የተደበደቡ ወይም ሌላ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች እስካሁን ለማግኘት አልቻልንም።
ተማሪዎች በየክፍላቸው መስኮቶች ላይ ቆመው ጥያቄያችን እስካልተመለሰ ድረስ ትምህርት አንጀምርም በማለት እየጮሁ ነው።
በጉዳዩ ዙሪያ የትምህርት ቤቱን አስተዳዳሪዎች ለማግኘት ያደረግነው መኩራ አልተሰካም።

በተያያዘ ዜና በጉምሩክ ባለሥልጣኖችና ባለሃብቶች ላይ የተጀመረው የምርመራ ሥራና ዘመቻ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ትዕዛዝና መመሪያ መሆኑ ተገለጠ



የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑትን አቶ ዓሊ ሱሌይማንን ጠቅሶ ሪፖርተር እንደዘገበው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሕይወት በነበሩበት ወቅት በሰጡት የሥራ መመሪያ መሰረት ጥናትተደርጎ የተከናወነ መሆኑን አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአመት ከአሥር ወር በፊት የሥራ መመሪያ መስጠታቸውን ለተወካዮች ምክር ቤት የተናገሩት ኮሚሽነሩ ጥናቱ ሲጠናቀቅ አቶ መለስ በመታመማቸው ውሳኔ አግኝቶ ወደሥራ ሳይገባ ቆይቷል ብለዋል።በኢትዮጵያ ባለው አሰራር ግማሹ ግብር ይከፍላል፣ ግማሹ ግብር አይከፍልም፣ ግማሹ ታክስ ከፍሎ ዕቃ ያስገባል፣ ግማሹ ታክስ ሳይከፍል ዕቃ ያስገባል ሲሉ ለም/ቤቱ የገለፁት ኮሚሽነር ዓሊ ሱሌይማን፣ በዚህ ምክንያት በንግዱ ኅብረተሰብ ውስጥ ሚዛናዊና የተደላደለ ውድድር እንዳይኖር ማድረጉን አብራርተዋል።

በጉምሩክ የሙስና ተግባር ተጠርጥረው ከታሰሩት መካከል ማንም ሰው ያለመከሰስ መብት ያለው አይመስለኝም ያሉት አቶ ዓሊ፣ ያለመከሰስ መብት ደግሞ ሊነሳ ይችላል ሲሉ አብራርተዋል።

አቶ መላኩ ፈንታ የብአዴንና የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሲሆኑ፣ ከባሕር ዳር ከተማ አዲስ አበባ ለመግባት አየር ላይ እያሉ የአማራ ም/ቤት ያለመከሰስ መብታቸውን ማንሳቱን ለማወቅ ተችሏል፡;

በገምሩክ ባለሥልጣናትና ነጋዴዎች ላይ የተደገረው ምርመራና ክስ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ መታዘዙ ሲገለፅ በአቶ መለስ ሞት ማግስት የተሾሙት ጄኔራሎችም በአቶ መለስ እንዲሾሙ የተመለመሉ ናቸው መባሉን በማስታወስ የገዢው ፓርቲ የሚሰራቸውን ሥራ ሁሉ በሞት ከተለዩት የድርጅቱ መሪ ጋር ማያያዝ አስገራሚነቱን ያጎላዋል የሚሉ በዝተዋል።

onsdag 15. mai 2013

በቻግኒ ከተማ የህዝብን ተቃውሞ ተከትሎ አንድ መስጊድ ታሸገ


በአዊ ዞን በቻግኒ ከተማ መስጊድ አረህማን እየተባለ የሚጠራው ነባር መስጊድ የታሸገው ህዝቡ መንግስት የወከለውን አሰጋጅ አንቀበልም በማለት ተቃውሞ በማሰማቱ ነው። በመስጊዱ መግቢያ ላይ የተለጠፈው ወረቀት ፣ ” ከዛሬ ጀምሮ በዚህ መስጊድ መስገድ በህግ ያስቀጣል” የሚል ይዘት እንዳለው የአይን እማኞች ተናግረዋል።

