lørdag 31. august 2013

አሁን በደረሰኝ መረጃ የሠማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ፖሊስ በገፍ በመኪና ጭኖ እያሰረ ነው፡፡


መንግስት የሚደገፈው የሐማኖቶች ጉባኤ  በመጪው እሁድ አክራሪነት እናወግዛለን በሚል አላማ በጠራው ሰልፍ ላይ የአዲስ አበባ እና እስከ 100 ኪሎሜትር በሚደርስ ርቅት ላይ  በአጎራባች የክልል ከተሞች የሚገኙ ዜጎች በብዛት እንዲገኙ የኢህአዴግ ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ሰንብተዋል።  የመንግስት ሰራተኞች ፣ በግል ስራ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች በሰልፉ ላይ እንዲገኙ ካልተገኙ ግን አክራሪነትን እንደደገፉ እንደሚቆጠርባቸው ሲነገራቸው መሰንበቱን ወኪሎቻችንን ዘግበዋል።
መንግስት ለፖለቲካ ትርፍ ብሎ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ፣ መንግስትም ራሱ ያልጠበቀውን ነገር ይዞበት ሊመጣ እንደሚችል ምልክቶች እየታዩ ነው። ድምጻችን ይሰማ የተባለው አካል ከአመት ከመንፈቅ በላይ ያካሄደውን ተቃውሞ ኢህአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ ተገኝቶ ተመሳሳይ ተቃውሞ እንደሚያሰማ መግለጫ ማውጣቱ እሁድ ምን ይፈጠር ይሆን የሚል ጥያቄ አስነስቷል።
ድምጻችን ይሰማ ባወጠው መርሀግብር ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሀይማኖት አባቶች ንግግር ካደረጉ በሁዋላ ነጭ ወረቀት ወይም የጨርቅ ማህረም እንዲያውለበልቡ፣  የመጅሊስ ሹሞች ንግግር ሲያደርጉ ጆሮን በመድፈን፣ ያለምንም ድምጽ ሁለት እጅን ወደ ላይ በማንሳትና በማጠላለፍ የታሰሩት የኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ እንደሚጠይቁ አስታውቀዋል።
ድምጻችን ይሰማ ይህን መርሀግብሩን በተግባር ካዋለ፣ አንድ መንግስት ለድጋፍ በማለት በጠራው ሰልፍ ላይ ተቃውሞ ሲስተናገድበት በታሪክ የመጀመሪያው ይሆናል። ምናልባትም ለኢህአዴግ ታላቅ የፖለቲካ ክስረት ሊያመታበት እንደሚችል አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
ኢህአዴግ ከውርደት ለመዳን የጸጥታ ሀይሎችን በብዛት ከማሰማራት ጀምሮ የክልል ደህንነቶች ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ እያደረገ ነው።
ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰልፍ ሊቀጥል እንደሚችል መታወቁ ሌላ ድራማ ሊፈጥር እንደሚችልም ይጠበቃል።
ሰሞኑን በተደረገው የሀይማኖት ጉባኤ አቶ በረከት ችግሩ ጊዜ የማይሰጥ መሆኑን ሲናገሩ አቶ ሀይለማርያም ደግሞ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል።

ነሐሴ 26 የመንግስት ድጋፍ ያለው የሀይማኖቶች ጉባኤ በአዲስ አበባ የጠራው ሰልፍ ያልተጠበቁ ነገሮችን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል።


በመንግስት የሚደገፈው የሐማኖቶች ጉባኤ  በመጪው እሁድ አክራሪነት እናወግዛለን በሚል አላማ በጠራው ሰልፍ ላይ የአዲስ አበባ እና እስከ 100 ኪሎሜትር በሚደርስ ርቅት ላይ  በአጎራባች የክልል ከተሞች የሚገኙ ዜጎች በብዛት እንዲገኙ የኢህአዴግ ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ሰንብተዋል።  የመንግስት ሰራተኞች ፣ በግል ስራ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች በሰልፉ ላይ እንዲገኙ ካልተገኙ ግን አክራሪነትን እንደደገፉ እንደሚቆጠርባቸው ሲነገራቸው መሰንበቱን ወኪሎቻችንን ዘግበዋል።
መንግስት ለፖለቲካ ትርፍ ብሎ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ፣ መንግስትም ራሱ ያልጠበቀውን ነገር ይዞበት ሊመጣ እንደሚችል ምልክቶች እየታዩ ነው። ድምጻችን ይሰማ የተባለው አካል ከአመት ከመንፈቅ በላይ ያካሄደውን ተቃውሞ ኢህአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ ተገኝቶ ተመሳሳይ ተቃውሞ እንደሚያሰማ መግለጫ ማውጣቱ እሁድ ምን ይፈጠር ይሆን የሚል ጥያቄ አስነስቷል።
ድምጻችን ይሰማ ባወጠው መርሀግብር ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሀይማኖት አባቶች ንግግር ካደረጉ በሁዋላ ነጭ ወረቀት ወይም የጨርቅ ማህረም እንዲያውለበልቡ፣  የመጅሊስ ሹሞች ንግግር ሲያደርጉ ጆሮን በመድፈን፣ ያለምንም ድምጽ ሁለት እጅን ወደ ላይ በማንሳትና በማጠላለፍ የታሰሩት የኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ እንደሚጠይቁ አስታውቀዋል።
ድምጻችን ይሰማ ይህን መርሀግብሩን በተግባር ካዋለ፣ አንድ መንግስት ለድጋፍ በማለት በጠራው ሰልፍ ላይ ተቃውሞ ሲስተናገድበት በታሪክ የመጀመሪያው ይሆናል። ምናልባትም ለኢህአዴግ ታላቅ የፖለቲካ ክስረት ሊያመታበት እንደሚችል አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
ኢህአዴግ ከውርደት ለመዳን የጸጥታ ሀይሎችን በብዛት ከማሰማራት ጀምሮ የክልል ደህንነቶች ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ እያደረገ ነው።
ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰልፍ ሊቀጥል እንደሚችል መታወቁ ሌላ ድራማ ሊፈጥር እንደሚችልም ይጠበቃል።
ሰሞኑን በተደረገው የሀይማኖት ጉባኤ አቶ በረከት ችግሩ ጊዜ የማይሰጥ መሆኑን ሲናገሩ አቶ ሀይለማርያም ደግሞ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል።

fredag 30. august 2013

ወታደራዊ ትጥቅማ ምረቻ ፋብሪካ በቃጠሎ ጉዳት ደረሰበት


ዛሬ በተነሳ የእሳት አደጋ ቃጠሎ በመከላከያ ሚኒስትር የትጥቅና ወታደራዊ ልብስ ስፌት ፋብሪካ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የአይን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ፡፡
ከአዳማ ከተማ ወደ ወንጂ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው ወታደራዊ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ በፋብሪካው ላይ ከፍተኛ የንብረት ጉዳት መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በ18 ሚሊዮን ብር ወጪ በቅርቡ የተገነባው ፋብሪካው የተለያዩ ወታደራዊ ዩኒፎርሞችን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ ሲሆን የደረሰው አደጋ መንስኤ ሊታወቅ አልቻለም፡፡
በፋብሪካው ላይ የደረሰውን ቃጠሎ ለማጥፋት ከአዳማ ከተማ የእሳት ማጥፊያ ባለመኖሩ ደብረ ዘይት ከሚገኘው አየር ሀይል እሳት ማጥፊያ እስከሚደርስ ድረስ የተነሳውን እሳት ማጥፋት አለመቻሉን የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡
ለአንድ ሰዓት ያህል በቆየው የእሳት አደጋ ግምታቸው ከፍተኛ የሆነ ማሽኖች ላይ ጉዳት እንደደረሰ የታወቀ ሲሆን ከአራት ቀናት በፊት መንግስት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የገዛቸው ማሽኖች በፋብሪካው ገብተው እንደነበረ ታውቋል፡፡

torsdag 29. august 2013

የአዲስ አበባ መስተዳድር ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ ሰልፍ የሚያደርግ ከሆነ፤ሰልፉ ህገወጥ ነው አለ።

