fredag 30. mai 2014

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በኑር መስኪድ ደማቅ ተቃውሞ አደረጉ

የሙስሊም የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት በፍትህ እጦት በእስር ቤት መሰቃየት መቀጠላቸውን በመቃወም በአዲስ አበባ በኑር መስጊድ በተደረገው ተቃውሞ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ መገኘቱን ዘጋቢያችን ገልጻለች።
ድምጻችን ይሰማ ቀደም ብሎ ባወጣው መግለጫ የተቃውሞው ዋና አላማ የሙስሊሙን ህዝብ ጥያቄ አንግበው በመያዛቸው በእስር እየተሰቃዩ ለሚገኙት መሪዎች ድጋፍ ለመግለጽ ነው መሆኑን ጠቅሷል።
በዘገየ ፍትህና በችሎት ድራማ እየተንከራተቱ የሚገኙት መሪዎች ሲታገሉለት እና ለእስር የተዳረጉበት አላማ የሙስሊም ህዝብ መሰረታዊ የመብት ጥያቄ አካል መሆኑን የገለጸው ድምጻችን ይሰማ፣ የእነሱ መስዋትነት ለህዝቡ የሰጡትን ቦታ፣ ለሃይማኖታቸው ያላቸውን ቀናኢነት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው ብሎአል።
ሙስሊም ኢትዮጵያውያኑ ” ኮሚቴው የህዝብ ነው፤ እኛም ኮሚቴው ነን፣ ፍትህ ለወኪሎቻችን ” የሚሉ መፈክሮች ከፍ አድርገው በመያዝ እንዲሁም እጆቻቸውን አጣምረው በመቆም፣ የመሪዎቻቸውን ስቃይ ከመጋራት አልፈው ከጎናቸው መቆማቸውን አመልክተዋል።
የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት የፍርድ ሂደት እንደቀጠለ ሲሆን፣ እስካሁን ድረስ መንግስት አባላቱን በሽብረተኝነት ለመክሰስ የሚያስችለው ይህ ነው የተባለ ማስረጃ ሊያገኝ አለመቻሉን የፍርድ ሂደቱን የሚከታተሉ ሰዎች ይገልጻሉ።
አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የሙስሊሞችን የመብት ጥያቄ ለማዳከም መቻላቸውን አስመልክቶ በአንድ ወቅት መግለጫ የሰጡ ቢሆንም፣ ድምጻችን ይሰማ አሁንም ጠንካራ ደጋፊዎች እንዳሉት የሚያሳይ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው።
ተቃውሞው ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ አንዳንድ የክልል ከተሞችም መካሄዱን ለማወቅ ተችሎአል።

torsdag 29. mai 2014

ሱዳን በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከአገሯ አስወጣች

በካርቱም ሁዳ እየተባለ በሚጠራው እስር ቤት ከ800 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የሚገኙ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል 40 እስረኞች ሰሞኑን ከእስር ቤት ወጥተው ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን ሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል።
ካርቱም አካባቢ የተሰበሰቡ  ከ600 በላይ ኢትዮጵያውያን ተጠርዘው ወደ አገራቸው መወሰዳቸውን እስካሁን ደረስ ኢትዮጵያ ይድረሱ አይደረሱ አልታወቀም።
የሱዳን ፖሊስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደ አዲስ በጀመረውን ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው የመመለስ ዘመቻ፣ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎች መሞታቸውንና ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል።
አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ከ15 አመት ላላነሰ ጊዜ በሱዳን እስር ቤቶች እንደሚገኙ እነዚሁ ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል።
የኢህአዴግ  መንግስት ተቃዋሚዎችን ይቀላቀላሉ ብሎ በመስጋቱ የሱዳን መንግስት በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙና የገዢው ፓርቲ አባል ያልሆኑትን ዜጎች እንዲያስወጣለት መጠየቁ ይታወሳል። ሁለቱ አገሮች በቅርቡ በተፈራረሙት የጸጥታ ስምምነት የኢትዮጵያ ጦር እስከ ተወሰኑ ኪሎሜትሮች ወደ ሱዳን ድንበር ዘልቆ በመግባት ለጸጥታ ስጋት ይሆናሉ ብሎ የሚያስባቸውን ኢትዮጵያውያንን አፍኖ የመውሰድ ወይም ጥቃት የመሰንዘር ፈቃድ አግኝቷል።
በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽነር አቤት ቢሉም አጥጋቢ መልስ ለማግኘት አልቻሉም።
በጉዳዩ ዙሪያ ሱዳን የሚገኘውን የኢትዮጵያን ኢምባሲ ወኪሎች ለማናገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

tirsdag 27. mai 2014

በሃረር ታስረው ክሚገኙት ነጋዴዎች መካከል የተወሰኑት ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

በቅርቡ በሃረር የደረሰውን የእሳት ቃጠሎ ተከትሎ ንብረታቸው የወደመባቸው  ነጋዴዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሳቸው ከሽብረተኝነት ወደ ባንዲራ ማቃጠል፣ ንብረት ማውደም እና አመጽ ማስነሳት መለወጡ ተነግሯቸዋል።
ከእሰረኞቹ መካከል 2ቱ በመታወቂያ ዋስ እንዲፈቱ ሲደረጉ፣ 20 ዎቹ እስረኞች ደግሞ ባንዲራ አውርዶ በማቃጠል፣ 500 ሰዎችን አስተባብረው አመጽ በማስነሳት፣ የመንግስትን ስራ በማስተጓጎልና የግለሰብና የመንግስት ንብረት በማውደም ክስ ቀርቦባቸዋል። የእያንዳንዱ ክስ የቅጣት ጣራ ከ15 አመታት በላይ የሚያሳስር በመሆኑ እስረኞቹ የዋስ መብት እንደሌላቸውና ጉዳያቸውን በእስር ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ውስኗል።
በዛሬው ፍርድ ቢኒያም ጌታቸው፣ ለይላ አሊ አህመድና ዙቤር አህመድ የተባሉት የክስ ቻርጅ የደረሰቻው ሲሆን ሌሎች 17ቱ ግን የክሱ ዝርዝር አልደረሳቸውም። ለይላ አህመድ የተባለችው ነጋዴ በእስር ቤት ማህጸኗ ላይ ባደረሱባት ድብደባ በህመም እየተሰቃየች እንደምትገኝ መዘገባችን ይታወሳል።
ቢኒያም ጌታቸው የተባለው ወጣት ደግሞ የኮምፒዩተር ጥገና ባለሙያ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም የሃረር ፖሊስ ጽህፈት ቤትን ኮምፒይተሮች በመጠገን፣ ያልተከፈለው 12 ሺ ብር እንዳለና ምናልባትም የእስሩ ምክንያት ከዚሁ ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል። ቢኒያምን በምንም አይነት ወንጀል መጠርጠር እንደማይችል የሚናገሩት ጉዳዩን የሚከታተሉ ምንጮች፣ ፖሊስ ኮሚሽን የራሱን ችግር ለመሸፋፈን ሲል እንዳሰረው አስተያየት ይሰጣሉ።
ድብደባ የተፈጸመባትና ዋስትና የተከለከለችው ለይላ ደግሞ  የመንግስትን ባለስልጣናት “እናንተ ናችሁ ቃጠሎውን ያስነሳችሁት ፣ ሌቦች” ብላ በመሳደቡዋ መታሰሩዋን ምንጮች ገልጸዋል።

