fredag 30. oktober 2015

የስልጤ ዞን ወጣቶች የመንግስት ኃይሎችን እየተጋፈጡ ነው * የተጎዱ ተማሪዎች አሉ

ከጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ
ፎቶ ከሳንኩራ ወረዳ በአልም ገበያ ከተማ የተደረገ ተቃዉሞ ነው

ህወሃት መራሹ መንግስት በስልጤ ዞን ተማሪዎችን ከትምርት ቤት፤ የመንግስት ሰራተኞችን ከስራ ገበታ ለማፈናቀል የጀመረዉ ግልጽ ዘመቻ ትኩረት የተሰጠዉ በሚዲያ ብቻ ነዉ። እነዚህ የነገን የብሩህ ተስፋ እሸት የጨበጡ ወጣቶች የራሳችንን አሳተሳሰብና አመለካከት በምንሻዉ መልኩ እንተገብራለን በማለት አንባገነናዊዉን ስርዓት ፊት ለፊት እየተጋፈጡት እየደሙ እየቆሰሉ ነዉ። አቅጣጫ የሚያሳይ፣ አይዞአቹ የሚል ወገንንም ይሻሉ። አንዳንድ ወንድሞችን ለማናገር ሞክሬ ነበር። ጉዳዩ አገራዊ ስለሆነ እንደ ስልጤ ጉዳይ ብቻ መታየት የለበትም በተናጠል የምናደርገዉ ነገር የለም ሲሉ ገልጸዉልኛል። አፋር ሲበደል፥ አፋር ያገር ያለህ ጩኸቴን ስሙኝ ብሎ ኢትዮጵያዊዉን በሙሉ ቢያሰልፍ፤ ሱማሌ፣አማራ፣ኦሮሞ ወዘተ በደልና ጭቆና ሲደርስበት የራሱን የመጀመሪያ የድረሱልኝ ጥሪ እያሰማ ወደ አገራዊ ጉዳይ የመቀየሩ ሒደት ያለና የነበረ ነዉ። ስለዚህ ባገርም ይሁን ባህር ማዶ ያለዉ የስልጤ ማህበረሰብ አቅሙ በሚፈቅደዉና ማድረግ በሚችለዉ መጠን አስቸኳይ ስብሰባዎችን በማድረግ፣መግለጫዎችን በማዉጣት፣ ሰላማዊ ሰልፎችን በማድረግ ከቅበት እስከ ሁልባረግ፤ ከሁልባረግ እስከ ዳሎቻና ጦራ ያለዉን ወገን የመታደግ ሐላፊነት አለበት። ዝምታዉ በቅቶ የተቀናጀ ስራ የሚሰራበት ወሳኝ ወቅት ላይ ነን። ልብ ያለዉ ልብ ይበል። ጅግ ባሎቲ ይከታን! ፎቶ ከሳንኩራ ወረዳ በአልም ገበያ ከተማ የተደረገ ተቃዉሞ ነው። ተማሪዎች እንደተጎዱ መረጃ ደርሶናል። -

onsdag 28. oktober 2015

የመኢአድ ሕጋዊው ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ የአሜሪካ ቪዛ ተከለከሉ

ህብር ሬዲዮ ( ላስ ቬጋስ) የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) ሕጋዊው ፕሬዝዳንትና በአገዛዩ ምርጫ ቦርድ ህገ ወጥ ውሳኔ ከቢሮ የተባረሩትና በቅርቡ ከእስር በነጻ የተፈቱት አቶ ማሙሸት አማረ በውጭ ከሚገኙ የፓርቲው ደጋፊዎች ጋር ለመነጋገር ወደ አሜሪካ አቅደውት የነበረው ጉዞ በዛሬው ዕለት ቪዛ በመከልከላቸው ሳይሳካ መቅረቱን ለህብር ሬዲዮ የፓርቲው ምንጮች የላኩልን መረጃ ያስረዳል።

 አቶ ማሙሰት አማራ ግብኖት 5 ቀን 2008 ከመንገድ ላይ በአገዛዙ ደህነቶች ታፍነው ከአራት ወራት በላኢ በተሌኤዩ እስር ቤቶች ሲንገላቱ የቆዩ ሲሆን በፓርቲው ውስጥ ከፕሮፌሰር አስራት ሊቀመንበርነት ጊዜ ጀምሮ ሲያገለግሉ የቆዩና በምርቻ 97 ከቅንጅት መሪዎች ጋር የታሰሩትን ጨምሮ በመረጡት ሰላማዊ ትግል ሳቢአያ ለስምንት ጊዜአት ታስረዋል። አገዛዙ መቶ በመቶ አሸነፍኩ ካለበት ምርቻ ዋዜማ መኢአድና አንድነት ያካሄዱትን ሕጋዊ ጉባዔ በምርቻ ቦርዱ አማካይነት ድጋሚ እንዲደረግ ሲያስገድድ ከመላው አገሪቱ የተሰባሰቡ የመኢአድ የጠቅላላ ጉባዔን በቀናት ልዩነት በድጋሚ ጠሩ ሲሆን ለሁለተኛ ጊዜ ፓርቲውን
Mamushet_Amare_us_embassy_02
በፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ መመረጣቸው ይታወሳል። የአገዛዙ ምርጫ ቦርድ የፓርቲውን ጉባዔ ውሳኔ በመሻር ቢሮውን በፖሊስ ቁጥጥር ስር በማድረግ አቶ ማሙሸትና ዛሬ በእስር ቤት የሚገኙትን የፓርቲውን የውጭ ግንኙነት ሀላፊና ሌሎች አመራሮችንና ውሳኔውን ያልተቀበሉትን አባላት አባሮ በምትካቸው ስልታኔን ለቅቄአለሁ ያሉትን ቀድሞ የፓርቲው ፕሬዝዳንት አቶ አበባው