ነባሩ መስጊድ እንዲታሸግ መደረጉን ተከትሎ ህዝበ ሙስሊሙ መንገድ ላይ መስገድ መጀመሩን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም 9 ሙስሊሞች ተቃውሞ በማሰማታቸው በስድስት ወራት እስራት መቀጣታቸው ይታወሳል።

መንግስት በሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚቀርበውን ተቃውሞ ለማፈን በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ እና መንግስት በመረጣቸው አሰጋጆች ለመስገድ ፈቃደኛ ያልሆኑ ሰዎች የሚሰግዱባቸውን መስኪዶች እያሸገ እንደሚገኝ መዘገባችን ይታወሳል።

በባህርዳር 17 ሰዎችን በጥይት አርከፍክፎ በግፍ የገደለው የፌደራል ፖሊስ አባል ከዘር ጋር የተያያዘ ምክንያት የለውም ሲሉ የአማራ ክልል የፖሊስ አዛዥ ተናገሩ



እሁድ ግንቦት4፣ 2005 ዓም ከምሽቱ 2 ሰአት ከ45 ደቂቃ ላይ ፣ የሁለት አመት ህጻንን ጨምሮ 17 ሰዎችን በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 11 ወይም በተለምዶ አባይ ማዶ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በግፍ የገደለው የፌደራል ፖሊስ አባል ማንነት መለየቱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አስታውቋል።

ኢሳት ትናንት ፖሊሱ የሌላ ብሄር ተወላጅ መሆኑን ጠቅሶ የዘገበ ሲሆን አንዳንድ ወገኖች ይህን በመንተራስ ጉዳዩ ከዘር ጋር ሊያያዝ ይችላል በማለት አስተያየት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

በዛሬው እለት የገዳይ ወታደር ኮንስታብል ፍቃዱ ናሻ አስከሬን ጨረጨራ እየተባለ በሚጠራው በጣና ሀይቅ እና በአባይ ወንዝ መለያያ አካባቢ በተሰራው ግድብ ውስጥ የተገኘ ሲሆን፣ ገዳዩ ፊቱ አካባቢ በአሳዎች እንደተበላ በስፍራው ነበሩ የአይን እማኞች ገልጸዋል። ወታደሩ እስከነ ሙሉ ዩኒፎርሙ በጠላቂ ዋናተኞች ሊወጣ መቻሉን የአይን እማኞች አክለው ገልጸዋል።

የሆኑት ሙሉጌታ ወርቁ ” ወታደር ፈቃዱ ግድያውን የፈጸመው ከዚህ ቀደም ያፈቅራት የነበረችው ጓደኛው ወ/ት ዘቢደር ከእርሱ ጋር ለመቀጠል ፈቃደኛ ባለመሆኗ በመበሳጨት በቂም በቀል በመነሳሳት ነው” ብለዋል። የግድያው መንስኤ ከዘር ጋር የተያያዘ ነው የሚለውን እንደማይቀበሉት ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

ባህርዳር ዛሬም በሀዘን ድባብ ውስጥ እንደምትገኝ ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።

lørdag 11. mai 2013

የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሀመድ ኡመር አድገናል በማለት የምናቀርበው ሪፖርት ሁሉ ውሸት ነው አሉ


ፕሬዚዳንቱ የካቢኔ አመራሮችን እና የሶህዴፓ ፓርቲ አባሎችን በመሰብሰብ እንደተናገሩት ክልሉ እንደ ለማ እንደ አደገ ተደርጎ ለመንግስት የሚቀርበው ሪፖርት ሁሉ ግምገማ ለማለፍ ተብሎ የሚቀርብ በውሸት የተሞላ ነው ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ በስሜት ውስጥ ሆነው ባደረጉት ንግግር “ እኛ እንዳደግን ፣ ጥሩ ደረጃ ላይ እንደደረስን ተደርጎ በየጊዜው የሚቀርበው ሪፖርት ፍጹም ትክክል ያልሆነ ውሸት ነው። አሁን በእጄ የያዝኩት ሪፖርት እውነት ስለመሆኑ እርግጠኞች አይደለንም፤ ከአሁን በፊት ይቀርቡ የነበሩ ሪፖርቶችም እንዲሁ ናቸው። ግምገማ ለማለፍ ተብሎ በውሸት የተሞሉ ሪፖርቶች ናቸው የሚቀርቡት ” ብለዋል