የግንቦት 20 በዓል 23ኛዓመትበአዲስአበባስታዲየም ሊያከብር ነው

የደርመንግስየወደቀበት 23ኛ ዓመት የግንቦት 20 በዓልገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በአዲስ አበባ ስታዲየም ለማክበር መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡
ኢህአዴግ የዘንድሮውን የግንቦት20 በአልለየትየሚያደርገውሕዝቡበተፈጠረውልማትሙሉበሙሉተጠቃሚበመሆኑነውብሎአል፡፡
ኢህአዴግመራሹመንግስትህዝቡንበቀንሶስትጊዜእንደሚያበላውቃልየገባለትቢሆንም፣ የህዝቡ ኑሮእጅግአሽቆልቁሎእንደሚገኝ፣  በአንጻሩጥቂትየሥርዓቱሹማምንትበሙስናናብልሹ አሠራርከገቢያቸውበላይሐብትአፍርተውታግለንለታልየሚሉትንሕዝብመልሰውፍዳየሚያሳዩበትአፋኝሥርዓት እየተጠናከረመምጣቱን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን እንደሚናገሩ ዘጋቢያችን ገልጿል።
ስርአቱበተቆጣጠራቸውየሕዝብሚዲያዎችእናየመንግስትንብረቶችያለክልካይሲጠቀምበትየሚታይሲሆንበአንጻሩተቃዋሚዎችሰልፍለማካሄድእንኩዋንያልቻሉበት፣በሕዝብመገናኛብዙሃንከፍለው  ማስታወቂያማስነገርያልቻሉበትየፖለቲካስነምህዳርመፈጠሩአንዱየግንቦት 20 ፍሬመሆኑን  አስተያየትሰጪዎችአስረድተዋል፡፡
ኢህአዴግ ለበአሉ ድምቀት ሲል የአስተዳደሩወረዳዎችናየቀድሞ ቀበሌሠራተኞችናካድሬዎችቤትለቤትበመሄድሕዝቡበነቂስእንዲወጣጥብቅማሳሰቢያ መስጠታቸውን አዲስ አበባዋዘጋያቢችንያነጋገረቻቸውነዋሪዎችአረጋግጠውላታል።
ካድሬዎቹበየቤቱበመሄድበሰልፉላይቢያንስከአንድቤትአንድሰውመገኘትእንዳለበትማሳሰቢያከመስጠትጀምሮየሚገኘውንሰውስምእናስልክቁጥርስጡንእያሉሲመዘግቡታይተዋል፡፡
በተጨማሪምለሰልፉ 50 ብር አበልና ሰርቪስመኪናመዘጋጀቱንበመግለጽነዋሪውንለማግባባትምጥረትእያደረጉመሆናቸውንለማወቅተችሎአል፡፡
ትናንት የአዲስአበባመስተዳደርባስተላለፈውትእዛዝመሰረት ደግሞ   የከተማውሁሉምየመንግስትሰራተኞች  ከሰዓትጀምሮየመንግስትስራዘግተውወደኤግዚቢሽንማዕከልእንዲሄዱ ተደርጓል፡፡
ማንኛውምሰራተኛመስሪያቤትውስጥእንዳይቀርበየኃላፊዎችጥብቅመልእክትየተላለፈለት ሲሆን፣  ከሰዓትጀምሮሰራተኛውየመንግስትስራዘግቶበከተማመስተዳድሩበኩልለከተማአንበሳአውቶቡስበተላለፈውመልእክትመሰረትሰራተኛው ወደ ማእከሉ ተጉዞ  የግንቦትሃያየትግልታሪክፎቶዎችንናዶክመንተሪዎችንእንዲያይተደርጓል።
ከቦታውማንምሰውእንዳይቀርየስም ቁጥጥር ይደረጋል በመባሉ ሰራተኛው ስራ ዘግቶ ተገኝቷል። ኢህአዴግ በአዲስ አበባ እየገጠመው የመጣውን ተቃውሞና ተቃዋሚዎች በቅርቡ ያካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ አስደንግጦታል የምትለው ዘጋቢያችን፣ ምናልባትም ህዝቡን አስገድዶ በማስወጣት አሁንም ድጋፍ እንዳለው ለዲፕሎማቲክ ኮሚኒቲው ለማሳየትና ለመጪው ምርጫ ለመዘጋጀት መሆኑን ገልጻለች።
የግንቦት20 በአል ዛሬ በደብረብርሃን ህዝቡ በሰልፍ ወጥቶ እንዲያከብር የተደረገ ሲሆን፣ ምንም የፖለቲካ እውቀቱ የሌላቸው የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ሳይቀር ተሰልፈው እንዲያከብሩ ተደርጓል። የኢህአዴግ ካድሬዎች ህዝቡን እያስገደዱ ሰልፍ እንዲወጣ ማድረጋቸውን የስፍራው ወኪላችን ገልጿል።
ነገ በአዳማ በሚካሄደው ሰልፍ ላይም ካድሬዎቹ ህዝቡ በስፋት እንዲወጣ እየቀሰቀሱ ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ ግንቦት20ን በተመለከተ የተለያዩ ሰዎች አስተያየቶችን በማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች እያሰፈሩ ነው። ሃብታሙ ዘውዱ ” ግንቦት20 ግልጹ ደርግ በድብቁ ደርግ” የሚል አስተያየት ሲሰጥ፣ አቤ ቶክቾው በበኩሉ ” ኢህአዴግከዚህበፊትደርግበእርሷእናበሌሎችላይሲያደርግየነበረውንአንድበአንድ፤ ዛሬበተቃዋሚዎች፣በጋዜጠኞችእናበነጻሃሳቢዎችላይእየፈጸመችውነው።ልዩነቱደርግአታድርጉብሎቀድሞያስጠነቅቅነበር፤ኢህአዴግደግሞአድርጉብላታሳስትናሲያደርጉጉድታደርጋለች። ዛሬምበእስርቤቶቻችንእነቀሽገበሩአሉዛሬምበየእስርቤቱእነአሞራውታስረዋል።የግንቦትሃያ ”ሰማህታት” የተሰዉትደርግንደምስሶደርግንለመቅዳትከሆነየበሃይሌአባት፤ ”ምንትሸጣለህትንባሆትርፍህምንድነውኡሁኡሁ” ያሉትነገርነውየተከሰተብን!” ብሎአል።
አገኘሁ አሰግድ ደግሞ ” አሁንአሁንስ “እንደጀመርንእንጨርሰዋለን!” ሲሉሕዝቡንእየመሰለኝነው!›› ሲልአቤጉበኛንአስታወሰኝ፤አቤጉበኛብዙጊዜሲጽፍ ‹‹ሰፊውየኢትዮጵያህዝብ›› ማለትያበዛል፤እናምአንዴ ‹‹ሰፊውህዝብ›› ማለትምንማለትነውተብሎሲጠየቅአቤእንዲህብሎመለሰአሉ፤ ‹‹ሰፊውህዝብማለትማብትገድለውብትገድለውየማያልቅማለትነው፡፡›› ብሎአል።
ወይኔ ሃገሬ የተባለው አስተያየት ሰጪ ደግሞ ” ግንቦት20 ኢትዮጵያን ለመበታተን በወያኔ መራሹ መንግስት አማካይነት የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት የተረገመ ቀን ነው” ሲል፣ ነጻነት ይበልጣል ደግሞ ” የአንድ ቀን ስልጣን ቢኖረኝ የግንቦት 20 እለት ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ አድርግ ነበር” ብሎአል።
የገዢው ፓርቲ ደጋፊ የሆነው ሳባዊ ደሳለኝ ደግሞ ” ነገ የቅድስቷ አገሬ የኢትዮጵያ ልደት ቀኗ ነው”  በማለት እለቱን አሞካሽቷል።
ከዚሁ ዜና ሳንወጣ ጠ/ሚ ሃይለማርያም  ደሳለኝ ግንቦት20 የብሄር የመድብና የግለሰብ መብቶችን በማረጋገጥ በኩል አስተማማኝ መሰረት እንዲኖረው አድርጓል ብለዋል።
“የድሮውንቁስልእያነሱመነጠልንየሚቀሰቅሱናየድሮውአስተዳደርበድጋሚስልጣንላይእንዲወጣየሚሹአካላትቢኖሩምየብሄርብሄረሰቦችአንድነትናፍቅርግንአሁንምደምቋል” ማለታቸውን የገዢው ፓርቲ ልሳን ፋና ዘግቧል።
“በመድብለፓርቲስርዓቱየህግየበላይነትንየሚፈታተኑየፖለቲካፓርቲዎችንአካሄድማስተካከልያስፈልጋል” ሲሉ አቶ ሃይለማርያም አክለዋል። የፓርቲዎችን አካሄድ በምን መንገድ እንደሚያካሂዱት የገለጹት ነገር የለም።

mandag 26. mai 2014

የኦሮሚያ ፖሊስ አስራት አብርሃን ሰወረ

የአራት ፓርቲዎች መድረክ የሆነው መድረክ ትናንት በአዲስ አበባ ላደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቀደም ብለው የቅስቀሳ ስራ ሲሰሩ የነበሩ አስራ ሁለት ሰዎች በቡራዩ ከተማ በፖሊስ መታሰራቸውን የሰሙት የአረና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ሐብታይ ገብረ ሩፋኤልና በቅርቡ አንድነት ፓርቲን የተቀላቀለው ደራሲና ፖለቲከኛ አስራት አብርሃ እስረኞቹን ሊጠይቁ በሄዱበት በወረዳው ከታሰሩ በኋላ ፖሊስ አቶ ሐብታይን ሲለቅ አቶ አስራትን በወረዳው አሳድሯቸው ነበር፡፡
Asrat Abraha
Asrat Abraha

ዛሬ ማለዳ አቶ አስራትንና የመድረክ አባላትን ለመጠየቅ ወደ ቡራዩ ያመሩት የአቶ አስራት ባለቤትና የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች አቶ አስራት በፖሊስ ጣብያው አለመታሰራቸው ተነግሯቸዋል፡፡አቶ ሐብታይ በስፍራው በመገኘት ‹‹አስራት ከእኔ ጋር ታስሮ ነበር››ቢሉም የኦሮሚያ ፖሊስ ‹‹የምትሉትን ሰው እኔ አላሰርኩትም›› የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
በቡራዩ ከተማ ሶስት ፖሊስ ጣብያዎች በመኖራቸው አስራትን ፍለጋ ወደ ፖሊስ ጣብያዎቹ ያመሩት የአንድነት አመራሮች ተመሳሳይ ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ተቃጠለ

በደቡብ ክልል የሚገኘው የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የቃጠሎ አደጋ ደርሶበታል። ትላንት ለሊት ላይ በወንዶች ማደሪያ በተነሳው ቃጠሎ ምክንያት የትምህርት ሂደቱ ተስተጓጉሏል።
Welkite university on fire
Welkite university on fire
በእሳት አደጋው የሰው ህይወት ስለመጥፋቱ እስካሁን የደረሰን ዘገባ የለም። በተጨማሪም የ እሳት አደጋው እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ሲደረግ ከነበረው ረብሻ ጋር ተያያዥነት ያለው መሆኑን ለግዜው አላወቅንም። ሆኖም ለሊቱን የጀመረው የ እሳት አደጋ የወልቅጤ ዩኒቨርስቲ እና የአካባቢው ነዋሪ ላይ ስጋት መፍጠሩ አልቀረም። ተጨማሪ መረጃዎችን ካገኘን ይዘንላችሁ እንመለሳለን።

fredag 23. mai 2014

የኢትዮጵያመንግሥትየጋዜጣናመጽሔትአከፋፋዮችንያለንግድፈቃድበመሥራትእናታክስባለመክፈልወንጀልለመክሰስ እየተዘጋጀመሆኑተሰማ፡፡


የጋዜጣናመጽሔትአከፋፋዮችበተለይመንግሥትንየሚደግፉጋዜጣናመጽሔቶችንሆንብለውከገበያያስወጣሉበሚልከቅርብጊዜወዲህየተጠናከረትችትከመንግሥትባለሰልጣናትበመቅረብላይሲሆንበአቶሬድዋንሁሴንየሚመራውየመንግስትኮምኒኬሽንጽ/ቤትእያካሄደያለውንጥናትማጠናቀቁ ታውቋል።
ምንጮችእንደገለጹትየጋዜጣናመጽሔትአከፋፋዮችንበሕገወጥነጋዴነትከመክሰስጎንለጎንእነሱሲሰሩ የነበሩትንሥራበአነስተኛናጥቃቅንነጋዴዎችበማስተላለፍመንግስትበአከፋፋዮችአማካይነትይደርሳልያለውንአፈናለማስቀረትእንደሚቻልጥናቱይጠቁማል፡፡ይህየመንግሥትሃሳብገናከውጥኑተቃውሞእየቀረበበትየሚገኝ ሲሆን፣  በተለይየሕትመትስርጭቱንበተዘዋዋሪመንገድመንግስትለመቆጣጠር  ማሰቡመንግስትየፈለገውንሲያሰራጭ፣ያልፈለገውንእንዲያፍንዕድልይሰጠዋል።
በአሁኑወቅት በገዢው ፓርቲ ልሳን በሆነው ራዲዮፋናከአከፋፋዮችጋርበተያያዘከጋዜጠኞችጋርውይይትእየተካሄደሲሆንበተለይየብሮድካስትባለስልጣንየቦርድአባልየሆኑትአቶዛዲግአብርሃብዙዎቹአከፋፋዮችሕገወጦችመሆናቸውንበመጥቀስመንግስትእርምጃለመውሰድእያጠናመሆኑንበግልጽተናግረዋል፡፡
በዚሁፕሮግራምላይአከፋፋዮቹከውጪገንዘብእየተቀበሉየተወሰኑየፕሬስውጤቶችንያፍናሉየሚሉውንጀላዎችምተደምጠዋል፡፡ ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ ገዢው ፓርቲ አይደግፉኝም የሚላቸውን ጋዜጦች በተለያዩ ወንጀሎች እየከሰሰ ከገበያ ሊያወጣቸው እየሞከረ መሆኑን መዘገባችን ይታወቃል።

torsdag 22. mai 2014

በአዲስ አበባ በህገወጥ መንገድ ተስርተዋል የተባሉ ቤቶችን የማፍረስ ሂደቱ እንደቀጠለ ነው

በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች እንደገለጹት መንግስት በህወገወጥ መንገድ ተስረተዋል ያላቸውን ቤቶች ያለምንም ተተኪ ቦታና ቤት በማፍረሱ በርካታ ቤተሰቦች ሜዳ ላይ እየተበተኑ ነው።
ኮልፌ አካባቢ አንፎ ሜዳ እየተባለ በሚጠራው ሰፈር ከ2 ሺ እስከ 3 ሺ ቤቶች መፍረሳቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚኖሩ ከ570 በላይ ቤቶች ይፈርሳሉ በመባሉ ነዋሪዎች አቤቱታዎችን እያሰሙ ነው። ልማት አልሙ ተብለን ለረጅም ጊዜ ገንዘብ በማዋጣት መንገድ ማሰራታቸውን፣ ውሃ እና መብራት የመሳሰሉትን አገልግሎቶችን ማስገባታቸውን ገልጸዋል። መንግስት አሁን በደንገት ቦታው ይፈለጋል በማለቱ የነዋሪዎች ህይወት አደጋ ላይ መውደቁን የህዝቡ ወኪሎች ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ መስተዳድር ከ15 አመታት ወዲህ የተገነቡ ቤቶችን በማፍረስ ቦታዎቹን ለባለሃብቶች በመሸጥ ላይ ይገኛል።

