mandag 30. juni 2014

እንደ ከሳሾቼ 100 ሺ የማከራየው ቤት የለኝም” ሲሉ አቶ ገብረውሃድ ተናገሩ

መንግስት በሙስና ወንጀል የከሰሳቸው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ የቀድሞዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ እና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ገብረ ዋህድ ወልደጊዮርጊስ የእምነት ክህደት ቃላቸውንለፌዴራልከፍተኛፍርድቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት የሰጡ ሲሆን፣ አቶ ገብረውሃድ “በኢትዮጵያቴሌቪዥን 16 ቤትአለውተብሎበካሜራተቀርፆመነገሩየሚያሳዝንመሆኑን ፣ እርሳቸውበአዲስአበባውስጥአንዲትጐጆእንደሌላቸውና ቢኖራቸው ኖሮ ልጆቻቸው መጠለያ እንደማያጡ ተናግረዋል።
‹‹እንደከሳሾቼ 100,000 የማከራየውቤትየለኝም፤›› በማለት ንጽህናቸውን ለማስረዳት የሞከሩት አቶ አቶ ገብረውሃድ፣ ከሳሾቼ ያሉዋቸውን ሰዎች  በስም ከመጥቀስ ተቆጥበዋል።
ሪፖርተር እንደዘገበው  አቶ ገብረውሃድ መሬት  መቀበላቸውንነገር ግንቤትለመሥራትአቅምስለሌላቸውምእንዳልሠሩበትዘግቧል።
ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መላኩ ፋንታ በበኩላቸው ” ልንመሰገንበት በሚገባ ስራ ወንጀለኞች መባላችን ያሳዝናል ” ሲሉ የቀረበባቸውን ክስ ክደዋል።
“አቶመላኩከገቢያቸውጋርየማይመጣጠንከ3.2 ሚሊዮንብርበላይየሆነንብረትናገንዘብአፍርተዋል”በሚልለቀረበባቸውክስ፣እንደማንኛውምሰው 175 ካሬሜትርቦታላይቤትመሥራታቸውን፣ይህደግሞለእሳቸውብቻተነጥሎወንጀልሊሆንእንደማይችልገልጸው፣ ዓቃቤሕግየቤቱንግምትአሳስቶማቅረቡንምተናግረዋል።
ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ ያስረዱልኛል ያላቸውን ምስክሮቹን ከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ አቅርቦ እንዲያሰማ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል።

lørdag 28. juni 2014

በአ.አ ዩኒቨርሲቲ 52 ተማሪዎች በ”ዲሲፕሊን” ሰበብ ፖለቲካዊ ክስ ተመሰረተባቸው

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመብት ጥያቄ አንስተው በሃገራዊ ጉዳይ ነቃ ያለ ተሳትፎ የሚያደርጉ 52 ተማሪዎች ላይ የዲሲፕሊን ክስ መመስረቱ ተሰማ። የዲሲፕሊን ክስ የተመሰረተባቸውን ተማሪዎች ስም ዝርዝር የያዘውን ወረቀት በማህበራዊ ድረገጾች ላይ የለቀቁት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ክሱ የተመሰረተባቸው ሰኔ 21 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ በ2 ሰዓት በተማሪዎች ጽ/ቤት እንዲገኙ ት ዕዛዝ ተሰጥቷል።
ምናልባትም እነዚህ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ትኩረት አድርገው የሚንቀሳቀሱት ተማሪዎች ላይ በዲሲፕሊን ሰበብ ፖለቲካዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚችል የቅርብ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ያስታወቁ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ይህን እርምጃ ከወሰደ ሌላ የተማሪዎች አመጽ እንዲነሳ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ታዛቢዎች ይናገራሉ።
በዲሲፕሊንክ ክስ ሰበብ የፖለቲካ እርምጃ ሊወሰድባቸው የተዘጋጁት ተማሪዎች ስምዝርዝር የሚከተለው ነው፦
students 1
students 2

