onsdag 31. juli 2013

የመድረክ ሕዝባዊ ስብሰባ የፊታችን እሁድ ይካሄዳል

የአራት ፓርቲዎች ግንባር የሆነው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በአደባባይ ላይ ሊያካሂድ ያቀደውን የአደባባይ ሰልፍ ተገዶ ወደ ሕዝባዊ ስብሰባ መቀየሩ ታውቋል፡፡ በዚሁ መሠረት ግንባሩ የፊታችን እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ/ም ሕዝባዊ ስብሰባ መጥራቱን የአዲስ አበባው ዘጋቢ ገልጿል፡፡
ከወቅታዊ የአገራችን ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስአበባ ከስድስት ኪሎ እስከድላችን ሐውልት ድረስ ሕዝባዊ ሰልፍ ለማካሄድ ግንባሩ መርሃግብር ነድፎ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም የአዲስአበባ ከተማ አስተዳዳር ከተማዋ በተለያዩ ልማቶች የተቆፋፈረች በመሆኑዋ ሰልፉን ለማካሄድ አመቺ አይደለም በሚል ምክንያት ፈቃድ መከልከሉ ታውቋል፡፡መድረክ የአደባባይ ሰልፉን በቤት ውስጥ ስብሰባ በመቀየር በድጋሚ ለአስተዳደሩ እንዲያውቀው ያስገባው ይፋዊ ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ አግኝቶ ስብሰባው በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው የመብራት ኃይል አዳራሽ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ለማካሄድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ታውቋል፡፡

tirsdag 30. juli 2013

ኢህአዴግ የመለስ ሙት አመት መታሰቢያን በልዩ ዝግጅት ሊያከብር ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሙት ዓመት አከባበር ሥነ ሥርዓት ጋር  በተያያዘ ሠራተኞቹን በየደረጃው ማወያየት ጀመረ፡፡ሕዝብ በከፍተኛ ደረጃ ከመሰልቸቱ ጋር ተያይዞ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሽፋናቸው እንዲቀንስ ተደርጎ የነበሩት የአቶ መለስ ርዕሰ ጉዳይ- ሙት ዓመታቸውን ተከትሎ እንደገና አዲስ አጀንዳ ሆኗል፡፡
የአስተዳዳሩ ምንጮች እንደገለጹት የአቶ መለስን ሙት ዓመት በአረንጓዴ የልማት ዘመቻ ለማክበር ታስቦ ሥራው መጀመሩን፣ የሻማ ማብራት ስነስርዓት እንደሚኖር፣ የእሳቸውንም ራዕይ ለማሳካት የተጀመረው ጥረት በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለሠራተኞቹ ተነግሯቸዋል፡፡
ባለፈው ዓርብ ዕለት የአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃን ሠራተኞች በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ላይ በመወያየት የመለስን ራዕይ አጠናክሮ ለመቀጠል እንደሚተጉ ባወጡት የአቋም መግለጫ ጠቅሰዋል፡፡
አንዳንድ የኢህአዴግ አባላትና ካድሬዎች በስብሰባው ላይ እንደ አዲስ ሲያለቅሱም ታይተዋል፡፡
ነሐሴ 14 ቀን 2005 ዓ.ም ታስቦ የሚውለውን የአቶ መለስ ሙት ዓመት በማስመልከት ከ40 ሚሊየን ብር በላይ ይገኝበታል የተባለ በሞባይል የሚካሄድ ሎተሪ እንደሚጀመር ለሠራተኞቹ እንደተገለጸላቸው፤ ይህም ገቢ ለመለስ ፋውንዴሽን ሥራዎች ይውላል ተብሎ እንደተነገራቸው ታውቋል፡፡
የፋውንዴሽኑ የቤተመጽሐፍትና ሙዚየም ግንባታ የመሰረት ድንጋይ በዚሁ ሰሞን ይጣላል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ለተመረጡ ተማሪዎች በአቶ መለስ ስም ስኮላርሺፕ መስጠትን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በእነ አርቲስት ሰርጸ-ፍሬ ስብሃት፣ ደበሽ ተመስገንና  ሰራዊት ፍቅሬ የሚመራ የስነጥበብ ባለሙያዎች ቡድን ለሙት ዓመቱ ለየት ያሉ  ስራዎች ለማቅረብ ደፋ ቀና እያለ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ጠቅሰዋል፡፡
የመለስ ፋውንዴሽን በአዋጅ ቁጥር 781/2005 ተቋቁሞ በመጋቢት ወር መጨረሻ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በተካሄደ ስነስርዓት በይፋ መመስረቱ የሚታወቅ ሲሆን በዕለቱም በተካሄደ የገቢ ማሰባሰቢያ በአንድ የእራት ምሽትብቻ ከ110 ሚሊየን ብር በላይ  መሰብሰቡ አይዘነጋም፡፡ ፋውንዴሽኑ በአዋጅ