ሰንደቅ እንደዘገበው በመጪው እሁድ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በማወዛገብ ላይ ነው።
ቀደም ሲል ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ ሰልፍ እንደሚያካሂድ ቢያስታውቅም፤ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት በበኩሉ ነሐሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ በተመሳሳይ ቀን ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ይፋ አድርጓል።
ይህንን ተከትሎ በፓርቲው እና የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ  “የቀደምኩት እኔ ነኝ” በማለት በመወዛገብ ላይ ሲሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ማሳወቂያ ጽ/ቤት በበኩሉ፤ ሰልፍ እንደሚካሄድ ቀድመው ያሳወቁት የሃይማኖት ተቋማቱ በመሆኑ በዕለቱ የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ የሚካሄድ ከሆነ ህገወጥ ነው ብሏል።
ስለጉዳዩ ተጠየቁት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ፤ ፓርቲው ከወር በፊት ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያካሂድ በጽ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ማድረጉን በማስታወስ፤ ፓርቲያቸው ሰላማዊ ሰልፉን ለማካሄድ በቅድሚያ ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረዋል።
እንደ ሊቀመንበሩ ገለፃ ፓርቲው አስቀድሞ ቀን መቁረጡንና በተባለውም ቀን ሰልፉን ለማካሄድ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍ፣ ስብሰባና የማኀበራት ፈቃድ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ጭምር የማሳወቂያ ደብዳቤ ማስገባቱን ተናግረዋል።
በወቅቱ ጽ/ቤቱ ደብዳቤውን ለመቀበል ፍላጎት ባያሳይም በህጉ መሠረት ማሳወቅ ብቻ በቂ በመሆኑ ደብዳቤውን በጽ/ቤቱ አስቀምጠው መመለሳቸውንና በኋላም ጽ/ቤቱ በፖስታ ቤት በኩል በሬኮማንዴ ለፓርቲው ሰልፍ የት እንደሚያካሂድ፣ ምን ያህል ሰው እንደሚሳተፍ ማብራሪያ በመጠየቁ ፓርቲው በበኩሉ ለጽ/ቤቱ ወዲያውኑ ምላሽ መስጠቱን ተናግረዋል።
ሆኖም ጽ/ቤቱ በህጉ መሠረት በ48 ሰዓታት ውስጥ ምላሽ መስጠት ሲገባው ዝምታን በመምረጡ፣ ዝምታው ደግሞ ሰልፉ እንደተፈቀደ የሚጠቁም በመሆኑ በሰልፉ ዙሪያ ፓርቲው ዝግጅት ማድረግ መቀጠሉን አስታውቀዋል።
ከጽ/ቤቱ እስካሁን  ደረስ ምላሽ ባለመገኘቱም ፓርቲው በዕለቱ የጠራውን ሰለማዊ ሰልፍ ከማካሄድ ወደኋላ የሚመልሰው የህግ መሠረት ባለመኖሩ ሰልፉን እንደሚያካሂድ አስታውቀዋል።
ፓርቲው ከነገ ሐሙስ ጀምሮ በአምስት ተሽከርካሪዎች በአስሩም ክፍለ ከተማ መጠነ ሰፊ ቅስቀሳ ለማካሄድ መዘጋጀቱን የተናገሩት ሊቀመንበሩ፤ በመላ ከተማዋና በአካባቢዋም በመቶ ሺህ የሚቆጠር ወረቀት እንደሚበተንና ሰልፉም ካለፈው ሰልፍ ልምድ በማግኘት ከፍተኛ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሰኞ ነሐሴ 20 ቀን 2005 በዋና ጽ/ቤቱ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ያስታወቀው የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ ሰብሳቢ ርዕሰ ደብር በሪሁን አርአያ ፤ በዕለቱ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን እንደማያውቁና ጽ/ቤታቸውም ቀደም ብሎ ለሰልፉ ሲዘጋጅ መቆየቱን ተናግረዋል።
ርዕሰ ደብር በሪሁን አርአያ የሃይማኖት ጽ/ቤቱ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ያሳወቀበትን ቀን ለመናገር አልፈለጉም።
ከዚህም በላይ ሰንደቅ እንዳለው፤ የርዕሰ ደብር በሪሁን  መግለጫ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት ሰልፉን ለማካሄድ ጥያቄ ያቀረበው ከነሐሴ 15 እና 16 በኋላ መሆኑን  የሚያመለክት ነው። በአንፃሩ ሰማያዊ ፓርቲ የማሳወቂያ ደብዳቤ፡ያስገባው ግን  ነሐሴ 16 ቀን 2005 ዓ/ም ነው።
ሀቁ ይህ ቢሆንም፤የአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማርቆስ ብዙነህ፦” የእውቅና ጥያቄ በማቅረብ ቀዳሚ የነበሩት የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት በመሆናቸው ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ ሰልፍ እንዲያካሂድ አልተፈቀደለትም” ብለዋል።
አክለውም፦”ፓርቲው ሰልፍ የሚያካሄድ ከሆነም ህገወጥ ነው” ብለዋል።
ሁለቱም ወገኖች የሰላማዊ ሰልፍ  ለማድረግ ስላሳወቁበትን ቀን እና ስለ ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ግን ከመናገር ተቆጥበዋል።

በሀይማኖት ጉዳይ የመጣው ችግር ጊዜ የሚሰጥ አልሆነም ሲሉ አቶ በረከት ተናገሩ

የጠቅላይ ሚ/ሩ አማካሪ አቶ በረከት ስምኦን ይህን የተናገሩት በመካሄድ ላይ ባለው የሀይማኖቶች ጉባኤ ላይ ነው።
በጉባኤው ላይ የተገኙት አንዳንድ የሀይማኖት አባቶች መንግስት “ትእግስቱን አብዝቶታል፣ እርምጃ ይውሰድልን” እያሉ መጠየቃቸውን ተከትሎ፣ አቶ በረከት ” መንግስት ሀይሉ እንዳለውና መታገሱ ጠቃሚ መሆኑን” ተናግረዋል።  “ይሁን እንጅ” ይላሉ አቶ በረከት “የተፈጠረው ችግር ጊዜ የሚሰጥ አልሆነም”።
አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ትናንት ባደረጉት ንግግር መንግስት እየወሰደ ያለውን የሀይል እርምጃ እንደሚቀጥል ተናግረው ነበር። በተለይም በአገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች አክራሪነትንና ሽብረተኝነትን መደገፋቸውን ካላቆሙ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አቶ ሀይለማርያም ገልጸዋል።
በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የሚገኘው መንግስት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻውን ከልማት ወደ ሀይማኖት ማዞሩን ዘጋቢያችን ገልጿል።

onsdag 28. august 2013

በመጪው እሁድ በአዲስ አበባ ሰማያዊ ፓርቲ እና ኢህአዴግ በየፊናቸው ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ተከትሎ አዝማሚያው ወደ ውጥረት እያመራ መሆኑን ታዛቢዎች ገለጹ።