fredag 27. juni 2014

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ” ለአንድነታችን በጽናት እንቆማለን” የሚሉ መፈክሮችን በማሰማት የረመዳንን ጾም ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሰላማዊ ተቃውሞ ታሪክ ውስጥ ረጅም ጊዜ በማስቆጠር ክብረወሰን የሰበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ፣  በረመዳን ጾም መግቢያም ” በአንድነታችን እንጸናለን” በሚል መፈክር ተካሂዷል።
እንደወትሮው ሁሉ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በአንዋር መስጊድ በተካሄደው  የጸሎት ስነስርአት፣ ሙስሊሙ “በአንድነታችን እንጸናለን” የሚሉ በወረቀት ላይ የተጻፉ መፈክሮችን ከፍ አድርጎ በማሳየትና እጅ ለእጅ በመያያዝ መልእከቱን አስተላልፏል። ዝግጅቱ ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ተጠናቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት የፍርድ ሂደት እንደቀጠለ ሲሆን ፣ ኢትዮጵያውያኑ ” የሃይማኖት ነጻነታችን ይከበር” የሚል ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ እጅግ አሰቃቂ እንግልትና በቃላት ሊገለጹ የማይችሉ ግፎች በወንዶችና በሴት እሰረኞች ላይ መፈጸማቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች በማህበራዊ ድረገጾች እየተለቀቁ ነው።
የኮሚቴ አባላቱ የሚያሳዩት ጽናት በርካታ ሙስሊሞች በጽናት እንዲቆሙ እንዳደረጋቸው ታዛቢዎች ይናገራሉ። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች መሪዎቻቸውን ለማየትና ለማበረታታት የፍርድ ቤት ቀጠሮች በሚኖሩበት ጊዜ እየተገኙ ድጋፋቸውን ይገልጻሉ።
በሙስሊሙ ትግል መፍትሄ ያጣ የሚመስለው መንግስት፣ ሙስሊሙ መሪዎቹ ሲታሰሩበት ትግሉን ያቆማል ብሎ መሪዎቹን ቢያስርም፣ ተቃውሞው ግን ሊቆም አልቻለም። ታዛቢዎች እንደሚሉት መንግስት መሪዎቹን ከእስር ካልፈታ፣ በሙስሊሙ ህዝብ ላይ ለፈጸመው በደል ይቅርታ ካልጠየቀና  ጥያቄዎቻቸውን  በአስቸኳይ ካልመለሰ፣ ተቃውሞው መቀጠሉ አይቀሬ ነው።

tirsdag 24. juni 2014

ኢቲቪ እንደእነ ቢቢሲ በኮርፖሬሽን ደረጃ ሊዋቀር ነው

የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ከእነቢቢሲ ያጠናውን  ልምድ መሰረት አድርጎ ስያሜው ወደ ኢትዮጽያ ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንዲቀየርለት የሚጠይቅ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማው ቀረበ፡፡
ድርጅቱ ለ19 አመታት ሲጠቀምበ ትየቆየውን አዋጅ ማሻሻል ያስፈለገው አደረጃጀቱን በማስተካከል የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በብቃት እንዲወጣ እንዲያስችለው ነው ተብሎአል፡፡
ለትርፍያልተቋቋመናተጠሪነቱለፓርላማውየሆነየመንግሥትየልማትድርጅትበመሆንበኮርፖሬሽንደረጃየሚዋቀረውኢትዮጵያብሮድካስቲንግኮርፖሬሽንየዚህኣይነትአደረጃጀትበልምድነትየቀሰምኩትከቢቢሲ፣ከኤስ፣ኤ፣ቢ.ሲ፣ከኬንያውኬ.ቢ.ሲእናከህንዱከኦልኢንዲያንስነውብሏል፡፡
አዋጁለዝርዝርዕይታለኮምቴተመርቷል።

mandag 23. juni 2014

የአንድነት የአዋሳ ሰልፍ “በእስር ተጀምሮ በእስር ተጠናቀቀ”

የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል አንድነት ፓርቲ በአዋሳ ሊያካሂደው የነበረው ሰልፍ ፣ የሰልፉ አስተባባሪዎችና የፓርቲው የአመራር አባላት በመታሰራቸው ምክንያት ሳይካሄድ ቀረ።
ሰልፉ ከመካሄዱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ በፓርቲው ቅስቀሳ የተደናገጡት የሚመስሉት የአዋሳ ባለስልጣኖችና ፖሊስ አባላት 37 የሚሆኑ በቅስቀሳ ላይ የተሰማሩ አመራሮችንና ደጋፊዎችን ይዘው በተለያዩ እስር ቤቶች አስረዋቸዋል።
በማግስቱ እስረኞችን ለመጠየቅና ስንቅ ለማቀበል ከሄዱት መካከልም አንዳንዶች መታሰራቸውን በስፍራው የሚገኘው የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ያሬድ አማረ ለኢሳት ገልጸዋል።
ከአዲስ አበባ የሄዱና የአዋሳ የፓርቲው አመራሮች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡና ክስ ሳይመሰረትባቸው በመታሰራቸው የረሀብ አድማ ያደረጉ ሲሆን፣ ዛሬ ሰኞ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ እየተጠበቀ መሆኑን አቶ ያሬድ አክለው ተናግረዋል።
መድረክ በአዋሳ በከፍተኛ ወከባ ውስጥ ሆኖ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጉ ይታወቃል። አንድነት ፓርቲ በተለያዩ ክልሎች እየዞረ በርካታ ህዝብ የሚሳተፍበት ሰላማዊ ሰልፎችን እያደረገ ነው። በአዋሳው ሰላማዊ ሰልፍ በኦሮሞ ወጣቶች ላይ የተወሰደው እርምጃ፣ የኑሮ ውድነት፣ ከማንነት ጋር በተያያዙ የሚታዩት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እና የመሳሰሉት ጉዳዮች ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር።
አንድነት በአዋሳ ለሚያካሂደው የተቃውሞ ሰልፍ ለክልሉ መንግስት የእውቅና ደብዳቤ ያስገባው ከአንድ ወር በፊት ነበር። የከተማው ምክር ቤት እስካለፈው አርብ ድረስ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት እየተነጋገርነበት ነው በማለት ሲያጓትተው ቆይቷል።
አንድነት ፓርቲ  በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ “በተለየ ሁኔታ በደቡብ ክልል እየታየ ያለው መንግስታዊ አፈናና ጸረ ህግ አቋም እንዲገታ ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን” ብሎአል።
“የስርዓቱ መንግስታዊ አፈናና ፀረ-ሕዝብ አቋም በመላ ኢትዮጵያ የተዘረጋ ቢሆንም ፓርቲያችን በእንቅስቃሴዎቹ ውስጥ እንደታዘበው በደቡብ ክልል በተለየ ሁኔታ ተጠናክሮ ቀጥሏል” ያለው አንድነት፣  “በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ሹማምንቶች ባደረባቸው የገዥነት መንፈስ ሰላማዊ እንቅስቃሴዎችን በማፈንና ብሎም ያለምንም ማስረጃና ምክንያት ሰላማዊ ታጋዮችን ወደ እስር ቤት በመክተት ተግባራዊ እያደረጉት ” ነው ብሎአል።
በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ወደእስር ቤት መወሰዳቸውን፣ ቁጫ ላይ ተጠርቶ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍም እንዲሁ በጉልበት፣ በእስርና አፈና እንዳይካሄድ መደረጉን የገለጸው አንድነት፤ የክልሉ ዋና ከተማ በሆነችው አዋሳ የተጠራው ሰልፍ በህገወጥ እስር መጠናቀቁን ገልጿል፡፡
“በክልሉ ለመዝጋት እየተሞከረ ያለውን የህዝብ ጥያቄ ከህዝብ ጋር በመሆን መፍትሔ እንዲያገኝ እናደርጋለን” የሚለው አንድነት ጉዳዩን ወደ ህግ እንደሚወስደውም ገልጿል።
ያለምንም ወንጀል የታሰሩ አባሎቻችንና አመራሮቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳ እንዲፈቱ የጠየቀው ፓርቲው ፣ በደቡብ ክልል እየታየ ያለውን መንግስታዊ አፈናና ፀረ-ሕዝብ አቋም እንደሚታገለው አስታውቋል።ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ በቅስቀሳ ላይ የነበሩት አመራሮች የዋስትና መብታቸውን ተከልክለው ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ ተደርጓል።
መስተዳድሩ ከጻፈው ደብዳቤ ለመረዳት እንደሚቻለው ሰዎቹ የታሰሩት በህገወጥ መንገድ ሲቀሰቅሱ ተገኝተዋል በሚል ነው።                                 

søndag 22. juni 2014

አንድነት ፓርቲ በአዋሳ ሊያደርገው የነበረው ሰልፍ አመራሮችንና አባላትን በማሰር ከተማዋን በፀጥታ ኃይሎች በመውረር ተደናቀፈ


በዛሬው ዕለት በአዋሳ ከተማ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በሀዋሳ ከተማ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የፓርቲው አባላት ከሐሙስ ዕለት ጀምሮ እስከ ትላንት ድረስ ከ30 በላይ በፖሊስ የታሰሩ ሲሆን የሲአን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለገሰ ላንቃሞ ለምን ይታሰራሉ ብለው በመጠየቃቸው እሳቸውንም አስረው ከምሽቱ 3፡30 ለቀዋቸዋል፡፡ በቅስቀሳው ወቅት ወረቀቶች የተበተኑ በመሆኑ ህዝብ በነቂስ ሊወጣ እንደሚችል ስጋት ያደረባቸው የደህዴን ካድሬዎች ትላንት ማታ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ተጨማሪ 7 የአንድነት የሀዋሳ አመራሮችና አባሎች በቁጥጥር ስር አውለዋል፡፡ የደቡብ ክልል የደህዴን ካድሬዎች ከተለቀቁ ነገ ሰልፉን ከማድረግ ወደኋላ አይሉም በሚል ለሁለት ተከፍለው ሲሟገቱ ማምሸታቸውንና አቶ መንድሙ ወታንጎ የተባሉት የደህንነት ኃላፊ መፈታት የለባቸውም መፍታት እንኳን ካለብን የሰልፉ ሰዓት ካለፈ በኋላ ነው በማለታቸው በእስር ቤት እንዲያድሩ መወሰኑና በዛሬውም ዕለት የሀዋሳ ከተማ በፀጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ጥበቃ ሥር መሆኗን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገልፀዋል፡፡