የአንድነት አባል የሆኑት አቶ ግርማ ወልደሰንበት አረፉ

አቶ ግርማ በህይወት ዘመናቸው ለሚወዷት ሀገራቸው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በተለያዩ ሀርፎች ያገለገሉ ሲሆን ወደ ፖለቲካው በመግባትም ትልቅ ዋጋ የከፈሉ የቁርጥ ቀን ልጅ ነበሩ ሲል አንድነት ፓርቲ ለኢሳት በላከው መግለጫ አመልክቷል።
አቶ ግርማ ወደ ተቃውሞ ጎራው ትግል የገቡት ለ1984 ዓ/ም ከፕ/ር አስራት ወልደየስ ጋር በመሆን መአህድን በመመስረት ነው። የመኢአድ አባልና የአዲስ አበባ ሰብሳቢ በሁዋላም የብርሀን ፓርቲ ም/ል ሊቀመንበር የነበሩ ሲሆን ከሁለቱ ፓርቲዎች ውህደት በሁዋላ ከዚህ አለም በሞት እስከተለዩበት ቀን ድረስ የአንድነት ፓርቲ የብሄራዊ ም/ቤት አብልና የፋይናንስ ቃሚ ኮሚቴ አባል በመሆን ደከመን ሰለቸኝ ሳይሉ በቁርጠኝነት ትግል ማካሄዳቸውን ፓርቲው ገልጿል።
አቶ ግርማ ወልደሰንበት ለኢሳት የነበራቸውን ድጋፍም በተለያዩ መንገዶች ሲገልጹ ቆይተዋል። በቅርቡም ታመው በሚሰቃዩበት ወቅት እንኴ የኢትዮጵያ ህዝብ ኢሳትን እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበው ነበር።
የኢሳት ባልደረቦች በአቶ ግርማ ወልደሰንበት ሞት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጆቻቸው እና ለትግል ጓደኞቻቸው መጽናናት
እነዲሆንላቸው ልባዊ ምኞታቸውን ይገልጻሉ

torsdag 25. juli 2013

የፓርላማው ውይይት መታፈኑን ያጋለጠው የኢቲቪ ጋዜጠኛ ከሥራ ተባረረ



የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈፃሚ ተቋማት ኃላፊነት” በሚል ርዕስ ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም ያደረገውን ውይይት በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በኩል ተቆራርጦና ተዛብቶ እንዲተላለፍ ተደርጓል በሚል አንድ ዜና መዘገቡ ይታወሳል።


ዜናው በሰንደቅ ጋዜጣ የህዳር 5 ቀን 2005 ዓ.ም ዕትም “ኢቲቪ የከፍተኛ ባለሥልጣናትን ውይይት በማፈን ተወቀሰ” በሚል ርዕስ ከቀረበ በኋላ፤ በዚህ ዘገባ ላይ ተመድቦ የሠራው የቀድሞ የኢቲቪ ባልደረባ ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ ረቡዕ ህዳር 12 ቀን 2005 ዓ.ም በጉዳዩ ላይ  ምላሽ መስጠቱ አይዘነጋም።


ዜናዎቹ መዘገባቸውን ተከትሎ ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ ለሚዲያዎች መረጃ እንደሰጠና ሚስጢር እንዳወጣ ተቆጥሮ የዲስፒሊን ክስ ቀርቦበታል።