ሰማያዊ ፓርቲ ቀደም ካሉት ጊዜያት ጀምሮ ለነሐሴ 26 ቀን 2013 ዓመተምህረት ሰልፍ እንደሚጠራ አስታውቆ የቅስቀሳ ሥራ መሥራት በጀመረበት ጊዜ፤ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ሰሞኑን  በዚያው ቀን ሰልፍ ለማድረግ ጥሪ ማቅረቡ ያታወቃል።
በተለይ በኢህአዴግ የሰልፍ ጥሪ  የሴትና ወጣት ማህበራት፣የመንግስት ሠራተኞች፣ የሀይማኖት ተቋማትና  ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጭምር በግዳጅ እንዲወጡ መታዘዛቸው፤ ሁኔታውን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ይወስደዋል ተብሎ ይጠበቃል።
ሰማያዊ ፓርቲ፤የ አፍሪካ መሪዎች አዲስ አበባ ላይ በተሰበሰቡበት ወቅት ሰልፍ ለማድረግ  ወስኖ ሳለ፤  የአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ ክፍል ፤ወቅቱ የመሪዎች ስብሰባ ከመሆኑ አንፃር በዕለቱ በቂ ሀይል እንደሌለውና ሰልፉን ለሳምንት እንዲያሸጋግሩ በጠየቀው መሰረት፤ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፉን ማሸጋገሩ ይታወሳል።
ይሁንና ያን ውሳኔ ያሳለፈው የመስተዳድሩ የሰልፍ ፈቃድ ክፍል ፤ ኢህአዴግ-ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ሊያደርግ ባቀደበት ተመሣሳይ ቀንና ከተማ ውስጥ ሰልፍ ለማድግ ሢነሳ ምንም አለማለቱ ታዛቢዎችን አስገርሟል።
ኢህአዴግ-የሸህ ኑሩን ሞት ተከትሎ በሌሎች ክልሎች እንዳደረገው ሁሉ በአዲስ አበባ ሊያደርገው በተዘጋጀው ሰልፍም የሙስሊሞችን የመብት ይከበር እንቅስቃሴ ከሽብርተኝነትና ከጽንፈኝነት ጋር በማያያዝ በሰልፈኛው ለማስወገዝ መዘጋጀቱ ታውቋል።
ከዚህም ሌላ የገዥው ፓርቲ ተቃዋሚዎች ሰልፍ በሚወጡበት ዕለት -ኢህአዴግ የከተማዋን ነዋሪዎች በግዳጅ “እኔን ደግፋችሁ ውጡ”ማለቱ፤ በህብረተሰቡ ዘንድ አላስፈላጊ መቃቃርን፣ መወጋገዝንና መለያዬትን  ለመፍጠር በማሰብ  ጭምር ነው የሚሉ አስተያየቶችም እየተሰነዘሩ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ  መንግስት  የጠራውን ሰልፍ እንዲሰረዝ ሰማያዊ ፓርቲ ጠየቀ።
ፓርቲው፦”መንግሥት ለተፈጠረው ችግር በአስቸኳይ ማስተካከያ እንዲያደርግ እንጠይቃለን!!”በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ፤ ሰማያዊ  ፓርቲ ግንቦት 25/2ዐዐ5 ዓ/ም. ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ማድረጉን አስታውሶ፦” መንግሥት ላቀረብናቸው ጥያቄዎች በሦስት ወር ውስጥ መልስ የማይሠጥ ከሆነ በተጠናከረና በተደራጀ መልኩ ጥያቄያችንን በድጋሚ በህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ እንደምናቀርብ በግንቦት 25/2ዐዐ5 ዓ/ም. በተደረገው ሠልፍ ላይ ለህዝብ ቃል በገባነው መሠረት ነሃሴ 26/2ዐዐ5 ዓ/ም. በድጋሚ ሰልፍ ጠርተን አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረግን መሆኑን ለህዝብ በልዩ ልዩ መገናኛ ዘዴዎች ገልፀናል” ብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም ለሰልፉ በሰላም መጠናቀቅ አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግልን አዋጁ በሚጠይቀው መሠረት ለአዲስ አበባ መስተዳድር ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማስታወቂያ ክፍል ጉዳዩን እንዲያውቀው አድርገናል ብሏል-ሰማያዊ ፓርቲ።
ይሁን እንጂ ፓርቲያችን የተቃውሞ ሰልፍ በጠራበት ግዜና ቦታ ላይ በሌላ አካል ሰልፉ መጠራቱን በትናንትናው ዕለት ነሀሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም በመንግሥት ቴሌቪዥን ዜና ሰምተናል ያለው ሰማያዊ ፓርቲ፤ከዚህም በላይ  የመንግሥትን መዋቅር በመጠቀም  ዜጐች በዚህ ሰልፍ ይገኙ ዘንድ  በግድ እንዲፈርሙ እየተደረገ መሆኑን ከአዲስ አበባ ኗሪዎች አረጋግጠናል ሲል አትቷል።
ሰማያዊ ፓርቲ አስፈላጊውን የህግ ቅድመ ሁኔታ አሟልቶ ነሐሴ 26/2ዐዐ5 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ ለህዝብ ያሳወቀና አስፈላጊውን ዝግጅት ያጠናቀቀ በመሆኑም፤ ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በጠራበት ቀንና ሠዓት በሌሎች አካላት የተጠራው ሰልፍ ከመረጃ እጥረት ከሆነ እንዲሠረዝ እንጠይቃለን ሲልም  ኢህአዴግ የጠራውን ሰልፍ እንዲሰርዝ  ጠይቋ ል።
ሰማያዊ ፓርቲ በማያያዝም፦”ይህ ካልሆነ ግን ሰማያዊ ፓርቲ በህጋዊ መብቱ የሚያደርገውን የተቃውሞ ሰልፍ ሆን ብሎ ለመረበሽና አቅጣጫውን ለማስቀየስና በዜጐች መካከል ግጭት ለመፍጠር የታቀደ ስለሆነ ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂ መንግሥት መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብና የሚመለከታቸው አካላት እንዲያውቁት በአፅንዖት እንገልፃለን፡፡” በማለት አሣስቧል።

አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ተቃዋሚዎችን በድጋሜ አስጠነቀቁ

መንግስት ባዘጋጀው በሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ” የአገሪቱ አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአክራሪዎችንና የአሸባሪዎችን እንቅስቃሴዎች ከመደገፍ ካልተቆጠቡ ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት እርምጃ እንወስዳለን” ብለዋል።
ማንኛውም ጸረ ሰላም እንቅስቃሴ በሚያደርጉትም ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የገለጡት አቶ ሐይለማርያም፣ የጥፋት ሀይሎችን ለማምከን የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
አዲሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ ጸረ ሰላም እንቅስቃሴዎች ሊወገዙ እንደሚገባ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት የበላይ ጠባቂ ሼክ ኪያር መሃመድ አማን በበኩላቸው ፣ የመቻቻል ባህሉ ለትውልድ መተላለፍ አለበት ብለዋል።
በጉባኤው ላይ የተለያዩ ባለስልጣናት እና እንግዶች ንግግር አድርገዋል።
መንግስት በቅርቡ በንጹህን ሙስሊሞች ላይ በወሰደው እርምጃ ሊጸጸት ቀርቶ እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና መንግስት የሀይል አማራጭ ብቸኛው መፍትሄ ነው ብሎ እንደሚያምን ከአቶ ሐይለማርያም ንግግር መረዳት መቻሉን ዘጋቢያችን ገልጿል።
በእስር ላይ ከሚገኙት ድምጻችን ይሰማ አመራሮች ጋር ስለመነጋገር ወይም ችግሩን በሰላም ስለመፍታት ከሀይማኖት አባቶችም አለመነሳቱን አውስቷል።
የስብሰባው አላማ መንግስት ስለወሰደውና ስለሚወስደው የሀይል እርምጃ ከሁለቱም የሀይማኖት መሪዎች ድጋፍ ማግኘትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ከዘጋቢያችን ሪፖርት ለመረዳት ይቻላል።

tirsdag 27. august 2013

መንግስት በቫንኩቨር ካናዳ ሊያደርግ የነበረው የቦንድ ሽያጭ ተቃውሞ ገጠመው

በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከአባይ በፊት ዘረኝነት የወገድ በማለት መቃወማቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
የመንግስት ወኪሎች ተቃውሞውን በመፍራት ሊሰበሰቡበት ተከራይተውት የነበረውን አዳራሽ በመተው በሰዎች ቤት ስብሰባውን በግለሰቦች ቤት ለማድረግ ተገደዋል።
በስፍራው ለተገኙት አንዳንድ አረጋውያን ለአባይ ቦንድ የሚገዙ ከሆነ የቤት መስሪያ ቦታ እንደሚሰጠቻው በስበሰባው መሪዎች ተነግሮአቸዋል።
መንግስት በውጭ አገራት የሚያደርገው የቦንድ ሽያጭ ቅስቀሳ በተደጋጋሚ ተቃውሞ ሲያጋጥመው ይታያል።

mandag 26. august 2013

The last of the Falash Mura? A final flight will ostensibly complete the aliya of 7,500 members of a Jewish community


Image

On Wednesday, (26 August 2013 ) a final flight will ostensibly  the aliya of 7,500 members of a Jewish community that had converted to Christianity. Is this really the end of a hugely controversial mass immigration process? Should it be? The Times of Israel reports from EthiopiaGONDAR, Ethiopia – The winter night was crisp and still. It was 5 a.m. The stars, glittering like slices of diamond in the jet-black sky, had not yet given way to the peeping sun. Silhouettes wrapped in gabis, white blanket-like scarves, walked slowly along the side of the road.

“They’re going to church,” Asher Seyum, head of the Jewish Agency in Ethiopia, said about the solitary figures, as he raced to bid farewell to a group of Falash Mura departing for Israel. (Falash Mura is a colloquial, albeit pejorative, term from Ge’ez describing Ethiopian Jews who converted to Christianity in the 19th and 20th centuries largely due to persecution and economic strife but who maintained a distinct communal identity.)

lørdag 24. august 2013

ከአዲስ አበባ ወደ ወልዲያ ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ ተገልብጦ በርካታ ሰዎች ሞቱ

ከአዲስ አበባ ወደ ወልድያ ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ አውቶቡስ ደሴ አካባቢ ሲደርስ በመገልበጡ የ21 ሰዎች ህይወት ጠፋ፣ የዛሬውን ጨምሮ በአንድ ሳምንት ውስጥ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 66 ደርሶአል።
የአደጋው  መንስኤ ጥራት የሌለው የአስፓልት መንገድ በጎርፍ በመቆረጡ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የወልድያ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ለኢሳት እንደገለጸው ደግሞ የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ባሙያዎች ከደሴ በመላካቸው መረጃው ተጣርቶ እስከሚቀርብ ድረስ አስተያየት ለመስጠት አይቻልም ብሎአል።
ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ሾፌሩን ጨምሮ የ3 ሰዎች አስከሬን በጎርፍ በመወሰዱ ለማግኘት አልተቻለም። የተወሰኑ አስከሬኖች ወደ ቀወጃ፣ ቆቦ፣ ወልድያና ሳንቃ ተልከው የቀብር ስነስርአታቸው ተፈጽሟል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአካባቢው የሚጥለው ዝናም የአስፓልት መንገዶችን እየጎመደ ጉዳት ማድረሱን  ነዋሪዎች ይናገራሉ። መንገዶቹ የውሀ ፍሳሽ የሌላቸው በመሆኑ በቀላሉ ለአደጋ እንደሚዳረጉ እነዚሁ ነዋሪዎች ይገልጻሉ።
ከሁለት ቀናት በፊት በአምባሰል ወረዳ አንድ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በጎርፍ በመወሰዷ የ15 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወቃል። በጉዳዩ ዙሪያ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣንን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

fredag 23. august 2013

ሆስኒ ሙባረክ ተፈቱ


የቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከእስር ተፈተው በሄሊኮፕተር ወደ ጦሩ ሆስፒታል ለምርመራ ተወስደዋል፣ ጊዚያዊው መንግስት ከቤታቸው እንደማይወጡ አስታውቋል።
ፕሬዚዳንቱ ከቀረረበባቸው የሙስና ክስ ነጻ በመሆናቸው መፈታታቸው ተገልጿል። ይሁን እንጅ ከሁለት አመት በፊት በግብጽ ከተካሄደው አብዮት ጋር በተያያዘ አሁንም ሌሎች ክሶች ቀርበውባቸዋል።
ደጋፊዎቸቻቸው ደስታቸውን ቢገልጹም፣ የሙስሊም ብራዘርሁድ ደጋፊዎች ደግሞ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
ግብጽ አሁንም በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንደምትገኝ ብዙ የፖለቲከኛ ተንታኞች ይናገራሉ።