ፕሬዚዳንቱ ” 10 ሚሊዮን እንስሶች ክትባት እንደተደረገላቸው ሪፖርት አድርገናል፤ ሪፖርቱ እውነት ስለመሆኑ እንኳ የግብርና ቢሮው ሃላፊው መማል ( ማረጋገጥ) አይችልም። እንኳንስ 10 ሚሊዮን 500 ሺ እንኳን ስለመከተቡ ምን ማረጋገጫ ይገኛል። ለመሆኑ ህዝቡ ይህ ሁሉ ሲከተብስ አያይም ወይ?” በማለት የሚቀርበው ሪፖርት በሙሉ ውሸት መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ አብዲ ሬዲዮ አዲስ አበባና ሬዲዮ ፋና ስለሌሎች አካባቢዎች እየዘገቡ ስለ ኦጋዴን ችግር አለመዘገባቸውንም ኮንነዋል።
“አዲስ አበባና ሬዲዮ ፋና ስለሌሎች አካባቢዎች ይዘግባሉ ፣ ነገር ግን ስለዚህ ህዝብ ችግር መዘገብ ነበረባቸው። አይዘግቡም። ማን ነበር ቃለምልልስ መስጠት የነበረበት? የወረዳ እና ዞን ሀላፊዎች ነበሩ።
አቶ አብዲ ” በክልላቸው ያሉ ባለስልጣናት በሰላም ገብተው በሰላም ማደራቸውንም እንኳ ለመንግስት ሪፖርት እንደማያደርጉ ገልጸዋል።

ኢሳት የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት የደረጉትን ሚስጢራዊ ንግግሮች ባቀረበው የመጀመሪያ ክፍል ፕሬዚዳንቱ ” ትግሬዎች፣ አማራ መልሶ ስልጣን እንዳይዝ ኦጋዴኖችን አስታጥቀው በጋራ አገሪቱን እንድንመራ ይፈልጉ ነበር፣ እኛ ግን እንደ አማራ ቆጥረናቸው ተኩስ ከፈትንባቸው፤ አማራ እና ትግሬ፣ አማራ እና ኦሮሞ መቼውንም አይታረቁም ፣ አይተባበሩም ስለዚህ የኦጋዴን ህዝብ ከትግሬ ጎን እንዲቆም፣ አማራ እና ትግሬን፣ አማራ እና ኦሮሞን አንድ አድርጎ አማራ እያለ መጥራቱን ያቁም” በማለት መናገራቸው ይታወሳል።

በጉዳዩ ዙሪያ የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንትን ለማግኘት ሙከራ ብናደርግም ፕሬዚዳንቱ ስብሰባ ላይ ናቸው በሚል ጸሀፊያቸው ልታገናኝን አልቻለችም።

fredag 10. mai 2013

አቶ መለስን የሚመጥን ጥቅስ ፍለጋ፤ “ኢህአዴግን ነፍስ ይማርልን!”



 አንዳንድ ወዳጆቻችን ልክ በህይወት ያሉ እስኪ “መስል ድረሰ መለስ ለልደትህ እንኳን አደረሰህ!… መልካም የልደት በዓል ይሁንልህ!” ሲሏቸው አይቼ ሳቅቼ ሳቅቼ ሞተውት! (ደግሞ እኮ …አንተ… ነው የሚሏቸው …ወይ ጫማ መለካካት!)

እንደ እውነቱ ስለ መለስ የልደት ቀን መታሰቢያ ለማድረግ ከኔ የሚቀድም አካል መኖር አልነበረበትም፡፡ ያ ሁሉ ወዳጅነታችን ከግባ መሬቱ ጋር አብሮ የተቀበረ አስመሰልኩት እኮ!