lørdag 21. juni 2014

በሺህ የሚቆጠሩ አማሮች ከምዕራብ ወለጋ ተፈናቀሉ

በሺህ የሚቆጠሩ አማሮች አማራ በመሆናቸው ብቻ ተመርጠው ከምዕራብ ወለጋ ከጊምቢ እና ቄሌም (እንፍሌ ወረዳ አሽ ቀበሌ) ተፈናቀሉ
በብዙ ሺህ የሚቆጠር የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያውያን ከምዕራብ ወለጋ ጊምቢ እና ቄሌም በኃይል አካባቢውን እንዲለቁ ከመደረጉ በላይ ድብደባ እናAmhara-People-in-Benshangul-Kilil1ግድያ እንደተፈፀመባቸው ቪኦኤ የአማርኛው አገልግሎት ሰኔ 12/2006 ዓም ምሽት ባስተላለፈው ዘገባ ገለፀ።
ዘገባው የተፈናቃዮችን ምስክርነት እንዳስደመጠው ድብደባው እና ግድያው በከተማው ሕዝብ እና ፖሊስ የታገዘ መሆኑን እና ህይወታቸውን ያተረፉት በኮርኒስ እና ጫካ በመደበቅ መሆኑን ሲገልጡ፣አንድ ምስክርነታቸውን ለቪኦኤ የሰጡ ተፈናቃይ አክለው እንደገለፁት ከጊምቢ ከተማ ብቻ ከሶስት ሺህ በላይ የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያውያን መፈናቀላቸውን ተናግረዋል።ሌላው ምስክርነት ሰጪ ደግሞ ቁጥሩን ከስምንት ሺህ ሕዝብ በላይ አድርሶታል።
አምስት ልጆች የነበራቸው መሆናቸውን የተናገሩት ሌላ ተፈናቃይ የነበራቸው መደብር መዘረፉን እና ካለምንም ሀብት መቅረታቸውን፣ጉዳዩን አቤት ለማለት ወደ ባለስልጣናት ቢሄዱም ሰሚ ማጣታቸውን አስታውቀዋል።
የቪኦኤ ጋዜጠኛ ጉዳዩን አስመልክቶ ቀደም ብሎ የአካባቢው የፀጥታ ጉዳይ ኃላፊ የተባሉ እሳቸው ግን የኦሕዴድ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ነኝ ያሉ አቶ አወቀ የተባሉ የክልሉ ባለሥልጣን ስለጉዳዩ ሲናገሩ ”ያባረረ የለም’ ሲሉ ተደምጠዋል።
የኦሮምያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳይ ኃላፊ ወ/ሮ ራቢያ ኢሳ ”ሰዎቹ የሄዱት ፈርተው ነው” ካሉ በኃላ ”ቁጥራቸው ”መቶ አይሞሉም ” ማለታቸው ግርምትን ፈጥሯል።የቪኦኤ ጋዜጠኛ አቶ ሰለሞን በመቀጠል ” ቁጥሩ አይደለም ወሳኙ አንድም ሰው ቢሆን ለምን ተፈናቀለ? ደግሞስ ምን ያስፈራቸዋል? ያብራሩልኝ ” ብሎ ለጠየቃቸው ወ/ሮ ራቢያ አጥጋቢ መልስ ለመስጠት ሳይችሉ ቀርተዋል።
የኢህአዲግ/ወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ሕዝቡን በአካል መለብለብ ከጀመረ ሰነበተ።ሺዎች የእዚህኛው ሌሎች የእዚያኛው ብሄር ተወላጅ ናችሁ እየተባሉ ተፈናቅለዋል።በተለይ ከአማራው ህዝብ ተወላጅ የሆኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከጉርዳፈርዳ፣ከበንሻጉል፣ከኢልባቦር እና ከወለጋ አሰቃቂ ግድያ እና ድብደባ እየተፈፀመባቸው ለዘመናት ያፈሩትን ንብረት እየተነጠቁ መባረራቸውን ያመለከቱ ዘገባዎች ሲወጡ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