መሐሪን ከቤታቸው በማምታት ቦርዱ ስልታን ላይ በማስቀመጥ ግለሰቡ ከማን ጋር ሲሰሩ እንደቆዩ ችምር ያጋለጠ ውሳኔ ነው ሲሉ የፓርቲው ሰዎች መግለጻቸው አይዘነጋም። አቶ ማሙሰት ቦርዱን ለፈጸመው ሕገ ወጥ ውሳኔ በፍርድ ቤት ክስ የመሰረቱት ቢሆንም ክሱ ዳር ሳይደርስ ግንቦት 5 ቀን 2008 ከቤታቸው አቅራቢያ በአገዛዙ ደህነቶች ታፍነው መጀመሪያ ቦሌ ምድብ ፖሊስ ጣቢያ

መታሰራቸው እና በሊቢያ በኤይሲስ የተቀሉና የተገደሉ ኢትዮጵአውያን ሐዘናቸውን በገለጹበት ወቅት ተገኝተህ አመጽ ቀስቅሰሀል የሚል ክስ ቀርቦባቸው የደህነት አባላት ቀርበው በሀሰት ከመሰከሩ ድርጊቱን መስቀል አደባባይ ተገኝተው ፈጽመዋል በተባሉበት ሚአዚያ 14 ቀን 2008 በቦታው እንዳልነበሩ፣ በዕለቱ ምርቻ ቦርድን ከሰው ልደታ ፍርድ ቤት ክርክር ላይ እንደነበሩ ከፍርድ ቤት

ማረጋገጫ አቅርበው፣በዕለቱ አብረዋቸው ፍርድ ቤት የነበሩ ጓዶቻቸውን አስመስክረው ፍርድ ቤቶ ክሱ ተቋርጦ በነጻ ይለቀቁ ቢላቸውም ሳይፈቱ ከእስር ቤት ወደ እስር ቤት መዛወራቸውን መዘገባችን ይታወሳል። አቶ ማሙሸት አማረ ከእስር ከተፈቱ በሁዋላ ለህብር ሬዲዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ ከዚህ በሁዋላ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ብታደርግ እንገድልሃለን መባላቸውንና የደህነቶች ክትትል

ከወቱም በሁዋላ እንዳልተቋረጠ ነገር ግን እስኪገሉኝ ሰላማዊ ትግሉን እቀጥላለሁ ማለታቸው ይታወሳል። አቶ ማሙሸት አማረ የመኢአድ ሕጋዊው አመራር እና ብዙሃኑ አባላት በምርቻ ቦርድ ሕገ ወጥ ውሳኔ ቢራችን ቢነጠቅም ተመልሰን ትግሉን እንቀጥላለን ሲሉ ከዚህ ቀደም በሰጡት ቃለ ምልልስ የገለጹ ሲሆን የሰሞኑ የአሜሪካ ጉዞዋቸው ከፓርቲው ደጋፊዎች ጋር ለመነጋገር የታቀደ ሲሆን በኤምባሲው ቪዛ ክልከላ ሳቢያ ጉዟቸው ተስተጓጉሏል።

tirsdag 27. oktober 2015

በጎንደር ከተማ 6 የፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ተፈፀመ፡፡

ባለፈው አርብ ዕለት ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጎንደር ከተማ ፖሊስ አባላት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋይ የሆነውን አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክሩ አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በታጠቀው ኮልት ሽጉጥ ተኩስ ከፍቶ 6 ፖሊሶችን መትቶ መሬት ላይ አጋድሟቸዋል፡፡


ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ ከጎንደር ከተማ እምብርት ፒያሳ ጀምሮ እጁን ሊይዙ የተከታተሉትን ፖሊሶች ቀበሌ 6 ቂርቆስ አካባቢ እስኪደርስ “አትቅረቡኝ! ብትመለሱ ይሻላችኋል…” እያለ የለመናቸው ሲሆን ነገር ግን ፖሊሶቹ ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ባለመቻላቸው ቆራጥ እና የማያዳግም እርምጃ ወስዷል፡፡

ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በያዘው ኮልት ሽጉጥ አንዲት ጥይት ብቻ እስክትቀረው እጁን ሊይዙ ከተከታተሉት ፖሊሶች ስድስቱን እያለመ ከረፈረፋቸው በኋላ በመጨረሻዋ ጥይት ራሱን ገድሏል፡፡

እጁን ለጠላት አሳልፎ ላለመስጠት እሳት ጨልጦ የአርበኛ ሞት በሞተው ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ የኮልት ጥይት ሰለባ ከሆኑት 6 የፖሊስ አባላት ሦስቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ ቀሪዎቹ ሦስቱ ደግሞ በጠና ቆስለው በሞትና በህይወት መካከል ሆነው ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ቆስለው በህክምና ላይ የሚገኙት ፖሊሶች የደረሰባቸው ጉዳት እጅግ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ከሞት ሊተርፉ እደማይችሉ እየተገለፀ ነው፡፡

 ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመን በህይወት ለመያዝ ሳይሳካላቸው የቀሩት የጎንደር ከተማ ጥቂት የህወሓት ተላላኪ ፖሊሶችና ደህንነቶች እንዲሁም የመስተዳደሩ አገልጋይ ባለስልጣናት አስከሬኑን በቁጥጥር ስር በማዋል “አንሰጥም” ብለው የነበረ ሲሆን በመጨረሻም በአካባቢው ህዝብ ግፊት የጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ አስከሬን ለቤተሰቡ ተሰጥቶ ስርዓተ ቀብሩ ተፈፅሟል፡፡

በተመሳሳይም ሳጅን ወለላው ዋናይሁን የተባለው የመተማ ወረዳ ፖሊስ የአመራር አባል እንደዚሁ አንድ በወወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክር ከነተከታዮቹ ተገድሏል፡፡
Source: (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)

fredag 16. oktober 2015

ለ539 ቀናት የተንገላቱት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የቀረበባቸው ክስ ምንም ደጋፊ ማስረጃ ስላሌለው ነጻ ወጥተዋል