የአዉሮጳ ሀገራት የሙዚቃ ዉድድር

ባለፉት ሳምንታት ለ 59ኛ ግዜ የተካሄደዉ፤ የአዉሮጳ ሀገሮች የሙዚቃ ዉድድር መድረክ፤ ደማቅ በሆነ የሙዚቃ ዉድድር የኦስትርያዉ ከያኒ 290 ነጥብን በማግኘት፤ እስከ ዛሪ በዉድድሩ ከተመዘገቡ የአሸናፊነት ነጥብ በአብላጫነት፤ የአራተኛ ደረጃን መያዙ ተነግሮለታል።
Eurovision Song Contest 2014
የአዉሮጳ ሀገሮች የሙዚቃ ዉድድር« ኦይሮቪዥን ሶንግ ኮንቴክስት» የሩብ እና የግማሽ ፍፃሜ ማጣርያ ዉድድር፤ ከተደረገ በኃላ ግንቦት ሁለት ቀን ቅዳሜ ምሽት 26 የተለያዩ አዉሮጳ ሀገራት፤ የተወዳደሩበት፤ በዓለም የተለያዩ ሀገሮች በቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት የተከታተሉት ዉድድር እጅግ ደማቅ ነበር። ዘንድሮ ለ 59 ዘጠነኛ ግዜ የተዘጋጀዉን ዉድድር አሸናፊ ኦስትርያ ስትሆን፤ ኦስትርያ በጎርጎረሳዉያኑ 1966 ዓ,ም፤ ከዛሬ 48 ዓመት በፊት፤ በዚሁ በአዉሮጳ ሀገሮች የሙዚቃ ዉድድር መድረክ ፤ለመጀመርያ ግዜ አሸናፊ የነበረች ይታወቃል። በዕለቱ መሰናዶአችን የዘንድሮዉን አዉሮጳ ሀገሮች የሙዚቃ ዉድድር መድረክ እንቃኛለን።
Conchita Wurst gewinnt Eurovision Song Contest 2014
የኦስትርያዉ አሸናፊ
«ኮንቺታ ቮርስት» በሚል የመድረክ ስሙ የሚጠራዉ፤ የ25 ዓመቱ ኦስትርያዊ፤ ቶም ኖይቪርት አሸናፊ ያደረገዉን ሙዚቃዉን ለማቀንቀን መድረክ ላይ የቀረበዉ፤ ረጅም ፀጉሩን በጀርባዉ ላይ ለቆ፤ ሙሉ ፂሙን አሳድጎ እና፤ እስከ እግር ጥፍሩ የሚደርስ ግሩም ረጅም ቀሚስን አጥልቆ ነበር። በርግጥ ባቀረበዉ ሙዚቃ በርካታ ነጥቦችን አግኝቶ፤ የዘንድሮዉ ዉድድር አሸናፊ ቢሆንም፤ ብዙዎች በአለባበሱ እና በመድረክ አቀራረቡ ነቀፊታን ጥለዉበታል። የኦስትርያዉ ከያኒ በርካታ ነቀፌታ ቢጣልበትም፤ በአንፃሩ አንድ ሰዉ የሰዉን መብት እስካልነካ እና ጉዳት እስካላደረሰ ድረስ፤ በዚች ምድር ላይ እንደፈለገዉ መሆን ይችላል፤ ሲሉ በርካታ ምዕራባዉያን ሀገሮች ደግፈዉታል። ከዩኤስ አሜሪካም እንዲሁ አንዳንድ ታዋቂ የሙዚቃ ሰዎች በመድረክ አቀራረቡ አወድሰዉታል። በመድረክ መጠርያ «ኮንችታ ቮርስት» እንደ አለባበስዋ ሁሉ በሴት ነበር የምትጠራዉ፤ የሩስያ ደጋፊዎችና ሩስያ ትዉልድ እንዳይቀጥል፤ በትዉልድ ላይ የሚደረግ ኢ-ሰብዓዊ ስነ-ምግባር ያልያዘ ስትል፤ የኦስትርያዉን ከያኒ ነቅፋለች። እንዲያም ሆኖ በአዉሮጳ የሙዚቃ ዉድድር ላይ በተለይ ከፍተኛ ነጥብ ያገኙትና ሙዚቃቸዉ የተወደደላቸዉ የኔዘርላንድ እና የስዊድን ከያኒዎችን በነጥብ በመብለጥ የሴት ቀሚስ ለብሶ መድረክ የቀረበዉ፤ የኦስትርያ ከያኒ አሸናፊ ሆንዋል። አሸናፊዉ ማን እንደሆነ እንታወቀ እና፤ የመድረኩ አስተናጋጅ እንኳን ደስ አለሽ፤ ኮንቺታ ለዚህ ክስተት፤ አሁን ልትናገር የምትችልበት አንደበት ይኖርሃል ተብሎ ሲጠየቅ፤ «የዛሬዉ ምሽት መታሰብያነቱ ሰላም እና ነፃነት እንዲመጣ ለሚያምኙ ሁሉ ነዉ» ሲል ነበር መልስ የሰጠዉ።
የአዉሮጳ ሀገሮች የሙዚቃ ዉድድር መድረክ አሸናፊ ወደ ሰማንያ ሽህ ይሮ እንደሚያገኝ ሲገለጽ በሌላ በኩል አሸናፊዉ የተለያዩ የአዉሮጻ ሀገሮች የተለያዩ የሙዚቃ ሥራዎችን በማቅረብ በተለያዩ የብዙሃን መገናኛዎች በመቅረብ እና ቃለ መጠይ በማድረግ እንዲሁም ራስን በማስተዋወቅ የሙዚቃ ስራቸዉን በመሸጥ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚያገኙ ተገልጾአል። የኦስትርያዉ ከያኒም በመጀመርያ ወደ ጀርመን በመጋበዝ፤ በተለያዩ የቴሌቭዥን ጣብያዎች በቅረብ ራሱን አስተዋዉቋል፤ በስሙ የምግብ ሸቀጥ ምልክት እስከ መሆን ደርሶአል። «ይሮቪዥን ሶንግ ኮንቴክስት» የተሰኘዉ በየዓመቱ በአንድ አሸናፊ ሀገር የሚካሄደዉ የአዉሮጳዉ ሙዚቃ ዉድድር መድረክ፤ አዉሮጳዉያን የዕርስ በርስ ጦርነትን አቁመዉ ለጋራ መተሳሰር እና መግባባት እንዲሁም በመደጋገፍ የጀመሩት ያጋራ መድረክ እንደሆነ፤ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የአዉሮጳዉ የሙዚቃ ዉድድር መድረክ፤ ሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት በተጠናቀቀ፤ በአስራ ሁለተኛ ዓመቱ፤ እንደ አዉሮጳዉያን አቆጣጠር 1956 ዓ,ም፤ «የአዉሮጳ የራድዮ ስርጭት ማህበር» ለመጀመርያ ግዜ ያቋቋመዉ፤ የሙዚቃ ዉድድር እንደሆነም ተዘግቦአል።
Conchita Wurst gewinnt Eurovision Song Contest 2014
የኦስትርያዉ አሸናፊ
ነገሩ የአዉሮጳዉያን የሙዚቃ ዉድድር መድረክ ተሰኘ እንጂ፤ አዉሮጳ ድንበር ክልል ዉስጥ የማይገኙ፤ የራድዮ ማህበሩ አባል ሀገሮች ሁሉ የሚሳተፉበት ነዉ። የማህበሩ አባላት ደግሞ እስራኤልን፤ የእስያ ሀገሮችን ብሎም የሰሜን አፍሪቃ ሀገራትንም ሁሉ ያጠቃልል። እስከ ዛሪ በዚህ ዉድድር፤ ከአፍሪቃ ሞሮኮ እንደ ጎርጎረሳዊዉ አቆጣጠር በ1980 ዓ.ም፤ በዚህ የሙዚቃ ዉድድር መድረክ ተሳትፋለች። በአዉሮጳዉ የራድዩ ስርጭት ማህበር ዉስጥ፤ አባል የሆኑና፤ በዚህ የሙዚቃ ዉድድር እስከ ዛሪ ያልተሳተፉ ሀገሮች ደግሞ፤ አልጀርያ፤ ቱኒዚያ፤ ሊቢያ፤ ግብጽ፤ ዮርዳኖስ እና ሊባኖን ይገኙበታል። የአዉሮጳ የራድዩ ስርጭት ማኅበር አባላት በአጠቃላይ ሰባ አምስት ሲሆኑ፤ ሃምሳ ስድስቱ አዉሮጳ ዉስጥ የሚገኙ ናቸዉ። ቀሪዎቹ አስራ ዘጠኝ ሀገራት ደግሞ ሰሜን አፍሪቃ እና እስያ ዉስጥ የሚገኙ ሀገሮች እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ዘንድሮ ለ 59ኛ ግዜ የተካሄደዉ የአዉሮጻዉ የሙዚቃ ዉድድር አዘጋጅ የሆነችዉ ዴንማርክ፤ ባለፈዉ የአዉሮጳዉያኑ ዓመት ስዊድን ከተማ ማሌሞ ላይ የተዘጋጀዉ ዉድድር አሸናፊ በመሆንዋ ነበር ፤ ዘንድሮ አዘጋጅ ለመሆን የበቃችዉ።
ያደመጣችኋቸዉ «ቶልማቺቭ ሲስተርስ» የተሰኙት ሁለት አንድ አይነት ልብስና አንድ አይነት ፀጉር ስራ ተሰርተዉ መንትያ መስለዉ የቀረቡት የሩስያ ከያኒዎች ነበሩ ። በዉድድሩ ሩስያ ሰባተኛ ደረጃን አግኝታለች። በዘንድሮዉ የአዉሮጳ የሙዚቃ ዉድድር ላይ የማኅበሩ አባል ሀገራት የሆኑት ሞንቴኔግሮ እና ሳን ማሪኖ የማጣርያ ዉድድርን አልፈዉ ለፍጻሜ ዉድድሩ ለመጀመርያ ግዜ መሳተፋቸዉ ተገልፆአል። ከኔዘርላንድ የመጡት ከያኒዎች በዉድድር መድረኩ ላይ ባቀረቡት ሙዚቃ እጅግ ከፍተኛ አድናቆትና ዉጤትን ቢያመጡም፤ የመጀመርያዉ ደረጃ ላይ ለመድረስ ግን በቂ ነጥብ አላገኙም።
«ይሮቪዥን ሶንግ ኮንቴክስት» በተሰኘዉ በዘንድሮዉ አዉሮጳ ሀገራት የሙዚቃ ዉድድር መድረክ ላይ፤ ሀገራት ለዉድድር ይዘዉ የሚቀርቡት ሙዚቃ፤ ከሶስት ደቂቃ ያልበለጠ መሆን ይኖርበታል። በዘንድሮዉ ዉድድር ኦስትርያ፤ ኔዘርላንድ፤ስዊድን ከአንድኛ እስከ ሶስተኛ ነጥብን ሲያገኙ፤ ጀርመን በዉድድሩ 18 ኛ ደረጃን ነዉ ያገኘችዉ። በዉድድሩ፤ ለግማሽ እና ለሩብ ፍፃሜ አልፈዉ ለደረጃ በዉድድሩ ከቀረቡት ሃያ ስድስት ሀገራት መካከል ፈረንሳይ፤ የመጨረሻዉን ማለትም የሃያ ስድስተኛን ቦታ ነበር ያገኘችዉ ። ኤሊዛ የሚል የቡድን ሥም ያላቸዉ ጀርመንን ወክለዉ የቀረቡት ሶስት ወጣት ሴቶች ምንም እንኳ በዉድድሩ 18 ኛ ነጥብን ይዘዉ ከኮፐን ሃገን ይመለሱ እንጂ፤ በጀርመን ሃገር ሙዚቃቸዉ ተወዳጅነትን አትርፎአል።
Eurovision Song Contest 2014 Russland
የሩስያ ተወዳዳሪዎች
ጀርመን የአዉሮጳዉ የሙዚቃ ዉድድር ማለትም የ «ይሮቪዥን ሶንግ ኮንቴክስት» ከተጀመረበት ከጎርጎረሳዉያኑ 1956 ዓ,ም ጀምሮ፤ በየዓመቱ ለፍጻሜ ዉድድር የቀረበች ሲሆን፤ በነዚህ የዉድድር ዓመታት ዉስጥ፤ 18 ሀገራት በተሳተፉበት በጎርጎረሳዉያኑ 1982 ዓ,ም፤ 161 ነጥብን በማምጣት፤ እንዲሁም በቅርቡ በጎርጎረሳዊዉ 2010 ዓ,ም፤ ኖርዊ ኦስሎ መዲና ላይ በተካሄደዉና፤ 25 ሀገራት ለነጥብ ዉድድር በቀረቡበት፤ የሙዚቃ ድግስ ላይ፤ አንደኛ መዉጣትዋ ይታወሳል።
ይህ ግዙፍ የሙዚቃ የዉድድር መድረክ፤ በቀጥታ የቴሌቭዥን ሥርጭት በበርካታ አዉሮጳ፤ እስያ እንዲሁም ሩቅ ምስራቅ ሀገራት የሚተላለፍ ሲሆን፤ ተወዳዳሬዎቹ ሀገራት ሙዚቃቸዉን ካቀረቡ በኃላ፤ የየሀገራቱ ተወካዮች፤ ከየሀገራቸዉ ዉድድሩ ወደ ተዘጋጀበት ሀገር፤በመደወል ለሶስት ሀገራት ነጥብ ከሰጡ በኃላ ነዉ የዉድድሩ አሸናፊ የሚለየዉ። ስልክ ደዉለዉ ለኛ ጥሩ ያሉትን ሙዚቃ ሲመርጡ ታድያ፤ የምዕራብ አዉሮጳ ሀገራትም ሆነ የምሥራቅ አዉሮጳ ሀገራት፤ ለየጎረቤት ሀገራት፤ አልያም አጋር ላሉት ሀገር ነጥብ የመስጠቱ እና የመጠቃቀሙ ሁኔታ፤ በዝቶ ባይታይም ይስተዋላል። መድረኩ ከመጠቃቀም ባሻገር የፖለቲካ መድረክም እየሆነ መምጣቱን፤ አንዳንድ ታዛቢዎች ይናገራሉ። ባለፈዉ በቀረበዉ ዝግጅት ላይ የሴት ልብስን ለብሶ፤ ፀጉሩን ጀርባዉ ላይ ለቆና ጢሙን አሳድጎ መድረክ ወጥቶ ያቀነቀነዉ ሙዚቀኛ፤ «ግብረሰዶማዊነት ከሰው ልጆች ተፈጥሮ ውጭ» ስትል በጥብቅ ለምትቃወመዉ ሩስያ እና መሰሎችዋ፤ ግብረሰዶም ደጋፊዎች አቋማቸዉን ያሳዩበት መድረክ ነዉ ሲሉ አስተያየታቸዉን የሰጡ ጥቂቶች አይደሉም።
በጎርጎረሳዉያኑ 1956 አ.ም ለመጀመርያ ግዜ በኦስትርያ ሉጋኖ ዉስጥ የተካሄደዉ ይህ የአዉሮጻ የሙዚቃ ዉድድር መድረክ በዓለም ዙርያ ተወዳጅ የሆኑ ሙዚቀኞችን አፍርቶአል። ታዋቂዋ የፖፕ የሙዚቃ ተጫዋች ሴሊን ዲዮን የአዉሮጳዉ የሙዚቃ ዉድድር መድረክ ለሰላሳ ሶስተኛ ግዜ ባቀረበዉ የዉድድር ስዊዘርላንድን ወክላ ዉድድሩ ላይ ባቀረበችዉ የፈረንሳይኛ ሙዚቃ ታዋቂነትን አትርፋ በዓለም የሙዚቃ መድረክ ኮከብ ለመሆን መብቃትዋ ይታወቃል።
Elaiza / ESC / Vorentscheid
የጀርመን ተወዳዳሪዎች
« አባ » በመባል የሚታወቁት የስዊድን የፖፕ ሙዚቃ ባንድ አባላትም፤ በጎርጎረሳዉያኑ አቆጣጠር በ1974 ዓ.ም፤ «ዋተር ሉ» የተሰኘዉን ሙዚቃጨዉን ይዘዉ በዉድድሩ መድረክ ከቀረቡ በኃላ፤ በታዋቂነት ዓለም እንዲገቡና እንዲወደዱ፤ ብሎም 380 ሚሊዮን አልብምን በመሸጥ በፖፕ ሙዚቃ ዓለም በዓለማችን የመጀመርያዎቹ ለመሆን በቅተዋል።
26 ሀገራት የተሳተፉበትን የዘንድሮዉን የአዉሮጳ የሙዚቃ ዉድድር መድረክ በጥቂቱ የቃኘንበት መሰናዶ እስከዚሁ ነበር። በሚቀጥለዉ ዓመት አዘጋጅ የሆነችዉ የዘንድሮ ዉድድር አሸናፊ ሀገር ኦስትርያ ላይ የሚካሄደዉን 60ኛዉን የአዉሮጳ ሀገራት የሙዚቃ ዉድድር ለማየት ያብቃን። ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማድመጫዉን በመጫን ይከታተሉ።