በአማራ ክልል በአንድ ሰምንት ጊዜ ውስጥ በጎርፍ ከ45 ሰዎች በላይ ሞቱ


 በአካባቢው በሚጥለው ከባድ ዝናም የተነሳ በክልሉ በሚገኘው ኦሮሚያ ዞን ባለፈው ሳምንት ከ30 ያላነሱ ሰዎች የተገደሉበትን ክስተት ጨምሮ ፣ በደቡብ ወሎ ዞን በአንባሰል ወረዳ አንዲት ሚኒ ባስ በጎርፍ በመወሰዷ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል። በጎርፍ የተወሰዱ ሰዎችን አስከሬን ለማግኘት በተደረገ ጥረት የ14 ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል። የአካባቢውን ፖሊስ አዛዥ ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።
በክልሉ እየጣለ ያለው ሀይለኛ ዝናብ ከፍተኛ ጉዳት እያመጣ መሆኑን ከክልሉ የሚደረሱን ዘገባዎች ያመለክታሉ። በአንዳንድ አካባቢዎች ትራንስፎርመሮች በመቃጠላቸው መብራት ለሳምንታት መቋረጡም ታውቋል።

onsdag 21. august 2013

የተወዳጁ የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኙ የእዮብ መኮንን የቀብር ሥነ-ስርዓት ነገ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከቀኑ 9 ፡00 ሰዓት ላይ ይፈጸማል።

የኢሳት ወኪል ከስፍራው ባደረሰን መረጃ  አስከሬኑ ዛሬ ንጋት ላይ ተኝቶ ሲታከምበት ከነበረው ከናይሮቢ -ወደ አዲስ አበባ ገብቷል።
እዮብ ከሳምንት በፊት ልጁን በብሽክሊሊት ትምህርት ቤት አድርሶ ከተመለሰ በሁዋላ ቤቱ መግቢያ በር ላይ ሲደርስ ድንገት ሰውነቱ አልታዘዝ ብሎት መዝለፍለፉን የገለጸችው ባለቤቱ ቲና፤ከዚያ እንደምንም የበሩን ደወል ተጭኖ መጥሪያ ካሰማ በሁዋላ መቆም አቅቶት በተደገፈው በር ሸርተት እያለ ወደ መሬት ሲወርድ ደርሰውበት መደንገጣቸውንና በአስቸኳይ በቅርብ ወደሚገኘው ሀያት ሆስፒታል እንደወሰዱት ተናግራለች።
የሀያት ሆስፒአል ሐኪሞች እዮብን ለመርዳት የተሻለ ህክምና ያለው በቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል እንደሆነ በነገሯቸው መሰረት በፍጥነት ወደዚያው ቢወስዱትም፤ እዚያም በደም ግፊት ወይም በስትሮክ ክፉኛ የተመታው እዮብ በውጪ አገር የተሻለ ህክምና እንደሚያስፈልገው በተነገራቸው መሰረት  ለህክምና ከተጠየቀው 25ሺህ ዶላር ውስጥ ቅድሚያ 22 ሺህ ዶላር ተከፍሎ በቅርብ ውደሚገኘው ወደናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ ሆስፒታል ወስደውታል።
ይሁንና ለቀናት ራሱን የሳተው የ37 ዓመቱ አርቲስት እዮብ ፤ናይሮቢ ሆስፒታል በገባ በማግስቱ እስከወዲያኛው አሸልቧል።
የኢሳት ወኪል ባደረሰን መረጃ መሰረት የእዮብ አስከሬን ዛሬ ጧት 1፡00 ሰዓት ላይ አዲስ አበባ የገባ ሲሆን፤ የቀብር ስነ-ስርዓቱ ነገ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።
ተወዳጁ አርቲስት እዮብ መኮንን የአንዲት የ13 ዓመት ሴት ልጅ አባት ነበር።
የኢሳት ባልደረቦች ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ፣ ለአድናቂዎቹና በእዮብ ሞት መሪር ሀዘን ለደረሰባቸው ሁሉ መጽናናት ይሆንላቸው ዘንድ ልባዊ ምኞታቸውን በድጋሚ ይገልጻሉ።

በዛሬው ዕለት ታስቦ ከዋለው የመለስ ሙት ዓመት በዓል ጋር በተያያዘ አብዛኛው አገልግሎት ሰጪ የመንግስት መ/ቤቶች ይፋዊ ባልሆነ መንገድ ዝግ ሆነው ዋሉ፡፡



 በዓሉን አስመልክቶም ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ 21 ጊዜ መድፍ ተተኩሶአል፡፡ የአቶ መለስ ሙት ዓመት ጉለሌ በሚገኘው የዕጽዋት ማዕከል የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣የጎረቤት አገር መሪዎች፣ዲፕሎማቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብርዋል፡፡ በተለይ የመንግስት ሠራተኞች በግዳጅ   በመስቀል አደባባይ የሻማ ማብራት ስነስርዓት እንዲያካሂዱ መታዘዛቸው ታውቋል፡፡
ይህን ተከትሎም በርካታ ሠራተኞች ዕለቱን እንደዕረፍት በመቁጠር በስራ ገበታቸው ላይ እንዳልተገኙ፣ የተገኙትም መደበኛ ስራቸውን ማከናወን ሳይችሉ እንደቀሩ የጠቆመው ዘጋቢያችን ኃላፊዎችም በዓሉን እያከበሩ በመሆኑ ስራ የሚከታተል ሀላፊ እንዳልነበርም አክሏል፡፡
በተለይ በአዲስአበባ ማዘጋጃ ቤት በሚገኙ የተለያዩ ቢሮዎች በመንግስት ወጪ ከፍተኛ መጠን ያለው ጧፍ ተገዝቶ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ሠራተኞቹ ተገኝተው የቀድሞ መሪያቸውን ሙት ዓመት እንዲያስታውሱ መመሪያ ተሰጥቶአቸዋል።
የመንግስት ሐብትና የስራ ሰዓት እየባከነ መሆኑ ገዥዎቻችን ልብ አላሉትም የሚለው አንድ አስተያየት ሰጪ  በአሁኑ ወቅት በመለስ ስም የተለያዩ ንብረቶች እየተገዙ እግረመንገድም  በየቢሮው ምዝበራው እየተጧጧፈ መሆኑ አሳዛኝ ነው ብሎአል።
የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎች እና የተለያዩ ህጻናት ሳይቀር በመኪኖች እየተጫኑ ለመለስ ሙት አመት እንዲገኙ መደረጉን  ዘጋቢያችን ከላከው ሪፖርት ለመረዳት ተችሏል።

tirsdag 20. august 2013

ለአቶ መለስ ሙት አመት መታሰቢያ የመንግስት ሰራተኞች በግድ እንዲገኙ ታዘዙ

የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሙት ዓመት በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ጉለሌ ዕጽዋት ማዕከል በልዩ ልዩ
ፕሮግራም ታስቦ እንደሚውል ለማወቅ የታቸለ ሲሆን፣ በዛሬው እለት ደግሞ  የተለያዩ የመንግስት ሰራተኞች ምሽትና ነገ  ሻማ በማብራት እን

fredag 16. august 2013

አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ የሚያዘጋጀው የታላቁ ሩጫ የንግድ ፈቃድ ተሰረዘ