የዛሬውን ችሎት አስመልክቶ ከዞን፱ ጦማር የተሰጠ ማስታወሻ

ዛሬ ጥቅምት 5 2007 በዋለው ችሎት አንድ አመት ከ5 ወር እስር ቤት የቆዪት አራት የዞን9 ጦማርያን ላይ ውሳኔ አስተላልፏል።
በውሳኔው መሰረት አንደኛ ተከሳሽ ሶልያና ሽመልስ መከላከል ሳያስፈልጋት ከክሱ ነፃ
ሶስተኛ ተከሳሽ ናትናኤል ፈለቀ መከላከል ሳያስፈልገው ከክሱ ነፃ
አምስተኛ ተከሳሽ አጥናፍ ብርሃኔ መከላከል ሳያስፈልገው ከክሱ ነፃ
ስድስተኛ ተከሳሽ አቤል ዋበላ መከላከል ሳያስፈልገው ከክስ ነፃ የተባሉ ሲሆን
ሁለተኛ ተከሳሽ ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ ከሽብር ክስ ነፃ የተባለ ሲሆን መአከላዊ ምርመራ በሃይል እና በማሰቃየት የሰጠው ቃል ላይ አመፅ እንዳነሳሳ አምኗል በሚል በወንጀል ህጉ 257 መሰረት እንዲከላከል ግን ዋስትና መጠየቅ እንደሚችል ተገልፇል።
የጦማርያኑ ጠበቃ በፍቃዱ ይግባይ እንዲሰጠው የጠየቁ ሲሆን አቃቤ ህግ ተቃውሞ አሰምቶ ይግባኙ ላይ ለጥቅምት 10 ለማየት ቀጠሮ ሰጥቷል።
ባለፉት 1 አመት ከ5 ወራት በማንኛውም በቻላችሁት አቅም ሁሉ ከጎናችን ለቆማችሁ ከፍተኛ ምስጋና እያቀረብን በፍቃዱ ይፈታ የሚለው ጥያቄያችን እንደሚቀጥል ለማሳወቅ እንወዳለን።
የዞን 9 ጦማርያን ከማረሚያ ቤት ሲወጡም የምናሳውቅ ይሆናል።
እልፍ ምስጋና ለዞን9 ነዋርያንና ወዳጆች
ስለሚያገባን እንጦምራለን 



torsdag 15. oktober 2015

የኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ሰቆቃ ዛሬም ከወደ ደ/አፍሪካ ይጣራል – “ይህ አስር ቤት ለእኔ በምድር ላይ ያለ ሴኦል ሆኖ ነው የሚታየኝ” የ 15 አመቱ ኢትዮጵያዊ እስረኛ

ከታምሩ ገዳ በተለያዩ ምክንያቶች ህይወታቸውን ለመለወጥ/ለማሻሻል በማለት ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት ሲሉ በጎረቤት ማላዊ በኩል ለማቋረጥ የሞከሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች በፖሊስ ተይዘው የተፈረደባቸወን የገንዘብ እና የእስራት ቅጣት ቢጨርሱም በአሳቃቂው የማላዊ እሰር ቤት ወስጥ ፈዳቸውን እያዩ እንደሚገኙ የፈረንሳዩ የዜና ወኪል (አጃንስ ፈራንስ ፕሬስ ) እሮብ ጥቅምት 14 2015 አኤአ አ ዘግቧል።
ethiopia 2


Ethiopia “ለተሻለ ኑሮ ወደ ደ/አፍሪካ ለመሻገር የቋመጡት ኢትዮጵዊያን ሰደተኞች ምኞታቸው ቅዠት ሆነ። “ ያለው ዜና ዘገባው ከመዲናይቱ ሎላንግዊ 85 ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኘው እና ለ 800 እስረኞች ተብሎ በተገነባው የዲደዛ እስር ቤት ውስጥ ወደ 2,650 የሚጠጉ እስረኞች ከእነዚህ መካከል 317 በላይ ኢትዮጵያዊያኖች ያለ በቂ ምግብ እና ውሃ አቅርቦት እየተሰቃዩ ይገኛሉ ብሏል።የ15 አመቱ ኢያሱ ታዲዮስ ባለፈው ሃምሌ ወር ከ 29 ጓደኞቹ ጋር ማላዊ ውስጥ ታሰረው በፍርድ ቤት የተጣለባቸውን የገንዘብ አና የእሰራት ቅጣት ቢፈጽሙም “ወደ አገራቸው የሚያጓጉዛቸ ተቋም በመታጣቱ ለተጨማሪ ሰቆቃ ተጋልጠዋል ተብሏል።እያሱ ሰለደረሰበት ሰቆቃ ሲናገር “ይህ እሰር ቤት ለእኔ በምድር ላይ ያለ ሲኦል ሆኖ ነው የሚታየኝ። ቀድሞ የነበረኝ ሕልም እና ተሰፋ ሁሉ እዚህ ላይ ተገቷል ። ከ 5 ጓደኞቼ ጋር የተጣለብን 62 ዶላር ቅጣትን ብንከፍልም እና እስራቱን ብንጨርስም እስከ አሁን ድረስ አልተፈታንም ። አሁን የምፈልገው ነገር ቢኖር ወደ አገሬ መመለስ ብቻ ነው ።” በማለት ሰውነቱ በደካም እና በረሃብ የጠወለገው ታዳጊው ወጣት ኢያሱ በማላዊው እስርቤት ውስጥ የደረሰበትን ሰቆቃ እና መጥፎ ገጠመኝ በመግለጽ “የድረሱልን” ጥሪውን አቅርቧል። ባለፈው መሰከረም ወር በአሜሪካው የሰደተ ተመላሾች ደረጅት አማካኝነት 70 ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች ነፍሳችውን ብቻ አትርፈው ወደ አገራቸው በበጎ ፍቃደተኝነት የተመለሱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በእሰራት ላይ ያሉተን 317 ወገኖቻችንን ወደ ኢትዮጵያ ለማጓጓዝ በትንሹ የ አሜሪካ 200,000 ዶላር እንደሚያሰፈልግ ተገምቷል።የአለም አቀፉ ከሰደት ተመላሾች ድርጀት ተሰፋ የጠፋባቸው ኢትዮጵያዊያኑ ሰደተኞችን ወደ አገራቸው ለማጓጓዝ የበኩሉን ጥረት ቢያደረግም የአለማቀፉ ማህበረሰብ ወቅታዊ ትኩረቱ ወደ መካከለኛው ምስራቅ (የሶሪያ ሰደተኞች) ላይ በመሆኑ አትዮጵያዊያኑ ሰደተኞች አሰተዋሽ አጥተዋል ተብሏል ። የደርጅቱ ዋና ሹም የሆኑት ሚስስ ካትሪን ሳኒ በበኩላቸው “እነዚህ ማስኪን ነፍሳት ከአገራቸው /ከኢትዮጵያ / እርቀው እንደዚህ አይነቱ አሰከፊ ሁኔታ ውስጥ መውደቃቸው በእጅጉ ያሳዝናል” በማለት በኢትዮጵያዊያኑ ሰደተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ችግርን በሃዘኔታ ለማስረዳት ሞክረዋል። በዚህ አጋጣሚ አገሪቱ በኢኮኖሚዋ “አድጋለች፣ ተመንደጋለች፣ ሰላም እና መረጋጋት ዙሪያ ገባዋን ሰፈኖባታል” ከተባለ ለምን ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ፖለቲከኞች ያልሆኑ ነገር ግን የወደፊቱ አገር ተረካቢ የሆኑ ሕጻናት እና ወጣቶች አስከፊውን የባህር እና የየብስ ጉዞ በማድረግ ለእንደዚህ አይነቱ እጅግ ዘግናኝ እና አሳቃቂ ችግር ይጋለጣሉ? ብለው -