የኢትዮጵያ .ሬዲዮ እና.ቴሌቪዥን  ድርጅት በዲስፒሊን ክሱ ላይ  አራት ከፍተኛ የሥራ አመራሮችን በምስክርነት ዘርዝሮ አቅርቧል።


የድርጅቱ የዲስፒሊን ኮሚቴ በከሳሽ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እና በጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ መካከል የክስ ዝርዝር እና የመልስ መልስ ደብዳቤዎች ሲያዳምጥ ከሰነበተ በኋላ ግንቦት 9 ቀን 2005 ዓ.ም በቁጥር ቴ02.1/131-304/02/8/ በተፃፈ ደብዳቤ ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ  ከግንቦት 10 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ከሥራ እንዲሰናበት የሚል ቅጣት አሳልፏል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ባለቤትነት በጠ/ሚኒስትሩ ቢሮ ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም የተካሄደው ስብሰባ በመልካም አስተዳደር፣ በተጠያቂነት፣ በሙስና ችግሮችና በመሳሰሉት ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት የተካሄደ መሆኑ ይታወቃል።



ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሁለተኛ ዙር መዋጮ የመንግስት ሰራተኞች ፈቃደኛ አልሆኑም ተባለ





 ባለፈው አመት የወር ደሞዛችን በአመት ከፍለናል አሁን ግን ዳግመኛ ለመከፈል አቅሙ ስሌለለን እና እየተባባሰ የመጣውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም  ስለማንችል፣ ከእንግዲህ ወዲህ ገንዘብ ልንከፈል   የምንችለው ባገኘንበት  ጊዜ ብቻ ነው ” በማለት በአማራ ክልል የሚገኙ የመምህራን ማህበራት አስታውቀዋል፡፡


መንግስት ከሐምሌ ወር ጀምሮ ከሰራተኛው ለመቁረጥ አቅዶት የነበረ ቢሆንም ፣  በክልል ቢሮዎች  ብቻ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የመንግስት ሰራተኛች ”  የተሰጠን ቦንድ ይወሰድ እና ነጸ እንሁን ፤ 10 ፐርሰንት ብቻ ይቆረጥብን ፤ በልቼ ማደር ስላልቻልኩ ለሚቀጥለው ዓመት ይተላለፍልኝ” የሚሉ እጅግ በርካታ ደብዳቤዎች ለፍትህ ቢሮ ፤ ለሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ በግልባጭ እንዲያቀውቁዋቸው ተደርገው በሰራተኞች ቀርበዋል፡፡


የተወሰኑት ሰራተኞች ደግሞ  ” የልጆቻችንን መሰረታዊ ፍላጎቶች ማሟላት ስላቃተን እና የትምህርት ክፍያ ስለበረታብን  ለብአዴን መዋጮ የሚቆረጥብን እንዲቆም እንጠይቃለን” የሚሉ ጥያቄዎችን አቅርበዋል።


የመንግስት አመራሮችም ” ያልተቸገረ የለም፣  ችግሩን ችላችሁ ገንዘብ እንዲቆረጥ ተስማሙ” በማለት ሰራተኛውን ለማሳመን ጥረት እያደረጉ ነው፡፡


አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ ህዝቡ ግድቡን ለማስፈጸም የሚያበረከትው ድርሻ ትንሽ መሆኑንና አብዛኛው በመንግስት ወጪ የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

 ይሁን እንጃ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒሰትር የግድቡን እቅድ ይፋ ሲያደርጉ፣ ግዱ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ድጋፍ ይሰራል ማለታቸው ይታወቃል።

onsdag 24. juli 2013

Human Rights Groups: Donor Countries Fuel Abuse in Ethiopia





Two new reports published this month say sustainable development in Ethiopia is impossible without a specific focus on human rights. The reports say donor countries should bear responsibility for ensuring their aid money is not used to fuel abuse.

Ethiopia receives billions of dollars in international aid every year. It is money that is used to help improve basic services like access to health and
education
.

But human-rights campaigners say there also is widespread abuse that takes place in Africa’s second most populous country. And they say donors need to face up to what role their aid money might play in fueling that abuse.