“ስለ አቶ መለስ ልደት ስናወራ የሚመጥነውን ጥቅስ ማግኘት ይከብዳል!” አለ አንድ ዋነኛ የኢህአዴግ ካድሬ እውነት ብሏል ስለ መለስ ለማውራት ራሳቸው በተለያዩ የሞቅታ ቀናት የተነገሯቸው ንግግሮች ካልሆኑ በቀር የሚመጥናቸውን ጥቅስ ማግኘት ከባድ ነው፡፡

ከሞቅታት በአንዱ ቀን አቶ መለስ ዜናዊ አስረስ፤ እንዲህ ብለው የማይረሳ ንግግር ተናግረው ነበር፤ “በአንድ ድርጅት ውስጥ የአንድ ሰው ስብዕና መግዘፍ ከጀመረ ያ ድርጅት ሞቷል ማለት ነው” ኦ…. ብፃይ መለስ አፌ ቁርጥ ይበለልዎ!
በህይወት እያሉ እኛ የሀገራችንን መልካም ገፅታ ስንገነባ እርሳቸው ግን የራሳቸውን መልካም ገፅታ ሲገነቡ ነበር፡፡

 እንዴት ያሉ የመልካም ገፅታ ግንበኛ መሰልዎት…! በስታድየም አካባቢ እንኳ ከሶስት በላይ ፖስተሮቻቸው ከኑሮ ውድነቱ በላይ ተሰቅለው ነበር፡፡ በየ ክፍለ ሀገሩ በየቀበሌው እና በየ ሰፈሩ ሳይቀር መለስ ያልተሰቀሉበት አልነበረም፡፡

አንዳንዶች “ይህንን መለስ አላዘዙም” ሲሉ ቢደመጥም እኛ ግን እናውቃለን ብንናገር እናልቃለን ብለን ፀጥ ብለን ቆይተናል፡፡
አንዳንድ ሰዎች የአቶ መለስን የህይወት ዘመን የስራ እንቅስቃሴ በአጭሩ ግለፁ ሲባሉ “…በተለይ ከሆነ ጊዜ ወዲህ እኛን በሳቅ ሲያፈርሱ፤ ራሳቸውን ደግሞ በምስል ሲገነቡ የኖሩ ታላቅ መሪ!” ይሏቸዋል፡፡

ሰሞኑን ደግሞ “አቶ መለስ የዋሉልን አንድ የማይረሳ ትልቅ ውለታ አለ” ሲል አንድ ወዳጄ ነገረኝ፤ ሁለመናዬን ጆሮ አድርጌ ምን ይሆን ወዳጄ… ብለው… “በጊዜ መሞታቸው” አለኝ!
አቶ መለስ ዜናዊ አሁን ሞተዋል፡፡ የገፅታ ግንባታቸው ግን አልሞተም፤

እውነትም አቶ መለስን ስናስብ ራሳቸው ከተናገሩት ውጪ ሌላ ጥቅስ ማግኘት ከባድ ነው፡፡ እስቲ እንድገማት፤ “በአንድ ድርጅት ውስጥ የአንድ ሰው ስብዕና ጎልቶ ከወጣ” ድርጅቱ ሞቷል ማለት ነው፡፡” ስለዚህ እንደ አቶ መለስ አነጋገር ኢህአዴግዬ የሞተችው ከእርሳቸውም ቀድማ ነው እናም ኢህአዴግ ሆይ… ነፍስ ይማርልን! ማለት አለብን ማለት ነው፡፡
በመጨረሻም፤

በአውሮጳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በጄኔቭ የተባበሩት መንግሥታት ዋና መ/ቤት ፊት ለፊት የሕዝብ ትዕይንት አደረጉ



ከአውሮፓ የተለያዩ ከተሞች የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት በጄኔቭ ስዊትዘርላንድ የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን በአማሮች ላይ የደረሰውን መፈናቀል የሚያሳይ የጽሑፍ፣ የድምፅና የምስል ማስረጃ ለሦስት ዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች ማስረከባቸውንም ባልደረባችን ወንድምአገኝ ጋሹ ከሥፍራው ዘግቧል።