onsdag 21. mai 2014

በቀጣይ ዓመት የሚጠናቀቀው የኢትዮጵያ መንግሥት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በአብዛኛዎቹ ዘርፎች እንደማይሳካ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ጠቆመ፡፡

ከ2003 እስከ 2007 ዓ.ም ሊከናወን የታቀደው የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከፋይናንስ አቅም ፣ከሰለጠነ የሰው ኃይል እና ከመሠረተ ልማት አለመሟላትና ከመሳሰሉ ጉዳዮች  ጋር በተያያዘ ፈተናዎች ገጥመውታል፡፡
በዕቅዱ ዓመታት  11 በመቶና ከዚያ በላይ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ የታሰበ ቢሆንም ባለፉት ሶስት የዕቅዱ ዓመታት የተመዘገበው እድገት 10 በመቶ ብቻ ነው፡፡ ከኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ አንጻር በሚጠበቀው አቅጣጫ እና በጎላ መልኩ ለውጥ ማምጣት አለመቻሉን መረጃው ይጠቅሳል፡፡
በተለይ ባለፉት ሶስት ኣመታት ካጋጠሙ ፈተናዎች መካከል በመጀመሪያዎቹ ሁለት ዓመታት የተከሰተው የዋጋ ንረት፣ የግብርና ዘርፍ ምርታማነት ዕድገት አርኪ አለመሆን፣ ኤክስፖርት የገቢ ድርሻ ማሽቆልቆል ፣ የኢምፖርት ድርሻ በከፍተኛ ደረጃ ማደግ፣ የግብርና ዘርፍ የምርታማነት ዕድገት የተፈለገውን ያህል አለመሆን፣ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከመነሻው መሠረተ ጠባብ መሆን፣ የግል ባለሃብቱ ተሳትፎ ማሽቆልቆል ፣ ከምንም በላይ የማስፈጸም አቅም ማነስ እና በየደረጃው የሙስናና ብልሹ አሰራር ፣የመልካም አስተዳደር ችግሮች መንሰራፋት ይጠቀሳሉ፡፡
የመካከለኛና ትልልቅ ኢንዱስትሪዎች ልማት በውጪ ንግድ የሚመራ፣ የውጪ ምንዛሪ እጥረትን የመቅረፍና ለግብርና ልማት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ከተቀመጡ ኣላማዎች አኳያ ባለፉት ሶስት የዕድገትና የትራንስፎርሜሸን ዕቅድ የትግበራ ዓመታት ክንውን ወደኃላ የቀረ መሆኑን የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መረጃ ይጠቅሳል፡፡
በፕሮጀክቶችም ደረጃ የታላቁ ህዳሴ ግድብ በአሁኑ ወቅት በመንግሥት መረጃ መጠናቀቅ የቻለው 30 በመቶ ያህል ብቻ ሲሆን በባቡር ፤ በስኳር፣ በማዳበሪያ ፋብሪካዎች ግንባታ የተያዙ ዕቅዶች ቀጣዩ የእቅዱ መጨረሻ ኣመት ድረስ የሚሳኩ አይደሉም፡፡
በዚህም ምክንያት ለመጪው ዓመት ምርጫ ድረስ የአዲስአበባ ቀላል ባቡርን ስራ ለማስጀመር ኢህአዴግ መራሹ መንግሥት የቻይና ኩባንያዎችን ጥብቅ መመሪያ የሰጠ ሲሆን ይህ ዓይነቱ የጥድፊያ አካሄድ በግንባታው ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ባለሙያዎች ከወዲሁ አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው፡፡
የአዲስአበባ ቀላል ባቡር ግንባታ በዕድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዱ ውስጥ የሌለና በእነአቶ መለስ ዜናዊ ደንገተኛ ውሳኔ የተጸነሰ ዕቅድ ሲሆን ግንባታው ከፍተኛ ወጪ የወጣባቸውን የመንገድ መሰረተ ልማቶች፣ ሕንጻዎች እያፈራረስ ከመምጣቱም ባሻገር የባቡሩ መስመር ዝርጋታ ለእግረኞችና ለተሸከርካሪዎች ማቋረጫ ግምት ውስጥ ባላስገባ መልኩ እየተከናወነ መሆኑ በባለሙያዎች ጭምር ጠንካራ ትችትን አስከትሎአል፡፡
የመንግሥት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ እጅግ የተለጠጠ እና በፋይናንስና በሰውኃይል አቅም ሊተገበር እንደማይችል በተለይ በአገር ውስጥ በሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቶዎችና በውጪ አገር በሚገኙ ኢትጽያዊያን ባለሙያዎች በሰፊው ሲተች የቆየ ቢሆንም ኢህአዴግ መራሹ መንግሥት ይህ የኒዮሊበራሊስቶች አፍራሽ አስተሳሰብ ነው በሚል ሲያጣጥለው ከመቆየቱም በላይ የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር በፓርላማ ተቃዋሚዎችን በኃላ ዕቅዱ ሲሳካ እንዳታፍሩ እስከማለት መድረሳቸው የሚዘነጋ አይደለም፡፡