onsdag 14. oktober 2015

ወገን እማማ ኢትዮጵያ ተርባለች … የድረሱልኝ ጥሪዋንም እያሰማች ነው?!

የ1966ቱ እና የ77ቱ ዓይነት የረሃብ እልቂት ከመድረሱ በፊት ለወገኖቻችን እንድረስላቸው! ከፍል- ፪   በዲ/ን ኒቆዲሞስ -

በአገራችን በኢትዮጵያ የተከሰተውን የረሃብ አደጋ አስመልክቶ ከሰሞኑን በመጀመሪያ ክፍል ያስነበብበኳችሁን ጽሑፍ ባወጣሁ ማግሥት አንዲት በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነች ወዳጄ የRFI ድረ-ገጽ ‹‹Sever Drought Threatens Millions of Ethiopia›› በሚል ርዕስ በአገራችን ስለተከሰተው ረሃብ የሚያትት ጽሑፍ በሾሻል ሚዲያ ላከችልኝ፡፡ ይህ የrfi ድረ ገጽ ያስነበበው ጽሑፍ እንደሚያትተው የኤሊኒኖ ክስተት በምሥራቅ አፍሪካና በኤዥያ በሚገኙ አገራት ባስከተለው የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት አገራችን በድርቁ በከፍተኛ ኹኔታ ተጠቂ መሆኗን ዘግቦአል፡፡

 ይህ ዘገባም አገራችን ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ1984-85 በርካታዎች ከቀዬአቸው በተፈናቀሉበትና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ካለቁበት የረሃብ ክስተት ጀምሮ አገሪቱ በምግብ እህል ራስን የመቻል ጥያቄ ውስጥ የወደቀች አገር መሆኗን በመግለጽ፤ የዘንድሮ በዝናም እጥረት ምክንያት የተከሰተው የድርቅም ከምሥራቅ አፋር ክልል እስከ ደቡብ ሶማሊያ ያለውን ሰፊ ቦታ እንደሚሸፍንና ረሃቡ በእነዚህ ቦታዎች ላይም ከፍተኛ የሆነ ማኅበራዊና ሰብአዊ ቀውስ እያደረሰ እንዳለ ይገልጻል፡፡

ይኸው rfi.fr ድረ ገጽ የተባበሩት መንግሥታት ባስነበበው ጽሑፉ ከጥቂት ወራት በፊት ያወጣውን ፬.፭ ሚሊዮን ተረጂዎች ቁጥር በአሁን ሰዓት ድርቁ ወደ ሌሎች የአገሪቱ ክልሎች በመስፋፋቱ የተነሣ ወደ ፰ ሚሊዮን እንዳሻቀበና ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊጨምር እንደሚችል ጠቁሟል፡፡ ይህን በአገራችን የተከሰተውን የረሃብ አደጋ

hanger

በተመለከተ በአፋርና በሶማሌ ክልሎች ባደረጓቸው ሰፊ ምርምሮችና ጥናቶች የሚታወቁት የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ክርስቶፈር ክላፕሃም ለRFI በሰጡት ጠቅለል ያለ አስተያየት፡- ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት ላለፉት ዐሥር ዓመታት ድርቅን ይህን ተከትሎም ሊከሰት የሚችለውን ረሃብን ለመከላከልና ዜጎቼ በምግብ እህል ራሳቸውን የሚችሉበትን የተሳካ ውጤታማ የሆነ ሥራን ሠርቼያለሁ በሚልበት በዚህ ወቅት እንዲህ ዓይነቱ የረሃብ አደጋ መከሰቱ ነገሩን እንቆቅልሽ ያደርገዋል ሲሉ ነው፡፡ አስተያየታቸውን የሰጡት፡፡ The Ethiopian government having established what is generally considered to be quite an efficient system for controlling the effects of drought and malnutrition is probably embarrassed and surprised that such a serious issue has risen, Christopher Clapham, a Professor specialized in the region at Cambridge University, told to rfi. አሳዛኙ እውነታ ደግሞ ይህ የረሃብ አደጋ በቀጣይ ዓመታትም ተባብሶ የሚቀጥል መሆኑን ነው ጥናቶች የሚጠቁሙት፡፡

ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት የኢትዮጵያ መንግሥት 33 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ መድቦ ድርቁ የከፋ አደጋ ባደረሰባቸው የአገሪቱ ክልሎች አፋጣኝ የሆነ የምግብ እህል እርዳታ እያደረገ መሆኑን ቢናገርም የተባበሩት መንግሥታት ከሰሞኑን ባወጣው ዘገባ ግን ለረሃብ የተጋለጡ ወገኖቻችንን ቁጥር መሻቀቡንና እነዚህን ወገኖቻችንንም ለመታደግ ከ237 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ጠቅሶአል፡፡ መንግሥት ዘግይቶም ቢሆን በአገሪቱ የተከሰተውን ድርቅ አስመልክቶ ለጋሽ አገራትና ዓለም አቀፍ እርዳታ ድርጅቶች እጁን እንዲዘረጉለት የተማጸነ ቢሆንም ድርቁ በአገሪቱ የጋረጠውን የከፋ የረሃብ አደጋና እልቂት በተመለከተ ግን ሰፋ ያለና የተብራራ መረጃ በመስጠት በኩል ጉልህ ችግር እንዳለበት የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና መገናኛ ብዙኃን በሰፊው እየተናገሩና እየወቀሱ ነው፡፡