ከቤኒንሻንጉል ጉምዝ ክልል በቅርቡ የተፈናቀሉትን አማሮች ሁኔታ በዋናነት በማንሳት ባለፉት 22 ዓመታት በሀገሪቱ የቀጠለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ በማውሳት የተቃውሞ ድምፃቸውን ያስተባበሩት ኢትዮጵያውያን ትዕይንተ ሕዝቡን ባዘጋጀው ግብረ ኃይል አባላት አማካኝነት ለተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ ለዓለም ዐቀፍ ቀይ መስቀል እንዲሁም ለዓለም አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት በሰነድ የተደገፈ አቤቱታቸውን አቅርበዋል።

በጽሑፍ፣ በምስል እና በድምፅ የተደገፈውን ማስረጃቸውን ለተዘረዘሩት ተቋማት ያቀረቡት ኢትዮጵያውያን በጎ ምላሽ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

 ዓለም ዐቀፉ ቀይ መስቀል የአፍሪካ ዋና ዳይሬክተር ኢትዮጵያውያኑን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን፤ ተፈናቃዮቹ መልሰው በሚታተሙበት ሁኔታ ላይ በሀገር ቤት ካሉት ወኪሎቻቸው ጋር እንደሚነጋገሩ ገልፀዋል።

የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ዋና ዳይሬክተርና ትዕይንተ ሕዝቡን ያስተባበረውን የኢትዮጵያውያኑን ግብረ ኃይል ያነጋገሩ ሲሆን፣ አዎንታዊ ምላሽ በመሥጠት ተፈናቃዮቹን ለመታደግ ያላቸውን ዝግጁነት እንደገለፁም ተመልክቷል።

ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ግብረ ኃይሉ ከሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኃላፊዎች ጋር ያደረገውን ቆይታ የተመለከተ ዝርዝር ሪፖርት ማግኘት አልቻልንም።

ታዋቂ የኢትዮጵያ ሶማሊ ተወላጆች የክልሉ ፕሬዚዳንት በድብቅ ያደረጉት ንግግር እየነቀፉ ነው



በኢህአዴግ የሽግግር መንግስት ወቅት ለሶስት አመታት በዲፕሎማትነት፣ በመምህርነት እና በጋዜጠኝነት የሰሩትና በርካታ የታሪክ መጽሀፎችን የጻፉት አቶ መሀመድ ሀሰን ለኢሳት እንደተናገሩት ፣ የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሙሀመድ ኡመር የተናገረው ከወያኔ በስሎ የቀረበለትን ነው በማለት ተናግረዋል። “ግለሰቡ ያልተማረ ነፍሰ ገዳይ ነው” የሚሉት አቶ ሙሀመድ ፣ የመለስ ዜናዊ ቀኝ እጅ እንደነበረም ገልጸዋል።

 ክልሉ ለወያኔ ጄኔራሎች የመወፈሪያ ክልል ነው ያሉት አቶ ሙሀመድ፣ ፕሬዚዳንቱ የተናገሩትም የራሳቸውን ባለመሆኑ እንደ ቁም ነገር አይቆጠርም

ኢሳት ይፋ ያደረገው ቪዲዮ የክልሉ ባለስልጣናት የአመራር ብስለት ምን ያክል ደረጃ እንደደረሰ ያሳያል ያሉት አቶ ሀሰን፣ የአመራር ችሎታ ያላቸው ሰዎች እንደማይፈለጉ ገልጸዋል

የፌደራሉ መንግስት በፕሬዚዳንቱ ላይ እርምጃ የሚወስድ ይመስልዎታል? ተብለው የተጠየቁት አቶ አብዲ ፣ ኢህአዴግ እሱን የመሰለ ጨካኝ ሰው እንደማያገኝ ገልጸው፣ ዋናው ነገር ኢህአዴግ መልእክቱን በግለሰቡ በኩል በማስተላለፉ አጠቃላይ የመንግስትን ፖሊሲ ለማወቅ መርዳቱን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ( ኦብነግ) የውጭ ግንኙነት ሐላፊና ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ሀሰን አብዱላሂ በበኩላቸው ፕሬዚዳንቱ የተናገሩት በትክክልም የወያኔን ፖሊሲ ነው ብለዋል