የሶማሊ ተማሪዎችን ከኦሮሞ ተማሪዎች ጋር ለማጋጨት ወሬዎች እየተናፈሱ ነው

በኦህዴድ -ህወሃት እንደተቀነባበረ በሚነገርለት አሉባልታ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚገኙ የሶማሊ ክልል ተወላጅ ተማሪዎችን ከኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ጋር ለማጋጨት ያለመ መሆኑን ለኢሳት ደረሰው መረጃ ያመለክታል።
የመንግስት ካድሬዎች ” የሶማሊ ተማሪዎች ከመንግስት ጎን ቆመው በኦሮሞ ተማሪዎች ዙሪያ መረጃ እየሰጡን ነው” የሚል አሉባልታ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች መነዛቱ፣ የሶማሊ ተማሪዎችን ስጋት ላይ የጣላቸው ሲሆን፣ ተማሪዎቹ ከመንግስት ጎን አለመቆማቸውንና እንዲህ አይነት አሉባልታ እየተነዛ ያለው የሁለቱን ብሄር ህዝቦች ለማጋጨት መሆኑን እየተናገሩ ነው።
የተማሪዎች ወላጆች በሚነዛው ወሬ መደናገጣቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።
ጉዳዩን በማስመልከት ጥያቄ ያቀረብንለት የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አማካሪ የነበረውና  የስዊድንን የአንቲገን ሽልማት አሸናፊ የሆነው አብዱላሂ ሁሴን ወሬው እንዲህ አይነቱ አሉባልታ በስፋት የሚሰራጨው የሁለቱን አካባቢዎች ተወላጆችን ለማጋጨት ነው ብሎአል።
ኦህዴድ /ህወሃት የተለያዩ ብሄረሰቦችን ተወላጆች ለማጋጨት እንቅስቃሴ መጀመሩን በተመለከተ ተከታታይ ዘገባዎችን ማቅረባችን ይታወሳል።

በጣሊያን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባለስልጣን መሞታቸው ታወቀ

የአባታቸው ስም ለጊዜው ያልታወቀውና በተጠባባቂ አምባሳደር ማእረግ ደረጃ ሲሰሩ የቆዩት አቶ ፍስሃ ጧት ስራ ከገቡ በሁዋላ መሞታቸው ታውቋል።
ኢሳት ስለ አሟሟታቸው ዝርዝር መረጃ ባያገኝም አንዳንድ ጣሊያን ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ግለሰቡ የሞቱት ከ3ኛ ፎቅ ላይ ራሳቸውን ወርውረው ነው ይላሉ።
ፖሊስ ወደ አካባቢው ደርሶ ምርመራ ካደረገ በሁዋላ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውንና መሞታቸውን ነዋሪዎች አክለው ተናግረዋል።
ስለ አሟሟታቸው መንስኤ እስካሁን ይህ ነው የተባለ መረጃ አልተገኘም።
ባለቤታቸው ወደ ሮም መምጣታቸውን፣ ሮም የሚገኘው ኢትዮጵያ ኢምባሲ ዝግ ሆኖ መዋሉን ኢሳት አረጋግጧል። ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን ለህዝብ እናቀርባለን።

በጣሊያን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባለስልጣን መሞታቸው ታወቀ

የአባታቸው ስም ለጊዜው ያልታወቀውና በተጠባባቂ አምባሳደር ማእረግ ደረጃ ሲሰሩ የቆዩት አቶ ፍስሃ ጧት ስራ ከገቡ በሁዋላ መሞታቸው ታውቋል።
ኢሳት ስለ አሟሟታቸው ዝርዝር መረጃ ባያገኝም አንዳንድ ጣሊያን ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ግለሰቡ የሞቱት ከ3ኛ ፎቅ ላይ ራሳቸውን ወርውረው ነው ይላሉ።
ፖሊስ ወደ አካባቢው ደርሶ ምርመራ ካደረገ በሁዋላ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውንና መሞታቸውን ነዋሪዎች አክለው ተናግረዋል።
ስለ አሟሟታቸው መንስኤ እስካሁን ይህ ነው የተባለ መረጃ አልተገኘም።
ባለቤታቸው ወደ ሮም መምጣታቸውን፣ ሮም የሚገኘው ኢትዮጵያ ኢምባሲ ዝግ ሆኖ መዋሉን ኢሳት አረጋግጧል። ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን ለህዝብ እናቀርባለን።

tirsdag 20. mai 2014

በቡራዩ ከተነሳው ተቃውሞ ጋር አሁንም በርካታ ወጣቶች ታስረው እንደሚገኙ ታወቀ

ከአዲስ አበባ አዲሱ ካርታ ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በቡራዩ ከታሰሩት ከ200 በላይ ወጣቶች መካከል ከ40 በላይ የሚሆኑት አሁንም ታስረው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑን የእስር ቤት ምንጮች ገልጸዋል።
አብዛኞቹ በ25 ሺ ብር ዋስ ወይም በቦታ ካርታ እንዲፈቱ ቢደረግም ገንዘብ መክፈል ያልቻሉትና ከኦነግ ጋር ግንኙነት ያላቸው ተብለው የተጠረጠሩት እንዳይፈቱ ተደርጓል። እስረኞቹ ፍርድ ቤት ሳይቀረቡ በፖሊስ ዋስ ብቻ 25 ሺ ብር እየከፈሉ እንዲወጡ መደረጉ ግልጽ ዘረፋ መሆኑን አንዳንድ ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል።
በእስር ላይ ከሚገኙት 6 ሴቶች መካከል አያንቱ የምትባለዋ ወጣት እጆቿ በድብደባ መሰባበሩንና በከፍተኛ ህመም ላይ እንደምትገኝ ታውቋል።
ጋዲሳ እና ዳውድ ሃሰን የተባሉት እስረኞች በኦነግ አባልነት በመጠርጠራቸው በዋስ እንዳይፈቱ ተደርጓል።
ጆቴ፣ ስራታ እና ስሮንሳ ፋይሳ ደግሞ የአዋሽ ባንክ ሰራተኞች ሲሆኑ እነሱም በእስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ ስቃይ እየተፈጸመባቸው ነው። ጋዲሳ የተባለው የመንግስት ሰራተኛም ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል ይጠቀሳል።
ንጉማ፣ ወጋሪ፣ ኡመድ ኡመርና ዳባ ቱፋ የተባሉትም እንዲሁ ከፍተኛ ድብደባ የተፈጸመባቸው በመሆኑ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።
በክልሉ ውስጥ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ተይዘው የታሰሩ ሲሆን አንዳንዶች በገንዘብ ዋስ ሲለቀቁ በርካቶች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ።
በሌላ ዜና ደግሞ በምስራቅና ምእራብ ወለጋ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች የሌሎችን ብሄር ሰዎች እያሰቃዩ መሆኑን ለኢሳት የሚደርሱት መረጃዎች ያመለክታሉ።
በወረዳና በዞን ደረጃ የሚሰሩ የኦህዴድ ሹሞች የሌሎች አካባቢ ተወላጆችን አቤቱታ እና ችግር ለማየት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ፣ የሌሎች አካባቢ ነዋሪዎች ለከፍተኛ ችግር እየተጋለጡ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ሆን ተብሎ እንደተቀናበረ በሚያሳይ መልኩ የተደራጁ ወጣቶች ማታ ማታ በሌሎች አካባቢ ተወላጆች ቤቶች ላይ ጉዳት ሲያደርጉ ሰንብተዋል።
ኢሳት ያነጋገራቸው ሰዎች እንደሚሉት የኦህዴድ ባለስልጣናት በሚዲያ ቀርበው የሚናገሩትና በተግባር እየፈጸሙ ያሉት ድርጊት የተለያየ ነው።
ህወሃት ብሄሮችን እርስ በርስ በማጋጨት በአገር ውስጥ የገጠመውን አስተዳደራዊ ችግር አቅጣጫ ለማስቀየር እየሞከረ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል።

በአዲስ አበባ ቤቶቻቸው የፈረሱባቸው ሰዎች ብሶታቸውን እየገለጹ ነው

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ እንደ አዲስ ተጠናክሮ በቀጠለው በህገወጥ መንገድ ተሰርተዋል የተባሉትን ቤት የማፍረስ ዘመቻ በርካታ ነዋሪዎችን ሜዳ ላይ እየበተነ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
አለም ባንክ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በርካታ ነዋሪዎች ባልተጠበቁት ሰአት ቤታቸው እንዲፈርስ በመደረጉ ነፍሰጡሮች ሳይቀር ለከፍተኛ ችግር ተደርገው ነበር። የመንግስትን ድርጊት የተቃወሙትም እንዲሁ እየተደበደቡ አንዳንዶች እንዲታሰሩ ተደርጓል።
ዛሬ ማክሰኞ ሰሚት እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በርካታ ቤቶች በመፍረሳቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች መጠለያ አልባ ሆነዋል። የመንግስትን ህገወጥ ድርጊት የተቃወሙት በፖሊሶች መደብደባቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል
የአዲስ አበባ መስተዳድር በገጠመው ከፍተኛ የቦታ እጥረት ህወገወጥ ቤቶች ብሎ የሰየማቸውን ሁሉ በማፍረስ በሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋን ነዋሪዎች ቤት አልባ አድርጓቸዋል።
የቀድሞው የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ኤርምያስ ለገሰ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ከ150 ሺ በላይ በአዲስ አበባ ዙሪያ ይኖሩ የነበሩ አርሶደአሮች መሬታቸውን ተነጥቀው የገቡበት እንደማይታወቅ ገልጸው ነበር።
በምርጫ 97 ኢህአዴግ መሸነፉን ተከትሎ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ባዶ ቦታዎች በአቶ መለስ ዜናዊ ትእዛዝ ተመዝግበው ከህወሃት ጋር ግንኙነት ላላቸው የአንድ አካባቢ ሰዎች እንዲሰጥ መደረጉን አቶ ኤርምያስ አክለው ገልጸዋል።
በሌላ ዜና ደግሞ የአዲስ አበባ መስተዳድር በ40 በ60 እና በ20 በ80 የኮንዶሚኒየም ቤት መርሃ ግብሩ ከ800 ሺ በላይ ነዋሪዎችን ቢመዘግብም እስካሁን ድረስ ያሰራው ከ1 ሺ 300 አለመብለጡ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ ቀድሞ ከተገመተውም በላይ በርካታ አመታትን እንደሚወስድ ታውቋል።
በእየአመቱ 50 ሺ ቤቶች ቢሰሩ እስካሁን የተመዘገቡትን የቤት ባለቤት ለማድረግ ከ16 አመታት በላይ እንደሚወሰድ መረጃዎችን ዋቢ አድርጎ ኢሳት ሲዘግብ ቢቆይም፣ አሁን በሚታየው አሰራር ዜጎች የቤት ባለቤት ለመሆን በርካታ አመታትን ለመጠበቅ ይገደዳሉ።
መስተዳድሩን ከገጠሙት ችግሮች መካከል አንዱ የመሬት አቅርቦት እጥረት ሲሆን፣ የኦሮምያ ልዩ ዞኖችን ከህዝብ ፈቃድ ውጭ በጉልበት ወደ አዲስ አበባ ማስገባት ካልተቻለ የኮንዶሚኒየሙ ፕሮጀክት ተግባራዊ እንደማይሆን ምንጮች ይናገራሉ።