 በአገራችን በተለያዩ ጊዜያት የተከሰቱትን የረሃብ አደጋዎች ከወዲሁ አስቀድሞ በመግለጽ፣ ቅድመ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ረገድና በረሃብ የሚያልቁ ወገኖቻችንን ለመታደግና አደጋውን ለመቀነስ መወሰድ ስላለበት አፋጣኝ ዕርምጃዎችን በተመለከተ ትልቅ ችግር እንዳለ ግልጽ ነው፡፡ የኢሕአዴግ መንግሥት ፈጣን ልማትና ዕድገት እያስመዘገብን ነው፣ ሚሊዬነር የሆኑ አርሶ አደሮችንና አርብቶ አደሮችን እያፈራን ነው፣ ረሃብ ካሁን ወዲያ ታሪክ ይሆናል እያለ ባለበት ወቅት እንዲህ ዓይነቱ አንገትን የሚያስደፋ የረሃብ አደጋ መከሰቱ ራሱን በደንብ መፈተሽ እንዳለበት ትልቅ መሳያ ይመስለኛል፡፡ ይኸው የረሃብ አደጋ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ብቻ ሣይሆን በከተሞችም እየተስፋፋ ያለ መሆኑን መስማት፣ ማወቅ ደግሞ እጅጉን የሚያሰቅቅ ነው፡፡

 የፌዴራሉ መንግሥት መቀመጫና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በሚገኙባትና የአፍሪካ ርእሰ መዲና በምትባለው በአዲስ አበባ ሣይቀር ባሉ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ሕፃናት በረሃብ የተነሣ በትምህርት ገበታቸው ላይ እያሉ ተዘልልፍለፈው እወደቁ መሆናቸውንና እንዲሁም በኑሮ ውድነት ምክንያት በርካታ ቤተሰቦች በፈረቃ ለመብላት
rehab
መገደዳቸውን በአገሪቱ የሚገኙ እንደ ሪፖርተር ጋዜጣና ሸገር ራዲዮ በተለያዩ ጊዜያት ዘግበዋል፡፡ በተለይ በብዙዎች ዘንድ አፍቃሪ ኢሕአዴግ፣ እንደው ያሰበውንና የተመኘውን ያህል ሰሚ ጆሮ፣ አስተዋይ ልቦና አላገኘም እንጂ የመንግሥት መልካም መካሪና ዘካሪ እንደሆነ አብዝቶ የሚታማው የሪፖርተር ጋዜጣ ባለፈው እሑድ ዕትሙ ርዕሰ አንቀጹ ላይ፡- ‹‹በድርቅ ለተጎዱትም ሆነ ለከተማ ድኅነት ፈጣን ምላሽ ያስፈልጋል›› በማለት ያስነበበው፣ በአደጋ ማስጠንቀቂያ የታጀበው ርዕሰ አንቀጹ አገሪቱ ያለችበትን እውነታና የተጋረጠባትን የረሃብ አደጋ ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነው ለማለት ያስደፍራል፡፡

 ዘንድሮ በአገራችን የተከሰተውን ድርቅና ይህንም ተከትሎ በአገራችን የተከሰተውን የረሃብ አደጋ በተመለከተ መንግሥትም ሆነ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የመገናኛ ብዙኃን ሰፊ ሽፋን ሰጥተው እየዘገቡት ነው ብሎ ለመናገር አያስደፍርም፡፡ ያው በታሪካችን እንደምናውቀው ሺዎች ከቀዬአቸው ካልተፈናቀሉና ካልሞቱ በስተቀር ‹‹ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም›› እንደሚባለው እየሆነ ያለ ነው የሚመስለው፡፡ ታሪካችን እንደሚነግረን በ፲፱፻፷ዎቹ በአገራችን ሰሜናዊ ክፍል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ከቀዬአቸው ሲፈናቀሉና ለአሰቃቂ ሞት ሲዳረጉ የዘውዱ መንግሥት በክብረ በዓልና በሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ነበር ተጠመዶ የነበረው፡፡ እናም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቹን ከቀዬአቸውና ላፈናቀለውና ለአሰቃቂ ሞት ለዳረጋቸው ለነበረው የረሃብ አደጋ ምላሽ የሰጠው ዘግይቶ ነበር፡፡

 በወቅቱ ይህ የረሃብ እልቂት እንዴት ወደ አደባባይ ሊወጣ እንደቻለ በሰማኒያዎቹ በሰሜን አሜሪካ ይታተም በነበረው ‹‹ሰምና ወርቅ›› በተባለው ጥናታዊ መጽሔት ‹‹ድርቅና ጠኔ በኢትዮጵያ›› በሚል ጥናታዊ ጽሑፋቸው ውስጥ ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ እንዲህ ገልጸውት ነበር፡፡ በወቅቱ የረሃቡን መከሰት የሰሙት ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ፣ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፣ ዶ/ር አሉላና ለሌሎች የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ባልደረቦቻቸው በግላቸው ሴስና አውሮፕላን ተከራይተው ረሃቡ የከፋ አደጋ ወዳደረሰበት ወደ አገራችን ሰሜናዊ ክፍል መረጃ ለመሰብሰብ ተጓዙ፡፡