Leslie Lefkow, the deputy director for Human Rights Watch’s Africa Division, said, “The Ethiopian government is resettling large numbers of pastoralists and semi-pastoralist communities in the name of better services. But often this resettlement process is accompanied by very serious abuses.”

Human rights groups say so-called “villagization” has been marred by violence, including rapes and beatings, and people are often forced to leave their homes against their will. They also say the new villages lack adequate food, farmland, healthcare and education facilities.

Lefkow said the World Bank is turning a blind eye. “In Ethiopia you have several years’ worth of rising concerns of human rights and yet you do not really see that being absorbed in the monitoring and in the practice of donors across the spectrum, so not just the World Bank,” she said.

The World Bank is the world’s top aid donor, with a $30 billion annual budget.
Right now the World Bank is undergoing a review of its safeguard policies, a process that began last year.

Human Rights Watch, a New York-based campaign group, says now is the time for it to commit to respecting and protecting human rights.

“Unlike some of the other international financial institutions, the European development bank and the African development bank, for example, is looking at reviewing some of its policies and explicitly committing to human rights, but the World Bank does not have that, even on paper.”

Another group, the U.S.-based Oakland Institute, published a report last week highlighting donor countries’ roles in alleged Ethiopian abuse.

It said Britain and the United States have ignored abuses taking place in the Omo Valley as the government forces tens of thousands of people from their land.

Executive Director Anuradha Mittal of the Oakland Institute, an independent policy think tank, says forced evictions are taking place in order to make way for commercial farming and a major new dam. She says money from donor countries supports the new projects.

“There is also support for infrastructure projects such as power lines and the rest, which are linked to the large dams that have been built, for instance, the dam in Lower Omo, which has been built to provide irrigation and electricity to the investors,” she said.

The Ethiopian government says sugar plantations in the region and the new dam, which will be Africa’s largest, are key to bringing energy and development to the country. VOA contacted the government for a reaction on the Oakland Institute report, but did not get a response.

Britain’s Department for International Development says its assistance in Ethiopia helps millions.

የፕሮቴስታንት ሀይማኖት ተከታዮች እየተሳደድን ነው አሉ



በሰሜን ወሎ ዞን ከወልድያ ከተማ በ140 ኪሜ ርቅት ላይ በትምገኘዋ መቀት ወረዳ የሚገኙ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ከፍተኛ እንግልት እደረሰባቸውና አካባቢውንም ለቀው እንዲወጡ ግፊት እየተደረገባቸው መሆኑን ገልጸዋል።


እስካሁን በደረሰን መረጃ 10 የሚሆኑ የሀይማኖቱ ተከታዮች አካባቢውን ለቀው የወጡ ሲሆን፣ አንድ ተመስገን የተባለ ወጣት ለተባባሪ ዘጋቢያችን እንደገለጸው አማኞቹ ድንጋይ ይወረወርባቸዋል፣ ቤታቸውም በድንጋይ ይደበደባል። ተመስገን ሀምሌ 1 ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞበት፣ ሞቷል ተብሎ ተጥሎ መትረፉንም ገልጿል።


የኦሮቶዶክስ ሀይማኖት ተከታይ የሆኑት መርጌታ ሙሴ ከፕሮቴስታንት ጋር ባላቸው ቀረቤታ መደብደባቸውን፣ ወርቁ ገበየሁ የተባለ ሰውም እንዲሁ ድብደባ ተፈጽሞበት እጁን መሰበሩን ተባባሪ ዘጋቢያችን ተናግሯል።



በወረዳው ውስጥ የሚኖሩ ፕሮቴስታንቶች ቤት ለመከራየትና ስራ ለመስራት አለመቻላቸውን በየጊዜውም እንገድላችሁዋለን የሚል ማስተጠንቀቂያ እንደሚደርሳቸው ለመረዳት ተችሎአል።


ጉዳት የደረሰባቸው መርጌታ ሙሴ ተክለብርሀን “በወረዳው ውስጥ ለህዝብ የሚቆረቆር መንግስት ህግ ባለመኖሩ” ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰነ ነው  ብለዋል።


የወረዳውን አስተዳዳሪ አቶ ይሄነው በላይን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ብንደውልም ስላካቸው አይነሳም።