torsdag 19. juni 2014

የዋስትና መብት የተነፈጉ ነጋዴዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

በሃረር በቅርቡ ከተነሳው ቃጠሎ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ ከሚገኙት ከ20 በላይ ነጋዴዎችና ሰራተኞች መካከል ፍርድ ቤት የቀረቡት 3ቱ ተከሳሾች እንደገና ሌላ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል።
የ25  አመቱ  ቢኒያም ጌታቸው፣ የ28 አመቱ ሲሳይ አሊ አህመድ እና የ16 አመቱ  ዙቤር  አህመድ  በ1996 ዓም የወጣውን የወንጀል ህግ በመተላለፍ ” በፌደራል ህገመንግስት የተቋቋመውን የሃረሪ ህዝብ ክልል መንግስት ፣ በዚህ ክልል መንግስት የተቋቋሙትን የአስፈጻሚ አካላትን የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች መስሪያ ቤቱ የእለት ተእለት ስራውን በተለይም የትራንስፖርት  መገናኛ ጽ/ቤት ባለስልጣን እና ሰራተኞች እንዲሁም የክልሉ ፖሊስ ሃይል አባላት የሃረር ብሀረሰብ እና ሰራተኞች በፌደራልና በክልል ህገመንግስት የተሰጣቸውን የማስተዳደር ስልጣን ለማደናቀፍ ተከሳሾች መጋቢት 1/2006 ዓም ከጠዋቱ ከ3፡00 እስከ 7 ሰአት ባለው ጊዜ በቀበሌ 14 ውስጥ በሚገኘው የትራንስፖርትና መገናኛ ጽ/ቤት እና ፊት ለፊቱ ባለው መንገድ ከ300 እስከ 500 የሚሆኑ ህወገወጥ ስለፈኞችን በመምራት በዛቻ፣ መንገድ በመዝጋት፣ ድንጋይ በመወርወር የመንግስት ሰራተኞች እና የክልሉ ነዋሪዎች ወደ እለት ስራዎች እንዳይሄዱ በመከላከል በመንገድ ትራንስፖርት መገናኛ ጽ/ቤት ላይ ግምቱ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ እና እንዲደርስ በማድረግ፣ አንድን ብሄረሰብ ነጥሎና ፖሊስን በመሳደብ፣ የመንገድ ትራንስፖርት መገናኛ ጽ/ቤት በእሳት ለማጋየት በሞመከር የክልሉን ሰንደቃላማ ከተሰቀለበት በማውረድ የመንግስትና የህዝብ ንብረት በማውደም የክልሉን ህገመንግስታዊ ተግባርን በማደናቀፍ ወንጀል” መከሰሳቸውን የክስ ቻርጁ ያመለክታል።
በተለይ አንደኛው ተከሳሽ ቢኒያም ጌታቸው የሃረሪ ክልልን ሰንደቃላማ በንቀት ከተሰቀለበት በማውረድና በማቃጠሉ የመንግስት ምልክት በመድፈር ወንጀል መከሰሱን የክስ ጃርጁ ያመለክታል።
ሶስቱም ተከሳሾች ” የሃረሪ ክልል ባለስልጣኖችን፣ ያሃረሪ ፖሊስን፣ የሃረሪ ብሄረሰብን ሌባ በማለት የሃሰት ወሬዎችን በመንዛት የፖለቲካና የዘር ጥላቻን በመቀስቀስ በፈጸሙት የሃሰት ወሬዎችን በማውራት ህዝብን በማነሳሳት ወንጀል መከሰሳቸውንም የክስ ቻርጁ ይዘረዝራል። ተከሳሾች በበኩላቸው የሃረሪን መንግስት እንጅ ህዝቡን አልተሳደብንም በሚል እየተከራከሩ ነው።
ፍርድ ቤቱ የዳኛ እጥረት አለብን በሚል ለሃምሌ 24 ቀጠሮ ሰጥቷል። በ20 ሰራተኞችና ነጋዴዎች ላይ የተመሰረተው ክስ ደግሞ ሰኔ 20 ቀን እንደሚታይ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በእነማይ ወረዳ የመኢአድ አባላት እየተዋከቡ ነው።

በምስራቅጎጃም ዞን  በነማይወረዳደንጎሊማቀበሌ የሚኖሩት አቶሞሳአዳነቅዳሜሰኔ 7 ቀን በኢህአዴግ ታጣቂዎች ከተገደሉ በሁዋላ ሌሎችም አባሎች እየተዋከቡ መሆኑን የወረዳው የመኢአድ ተወካይ መቶ አለቃ ደመላሽ ጌትነት ተናግረዋል።
ግለሰቡ ገበያ ውሎ ሲመለስ አዲሱ ጫኔ እና ብርሃኑ ታምሩ የተባሉ ካድሬዎች መንገድ ላይ አስቁመው በዱላ ደብድበው እንደገደሉት የሟቹ ወገን የሆኑትና በህይወትና በሞት መካከል ባለ ጊዜ ደርሰው ቃሉን የተቀበሉት አቶ ይልቃል የሻነው ተናግረዋል።
አቶ ይልቃል እርሳቸውንም ለመግደል ሙከራ በመደረጉ አካባቢውን ለቀው መሰደዳቸውን ገልጸዋል። ፖሊስ ምንም የተጨበጠ መልስ እንዳለስጣቸውም አክለዋል
አቶይበልጣልወንድሜነህ የተባሉ በደብረጥሞና ቀበሌ የሚኖሩት ሌላው የመኢአድ አባል ደግሞ  መሣሪያ ደብቀሃል በሚል ቤታቸው ተከቦ እንደሚገኝ ግለሰቡ ግን ማምለጣቸውን መቶ አለቃ ደመላሽ ተናግረዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የወረዳውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

tirsdag 17. juni 2014

የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉት ዜጎች ለክስ የሚያበቃ በደል አልደረሰባቸውም አለ።

ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎች በተወካዮቻቸው አማካኝነት የመሰረቱት ክስ በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 8ኛ ፍትሃ ብሄር ምድብ በዋለው ችሎት የታየ ሲሆን ፣ በቀረበው ክስ ላይ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና የቤንሻንጉል ክልል መንግስት መልስ ሰጥተዋል።
ከሳሾች ለበርካታ አመታት ከኖሩበት ቀየ በህገወጥ መንገድ በመፈናቀላቸው ሃብትና ንብረታቸውን ማጣታቸውን በጠበቃቸው አማካኝነት ተናግረዋል።
የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በበኩሉ ከሳሾቹ ቤት ንብረት አለማፍራታቸውን ጠቅሶ፣ ምንም ለክስ የሚያበቃ ነገር ሳይኖራቸው ጉዳያቸው ለፖለቲካ ፍጆታነት እየዋለ ነው በማለት መልስ ሰጥቷል።
በጉዳዩ ዙሪያ ላይ ያነጋገርናቸው ጠበቃው ዶ/ር ያእቆብ ሃይለማርያም  የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ‘ጉዳዩ የሚመለከተው የክልሉን መንግስት እንጅ የፌደራሉን አይደለም’ በማለት የሰጠው መልስ ትክክል አለመሆኑን ተናግረዋል። የህገመንግስቱ አንቀጽ 52 ማንኛውም የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲፈጸም የፌደራል መንግስቱን እንደሚያገባው፣ በዚህም የተነሳ የፌደራል መንግስቱ አይመለከተኝም ማለት እንደማይችል ገልጸዋል።
ዶ/ር ያእቆብ   ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ‘ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ያደረጉትን ለፍርድ እናቀርባለን’ በማለት ተናግረው  እንደነበር አስታውሰዋል። አሁን እየታየ ያለው ግን የዚህ ተቃራኒ ነው ነው ሲሉ አክለዋል።

lørdag 14. juni 2014

ያለ ክስ ለ 50 ቀኖች በእስር የሚገኙት ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች ክስ እንዲቀርብባቸው ዳኛው ፖሊስን አዘዙ

bloggers1


ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 7፣ 2006 ዓ.ም በቀጠሯቸው መሠረት አራዳ በሚገኘው ፍርድ ቤት የቀረቡት ሦስት ጋዜጠኞች አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ፣ ተስፋለም ወልደየስ ኤዶም ካሳዬ እና ሦስት ጦማሪያን ዘላለም ክብረት፣ አጥናፍ ብርሃኔ፣ ናትናኤል ፈለቀ እንደተጠበቀው በፖሊስ ተጨማሪ የ28 ቀናት ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ሲሆንፍርድ ቤቱም ለሐምሌ 5 ፣ 2006 ዓ.ም እንዲቀርቡ የተጠየቀውን የጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል፡፡

አራዳ ምድብ ችሎት ከወትሮው በርከት ያሉ የተጠርጣሪ ቤተሰብና ወዳጆች በፍርድ ቤቱ ግቢ ተገኝተዋል፡፡ ግንቦት 9፣ 2006 በነበረው ችሎት ከእያንዳንዱ ተጠርጣሪ ሦስት ቤተሰብ ወደ ችሎት እንዲገባ ተደርጎ የነበረ ሲሆን በዛሬው ችሎት ላይ ግን ማንም ድርሽ እንዲል አልተፈቀደለትም፡፡ የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ አቶ አመሃ መኮንን ጉዳዩ በዝግ ችሎት እንዲታይ አለመወሰኑን ገልጸው የችሎት አዳራሾቹ እጅግ ጠባብ መሆን እና የፖሊስ ፈቃደኛ ሆኖ አለመገኘት ምክንያት እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡


ፖሊስ በድጋሚ ቀጠሮ በሚጠይቅበት ወቅት በደፈናው ‘በርካታ ሥራዎችን ሰርተናል፤ የሚቀሩን ነገሮች አሉ…’ ቢልም ዳኛዋ ግን ተሰርተዋል የተባሉት ነገሮች እና አላጠናቀቅናቸውም የሚሏቸውን ነገሮች በዝርዝር እንዲያቀርቡ ጠበቅ ያለ ማሳሰቢያ ስለሰጡ ፖሊስ ምላሽ ለመስጠት መገደዱን የተናገሩት አቶ አመሃ፤ ‘ምስክሮች ይቀሩናል፣ ተባባሪዎች ወደ ክልል ስለሸሹ እነሱን የሚያመጣ የፖሊስ ኃይል ልከናል፣ ሰነድ ማስተርጎሙም አላለቀልንም…’ የሚሉትን በየቀጠሮው የሚያቀርቧቸውን ምክንያቶች አሁንም እንዳቀረቡ ተናግረዋል፡፡


ጠበቆች በፖሊስ ምላሽ ላይ አስተያየት እንዳላቸው ተጠይቀው “ልጆቹ ከታሰሩ 50ኛ ቀናቸው ነው፡፡ የፈለገውን ያህል የተወሳሰበ ወንጀል ቢሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ማውጣት ይቻል ነበር፡፡ ነገሮች የሚያሳዩት ግን ፖሊስ እነዚህ ሰዎች ማስረጃ ሳይሰበስብ የያዛቸው መሆኑን ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሀገሪቱን ሕግ የጣሰ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ የተጨማሪ ቀጠሮ ጥያቄውን እንዳይቀበለው ጠይቀናል ያሉት አቶ አመሃ በሁለተኛ ደረጃ የሰነድ ማስተርጎም በፖሊስና በተርጓሚው መሃከል የሚካሄድ ነው ተጠርጣሪዎቹን በእስር ለማቆየት የሚያበቃ አይደለም፤ የቴክኒክ ምርመራ የሚባለውም ቢሆን እዚያው ፌደራል ፖሊስ የሚካሄድ በመሆኑ ልጆቹ በዋስ እንዲለቀቁ፤ ይኽ ካልሆነ ግን ፖሊስ ቀጠሮ የጠየቀበት ሕጋዊ ምክንያት አለው እንኳን ከተባለ የመጨረሻ ቀጠሮ እንዲሆን ፍርድ ቤቱን መጠየቃቸውን ገልጸዋል፡፡