ከወሬ ባለፈ በዓይናቸው ያዩትና ምስክር የሆኑበት የረሃብ አደጋና የወገኖቻቸው አሰቃቂ የሆነ እልቂት እጅጉን ልባቸውን የነካቸው እነዚህ ምሁራን በድርቅ የተጋለጡትን የአገሪቱን ግዛቶች፣ በረሃቡ የተነሣ እጅጉን የተጎዱትን ወገኖቻቸውን በማነጋገር በምስልና በቪዲዮ ያሰባበሰቧቸውን መረጃዎች በፕ/ር መስፍን አማካኝነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ እንዲታይ ተደረገ፡፡ ይህን አሰቃቂ የሆነ የወገኖቻቸውን እልቂት፣ የሞት ጥላ ያንዣበባቸውን፣ ቆዳቸው ገርጥቶና አንጀታቸው ተጣብቆ፣ ከሰው መልክና ወዘና የወጡትን ወገኖቻቸውን፣ በእናቶቻቸው ደረት ላይ ተጣብቀው የሟች እናቶቻቸውን ጡት ሲመገምጉ የሚታዩ ሕፃናትን ምሰልና ቪዲዮ የተመለከቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ማኅበረሰብ ወገኖቻችን በረሃብ እያለቁ አንማርም፣ መንግሥት የረሃቡን እልቂት ለለጋሽ አገራትና ለዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ያጋልጥ በሚል ያስነሱት ዓመፅ ቀስ በቀስ ተባብሶ ለዘውዱ ሥርዓት መገርሰስ ምክንያት ሊሆን እንደበቃ እናውቃለን፡፡ ፕ/ሮ ጌታቸው ኃይሌ በዚሁ ጥናታዊ ጽሑፋቸው ላይ እንደሚያትቱት በወቅቱ ረሃቡ በአገሪቱ ላይ ያደረሰውን የከፋ እልቂት ያሰባበሱትን መረጃዎች ለኤምባሲዎችና ለውጭ አገራት በመስጠታቸው ረሃቡ ሊጋለጥ መቻሉንና ከዚሁ የ፷፮ቱ የከፋ የረሃብ እልቂት ጋራ በተያያዘ ስሙ በእጅጉ የሚነሳው ጆንታን ዲምቢልቢም ረሃቡ የከፋ አደጋ ባደረሰበት በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ተገኝቶ መረጃውን በዓለም ሁሉ እንዲናኝ ያደረገው ከነፕሮፌሰር ባገኘው መረጃ በመነሣት እንደሆነ ጠቅሰውታል፡፡ ፕ/ር ጌታቸው በዚሁ ጥናታዊ ጽሑፋቸው መደምደሚያ ላይም፡- ‹‹ኢትዮጵያ ትገብር ፋሲካ ታኅፂባ በደም ውሉዳ፣ ወንዞቿንም በከንቱ ወደ ግብጽ ምድር ሰዳ›› በማለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ን በፋሲካ በዓል ሌሊት፣ ካህናቱና ሊቃውንቱ ‹‹ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ታኅፂባ በደም ክርስቶስ››፣ ‹‹ምድር በክርስቶስ ኢየሱስ ደም ታጥባና ነጽታ በሐሤትና በደስታ የፋሲካን በዓል ታድርግ!›› የሚለውን ማኅሌት ‹‹ኢትዮጵያ በአብራኳ ክፋይ በገዛ ልጆቿ ደም ተነክራና ታጥባ፣ ከፈጣሪ የተሰጣትንም የተፈጥሮ ጸጋ ወንዞቿን ሳትጠቀምባቸው እንዲሁ በከንቱ ወደ ምድር ግብጽ ሰዳ በዓለ ፋሲካዋን ታድርግ!›› በማለት አገሪቱ በረሃብ አለንጋ የምትገረፍ፣ ልጆቿ በረሃብ የሚያልቁባት፣ ትውልድ በእርስ በርስ ጦርነት የሚጫረስባት፣ የእልቂት ምድር፣ አኬል-ዳማ መሆኗን እንዲህ አመስጥረውታል፤ ገልጸውታል፡፡ የ፷፮ቱን ረሃብ ተከትሎ ከዐሥር ዓመት በኋላ በ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. በሰሜኑ የአገራችን ክፍል የተከሰተው ድርቅ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን ሲያፈናቅልና ብዙዎችንም ለሞት ሲዳርግ የደርግ መንግሥት ግን የአብዮቱን ፲ኛ ዓመት ለማክበር ሽር ጉድ እያደረገ፣ ሰማይ ምድሩ ጠቦት ፌሸታ ላይ ነበር፡፡ በተመሳሳይም በዘመነ ኢሕአዴግም በዘንድሮው ዓመት ስለተከሰተው የረሃብ አደጋ ለሕዝቡም ሆነ ለለጋሽ አገራት በቂ የሆነ መረጃ በመስጠት አፋጣኝ የሆነ ዕርምጃ ተወስዷል ብሎ ለመናገር አያስደፍርም፡፡

 ለአብነትም መንግሥት በወርኻ ክረምቱ ማብቂያ ላይ ‹‹የዲያስፖራ ቀን›› ብሎ በሰየመው ሳምንት በሺዎች ሚቆጠሩ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሰብስቦ በግብዣ ሲያንበሸብሻቸውና የልማታችን ውጤት ነው በሚል ፌሽታና ፈንጠዝያ ሲያደርግ በአገሪቱ ስለተከሰተው ድርቅና ስለተጋረጠብን ክፉ የረሃብ አደጋ በቅጡ አለመናገሩንና በቂ የሆነ የተብራራ መረጃ አለመስጠቱን ነው ያስተዋልነው፡፡ ወይስ መንግሥት ሆይ የድርቁ፣ የረሃቡ አደጋ ዜና ለመሆን የሚበቃው ሺዎችን ከቀዬአቸው ሲያፈናቅልና ለአሰቃቂ ሞት ሲዳርጋቸው ብቻ ነው ማለት ነው እንዴ …!? በሌላም በኩል ከጠቅላይ ሚ/ሩ እስከ ታች ባሉ የወረዳ ካድሬና ሹመኛ ድረስ እስኪሰለቸን በነጋ ጠባ የሚነገረን፣ የሚደሰኮረው አገሪቱ አስመዝግበዋለች ስለሚሉት ባለ ኹለት ዲጂት ዕድገትና ፈጣን ልማት ጉዳይ ነው፡፡ እንደ ዜጋ እንደ ኢትዮጵያዊ የአገራችን ፈጣን ዕድገትና ልማት ሁላችንንም ያስደስተናል፡፡ የሁላችንም ምኞት አገራችን በልጽጋና አድጋ፣ ሕዝባችንም ከስደትና ከጉስቁልና ወጥቶ ማየት ነው፡፡