መንግስት ፈቃዱን የቀማው ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ሲንቀሳቀስ ተገኝቷል በሚል ነው። ከታላቁ ሩጫ በተጨማሪ  እስላማዊ የምርምርና የባህል ማዕከል ፣ ጎህ ቻይልድ ዩዝ ውመንስ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ፣ዋን ዩሮ ኢትዮጵያ ፣ ብራይት አፍሪካ ኢንተግሬትድ ዴቨሎፕመንት አሶሲየሽን እና ፓድ ኢትዮጵያ ሊትሬሲ ኢዱኬሽን ኤንድ ቮኬሽናል ሴንተር ናቸው።
የድርጅቶቹን ሃብትና ንብረት በስማቸው በማዞር ሲጠቀሙ ፥ የፋይናንስ ምንጫቸውም ከተፈቀደው በላይ የሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም በሰራተኞቻቸው ላይ አስተዳደራዊ በደሎች የፈፀሙት ድርጅቶች መዘጋታቸውን የመንግስት የመገናኛ ብዙሀን ገልጸዋል። ድርጅቶቹ  በንግድ ስራ መሰማራት ፣ ባልተገባ ሃይማኖታዊ ተግባር መሳተፍ እና የድርጅትን ገንዘብ ለግል ጥቅም ማዋል በሚሉትም ተከሰዋል።
14 የሚሆኑ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችም በአቅም ውስንነት ፣ በፕሮጀክቶቹ መጠናቀቅ እና በሌሎችም ምክንያቶች ተዘግተዋል።

torsdag 15. august 2013

የአቶ መለስ መሞት ወደ ውጭ በወጣው 11 ቢሊዮን ዶላር ምርመራ ላይ ተጽኖ መፍጠሩ ተገለጸ

ከኢትዩጵያ በህገ ወጥ የተሻገረውን 11 ቢሊዩን ዶላር ለማስመለስ እና የባለስልጣናትን የሀብት መጠን ይፋ ለማድረግ የተያዘው ቀጠሮ በመለስ ሞት ምክንያት ዳር ሳይደርስ መቅረቱን የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኪሚሺን ኪሚሺነር አቶ ዓሊ ሱሊማን ተናገሩ፡፡
አቶ አሊ በጠቅላይ ሚኒስተር መልስ ዜናዊ የስራ ትጋት እና አርቆ  አሳቢነት ምስክርነት

የኬንያ ልዩ ተጠባባቂ ሀይል ከኢትዮጵያ ሰርገው በገቡ ታጣቂ ሀይሎች ላይ ዛሬ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ይፋ አደረገ

በቅርቡ ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ የገቡ ታጣቂ ሀይሎች አራት የኬንያ ተጠባባቂ ፓሊሶችንና ስድስት አሳ አጥማጆችን በመግደላቸው በሁለቱ ድንበር አካባቢ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል፡፡

tirsdag 13. august 2013

በአማራ ክልል የመልካም አስተዳደር ችግር ስር የሰደደ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ተናገሩ

የመልካም አስተዳደር ኮማንድ ፖስት እየተባለ የሚጠራው መስሪያ ቤት በክልሉ ባሉ የአስተዳደር ቢሮዎች ባካሄደው ቅኝት የመልካም  አስተደዳር ችግር በክልሉ ተባብሶ መቀጠሉን ገልጿል፡፡
በተለይም በፍትህ ፤ በፖሊስ ፤ በማረሚያ ቤቶች ፤ በመሬት ፤ኢንቨስትመንት፤ መብራት እና ውሃ ደግሞ የችግሩ መለያ ቦታዎች መሆናቸውን ለክልሉ ካቢኔ የቀረበው ሪፖርት የቅሬታ ምንጭ መሆናቸውን ያወሳል፡፡
በክልሉም ከጊዜ ወደ ጊዜ የቅሬታዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የሚያወሱት የኮማንድ ፖስት መሪው አቶ አምባቸው ከ115 ሺ በላይ ቅሬታዎች በመልካም አስተዳደር ዙሪያ በዚህ አመት ቀርበዋል፡፡እነዚህ ቅሬታዎች እድል አግኝተው ከክልሉ ርዕሰ መዲና ባህርዳር የደረሱ ናቸው፡፡ በመሬት ዙሪያ ደግሞ ከ 46 ሺ የአካባቢ ጥበቃ መስሪያ ቤቶች ከ 60ሺ በላይ ቅሬታዎች ተሰተናግድዋል፡፡
የመናሃሪያና የፍትህ አካላት፤የትራንስፖርት ችግር የህገወጥ መሳሪያዎች ዝውውር መበራከት ባለበት እንደቀጠለ ነው፡፡
ያለው ኮማንድ ፖስት በፌደራል ወይም በማእከላዊ መንግስት የሚተዳደሩ ተቋማት የችግሩ መንስኤ መሆናቸውን የክልሉ ኮሚንኒኬሺን ጉዳይ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ይናገራሉ፡፡
የከልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ በበኩላቸው ባለፈው ስድስት ወራት መልካም አሰተዳደርን ለማስፈን የተደረገው ጥረት ውጤት አልባ ሆኗል ብለዋል፡፡
ከክልሉ ዜና ሳንወጣ በህዳር ወር 2005 ዓ.ም በባህርዳር ከተዘጋጀው 7ኛው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ጋር በተያያዘ የተሠራችው “ህብር” የተሠኘች ጀልባ በቴክኒክ ችግር ምክንያት አገልግሎት መስጠት አለመቻሏ ተገለጸ፡፡
ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ወጥቶባት በእርግብ ቅርጽ የተሰራችው እና እስካሁን ካሉት ጀልባዎች በውስጣዊ ይዘቷ ትለያለች የተባለችው ይህቺው ጀልባ ህዳር 29 በጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ከተመረቀች በኃላ በቴክኒክ ችግር ምክንያት አገልግሎት መስጠት ባለመቻሏ ያለስራ ለመቆም መገደድዋን ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
የጣና ሐይቅ ትራንስፖርት ድርጅት የመከላከያ ንብረት ከሆነው ከብረታብረት ኢንጂነሪንግ ድርጅት እና ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የክልሉ መንግስት በመደበው ገንዘብ የሠራት ህብር የተሰነችው ይህቺ ጀልባ የቴክኒክ ችግሯ መቀረፍ ባለመቻሉ ምክንያት እዚያው በቆመችበት የስብሰባ አዳራሹን ወደሲኒማ ቤት ለመቀየር ሃሳብ መኖሩ ታውቋል፡፡
በዘመነ ደርግ የተሰራችው ንጋት በመባል የምትታወቀው ጀልባ በሆላንድ ባለሙያዎች ጭምር አሰራርዋ አድናቆት ያገኘና እስካሁንም አገልግሎት እየሰጠች ነው፡፡

ኦህዴድ ኢሳትን ለማስቆም እንደሚሰራ አስታወቀ

ሰሞኑን የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በነቀምት ባደረጉት ስብሰባ ህዝቡ ኢሳትን እንዳይመለከት ካድሬዎች ከፍተኛ ስራ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
አመራሮቹ ኢሳት የአሸባሪ ድርጅቶች ንብረት በመሆኑ፣ ህብረተሰቡ ኢሳትን መመልከቱን እንዲያቆም ባለስልጣኖቹ ወትውተዋል።
በስብሰባው ወቅት ለካድሬዎች ከተነገራቸው ነገር መካከል አንዱ ኢሳትን በሚመለከት ህግ ሊወጣ ነው መባሉ ነው። ምን አይነት ህግ እንደሚወጣ ግን ባለስልጣኖቹ ከማብራራት ተቆጥበዋል።
ኢሳት በናይልሳት የሚያሰራጨው ስርጭቱ በአፈና እንዲቋረጥ ከተደረገ በሁዋላ ላለፉት 7ወራት  በኤስ ኢ ኤስ 5 እና በአሞስ ላይ የቴሌቪዥን ስርጭቱን እንዲሁም በተለያዩ የሬዲዮ ሞገዶች የኢትዮጰን ህዝብ እያገለገለ ይገኛል።

ኦህዴድ ኢሳትን ለማስቆም እንደሚሰራ አስታወቀ

ሰሞኑን የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በነቀምት ባደረጉት ስብሰባ ህዝቡ ኢሳትን እንዳይመለከት ካድሬዎች ከፍተኛ ስራ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
አመራሮቹ ኢሳት የአሸባሪ ድርጅቶች ንብረት በመሆኑ፣ ህብረተሰቡ ኢሳትን መመልከቱን እንዲያቆም ባለስልጣኖቹ ወትውተዋል።
በስብሰባው ወቅት ለካድሬዎች ከተነገራቸው ነገር መካከል አንዱ ኢሳትን በሚመለከት ህግ ሊወጣ ነው መባሉ ነው። ምን አይነት ህግ እንደሚወጣ ግን ባለስልጣኖቹ ከማብራራት ተቆጥበዋል።
ኢሳት በናይልሳት የሚያሰራጨው ስርጭቱ በአፈና እንዲቋረጥ ከተደረገ በሁዋላ ላለፉት 7ወራት  በኤስ ኢ ኤስ 5 እና በአሞስ ላይ የቴሌቪዥን ስርጭቱን እንዲሁም በተለያዩ የሬዲዮ ሞገዶች የኢትዮጰን ህዝብ እያገለገለ ይገኛል።