ፍርድ ቤቱ በሚቻል መንገድ ፖሊስን ጫን ብሎ መጠየቁን የሚናገሩት አቶ አመሃ መኮንን ፖሊስ በየጊዜው የሚቀርባቸው አራት ምክንያቶች ‘ተባባሪ አልያዝንም፣ ምስክሮች አልተቀበልንም፣ የሰነዶች ትርጉም አልመጣልንም እና ከባንክ ለሽበርተኝነት ተግባር እንዲሆን ስለመጣላቸው ገንዘብ የሚገልጽ ሰነድ አልመጣልንም ’የሚሉት ምክንያቶች ከዚህ በኋላ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ሆነው መቅረብ እንደማይችሉ ዳኛዋ በመዝገብ ላይ ማስፈራቸውንም ገልጸዋል፡፡


ፖሊስ ሌላ ቀጠሮ ለማራዘም የሚያስችል ምክንያት ካለው ማቅረብ የሚችል ሲሆን ከዚህ ቀደም ያቀርባቸው የነበሩት ምክንያቶች ከዚህ በኋላ ተቀባይነት አይኖራቸውም ቢባልም ፍርድ ቤቱ የሐምሌ 5ቱ ቀጠሮ የመጨረሻው ነው ብሎ እንዳልደመደመ አቶ አመሃ አስረድተዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ፈቅዶ እያለ ፖሊስ ጠያቂ እንዳያገኘን ከልክሎናል ብለው ቅሬታቸውን ያሰሙ ሲሆን ፖሊስ በሰጠው ምላሽ ጠያቂ እንዳልተከለከለ ገልጾ ከቢሮ የአስተዳደር ችግሮች አንጻር ሁሌ ላይሳካ ይችላል ሲል መልሷል፡፡


 ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ ለረዥም ጊዜ የሚያሰቃየው የጀርባ ህመም እያስቸገረው በመሆኑ ወንበር እንዲገባለት ጠይቆ ይህ እንዳልተፈጸመለት ተናግሯል፡፡ በእለቱ የአስማማውን ጉዳይ የያዙት መርማሪ በመገኘታቸው ‘አስማማው ቢጠይቀኝ አደርጋለሁ’ ሲሉ መልሰዋል፡፡ ይኽ የጤና ጉዳይ በመሆኑ ለድርድር የማይቀርብ በመሆኑ የሚጠይቁት ነገር አቅም በፈቀደ መጠን እንዲሟላ ዳኛዋ ማዘዛቸውንም ጠበቃ አመሃ ተናግረዋል፡፡

JUDGE TELLS POLICE TO BRING CHARGES AGAINST ETHIOPIAN BLOGGERS, JOURNALISTS

bloggers1
A judge at the Arada First Instance Court, First Bench, told the police this morning to finalize its investigations and bring charges against three independent journalists and three members of the blog Zone9 detained without charges since 25th and 26th of April this year.
Defense lawyer Amha Mekonnen told journalists at the scene of the court that the judge has told the police to finalize their investigations and bring charges during the next appearance, which is adjourned for Sunday July 13th.  
An earlier indictment filed by the police accuses the detainees of accepting money and working with foreign organizations and rights activists and using social media to destabilize the country and that it requested the court for more days to establish evidence supporting its claim.
However, the police have not yet been able to present sufficient evidence but kept on asking for more days claiming the investigation has taken a complex nature. In three different appearances so far, the police have claimed that they needed more time to finalize translating documents written in English into Amharic, looking into bank transfer details, and interviewing collaborators. Today, the police have said they haven’t finished looking into bank transfer details; they have also said although the police have interviewed some witnesses, many of the collaborators of the detainees that they wanted to interrogate have gone into hiding in the countryside.
In today’s court appearance, however, the judge told the police that she wanted them to finalize enough evidence and in all the allegations the police have made so far during the next court appearance, according to defense lawyer Amha.
On May 17th the police have said that all the detainees were to be charged with the country’s infamous anti-terrorism proclamation 652/2009. The proclamation grants the police to request 28 days during each court appearance for four times until charges are brought against detainees. Ethiopia’s anti-terrorism proclamation is widely criticized for being indiscriminately broad and open for interpretation.
This morning the police have brought Journalist Tesfalem Wadyes, a freelance journalist who was writing for the weekly English Fortune and the monthly Addis Standard, journalist Asmamaw Hailegiorgis, senior editor at an influential Amharic weekly magazine Addis Guday, and journalisEdom Kassaye, who previously worked at state daily Addis Zemen Newspaper and an active member of the Ethiopian Environmental Journalists Association (EEJA) and a close associate of Zone9 bloggers; as well as three members of the blog Zone9 Atnaf Berhane IT professional, Natnail Feleke from the Construction and Business Bank, and Zelalem Kibret, from Ambo University.
The case for the other three members of the blog Zone9: Mahlet Fantahun, Data expert, Befekadu Hailu from St. Mary’s University College, Abel Wabella, an employee of Ethiopian Airlines. They case is adjourned for June 28th.
The hearings are still being conducted behind closed doors and there is a large presence of armed police officers who are tightly guarding hundreds of fans who continue to show up to expresses their solidarity with the detainees.
With our e-mail alerts, you will get everything from breaking news about Ethiopia to the days most popular videos, drama, health tips and stories sent straight to your inbox.