ግና መንግሥት አገሪቱ አስመዝግበዋለች በማለት ከሚያስተጋባው ፈጣን የሆነ የልማትና የዕድገት ድምፅ ይልቅ የሚሊዮኖች ወጎኖቻችን የዋይታና የሰቆቃ፣ የእልቂትና የመከራ ድምፅ፣ እንባና ጩኸት በምድሪቱ ኹሉ ጎልቶና ደምቆ እያስተጋባ መሆኑን ልብ ሊለው ይገባል፡፡ ኢሕአዴግ ከአጋር ድርጅቶች ጋራ በመሆን ባለፈው ባደረገው ዓመታዊው ስብሰባውና ግምገማው የመልካም አስተዳደር እጦት ድርቅ መመታቱን፣ ኪራይ ሰብሳቢነትና ሙስና ለሥርዓቱ የከፋ አደጋ መሆናቸውን መማመኑንና ይህ አደጋም በአፍጢሙ ሊደፋው ያለ መሆኑን  የገለጸበት እውነታ፣ የሙሰኛ ባለሥልጣናቱ ማን አለብኝነትና አምባ ገነንነት፣ ግፍና ዓመፃ፣ የፍትሕ ረሃብና የመልካም አሥተዳደር መታጣቱ ከተጋረጠብን የረሃብ አደጋ ባልተናነሰ ሕዝባችንን ክፉኛ አስጎብጦትና እንደ መርግ ተጭኖት፣ ምድሪቱን በእንባ አጨቅይቶ፣ የዋይታና የሰቆቃ ምድር እያደረጋት ነውና መንግሥት ቆም ብሎ አብዝቶ ሊያስብ፣ ሊጨነቅ ይገባዋል፡፡ አለዚያ አደጋው እጅጉን ሊከፋ እንደሚችል አያጠያይቅም!!

tirsdag 13. oktober 2015

ሐብታሙ አያሌው በኩላሊት ጠጠር መታመሙ ተገለጸ * እነ አብርሃ ደስታ ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ



በ እስር ቤት የሚገኘው ታዋቂው ፖለቲከኛ ሃብታሙ አያሌው ዛሬ በድንገተኛ ህመም ዘውዲቱ ሆስፒታል ተወስዶ እንደነበር ተዘገበ::  ሃብታሙ ከ እስር ቤት ወደ ዘወዲቱ ሆስፒታል የተወሰደበት ምክንያት በሁለቱም ጎኖቹ ላይ የህመም ስሜት ስለተሰማው ነበር:: የዘውዲቱ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ምርመራ ካደረጉለት በኋላ ህመሙ የኩላሊት ጠጠር መሆኑን ለባለቤቱ ወ/ሮ ቤተልሄም መናገራቸውን እነዚሁ ምንጮች አብራርተዋል:: ሃብታሙ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የተመለሰ ሲሆን በነገው ዕለትም ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ተገልጿል:: ከሃብታሙ አያሌው ጋር አብረው የተከሰሱትና በቅርቡ በከፍተኛው ፍርድ ቤት በነፃ የተለቀቁት አብርሃ ደስታ; ዳንኤል ሺበሺና የሺዋስ አሰፋም በነገው ዕለት አቃቤ ሕግ ይግባኝ በጠየቀባቸው ክስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርበው የቃል ክርክር ያደርጋሉ ሲሉ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::


torsdag 8. oktober 2015

የላይ አርማጭሆ ገበሬዎች በህወሓት አገዛዝ ፌደራልና ልዩ ኃይል ፖሊሶች በገፍ እየታፈሱ ወደ እስር ቤት እየተጋዙ ነው






የላይ አርማጭሆ ገበሬዎች በህወሓት አገዛዝ ፌደራልና ልዩ ኃይል ፖሊሶች በገፍ እየታፈሱ ወደ እስር ቤት እየተጋዙ ነው፡፡ ዘረኛው እና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከልዩ ኃይል እና ከመከላከያ ተመርጦ የተውጣጣ ሰራዊት በላይ አርማጭሆ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ማለትም በሙሴ ባንብ በጃኒካው፣ በገንበራ እና በሌሎች በርካታ አካባቢዎች ያሰራጨ ሲሆን ከሦስቱ ክፍሎች የተጣመረው ኃይል በየገበሬው መንደር ተሰግስጎ በማሸበር በመሳሪያ ገፈፋና በአፈሳ ተግባራት ላይ በሰፊው ተሰማርቶ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በላይ አርማጭሆ ገንበራ ቀበሌ ብቻ • አቶ አራጋው አበራ(የሚሊሻ ኮማንደር የነበረ) • አቶ አወቀ ጎሉ • አቶ ተቀባ ብርሃን • ወጣት ቴዎድሮስ ሙሉ • ወንድሙ ሙሉ እና • ወይዘሮ ደብሬ የኔዓለም የተባሉ ገበሬዎች ታፍነው ተወስደዋል፡፡ እነኚህን ስማቸው የተዘረዘሩትን ጥቂት ድሃ ገበሬዎች ጨምሮ በአገዛዙ የታጠቁ ኃይሎች በየቀኑ ከቀያቸው እየታፈኑ የሚወሰዱት ሰዎች በትክል ድንጋይ ልዩ ኃይል የጦር ካምፕ ውስጥ ታጉረው እደሚገኙ ተገልጿል፡፡

tirsdag 6. oktober 2015

የስኳር እጥረት ተከሰተ * በወያኔ ታሪክ እንደ ዓባይ ፀሀዬ ያለ ዓይን ያወጣ ዘራፊ በሙስና ሌብነት ለየስሙላ እንኳ ተከሶ አያውቅም

Image result for abay tsehaye

(ፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ) ወያኔ በኦሞ ራቴ በኩራዝ ወረዳ የጀመረው የሸንኮራ እርሻ ጠንካራ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ በወያኔ ታሪክ እንደ ዓባይ ፀሀዬ ያለ ዓይን ያወጣ ዘራፊ በሙስና ሌብነት ለየስሙላ እንኳ ተከሶ አያውቅም፡፡