mandag 19. mai 2014

በግብርናው ዘርፍ የግል ባለሀብቱ ተሳትፎ መዳከሙን አንድ ሪፖርት አመለከተ

መንግሥትለግብርናኢንቨስትመንትካዘጋጀውሰፋፊመሬቶችውስጥየግልባለሃብቱሊጠቀምበትየቻለው 11 በመቶያህሉንብቻበመሆኑየዘርፉእንቅስቃሴእጅግየተዳከመአፈጻጸምማሳየቱንከግብርናሚኒስቴርየተገኘሪፖርት ጠቁሟል።
ሪፖርቱእንደሚያሳየውየግብርናኢንቨስትመንትንለማበረታታትበመንግሥትእየተሰራ
ያለውሰፋፊየእርሻመሬቶችንበፌዴራልየግብርናኢንቨስትመንትመሬትባንክበኩልየመለየት፣ለባለሀብቶችየማስተላለፍናእንዲለሙየማድረግተግባርነው፡፡
በዚህዙሪያእስከ 2005 በጀትዓመትበድምሩ 3 ነጥብ 31 ሚሊዮንሔክታርመሬትከክልሎችወደመሬትባንክእንዲገባተደርጓል፡፡
ከዚህምውስጥእስከ 2005 በጀትዓመት ድረስ 473 ሺህሔክታርመሬትወደባለሃብቶችየተላለፈሲሆን፤ከዚህምውስጥመልማትየቻለው 11 በመቶብቻ ነው፡፡
ይህመረጃበቀጣይአቅሙናዝግጁነቱያላቸውንልማታዊባለሃብቶችበጥንቃቄመመልመልእንደሚያስፈልግአመልካችመሆኑንሪፖርቱጠቅሶዋል፡፡
በተጨማሪምእስካሁንመሬትየወሰዱባለሃብቶችበፍጥነትወደልማት መግባታቸውንናበገቡትውለታመሠረትእየተንቀሳቀሱመሆናቸውንለማረጋገጥጥብቅክትትልማድረግእንደሚገባም ሪፖርቱይጠቅሳል፡፡
በመሬትወረራከፍተኛክስከሚቀርብባቸውኩባንያዎችአንዱየሆነውናበኢትዮጵያመንግሥትልማታዊባለሃብትነቱበሰፊውሲመሰከርለትየቆየውየህንዱካራቱሪኩባንያበጋምቤላክልል 300ሺሄክታርመሬትተረክቦማልማትየቻለው 800 ሄክታርብቻሲሆንከኢትዮጵያንግድባንክምወደ 62 ሚሊየንብርወስዶባለመመለሱንብረቱተይዞበሐራጅበመሸጥሒደትላይመሆኑይታወቃል፡፡
ኩባንያውለግብርናኢንቨስትመንትበተፈቀደውማበረታቻከቀረጥነጻ ያስገባቸውንማሽነሪዎችበማከራየትናበመሸጥባልተፈቀደለትየንግድስራውስጥገብቶመገኘቱምየሚታወቅነው፡፡
በተመሳሳይሁኔታበሼህአልአሙዲእናበሳዑዲመንግሥትየሚካሄደውየሳዑዲስታርየግብርናፕሮጀክትምበታሰበውመልኩእየተካሄደአለመሆኑምለመንግሥትትል

ኦነግ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከኦሮሞ ተማሪዎች ጎን እንዲሰለፉ ጥሪ አቀረበ

በጄ/ል ከማል ገልቹ የሚመራው የኦሮሞ ነጻ አውጭ ድርጅት በላከው መግለጫ የኦሮሞ ተማሪዎች ጥያቄ  የኦሮሞ ገበሬዎችን የአለአግባብ መፈናቀላቸውን በመቃወም የተደረገ በመሆኑ መላው ህዝብ ከጎናቸው ቆሞ ሊደግፋቸው ይገባል ብሎአል።
ገዢው ፓርቲ አንዱን ብሄር ከሌላው ጋር እያጋጨ በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያደርገው ጥረት ዞሮ ዞሮ አገሪቱን የሚጎዳ በመሆኑ፣ ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን ትተው በጋራ እንዲታገሉ ጥሪ አቅርቧል።
ገዢው ሃይል ታሪካዊውን የዋልድባን  ገዳም ለስኳር ልማት በሚል ማፍረሱ  በኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርስ ላይ የተካሄደ ዘመቻ መሆኑን እንዲሁም በጋምቤላ ህዝቡን በማፈናቀል መሬቱን ለውጭ ባለሃብቶች የመቸብቸቡ ሂደት አደገኛ እና  ሊወገዝ እንደሚገባው ገልጿል። የኦሮሞ አርሶአደሮችን በማፈናቀል የሚወሰደው መሬትም በተመሳሳይ መልኩ ለባለሃብቶች ለመቸብቸብ የታቀደ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ሊቃወሙት ይገባል ብሎአል።
በአዲሱ የአዲስ አበባ መሪ ካርታ የተነሳ የሚፈናቀሉት ገበሬዎችን ለመታደግ የተጀመረው ተቃውሞ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የገለጸው ድርጅቱ፣ ኢትዮጵያውያን በብሄር፣ አካባቢ ወይም ሃይማኖት ሳይከፋፈሉ በጋራ ሊነሱ ይገባል ብሎአል።
በሌላ ዜና ደግሞ  በአምቦና በሌሎችም ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን የግድያ እርምጃ በማውገዝ ከትናንት በስትያ በጀርመን ሙኒክ የተቃውሞ ሰልፍ ተደርጓል።

lørdag 17. mai 2014

ከዞን-9 ታሣሪዎች ስድስቱ ፍርድ ቤት ቀረቡ

ፖሊስ በሽብር አድራጎት እጠረጥራቸዋለሁ ብሏል፤ ፍርድ ቤት የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
የዞን-9 ብሎገሮች በእጅ ብረት ታስረው ወደ ችሎት ሲወሰዱ
የዞን-9 ብሎገሮች በእጅ ብረት ታስረው ወደ ችሎት ሲወሰዱ

  
የታሠሩት ብሎገሮችና ጋዜጠኞች /የፎቶ ምንጭ - ኢንተርኔት/የታሠሩት ብሎገሮችና ጋዜጠኞች /የፎቶ ምንጭ - ኢንተርኔት/

ላለፉት 23 ቀናት ክሥ ሳይመሠረትባቸው ታስረው ከሚገኙት ዘጠኝ የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት ሚድያ ፀሐፊዎች የሆኑ ጋዜጠኞችና አምደኞች ስድስቱ ዛሬ፤ ቅዳሜ፣ ግንቦት 9/2006 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡


የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ስምንተኛ ወንጀል ችሎት የጋዜጠኞቹንና የአምደኞቹን ጉዳይ ያየው በዝግ ሲሆን የቀረቡት ጋዜጠኞቹ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፣ ተስፋዓለም ወልደየስ እና ኤዶም ካሣዬ እንዲሁም ሌሎች ሦስት አምደኞች መሆናቸው ታውቋል፡፡
 
የዞን-9 ጋዜጠኞችና ብሎገሮች አራዳ ፍርድ ቤት ቀረቡየዞን-9 ጋዜጠኞችና ብሎገሮች አራዳ ፍርድ ቤት ቀረቡ
ዛሬ ችሎት ያልቀረቡት አምደኞች መቼ እንደሚቀርቡ ለጊዜው በትክክል ባይታወቅም ሰሞኑን ይቀርባሉ የሚል ጭምጭምታ ተሰምቷል፡፡

የስምንት ታሣሪ ጋዜጠኞችና አምደኞች ተከላካይ ጠበቃ አቶ አምሃ መኮንን  እንደገለፁት ፖሊስ ጋዜጠኞቹንና አምደኞቹን በሽብር አድራጎት እንደሚጠረጥራቸው ለችሎቱ አስታውቆ ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ “ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት” ያለውን ከፍተኛ ጊዜ የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል፡፡
 
አራዳ ፍርድ ቤትአራዳ ፍርድ ቤት
ፍርድ ቤቱም የፖሊስን ጥያቄ ተቀብሎ የ28 ቀናቱን የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱንና ጉዳዩንም ለፊታችን ሰኔ 7/2006 ዓ.ም መቅጠሩን ተከላካይ ጠበቃው አቶ አምሃ መኮንን ገልፀዋል፡፡

fredag 16. mai 2014

ትኩረት በህወሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድ ላይ ይሁን!!!


ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ መንታ መንገድ ላይ ትገኛለች። በአንድ በኩል ህወሓት እና አገልጋይ ድርጅቶቹ በተለይም ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድ የተነሳባቸው ሕዝባዊ ተቃዉሞ ለመሸፈን የሕዝብ ለሕዝብ ጠብ ለመጫር የተቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ ነው። በየተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ዘርን መሠረት ያደረጉ ስድቦች፣ ዘለፋዎችና ጥቃቶች እንዲኖሩ በካድሬዎቻቸውና በቅጥረኞች አማካይነት እየጣሩ ነው። በዚህ እኩይ ተግባር ውስጥ ባለማወቅ በስሜት ብቻ የሚነዱ የወያኔ ደጋፊ ያልሆኑ ወገኖችም እየተሳተፉበት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በዘውግም ይሁን በአገር ደረጃ የተደራጁ የፓለቲካ ድርጅቶች መሪዎች የጋራ ጠላቶቻችን ወያኔና ግብረአበሮቹ ስለመሆናቸው የጠራ አቋም እየያዙ ነው። ወያኔና ግብረአበሮቹን ለማስወገድ በጋራ መታገል የሚያስፈልግ መሆኑ እና ከወያኔ አገዛዝ በኋላ በእኩልነት ላይ የተመሠረተ አገር የመገንባት የጋራ ኃላፊነት ያለብን መሆኑ ሰፊ ግንዛቤ እያገኘ መጥቷል።
ይህ መንታ መንገድ በሁሉም ቦታ በባሰ ኦሮሚያ ውስጥ ጎልቶ እየታየ ነው። በኦሮሚያ አካባቢዎች የሚደርሰው ጥቃትና መፈናቀል ያስቆጫቸው ወጣቶች የሚያደርጉት ፍትሃዊ ተቃውሞ ቀጥሏል። በአምቦ፣ በነቀምት፣ በጊምቢ፣ በሀረር፣ እና ሌሎችም አካባቢዎች በተለይም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሥርዓቱን በመቃወማቸው ከፍተኛ ጥቃት እየደረሰባቸው ነው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ታስረዋል። በእነዚህ ቦታዎች ሁሉ የእንተባበር ጥሪዎች ጎልተው እየተሰሙ ነው። በኦሮሚያ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የሌሎች አካባቢዎች ተማሪዎች ከጎናቸው እንዲቆሙ የኦሮሞ ተማሪዎች ተደጋጋሚ ጥሪዎችን አቅርበዋል። የሌሎች አካባቢዎች ተማሪዎችም ከኦሮሞ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጎን ቆመዋል። ይህ ተስፋ የሚሰጥ እና መበረታታት ያለበት ነገር ነው። ሆኖም ግን ከዚሁ ጎን ለጎን ህወሓትና ኦህዴድ የሕዝቡን ጥያቄ ወደ ዘር ግጭት ለማዞር እየሠሩ ነው። በተማሪዎች መፈክሮች ውስጥ ዘርን ለይተው የሚያንቋንሽሹ መልዕክቶች ሰርገው እንዲገቡ እየተደረገ ነው። ኦሮሞ ባልሆኑ በተለይም በአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት እየደረሰ ነው። የወያኔ ጆሮ ጠቢዎችና ካድሬዎች በስሜት የተገፋፉ ወጣቶችን ወደ ዘር ግጭት እየመሯቸው ነው።ይህ እጅግ አሳሳቢና በአስቸኳይ መቆም የሚኖርበት ነገር ነው።
ከመንታ መንገዶቹ ለአገርና ለወገን እንዲሁም ለወደፊቱ ትውልድ ደህንነት የሚበጀውን የመረዳዳት፣ የመደጋገፍ እና የመተባበርን መንገድ መርጠን እርምጃችንን ካላፋጠንን አሁን የደረስንበት ደረጃ እጅግ አስጊ ነው። ማሰብ፣ ማስተዋል እና ጠላትን መለየት በሚያፈልግበት ወሳኝ ወቅት ላይ ነው የምንገኘው። ድሃ አማራ ለድሃ ኦሮሞ ወገኑ ብቻ ሳይሆን የትግል አጋሩ ነው። ኦህዴድ ውስጥ ያሉ የወያኔ አገልጋዮች ደግሞ ኦሮሞች ስለሆኑ የድሃ ኦሮሞ ወዳጆች አይደሉም። እነሱ የወያኔ ተቀጥላዎች ናቸው። የትውልድ መንደራቸውን ሳይቀር አዘርፈው የሚዘርፉ ስግብግቦች ናቸው።
የኦሮሞ ሕዝብ ትግል በወያኔ እና ተቀጥላዎቹ ድርጅቶች እንጂ በአማራና በኦሮሞ ወይም በኦሮሞና በትግሬ ሕዝብ መካከል አይደለም። የአማራ ሕዝብ ትግል በወያኔ እና ተቀጥላዎቹ ድርጅቶች እንጂ ከማንኛውም አካባቢ ሕዝብ ጋር አይደለም። ወደ እርስ በርስ ቅራኔ ሊዘፍቁን የሚፍጨረጨሩትን ህወሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድን ከሕዝብ መነጠል መቻል አለብን። እዚህ እኩይ ኃይሎች ሥልጣን ላይ እስካሉ ድረስ ፍትህና ሰላም ማግኘት አንችልም። እዚህ እኩይ ኃይሎች እርስ በርሳችን ሊያጫርሱን እየሠሩ መሆኑን አውቀን ኃይላችንን በማስተባበር እንመክታቸው።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በማናቸውም የኢትዮጵያ ግዛት የሚደርስን የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በፍጹም ቁርጠኝነት በጋራ እንታገል፤ በስሜት ከተሞሉና ለእርስ በርስ ግጭቶች ከሚዳርጉ ነገሮች እንቆጠብ፤ አርቆ አስተዋይነትና ታጋሽነት በተላበሰ መንገድ የጋራ ጠላቶቻችን በሆኑትን በህወሓት እና አጫፋሪዎቹ ኦህዴድ፣ ብአዴን እና ደህዴድ ላይ በጋራ እንነሳ ሲል ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪ ያደርጋል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