እኛ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ጥላቻ የለንም ያሉት አቶ ሀሰን፣ ወያኔ ህዝቡን ከፋፍሎ ለመግዛት የሚጠቀምበት ስልት ነው ብለዋል።
መንግስት በፕሬዚዳንቱ ላይ እርምጃ ይወስዳል ብለው ያስባሉ ተብለው የተጠየቁት አቶ ሀሰን “በፍጹም” በማለት መልሰዋል
ኢሳት የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሙሀመድ በድብቅ ከአካባቢው ሽማግሌዎች ጋር ያደረጉትን ውይይት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

torsdag 2. mai 2013

መንግስት በድምጻችን ይሰማ አስተባባሪዎች ላይ በድጋሜ ዘመቻ ሊከፍት ነው



ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ባገኘው አስተማማኝ መረጃ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ድምጻችን ይሰማ በማለት በየሳምንቱ የሚያቀርቡት ተቃውሞ የስርአቱን ህልውና እየተፈታተነው በመምጣቱ መንግስት ችግሩን በድርድር ከመፍታት ይልቅ በከፍተኛ እና መካከለኛ እንዲሁም በቀበሌዎች አካባቢ ያሉ የተቃውሞ አስተባባሪዎችን በመለየት ሰብስቦ ለማሰር እና ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላቸው የሚል ክስ ለመመስረት ማቀዱ ታውቋል።

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ታማኝ የኢህአዴግ ካድሬዎች በቅርቡ በጦላይ እና በብርሸለቆ ለዚሁ ተግባር የሚያገለግል ስልጠና ለመውሰድ እንደሚገቡ ታውቋል። ከህብረተሰቡ፣ ከቀበሌ አመራሮች እና ከአባላት የሚውጣጡት ሰልጣኞች ስልጠናቸውን እንደጨረሱ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ይመራሉ የሚሉዋቸውን ሰዎች በመለየት ለዚህ ስራ ተብሎ ለተቋቋመው አካል ሪፖርት ያደርጋሉ።

መንግስት ልዩ ትኩረት ይደረግባቸዋል ብሎ የዘረዘራቸው አካላት የዩኒቨርስቲ እና የሁለተኛ ደረጃ መምህራን ፣ነጋዴዎች እና በየአካባቢው የእስልምና ትምህርት በሚሰጥባቸው መደርሳዎች ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ናቸው።

 በአሁኑ ጊዜ ልዩ ትኩረት የተጣለባቸው የድምጻችን ይሰማ አመራሮች በድብቅ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑንም ከምንጫችን ለመረዳት ተችሎአል።

ለወደፊቱ በሚያዙት አመራሮች ላይ የግንቦት7 ቅጥረኞች፣ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙትን ደግሞ የኦነግ ቅጥረኞች እና የተለያዩ አክራሪዎች መናጆ በመሆን ለህገምንግስታዊ ስርአቱ አደጋ በመደቀን ክስ ለመመስረት መታቀዱንም ለማወቅ ተችሎአል።

መንግስት በአቶ አቡበክር አህመድ የሚመራው የድምጻችን ይሰማ ኮሚቴ አባላትን ካሰረ በሁዋላ የሙስሊሞች እንቅስቃሴ ሊበርድ ይችላል የሚል እምነት የነበረው ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ እምነቱ ወደ ተግባር ሲለወጥ አልታየም። በዚህም የተነሳ በአሁኑ ጊዜ ተቃውሞውን በየአካባቢው ያስተባብራሉ በማለት የጠረጠራቸውን ሙስሊሞች በማጥናት በድጋሜ ለማሰር በዝግጅት ላይ ነው።

የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች በሙስሊሙ ጉዳይ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መግባታቸውን ከከፍተኛ ባለስልጣናቱ ያገኘነው መረጃ የሚያመለክት ሲሆን፣ የሀይማኖት እንቅስቃሴው ቀስ በቀስ ወደ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ሊለወጥ እና መላውን ህዝብ ያሳተፈ እንቅስቃሴ ሊጀመር ይችላል የሚል ድምዳሜ ላይ እየደረሱ መምጣታቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ችግሩን ውስብስብ ያደረገው ደግሞ አብዛኞቹ የኢህአዴግ ሙስሊም አባላትና ደጋፊዎች የድምጻችን ይሰማ እንቅስቃሴን መደገፋቸው ነው።