 የስኳር ልማት ኃላፊው ዓባይ ፀሀይ በየጊዜው የሚመደበውን ገንዘብ እየዘረፈ የስኳር ልማቱ ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ መሆኑ በስፋት እየተነገረ ይገኛል፡፡ እስካሁን በስፋት በማምረት ላይ ያሉት መተሀራ፣ ወንጂ፣ ፊንጫ ስኳር ፋብሪካዎች በተለየዩ ምከንያቶች ከአቅም በታች እያመረቱ መሆናቸው በተደጋጋሚ የታወቀ ጉዳይ ነው፡፡

ሰባት አዳዲስ ፋብሪካዎች ያመርታሉ ተብሎ ቢጠበቅም ለአገር ውስጥ የሚፈለገውን 6.5 ሚሊዮን ኩንታል ማምረት ተስኗቸዋል፡፡ በሚፈለገው መጠን የሸንኮራ አገዳ አቅርቦት አለመኖሩ አንዱ ምክንያት መሆኑን ኮርፖሬሽኑ ቢያቀርብም ዋናው ምክንያት ግን ለሸንኮራ ልማት የሚመደበው ገንዘብ ወያኔዎች ሙልጭ እያደረጉ ስለዘረፉት እንደሆነ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ያስረዳሉ፡፡

 ከተመረጡት የሸንኮራ አገዳ እርሻ አካባቢዎች አንዱ የሆነው በደቡብ ኦሞ የሚገኘው ነው፡፡ ይህን የእርሻ ልማት ለማካሄድ መወሰኑን ለአካባቢው ሕዝብ ለውያይት አቅርበው ማስወሰን ሲገባቸው በማን አለብኝነት በመሬቱ ላይ የሰፈሩትን በማፈናቀል በመሆኑ ሕዝቡ ተቃውሞውን እየገለጸ ይገኛል፡፡

 ከአሁ ቀደም የግልገል ግቤ ግድብ ሲገነባ የውሀው ፍሰት ለአካባቢው ሕዝብ ችግር እንደ ሚፈጥር በመጥቀስ ሕዝቡ ተቃውሞውን ባሰማበት ወቅት የወያኔ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በአካባቢው ሰፍሮ የሚያስተባብሩትን እንደ ደበደበና እንዳሰቃየ ይታወሳል፡፡

 ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ውስጥ ስኳር በከፍተኛ ደረጃ ከገበያ እየጠፋ በመሆኑ የህንድ አግሮ ክሮፕ ኢንተርናሽናል ከሚባል ድርጅት 75 ሺ ቶን ስኳር በ29.7 ሚሊዮን ዶላር ለመግዛት ስምምነት ፈጽሟል፡፡

 በአሁኑ ወቅት ገበያ ላይ ያለው ስኳር ብዙዎቹ የኬሚካል ቅልቅል እንዳለበት በማማረር ሲናገሩ ይሰማል፡፡ ወያኔ ልክ እንደ ቅባት እህል የስኳር ምርትን በአብዛኛው ለውጪ ገበያ እያቀረበ በምትኩ በጤና ላይ ችግር ሊያስከትል የሚችል ማስገባቱ የወያኔን ደንታ ቢስነት ብቻ ሳይሆን ፀረ- ሕዝብነትም የሚሳይ መሆኑን በርካቶች ይስማሙበታል

fredag 2. oktober 2015

በወልቃይት በርካታ አካባቢዎች የሚገኙ ገበሬዎች አዝመራቸውን እንዳይሰበስቡ በፌ. ፖሊስ በመታገዳቸው ጥይት ያታኮሰ ከፍተኛ ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ


በተኸለ አምባ እና በሌሎች የወልቃይት በርካታ አካባቢዎች የሚገኙ ገበሬዎች አዝመራቸውን እንዳይሰበስቡ በፌደራል ፖሊስ በመታገዳቸው ጥይት ያታኮሰ ከፍተኛ ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ ውጥረቱ አሁንም ተባብሶ እንደቀጠለ ነው፡፡ በወልቃይት የሚገኙ ገበሬዎች ማንኛውም ሰው ተነስቶ የሚያርሰውን በተለምዶ “ሞፈር ዘመት” እየተባለ የሚጠራውን መንገድ ተጠቅመው በግንቦትና በሰኔ ወራት ጫካ መንጥረው ምድረ በዳውን በማረስ የተለያዩ አዝዕርቶችን በተለይም ሰሊጥ ዘርተው ያበቀሉ ሲሆን አሁን በመኸር ክወና ላይ ተሰማርተው ባሉበት የህወሓት አገዛዝ ደን ጨፍጭፋችሁ አርሳችኋል በሚል ተልኮሻ ምክንያት ፌደራል ፖሊስ

 በየማሳቸው በማሰማራት ለማገድ በመሞከሩ ነው “ግንቦት እና ሰኔ ገና መሬቱን ማልማት ስንጀምር ከተቆረቆራችሁ ለምን አልከለከላችሁንም?” በሚል ህዝቡ በአንድነት ተነስቶ ግጭት የተቀሰቀሰው የህወሓት ፌደራል ፖሊሶች ተክላይ የተባለውን ገበሬ ከማሳው አስረው ወስደው አደባይ ላይ በመረሸናቸው የዘርባቢትና እድሪስ ቀበሌዎች ነዋሪዎች በአንድነት “ሆ” ብለው ተነስተው ፖሊሶችን ትንቅንቅ ገጥመዋቸዋል፡፡ በተለይም የአካባቢው ሚሊሻዎች ከህዝቡ ጎን በመቆም በፌደራል ፖሊሶች ላይ ተኩስ ከፍተው ውጊያ በመግጠም ሁለት ፖሊሶችን አቁስለዋል፡፡

 በአካባቢው የታጠቁ ሚሊሻዎችና ገበሬዎች የደረሰ አዝመራቸውን እንዳይሰበስቡ ለማገድ በየማሳው በተሰማሩ ፌደራል ፖሊሶች መካከል የተከፈተው ጦርነት ለማስቆም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ኃይል በአካባቢው ተሰማርቶ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን ግጭቱ የባሰውን ተቀጣጥሎ የሰፈነውን ውጥረት እንዲያይል አደረገው እንጂ ሊያረግበው እንዳልቻለ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