የክርስትናና እሥልምና መቻቻል በኢትዮጵያ

የጀርመን ፍሪድሪኽ ኤበርት ድርጅት (እሽቲፊቱንግ) ፣ አዲስ አበባ ውስጥ ትናንት በሒልተን ሆቴል ባዘጋጀው ስብሰባ፤ የክርስትናና እሥልምና የዘመናት የመቻቻል ታሪክ ትኩረት እንደተደረገበት ተገለጠ። ድርጅቱ ፤ ከፓሪስ ዩንቨርስቲ ፣ በአፍሪቃ ቀንድና
በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ የተመራመሩትን ፤ የታሪክና የሥነ ሕዝብ ምሁር ፤ ፕሮፌሰር ኤልዌይ ኢፍኬን በመጋበዝ ጠቃሚ ንግግር እንዲደመጥ አብቅቷል። በስብሰባው የተገኙ ተሳታፊ ምሁራንም ምሁራዊ ማብራሪያ አጠተዋል። 

ኢህአዴግ መሬት በመስጠት የምርጫ ቅስቀሳውን ጀመረ

ኢህአዴግ የ2007 ዓም የምርጫ ቅስቀሳውን ለአማራ ክልል የከተማ ነዋሪዎች መሬት በማከፋፈል አንድ ብሎ መጀመሩን ለማወቅ ተችሎአል።
የከተማ ነዋሪዎች 20 ሺ ብር ባንክ አስገብተውና በማህበር ተደረጅተው 1 መቶ 80 ካሬ ሜትር የቤት መስሪያ ቦታ  እንደሚሰጣቸው ከተነገራቸው በሁዋላ ቀበሌዎች ይህንኑ ለማስፈጸም ምዝገባ ሲያከናውኑ ሰንብተዋል።
ገንዘቡ ያላቸውና በአብዛኛው የገዢው ፓርቲ አባላት የሆኑ ሰዎች ገንዘብ ለማስያዝ የማይችሉ ነዋሪዎችን  ገንዘብ እየሰጡና እያደራጁ ሲሆን፣ ሰዎቹ ቦታውን ከተቀበሉ በሁዋላ እስከ 40 ሺ ብር ከፍለው  መሬቱን መልሰው ለመውሰድ እየሰሩ መሆኑን   የክልሉ ዘጋቢያችን ገልጻለች።
በንግድ ስራ ላይ መሰማራት የሚፈልጉ ወጣቶችም እንዲሁ 40 ሺ ብር አስይዘው የገበያ ማእከላትን እንደሚገነቡ የተገለጸላቸው ሲሆን፣ ገንዘቡ ያላቸው ወጣቶች ተደራጅተው ሲመዘገቡ፣ ገንዘቡ የሌላቸው ደግሞ ገንዘቡ ባላቸው ሰዎች ድጋፍ ተደራጅተው ቦታውን ከተረከቡ በሁዋላ የተወሰነ ክፍያ ተከፍሎአቸው ቦታውን ገንዘቡ ላላቸው ሰዎች መልሰው ለማስረከብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው።
ኢሳት ከአንድ ወር በፊት ይፋ ባደረገው ዘገባ ለአርሶአደሩየማዳበሪያእዳእፎይታበ2006/2007 የመኸርምርትዘመንእንደሚሰጥ፣ለከተማነዋሪዎችደግሞ  በ20 ሺብርቅድመክፍያለመኖሪያቤትግንባታየሚውሉቦታዎችንእንደሚታደሉዋቸው ገልጾ ነበር።
ኢህአዴግ ባዘጋጀው የ 2007 የምርጫ የማሸነፊያስትራቴጂዎችላይ  ”  አርሶ አደሩንና አመራሩን የመዳበሪያ እዳ እፎይታ በ2006/2007 የመኽርምርት ዘመን እንዳ ለመንገር ፤ ተቃዋሚችን ማንኳሰስ ፣ በኢህአዴግ ላይሊነሱ የሚያስቡትን እስከ ማግለል እንዲደርስ ማሰረዳት ፣ ምርጫውን በ1 ለ 5 እንዴት ድምፅ እንደሚሰጡ ማስረዳት እና በሙከራ ማሳየት፣ያለውን የፍትህ እና የልማት ችግር ወደፊት እንደሚፈታ በተስፋ መሙላት” የሚሉትይገኙበታል።
አስተማማኝ የሆነ ድጋፍ በማይገኙባቸው በአማራእናየኦሮምያክልሎች ደግሞ   “አመራሩ  ኢህአዴግ ከወደቀ እስር ቤት እንደሚገባ ፤ የሚመጣው መንግስት አሁን በስልጣን ላይ ያሉትን የአመራር አካላት ቤተሰብ ምጭምር ህይወት የሚያመሳቅል መሆኑን በማስረዳት ፣’ ኢህአዴግ ወይም ሞት’ ብሎ በመነሳት ሊያሰፈፅም ይገባዋል ” የሚል ቃል በሰነዱ ላይ መስፈሩን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል።

torsdag 15. mai 2014

የጸረሙስናኮምሽን 204 ሚሊየንብርግምትያለውመሬትበግለሰቦች እጅ መያዙን አስታወቀ፡፡

የኮምሽኑ የአስርወራትሪፖርትእንደሚያስረዳውየሐሰተኛየመሬትባለይዞታነት ሰነድበማዘጋጀትናሕጋዊቅድመሁኔታላላሟሉሰዎችየመንግስትመሬትአለአግባብበመስጠትበሶስትምርመራዎች በ12 ተጠርጣሪዎችላይምርመራአካሂዶለአቃቤሕግውሳኔአቅርቦአል፡፡
በዚህየምርመራስራበተሰበሰበውመረጃ መሰረትግምቱ  ብር 203 ሚሊየን 549 ሺ144 የሆነ 155 ሺ 208 ካሬሜትርየመንግስትመሬትበግለሰቦች አለአግባብመያዙንጠቁሟል፡፡
ሆኖምይህመሬትበየትኛውክልልወይምቦታእንደሚገኝሪፖርቱአልጠቆመም፡፡ በተጨማሪምበእያንዳንዱጉዳይከብር 45 ሺእስከ 350 ሺድረስጉቦበመስጠትናበመቀበልበሃሰተኛየፍርድቤትትዕዛዝፍርደኞችንበለቀቁየፌዴራልማረሚያቤቶችመካከለኛአመራሮችእናይህንኑሐሰተኛየፍርድቤትውሳኔበገንዘብበማሰራትከማረሚያቤትአለአግባብበወጡታራሚዎችናተባባሪዎቻቸውላይምርመራተጣርቶክስእንደተመሰረተባቸውምሪፖርቱያስታውሳል፡፡
በሙሰኞችየተመዘበረንሐብትለማስመለስይቻልዘንድባለፉትአስርወራት 72 ሺ 673 ካሬሜትርመሬት፣152ተሸከርካሪዎች፣137 መኖሪያቤቶች፣3 ህንጻዎች፣ 1 ፋብሪካ፣ 320 ሚሊየንብርበጥሬገንዘብ፣ 19 ነጥብ 3ሚሊየንየሚያወጣአክስዮን፣ 18 ሚሊየንብርየሚያወጣቦንድ፣ 5 የንግድመደብሮች፣ 12 የነዳጅመጫኛቦቴዎችበፍ/ቤትትዕዛዝእንዲታገዱመደረጉንሪፖርቱጠቁሟል።
ኮሚሽኑየሚወርሳቸውንንብረቶችከማስተዳደርአቅምማነስጋርበተያያዘበተለይተሸከርካሪዎችበየቦታውበስብሰውናሳርበቅሎባቸውየሚገኙመሆኑይታወቃል፡

በወለጋ ዩኒቨርስቲ ፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ተማሪዎች መገደላቸው ተሰማ

የፌደራል ፖሊስ በተማሪዎቹ ላይ በወሰደው ሃይል የተቀላቀለበት እርምጃ 3 ተማሪዎች መገደላቸውን  የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።
በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ተጎድተው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውንና የፌደራል ፖሊሶች ተማሪዎቹ የመጀመሪያ እርዳታ እንዳያገኙ መከልከላቸውን ተከትሎ በሃኪሞችና በፖሊስ አዛዦች መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ እንደበር ምንጮች አክለው ገልጸዋል። የሆስፒታሉ ሰራተኞች በአቋማቸው በመጽናታቸው ተማሪዎች ህክምና ለማግኘት መቻላቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች መታሰራቸውን እንዲሁም በዛሬው እለት ፖሊሶች ግቢ ውስጥ የቀሩ አንዳንድ ተማሪዎች ከግቢ እንዳይወጡ ከልክለው ከፍተኛ ጥበቃ ሲያደርጉ ውለዋል። በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ የፌደራል ፖሊስ እየወሰደ ያለው የሃይል እርምጃ የአካባቢውን ማህበረሰብ እያስቆጣና ምናልባትም ለተቃውሞ ወደ አደባባይ እንዲወጣ ሊያደርገው ይችላል በማለት አስተያየታቸውን ተናግረዋል።
መንግስት እስካሁን ድረስ በግጭቱ ዙሪያ የሰጠው መግለጫ የለም፣ የአካባቢውን መስተዳድርና የዩኒቨርስቲውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራም አልተሳካም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን ጭካኔ የተሞላበት እርምጃና ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት በመቃወም በለንደን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተቃውመውታል።

onsdag 14. mai 2014

አዲስ አበባ በአንበጣ መንጋ መወረሩዋን ነዋሪዎች ገለጹ

እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው የአንበጣ መንጋ አዲስ አበባን መውረሩን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ኮተቤ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች አካባቢያቸው በአምበጣ መንጋ እንደተወረረ ገልጸዋል።
በቅርቡም እንዲሁ በምስራቅ የአገሪቱ ክፍል ተመሳሳይ የአምበጣ መንጋ ወረርሽኝ ታይቶ ነበር።
የአንበጣ መንጋው ከየት አካባቢ እንደመጣ ለማወቅ አልተቻለም።
በአዲስ አበባ የአምበጣ ወረርሽኝ የተለመደ ነገር አለመሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የጅቡቲ መንግስት 30 ስደተኞችን ለኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች አሳልፎ ሰጠ