ኦህዴድ ኢሳትን ለማስቆም እንደሚሰራ አስታወቀ

ሰሞኑን የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በነቀምት ባደረጉት ስብሰባ ህዝቡ ኢሳትን እንዳይመለከት ካድሬዎች ከፍተኛ ስራ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
አመራሮቹ ኢሳት የአሸባሪ ድርጅቶች ንብረት በመሆኑ፣ ህብረተሰቡ ኢሳትን መመልከቱን እንዲያቆም ባለስልጣኖቹ ወትውተዋል።
በስብሰባው ወቅት ለካድሬዎች ከተነገራቸው ነገር መካከል አንዱ ኢሳትን በሚመለከት ህግ ሊወጣ ነው መባሉ ነው። ምን አይነት ህግ እንደሚወጣ ግን ባለስልጣኖቹ ከማብራራት ተቆጥበዋል።
ኢሳት በናይልሳት የሚያሰራጨው ስርጭቱ በአፈና እንዲቋረጥ ከተደረገ በሁዋላ ላለፉት 7ወራት  በኤስ ኢ ኤስ 5 እና በአሞስ ላይ የቴሌቪዥን ስርጭቱን እንዲሁም በተለያዩ የሬዲዮ ሞገዶች የኢትዮጰን ህዝብ እያገለገለ ይገኛል።

ኦህዴድ ኢሳትን ለማስቆም እንደሚሰራ አስታወቀ

ሰሞኑን የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በነቀምት ባደረጉት ስብሰባ ህዝቡ ኢሳትን እንዳይመለከት ካድሬዎች ከፍተኛ ስራ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
አመራሮቹ ኢሳት የአሸባሪ ድርጅቶች ንብረት በመሆኑ፣ ህብረተሰቡ ኢሳትን መመልከቱን እንዲያቆም ባለስልጣኖቹ ወትውተዋል።
በስብሰባው ወቅት ለካድሬዎች ከተነገራቸው ነገር መካከል አንዱ ኢሳትን በሚመለከት ህግ ሊወጣ ነው መባሉ ነው። ምን አይነት ህግ እንደሚወጣ ግን ባለስልጣኖቹ ከማብራራት ተቆጥበዋል።
ኢሳት በናይልሳት የሚያሰራጨው ስርጭቱ በአፈና እንዲቋረጥ ከተደረገ በሁዋላ ላለፉት 7ወራት  በኤስ ኢ ኤስ 5 እና በአሞስ ላይ የቴሌቪዥን ስርጭቱን እንዲሁም በተለያዩ የሬዲዮ ሞገዶች የኢትዮጰን ህዝብ እያገለገለ ይገኛል።

ኦህዴድ ኢሳትን ለማስቆም እንደሚሰራ አስታወቀ

ሰሞኑን የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በነቀምት ባደረጉት ስብሰባ ህዝቡ ኢሳትን እንዳይመለከት ካድሬዎች ከፍተኛ ስራ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
አመራሮቹ ኢሳት የአሸባሪ ድርጅቶች ንብረት በመሆኑ፣ ህብረተሰቡ ኢሳትን መመልከቱን እንዲያቆም ባለስልጣኖቹ ወትውተዋል።
በስብሰባው ወቅት ለካድሬዎች ከተነገራቸው ነገር መካከል አንዱ ኢሳትን በሚመለከት ህግ ሊወጣ ነው መባሉ ነው። ምን አይነት ህግ እንደሚወጣ ግን ባለስልጣኖቹ ከማብራራት ተቆጥበዋል።
ኢሳት በናይልሳት የሚያሰራጨው ስርጭቱ በአፈና እንዲቋረጥ ከተደረገ በሁዋላ ላለፉት 7ወራት  በኤስ ኢ ኤስ 5 እና በአሞስ ላይ የቴሌቪዥን ስርጭቱን እንዲሁም በተለያዩ የሬዲዮ ሞገዶች የኢትዮጰን ህዝብ እያገለገለ ይገኛል።

fredag 9. august 2013

Journalist, educator Reeyot Alemu writes from prison cell


Ethiopian journalist and educator, Reeyot Alemu, who is serving a five year sentence on alleged terrorism charges, has sent a letter from Kaliti Prison.
In her letter, Reeyot asked the public to continue opposing the anti-terrorism laws which she said is being “unfairly used by the ruling party to prolong its stay on power”.  She said the ongoing protests and other peaceful opposition activities should continue. Reeyot urged that the protests should mainly be against the ruling EPRDF government, which she says is the “source” of the countless issues of national concern and problems of Ethiopia.

“We have witnessed that the ruling EPRDF can do anything as long as it assumes it can elongate its grip on power. And the causes of all these acts of the ruling party are racism, lust for power and corruption.” She said.

She stressed that sacrifices should be made by using all methods of modern and peaceful struggle to change the current system.  Reeyot said, when we think of changing the system, we should also deeply think about the ethnic, religious, political ideology and opportunistic divisions that the incumbent has created.

Reeyot advised that fragmented oppositions and protests should be united and all responsible citizens particularly opposition parties should also critically think and discuss about the post EPRDF Ethiopia.

Reeyot won the 2012 International Women’s Media Foundation Courage Award. She was arrested in June 2011 and was indicted of involvement in “a terrorism plot”. Her sentence has been reduced from 14-year prison sentence to five years in January of last year.

torsdag 8. august 2013

Ethiopian repression of Muslim protests must stop | Amnesty International

Ethiopian repression of Muslim protests must stop | Amnesty International

በአዲስአበባ የኢታኖል ድብልቅ ቤንዚን ዋጋ ጨመረ

በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ ባልጨመረበት ሁኔታ በአዲስ አበባ ብቻ የኢታኖል ቤንዚን ድብልቅ ነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በ0.16 ሳንቲም ከፍ በማለት በሊትር 18 ብር ከ94 ሳንቲም እንዲሸጥ የንግድ ሚኒስቴር መወሰኑን አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ እንዳመለከተው የዓለም የነዳጅ ዋጋ የመዋዥቅ ሁኔታ ማሳየቱን ተከትሎ ጭማሪ ለማድረግ መገደዱን ይግለጽ እንጂ በዓለም ገበያ በዚህ ወቅት ነዳጅ ዋጋ የተለየ ጭማሪ አለማሳየቱን የዜና ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡
በዚሁ መሠረትም በአዲስ አበባ የኢታኖል ቤንዚል ድብልቅ ነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሊትር ትላንትና ይሸጥበት ከነበረበት ብር 18 ብር 78 ሳንቲም ወደ ብር 18 ብር ከ94 ሳንቲም ከፍ እንዲል የተወሰነ ሲሆን የተቀሩት የነዳጅ ምርቶች ማለትም ነጭና ጥቁር ናፍታ፣አብዛኛው ህብረተሰብ ለማገዶ የሚጠቀምበት ኬሮሲን፣ የአውሮፕላን ነዳጅ በሐምሌ ወር በሥራ ላይ የነበረው ዋጋ በያዝነው ነሐሴ ወርም በተመሳሳይ እንዲቀጥል ወስኖአል፡፡
በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ ሁኔታ መነሻ በማድረግ እንደ አስፈላጊነቱ ከነሐሴ ወር በኃላም ማስተካከያ ሊደረግ እንደሚችልም ሚኒስቴሩ ገልጾአል፡፡
ሚኒስቴሩ በየወሩ የሚያደርገው የነዳጅ ዋጋ ክለሳ ተከትሎ የትራንስፖርት ክፍያ በከፍተኛ ሁኔታ እየናረ የመጣ ሲሆን ይህም የተለያዩ ሸቀጦች ዋጋ እንዲንር ምክንያት ሲሆን ቆይቷል፡፡ በአዲስአበባ በአሁኑ ወቅት የአንድ ሲኒ ቡና ዋጋ ከ5-9 ብር የሚሸጥበት ዋናው ምክንያት ከነዳጅ ጭማሪ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ሲሆን የነዳጅ ዋጋ በሚቀንስበት ወቅትም የጨመሩት የሸቀጥ ዋጋዎች ባሉበት መቀጠላቸው የሚታወቅ መሆኑን ዘጋቢያችን ከአዲስአበባ የላከው ዜና ጠቁሟል