fredag 13. juni 2014

የኢህአዴግን የልማት ስኬት እንዲመሰክሩ የተጠሩ ሰዎች ያልተጠበቁ ችግሮችን አነሱ

በመጪው ምርጫ ለአሸናፊነት ያበቃኛል በማለት ኢህአዴግ በተለያዩ አካባቢዎች  የተመረጡ ሰዎች በአምስት አመታት ውስጥ ስለተሰሩ ስራዎች  እንዲመሰክሩ በማድረግ ላይ ቢሆንም፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ያልተጠበቁ አስተያየቶችን እያስተናገደ ነው።
በደብረብርሃን ሰሞኑን ተካሂዶ በነበረው ውይይት ህዝቡ የተለያዩ የማህበራዊ አግልግሎት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን አንስቷል። ርዕሰ መምህር ከፈለኝ ዘውዴ እንደተናገሩት በከተማዋ ውስጥ ከ15 ሺ ያላነሱ ነዋሪዎች ለ7 ዓመታት መብራት ሳያገኙ መቆየታቸውን ተናግረዋል።
አቶ አባይነህ የተባሉ ነዋሪም እንዲሁ በከተማው ውስጥ የሚታየውን የመብራት እና የስልክ አገልግሎት ችግሮችን አንስተዋል ተስፋየ ዘነበ የተባለ ነዋሪ ደግሞ የከተማው ወጣት በልማቱ ተጠቃሚ አለመሆኑን ገልጿል ወርቁ ገብረኪዳን የተባለ ሰው ደግሞ የጨለማው ሰፈር በሚባል ቦታ እንደሚኖሩ ገልጸው መብራት ካጡ 8 ዓመታት መቆጠሩን ተናግረዋል።
አቶ ወርቁ በከተማቸው የሚታየውን የኑሮ ውድነት አንስተው  መልካም አስተዳደር አለ ብሎ ለመናገር አይቻልም ብለዋል በህዝቡ አስተያየት የተደናገጡት የኢህአዴግ ሹሞች ለደጋፊዎቻቸው ድል ያለ ግብዣ ሲያዘጋጁ ነቀፌታ ሲያሰሙ የዋሉትን ከግብዣው አግልለዋቸዋል።
ኢህአዴግ ምርጫ 2007ትን አስታኮ የህዝብ ድጋፍ ያስገኛሉ የሚላቸውን እርምጃዎች ሁሉ እየወሰደ ነው።

የቅድመ ውህደት ስምምነቱ የቅንጅትን ህዝባዊ መንፈስ ይመልሳል ሲል አንድነት አስታወቀ

ፓርቲው ” ውህደታችንን በማጠናከር  የቅንጅትን ህዝባዊ መንፈስ ዳግም እንመልሳለን በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ሁለቱ ፓርቲዎች “ከጥልቅ ውይይት በኋላ ወቅታዊው የፖለቲካ ሁኔታ የሚፈልገውን በመገንዘብ፤ የህዝቡን ጥያቄ መመለስ የሚችል የተባበረ የፖለቲካ ሃይል ለመፍጠርና የቅንጅትን ህዝባዊ መንፈስ ለመመለስ የሚያስችላቸው ደረጃ ላይ ” ደርሰዋል ብሎአል።
ሁለቱ ፓርቲዎች ሰኔ 1 ቀን ለበርካታ ወራት በጋራ ሲሰሩበት የነበረውን የውህደት ስምምነት ከጫፍ በማድረስ የቅድመ ውህደት ስምምነት መፈረማቸውን ያወሳው ፓርቲው፣  ህዝቡ በስምምነቱ ቢደሰትም  የስርአቱ ደጋፊዎች ውህደቱ እንዳይሳካ ሙከራ አድረገው እንደከሸፈባቸው አትቷል።
ፓርቲው ውህደቱን ለመፈጸም ቀሪ ስራዎች እንዳሉ ቢገልጽም፣ ውህደቱ ተፈጻሚ እንደሚሆን ያለውን እምነት ገልጿል። ሌሎች ፓርቲዎችም ተመሳሳይ ውህደት በመፈጸም የቅንጅትን መንፈስ እንዲያድሱ ጥሪ አቅርቧል።