የአገሪቱ መንግስት ከኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ጋር በመተባበር ያሰራቸውን ስደተኞች ከፍተኛ ስቃይ ወደ ሚፈጸምበት ጅጅጋ እስር ቤት መውሰዱን የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር አስታውቋል።
ግንባሩ እንዳለው እርምጃው የተወሰደው የኦጋዴን ተወላጅ የዳያስፖራ አባላት በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የደረሰውን ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ካወገዙ በሁዋላ ነው።
ጅቡቲ በኦጋዴን አካባቢ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደምትደግፍ ግንባሩ አስታውቆ፣ ጅቡቲ የኦጋዴን ስደተኞችን ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፎ ሲሰጥ የአሁኑ ለ6ኛ ጊዜ ነው።
የአለማቀፉ ማህበረሰብ የጅቡቲን ድረጊት እንዲያወግዝ ግንባሩ አክሎ ጠይቋል።

የወለጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በፖሊሶች ተደበደቡ

መንግስት በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ጓደኞቻቸው እንዲፈቱላቸው በሰላማዊ መንገድ ጥያቄያቸውን ሲያቀርቡ የነበሩ የወለጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ወደ ግቢው ዘልቀው በገቡ የፌደራል ፖሊስ አባላት ሲደበደቡ መዋላቸውን ተማሪዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች  ለኢሳት ተናግረዋል።
የግቢው ተማሪዎች ጥያቄያቸውን  ሰላማዊ በሆነ መንገድ በማቅረብ ላይ ሳሉ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ውስጥ ሰብረው በመግባትና የጪስ ቦንብ በመወርወር ተማሪውን በሰደፍና በዱላ መደብደባቸውን ተማሪዎች ገልጸዋል።
ተማሪው እንደሚለው በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ቆስለው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ታፍሰው ደዴሳ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ወደሚገኝ እስር ቤት መጋዛቸውን ገልጿል።
በወለጋ የሁሉም አካባቢ ተማሪዎች በአንድነት ድምጻቸውን ሲያሰሙ መዋላቸውን አክሎ ገልጿል
በሌላ ዜና ደግሞ ከአዳማ ዩኒቨርስቲ 5 ተማሪዎች ተይዘው መታሰራቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
የደህንነት ሃይሎች ወደ ግቢ በመግባት ከ20 በላይ ተማሪዎችን ይዘው የወሰዱ ቢሆንም፣ 5 ተማሪዎችን አስቀርተው ሌሎችን መልቀቃቸው ታውቋል። ከ20 በላይ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መታሰራቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
በሌላ ዜና ደግሞ በጊምቢ እና በምእራብ ወለጋ የሚኖሩ ከሌሎች አካባቢ የመጡ ሰዎች መረጋጋት መጀመራቸውን ለኢሳት ገልጸዋል
የኢህአዴግ መንግስት ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ በኦሮምያ ክልል የተነሳውን ተቃውሞ የትኩረት አቅጣጫ ለማስለወጥ የተለያዩ አሉባልታዎችን የሚነዙ ካድሬዎችን ማሰማራቱን ኢሳት በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።

tirsdag 13. mai 2014

በአዲስ አበባ ካርታ ዙሪያ የተቃወሙ ሃሳብ ያቀረቡ የኦህዴድ አባላት እየታደኑ ነው

ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የህወሃት አጀንዳ ነው በማለት ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩትን የኦህዴድ አባላት ለማሰር እንቅስቃሴ መጀመሩን  ከኦህዴድ ምንጮች የደረሱን ዜና አመለከተ።
ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉት እነዚህ አባላት እንደተናገሩት፣ ድርጅቱ አዲሱን የአዲስ አበባ ፕላን በተመለከተ አባላቱ እንዲወያዩበት ቢያስደርግም፣ በውይይቱ ወቅት የተቃውሞ ሃሳባቸውን ሲያሰሙ የነበሩትን ሰዎች ማሰር ተጀምሯል። በርኴታ የድርጅቱአባሎች ደግሞ  ከእስራት ለመሸሽ  መደበቃቸው ታውቋል።
ኦህዴድ የህወሃት ደጋፊና የህወሃት ተቃዋሚ በሚል ከሁለት መከፈሉን ተከትሎ የህወሃት ደጋፊው ወገን ደጋፊ ያልሆነውን ወገን እያሳደደው መሆኑን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሚደረገው ጥረት ፣ የህወሃት ደጋፊ በሆኑ የኦህዴድ አባላት ተጠናክሮ ቀጥሎአል።
ኢህአዴግ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የተነሳበትን ተቃውሞ የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት የሌለውን የብሄር አጀንዳ በማንሳት ብሄሮች እርስ በርስ እንዲጣሉ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን አባሎቹ ተናግረዋል።
በዩኒቨርስቲዎች ሆን ተብሎ አሉባልታ የሚነዙ ካድሬዎች መሰማራታቸውን እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች በቡድን የተደራጁ ስራ አጥ ወጣቶችንበሌሊት ወደ ሌሎች ብሄር ተወላጆች ቤት በመላክ ግጭት እንዲያነሱ በኳድሬዉች ግፊት እየተደረገመሆኑን እነዚህ ወገኖች አክለው ገልጸዋል።
በምስራቅ እና በምእራብ ወለጋ ኦህዴድ ያደራጃቸው ወጣቶች የሰዎችን ቤቶች እየመረጡ በሌሊት  ከመደብደብ ጀምሮ እስከ ማቃጠል መድረሳቸውን እንዲሁም ንብረቶችን እየዘረፉ እንደሚገኙ የሚናገሩት አባሎቹ፣ ህዝቡ በትእግስትና በተለመደው የመከባበር ባህሉ ይህን ችግር እንዲያልፈው አሳስበዋል።
በሌላ ዜና ደግሞ በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ ከመቶ በላይ ተማሪዎች ሲለቀቁ፣ 40 ተማሪዎች ግን አመጹን ከቅስቅሳችሁዋል በሚል በእስር ላይ እንዲቆዩና ምርምራ እንዲደረግባቸው ፖሊስ መወሰኑ ታውቋል።
በተመሳሳይ ዜና ከሃሮማያ ዩኒቨርስቲ የወጡትን ተማሪዎች አስጠግተው የነበሩ ቤተክርስቲያኖች፣ ተማሪዎቹን እንዲያስወጡ _ክልሉን በሚመራው የምስራቅ እዝ  ወታደራዊ አዛዦች ትእዛዝ ተሰጥቷቸው እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ማንነታቸውን ያልገለጹ የምስራቅ እዝ ባለስልጣናት ቤተከርስቲያኑዋ በአስቸኳይ ተማሪዎችን እንድታስወጣ ትእዛዝ ከሰጡ በሁዋላ ተማሪዎቹንሸራ በለበሱ መኪኖች ተጭነው መውሰዳቸውን ጉዳዩን በቅርበት ከሚከታተሉ ወገኖች የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ሰኞ እለት ትምህርት ቢጀመርም በግቢው የሚገኙ ተማሪዎች ቁጥር አሁንም እጅግ አነስተኛ ነው።
በኦሮምያ ክልል ያለውን የጸጥታ ችግር በተመለከተ የክልሉን ፖሊስ ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።

መንግስት 22 ነጋዴዎችን በሽብረተኝነት ወንጀል ከሰሰ

ከወራት በፊት በሃረር የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ፣ የንግድ ድርጅታቸው የተቃጠለባቸው 22 ነጋዴዎች ሁከት በማስነሳት የተከፈተባቸው ክስ ወደ ወደ ሽብርተኝነት በመለወጡ፣ ዋስትና ተከልክለው በሃረሪ እስር ቤት እንዲቆዩ መደረጉን የኢሳት ዘጋቢ ገልጿል።
የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነጋዴዎች በዋስ እንዲለቀቁ ውሳኔ  አሳልፎ የነበረ ቢሆንም፣ ፖሊስና አቃቢ ህግ ክሱን ወደ አሸባሪነት በመለወጣቸው  ነጋዴዎቹ ከእስር ቤት እንዳይወጡ ተደርጓል። ከእስረኞቹ መካከል 2ቱ ሴቶች ሲሆኑ አንደኛዋ በድበደባ ወቅት ማህጸኗ አካባቢ በመረገጡዋ በከፍተኛ ህመም እየተሰቃየች መሆኑን ዘጋቢያችን ገልጿል።
ዘጋቢያችን እንደገለጸው በእስር ላይ የሚገኙት ነጋዴዎች ድርጅታቸው ተቃጥሎባቸው ለኪሰራ መዳረጋቸው ሳያንስ አሁን ደግሞ በሽብረተኝነት ተከሰው የወስትና መብት መከልከላቸው በክልሉ ውስጥ የተንሰራፋውን ስርአት አልበኝነት ያሳያል በማለት አስተያየት ሰጪዎች ጠቅሶ ዘግቧል።
“ሀረር ከተማ ተረስታለች” የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች፣ አስተዳዳሪዎቹ በነዋሪዎች መካከል ግልጽ የሆነ አድልዎ የሚያደርጉ በመሆኑ የከተማዋ ችግር እየተባባሰ መምጣቱ” ገልጸዋል።

mandag 12. mai 2014

በጊምቢ ከተማ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች የዘር ፍጅት ሊነሳ እንደሚችል አስጠነቀቁ

በኦሮምያ ክልል በምእራብ ወለጋ በጊምቢ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የአማራ ተወላጆች፣ ከአካባቢው እንዲወጡ በሚፈልጉ ወጣቶች ቤታቸው እየተደበደበ መሆኑንና ህይወታቸውም አደጋ ላይ መውደቁን ተናግረዋል።
አንድ ከወሎ አካባቢ የመጡ የመንግስት ሰራተኛ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ባለቤታቸውን አግብተው ለዘመናት ከኖሩ በሁዋላ፣ ሰሞኑን ወደ መጣህበት ሂድ ተብለው በባለቤታቸው ልመና ከሞት እንደተረፉና የቤታቸው ጣሪያም ወንፊት እንደሆነባቸው እያለቀሱ ተናግረዋል።
ባለቤታቸውም በከተማዋ ውስጥ ያንዣበበውን አደጋ በተመለከተ በኦሮምኛ ቋንቋ ስሜታቸውን ገልጸዋል።
ህወሃት ከኦህዴድ ጋር በመሆን የአማራንና የኦሮሞን ብሄሮች ለማጋጨት እቅድ መንደፉን እና ህዝቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኢሳት ሲያሳስብ ቆይቷል።
ህወሃትና ኦህዴድ ያሰማሩዋቸው ካድሬዎች ” ኦሮሞው” ባህርዳር ላይ ተሰደበ በሚል ከአዲስ አበባ የመሬት መስፋፋት ጋር በተያያዘ የተነሳውን ጥያቄ የብሄር አጀንዳ ለመስጠት እየሞከሩ ነው።
በጄ/ል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ፣ በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱት የኦሮሞ ፌደራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የኦሮሞ ወጣቶች ትኩረታቸውን በህወሃት አገዛዝ ላይ ብቻ እንዲያደርጉ ማሳሰባቸው ይታወቃል።