የወልድያ ነዋሪዎች አገራችሁንና ባንዲራችሁን አድኑ የሚል ጥሪ ቀረበላቸው

በድምጻችን ይሰማ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን እንቅስቃሴ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የገባው መንግስት ፣ በካድሬዎቹ አማካኝነት ” የአገርህ ባንዲራ ተደፍራለችና ስልፍ ውጣ እያለ” ትናንት ህዝቡን ሲያስፈርም መዋሉን የአይን እማኞች ገልጸዋል። አንዳንድ ካድሬዎች “ጊዮርጊስ አድዋ ድረስ ሄዶ ተዋግቷል፣  አንተም አገር ሊያጠፉ የመጡትን ተነስትህ ተዋጋ”የሚሉ ቅስቀሳዎችን መዋላቸውንም እነዚሁ እማኞች ተናግረዋል።
በእድሜ ለገፉት ደግሞ አሸባሪዎችን ለመቃወም ከወጣችሁ እርዳታ እንሰጣችሁዋላን በማለት በድለላ በዛሬው ሰልፍ ላይ እንዲገኙ አድርገዋል። በሰልፉ ላይም ” ፣ አሸባሪነት እናወግዛለን፣ ተቻችለው የሚኖሩትን ህዝብ የሚነጥሉትን ዋህብያዎችን እናወግዛለን” የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ መንግስት የባንዲራን ክብር ያዋረደውን ግለሰብ ለፍርድ ያቅርብ ሲል ድምጻችን ይሰማ ባወጣው መግለጫ ጠየቀ።
ሐምሌ 19 ቀን 2005 የተደረገው ዓለም አቀፍ ተቃውሞና በአዲስ አበባው ኑር መስጂድ፣ በክልል ከተሞችና በውጪ አገራት የተቀዳጀው ስኬት ያልተዋጠለት መንግስት በዚያው ምሽት በኢትዮጵያ ቴሌቪዠን ባሰራጨው ‹‹ዘገባ›› በእለቱ ተቃውሞ ሙስሊሞች የኢትዮጵያን ባንዲራ እንዳዋረዱ መግለጹን፣  ቴሊቪዥኑ ለተወሰኑ ሰኮንዶች ባቀረበው ቪዲዮ አንድ ግለሰብ ያረጀ እና የተቀዳደደ ባንዲራ ሲያውለበልብ መታየቱን ገልጿል።
ሕገ መንግስታዊ ጥያቄዎችን ያነሳውንና በሰላማዊ መንገድ እየታገለ ያለውን ሙስሊም ህብረተሰብ ማንበርከክ የተሳነው መንግስት ይሄን መሰል ፕሮፖጋንዳ መንዛቱ ከዚህ ቀደም ሲፈጽም የነበረውን ፕሮፖጋንዳ ለተከታተለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፈጽሞ የሚገርም አይደለም ያለው ድምጻችን ይሰማ፣  መንግስት ሰላማዊ ትግሉን ለመፈንቀል እንኳን ሙስሊሞችን በጸረ-አገርነት መፈረጅ ይቅርና ሌላም ሊፈጽም እንደሚችል የሚታወቅ ሃቅ ነው፡ ብሎአል።
እኛ ኢትዮጵያውያን ለአገራችን ያለን ፍቅር ከሌሎች ወገኖች ጋር የተሳሰርንበት ጠንካራ ገመድ በመሆኑ በተራ ፕሮፓጋንዳ ሊጠለሽ የሚችል እንዳልሆነ ግልጽ መሆን አለበት ያለው የሙስሊሙ ኮሚቴ፣  ልክ እንደሌሎች ወንድሞቹ ሁሉ ኢትዮጵያዊው ሙስሊምም ለባንዲራውና ለአገሩ ፍቅር ደሙን አፍስሶ፣ አጥንቱንም ከስክሶ መክፈል ያለበትን መስዋእትነት ሲከፍል የቆየ በመሆኑ ትግላችን እስከህይወት መስጠት የደረሰ መስዋእትነት እየከፈልን የምንገኘውም ለአገራችን ካለን ከፍተኛ ፍቅር በመነሳት ነው ብሎአል።
ኮሚቴው ” ንቅናቄያችን አገራዊ እና ኢትዮጵያዊነትን የተላበሰ መሆኑ ምንም ጥያቄ የለውም” ሲል ገልጾ፣ ” ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ስለ አገር ያለን ክብር ከሃይማኖታችን አስተምህሮ የመነጨም ጭምር መሆኑን ሁሉም ከግንዛቤ ሊከተው ይገባል” ብሎአል።
መንግስት ደጋግሞ በሚዲያ በነዛው ፕሮፖጋንዳ የሚታየውና የተቀደደ ባንዲራውን የሚያውለበልበው ግለሰብ በመንግስት ተልእኮ የተሰጠው ቅጥረኛ ነው ሲል አክሏል።
” ይህ ሰርጎ ገብ ግለሰብ ይህንኑ ባንዲራ ማውለብለብ ገና ከመጀመሩ በሰኮንዶች ውስጥ በዙሪያው የነበሩ ግለሰቦች ቢያስቆሙትም፣  ይህንኑ ድራማ ለመቅዳት በአንዋር መስጊድ ዙሪያ ባሉ ፎቆች ላይ ካሜራቸውን ደግነው ሲጠባበቁ የነበሩት የመንግስት የካሜራ ባለሞያዎች ይህችኑ ለሰኮንዶች የተሳካችላቸውን ቀረጻ ህብረተሰቡ ሲከለክለውና ሲያስቆመው የሚያሳየውን ትዕይንት ቆርጠው ‹‹ሕዝቡን የሚወክል ነው›› በማለት ለፕሮፖጋንዳ በስፋት ተጠቅመውበታል ሲል መግለጫው አብራርቷል።
መግለጫው በመጨረሻም ” ባንዲራን የማዋረድ ተግባር እኛ ሙስሊሞች አጥብቀን የምናወግዘው ተግባር ሲሆን ከመሰረታዊው የ‹‹ፍትህ ይከበር!›› ትግላችንም በእጅጉ ያፈነገጠ  ነው፤ ይህን ባንዲራ የማዋረድ ተግባር የፈጸመው ግለሰብ ማንም ይሁን ማን ተጠያቂ መሆን እንዳለበት እናምናለን፡፡ ግለሰቡ በግሉ በፈጸመው በዚህ የማዋረድ ተግባር ተገቢውን ቅጣት ማግኘት ያለበት ሲሆን ይህንንም ሀላፊነት ሊወስድ የሚገባው መንግስት ራሱ ነው፡፡ መንግስት የተቀደደ ባንዲራ ሲያውለበልብ ለሰኮንዶች ቀርጾ ያሳየውን ግለሰብ በህግ አስከባሪዎቹ በቁጥጥር ስል ማዋልና በአገሪቱ ህግም ተገቢውን ቅጣት የማሰጠት ግዴታ አለበት ፤  የህዝብን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ መሰል አጀንዳዎችን ተጠቅሞ አንድን ህዝብ በሌላው ላይ ለማነሳሳት መሞከር እጅግ አጥፊ ተግባር መሆኑንም በአጽንኦት ልናሳስብ እንወዳለን” ብሎአል።
በተያያዘ ዜና  ባለፈው ቅዳሜ ሐምሌ 26 ቀን የመንግስት ወታደሮች በሙስሊም ዜጎች ላይ ያካሄዱትን የጅምላ ግድያ ኢሕአፓ በጥብቅ አውግዞ ወንጀሉን ያዘዙትና ድርጊቱን የፈጸሙትም ባስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል።
ኢህአፓ ” በግፍ የታሰሩባቸው የሃይማኖት አባቶች (ኢማሞች) እንዲፈቱላቸውም ጠይቋል።
ፓርቲው  ” የሰሞኑ የወያኔ አገዛዝ አረመኔያዊ ድርጊት በጽኑ መወገዝ ያለበት ቢሆንም ድርጊቱን በማውገዝና ተቃውሞን በማሰማት ብቻ የወያኔን አረመኔያዊና ጸረ ሕዝብ ጭፍጨፋ ማስቆም አእንደማይቻል ገልጾ፣ የሕዝብን ስቃይና በደል ለአንዴም ለሁሌም ማስቆም የሚቻለው ሁለገብ በሆነ መንገድ ታግሎ አገዛዙን ከስልጣን ማስወገድ ሲቻል ስለሆነ የአገር ፍቅር የሚሰማው ዜጋ ሁሉ ኃይሉን አስተባብሮ በአረመኔው አገዛዝ ላይ ጥቃት እንዲሰነዝር ” ጥሪ እናቀርባለን ብሎአል።
በሌላ ዜና ደግሞ ነጃሺ ጄስቲስ ካውንስል የተባለ ተቀማጭነቱ አሜሪካ የሆነው ድርጅት ባወጣው መግለጫ፣ መንግስት በምእራብ አገራት ኢምባሲዎች ላይ ጥቃት እንደሚፈጸም አድርጎ በማስጠንቀቅ፣ የሙስሊሙን ጥያቄ ለማፈን የሚጓዝበት መንገድ በዜጎች ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ከዚህ ድርጊቱ እንዲቆጠብ እንዲያደርጉ ጠይቋል።

tirsdag 6. august 2013

አንድነት ፓርቲ በባህር ዳር እና አርባ ምንጭ ያካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ



 በባህርዳር ስለነበረው ሰልፍ በስፍራው የተገኘው ዘጋቢያችን ሲገልጽ ” ለ ስምንት አመታት የተዘጉ ልሳኖች ተከፈቱ ፤ መከራና ስቃይ ፣ የኑሮ ውድነት ያንገበገባቸው ፤ስራ አጥነት ያማረራቸው ፤ የፍትህ እጦት ያስነባቸው ወገኖች በአደባባይ ተገኝው ድምፃቸውን አሰሙ ብሎአል።
• የታሰሩ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ይፈቱ
• መንግስት ህገ-መንግስቱን ያክብር

fredag 2. august 2013

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን ሶስት ሕጎችን በማሻሻል ላይ መሆኑ ተሰማ፡፡

በዚህ ሕግ መሠረት የሕዝብ ገንዘብ ዘርፈው ወደውጪ አገር ፈርጥጠዋል የሚባሉ ሰዎች ተጠያቂ ይሆናሉ ተብሎ ይገመታል ፡፡
የሚሻሻሉት ሕጎች የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የስነስርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅ እንደገና ለማሻሻል የወጣውን
ረቂቅ አዋጅ፣ የተሻሻለውን የስነምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን ማቋቋሚያ አዋጅ እንደገና ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ
አዋጅ እና የሙስና ወንጀሎችን እንደገና ለመደንገግ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ናቸው፡፡
ረቂቅ አዋጆቹ በኮምሽኑ ተዘጋጅተው የሚመለከተው የመንግስት አካል አስተያየት እንዲሰጥበት የተደረገ ሲሆን በቅርቡ
ለሚኒስትሮች ም/ቤት ቀርበው በቀጣይ ዓመት ፓርላማው ያጸድቃቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የፓርላማ ምንጮች ጠቅሰዋል፡፡
ምንጫችን እንዳብራራው በተለይ የኮምሽኑን ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻያ ውስጥ የግሉ ዘርፍ በሙስና ወንጀል ለመጠየቅ
የሚያስችለው አንቀጾች ተካተውበታል፡፡
አሁን በስራ ላይ ያለው አዋጅ ኮምሽኑ የሚመለከተው የሙስና ወንጀል በአመዛኙ የመንግስትን ተቋማት ብቻ የሚመለከት ሆኖ ነገር ግን ወንጀሉ ከግሉ ዘርፍ ጋር በትብብር መፈጸሙ ማስረጃ ካለ የግሉን ዘርፍ በተጨማሪነት መክሰስ የሚያስችለው ነው፡፡ በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ በተለይ ከሕዝብ በአክስዮን መልክ ገንዘብ ሰብስበው ዞር የሚሉ ሌቦችን ለመቅጣት እንዲያስችለው አክስዮን ማኀበራትን፣ ባንኮችን፣  ኢንሹራንሶችን ፣የልማት ማኀበራትንና የመሳሰሉትን ሕጉ እንዲያቅፍ ተደርጓል፡፡
በግል ባንኮች በተመሳሳይ መንገድ ያለበቂ ዋስትና ብድር የሚሰጥበት፣ ባንኮቹ ከፍተኛ አክስዮን ባላቸው
ግለሰቦችን ተጽዕኖ ስር ሲወድቁና ገንዘባቸው ያለአግባብ በብድር ስም ሲመዘበር ዝም ብሎ ማየት ወይም ተባባሪ
የመሆን ሁኔታ በተደጋጋሚ መከሰቱን፤ በዚህም መንገድ የሕዝብ ገንዘብ ተበልቶ የሚቀርበት ሁኔታ በስፋት በመኖሩ
ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የሕጉ መሻሻል እጅግ ጠቃሚ ያደርገዋል ተብሎአል፡፡
ይሁን እንጅ ህግ ማውጣት  ብቻውን ሙስናን ለመከላከል በቂ አለመሆኑን ጉዳዩን የሚከታተሉ ወገኖች ይገልጻሉ። ጸረ ሙስና ኮሚሽን በቅርቡ በገቢዎች ሚ/ር ሰራተኞች ላይ ክስ ከመሰረተ በሁዋላ ተጨማሪ እንቅስቃሴ ሲያደርግ አልታየም።

አንድነት ፓርቲ በወከባ ውስጥ ሆኖ የተቃውሞ ሰልፎችን ለማዘጋጀት እየጣረ ነው



ፓርቲው በመጪው እሁድ በመቀሌ፣ ባህርዳር፣ ጅንካ እና አርባ ምንጭ የሚያደርገውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ የገዢው ፓርቲ ሰዎች ሰልፎችን ለማደናቀፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው። በመቀሌ የአንድነት አመራሮች መጉላላት የደረሰባቸው ሲሆን፣ በጅንካ ደግሞ አካባቢው የሽብርተኞች ጥቃት ኢላማ በመሆኑ ሰልፉን ማድረግ አይቻልም የሚል መመሪያ እስከ ማስተላለፍ ተደርሶ ነበር። የአንድነት አመራሮች ባሳዩት የአቋም ጽናት ሰልፉ እንዲደረግ ፈቃድ ማግኘታቸው ታውቋል።

torsdag 1. august 2013

ከ2 ቢሊዩን ብር በላይ በሆነ ወጭ የተገነቡ የውሃ ተቌማት ላይ ጉዳት ደረሰ

በአማራ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ዞንና ወረዳዎች በበጎ አድራጊዎች ድጋፍና በህብረተሰቡ የተገነቡ ከ110 በላይ  የውሃ ተቌማት ላይ የእጅ ፓምፕ ዝርፊያ በመፈጸሙ በውሀ አቅርቦቱ ላይ ችግር ተፈጥሯል።
ዝርፊያውን ተከትሎ የወረዳ አመራሮች ለህዝቡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ናቸው እያሉ ፤ ፓርቲዎችን የማሰጠላት ዘመቻ እያከናወኑ ነው፡፡
በተለያዩ  አካባቢዎች እየተከሰተ ባለው የውሃ ተቋማት ዝርፊያ እስካሁን ወደ 250 የሚጠጉ ሰዎች  ከ2 ወር እስከ 12 ዓመት በእስራት እንዲቀጡ ተደርጓል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ በደቡብና ሰሜን ጎንደር ፤ደቡብና ሰሜን ወሎ የእጅ ውሃ ማውጫ ፓምፖች ተሰርቀው ከጥቅም ውጭ ሁነዋል፡፡
የጉዳቱን መጠንና ችግሩን በተመለከተ የክልሉ ውሃ ሃብት ቢሮው ይፋ ያላወጣው ሪፖርት እንደሚያመለክተው የችግሩ መጠን መባባሱን ያሳያል፡፡ በዚህ ሂደት ተሳታፊ ናቸው የተባሉ ወገኖች ላይ እርምጃ ለመውሰድ የተሞከረ ቢሆንም እስካሁን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ማዋል አልተቻለም፡፡

በጎንደር ከተማ ህዝበ ሙስሊሙ በመንግስት ላይ ቅሬታውን እየገለጠ ነው፡፡

የመቃብር ቦታ ጥያቄያችን አልተመለሰም ፤ ለመስጊዶቻችንን  የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ተከልክለናል፡፣ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ፍትህ አጥቷል” በማለት ሙስሊሞች ተናግረዋል።
የጎንደር ከተማ ኗሪ የሆኑት ሐጅ ሙርፉቅ ሙስሊሙ ከመንግስት ጋር ሆድና ጀርባ መሆኑን ገልጸዋል።
በየቀኑ ደብዛቸው እየጠፋ በአፋልጉኝ የሚጠሩት ህዝበ ሙስሊሞች የመንግስት የአፈና ውጤት መሆናቸውን የተናገሩት የጎንደር ህዝበ ሙስሊሞች፤ያለምንም ፍትህ የሚያስረውና የሚያንገላታው ኢህአዴግ የማሰተዳደር አቅሙ ደካማነትን የሚያረጋግጥ የእምነት አፈናው ውጤት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የህዝበ ሙስሊሙን ድምጽ በማፈን ስልጣንን ማቆየት አይቻልም በማለት የተበሳጩ አንዳንድ ወጣቶች ፤ ለዘገባ በሄዱ በአማራ ክልል ጋዜጠኞች ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል፡፡
ጋዜጠኞቹ ፤ የረመዳንን ክብረ በዓል ለማክበር  የቅድመ ዝግጅት ቀረጻ ለማድረግ ፤ ቅዳሜ ገበያ ዋናው  መስጊድ የሶላት ስርዓትን ለመቅረጽ በተገኙበት ስዓት ነው ጥቃቱ የተሰነዘረባቸው። ” ያለ ፈቃዳችን መንግስት እየቀረጸ ‹‹ ጅሃዳዊ ሃረካት›› የተሰኝ ፊልም ቆርጦ በመቀጠል ለሚያዘጋጀውና ሙስሊሞችን በመወንጀል ለሚተባበር እውነት አልባ ሚዲያ ፤ ልንቀረጽ አይገባም” በማለት ባነሱት ተቃውሞ ፤ በመስል ቀራጩ ወይም ካሜራ ማኑ ላይ አካላዊ ጉዳት አድርሰውበታል ።  ካሜራ ማኑ የያዘውን ካሜራም መሬት ላይ ከስክሰውታል።  አድማ በታኞች ፖሊሶች በስፍራው ሲደረሱ ወጣቶቹ ሮጠው  አምልጠዋል።
ህዝበ ሙስሊሙ መንግስት ፤ በሚያደርስብን ጭቆና ፤ ከእምነት ተቋማችን እንዲደርስ አንፈልግም ‹‹አላህ ወ አክብር ›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ በመላ ሐገሪቱ እየበረታ መምጣቱን ተከትሎ በመላ ሐገሪቱ ከጅማ ፤ከከሚሴ ፤ደሴ ፤ ወልድያ፤ ቀጥሎ በአራተኛነት ደረጃ ጎንደር በስጋት ቀጠና መንግስት በሐይማኖት አክራሪነት የፈረጃቸው ከተማዎች ናቸው ፡፡