በደቡብ ወሎ ዞን በሚገኘው ኩታበር ወረዳ አንድነት ፓርቲ ሐምሌ 7 ቀን 2005ዓ.ም. በደሴ ያካሄደውን ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በመቃወም ህዝቡ ሰላማዊ እንዲወጣ ኢህአዴግ እያስገደደ መሆኑን ፍኖተ ነፃነት ዘገበ ፡፡



ሰልፉ ረቡዕ ሐምሌ 17 ቀን 2005 ዓ.ም. ጠዋት ላይ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡  በወረዳው ቀበሌ 05፣06 እና 07 ሰፊ የማስፈራሪያና የቅስቀሳ ስራ እየተካሄደ መሆኑንም ጋዜጣው ዘግቧል፡፡


ጋዜጣው የኢህአዴግ ካድሬዎች ገበሬውን በግድ ከአቅሙ በላይ የዘር ማዳበሪያ ውሰድ እያሉ ከፍተኛ ገንዘብ ከማስከፈላቸው በተጨማሪ ለአማራ ልማት ማኀበር፣ለአባይ፣ ለመሬት ግብር እየተባለ የሚጠየቀው መዋጮ በመብዛቱ ነዋሪዎቹ ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ሲናገሩ ወደ እስር ቤት እየተወሰዱ ና ቤት ንብረታቸውን ጥለው ከአካባቢው እየተሰደዱ መሆኑንም ገልጿል።


አንድነት ፓርቲ በተለያዩ ከተሞች የጠራውን ሰልፍ ተከትሎ የኢህአዴግ ከፍተኛ ሹማምንት በተለያዩ ቦታዎች እየተነቀሳቀሱ ህዝቡ እንዳይገኝ ለበታች አመራሮች መመሪያ እየሰጡ ነው።


ተቃዋሚዎች እየወሰዱት ባለው እርምጃ የተደናገጠ የሚመስለው ኢህአዴግ ተቃዋሚዎች የሙስሊሙን የድምጻችን ይሰማ ጥያቄ ለራሳቸው አጀንዳ ማስፈጸሚያ ሊያውሉት እየተሩዋሩዋጡ ነው በማለት ይተቻል።


አንድነት ባወጣው የህዝባዊ ንቅናቄ እቅድ መሰረት ሀምሌ 21 እና 28 በአዲስ አበባ 2 ቦታዎች እንዲሁም ሀምሌ 28 በወላይታ ሶዶና በመቀሌ ህዝባዊ ስብሰባዎች ሲደረጉ፣ በተመሳሳይ ቀን ሀምሌ 28 በባህርዳር፣ ጅንካና አርባምንጭ የተቃውሞ ሰልፎች ይደረጋሉ።


ነሃሴ 12  አዳማ፣ ባሌ፣ ወሊሶ እና ፍቼ የተቃውሞ ሰልፎችን ሲያስተናግዱ ነሃሴ 26 ደግሞ ጋምቤላና አሶሳ ያስተናግዳሉ።


 ድሬዳዋ አዋሳ፣ አምቦና ደብረማርቆስ   ነሀሴ 26 ህዝባዊ ስብሰባዎችን ያደርጋሉ። መስከረም 5፣ 2006 ዓም ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አንዱአለም አራጌ የታሰሩበትን 2ኛ አመት ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የማጠቃለያ የተቃውሞ ሰልፍ ይደረጋል።







tirsdag 23. juli 2013

ኢህአዴግ አንድነት ፓርቲ የጠራው ሰልፍ እንዳይሳካ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው







አንድነት የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በማለት የጠራው ህዝባዊ ንቅናቄ ገዢውን ፓርቲ በማስደንገጡን አዲስ ከጀመራቸው ግምገማዎችና የህብዕ እንቅስቃሴዎች ለመረዳት ተችሎአል።


በደሴ እና በጎንደር የተካሄደውን ስላማዊ ሰልፍ ተከትሎ  የፖሊስ እና የቀበሌ የፖለቲካ አመራሮች በጠንካራ ግምገማ ተይዘው መሰንበታቸውን ከኢህአዴግ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


ስማችን እና ድምጻችን አይተላለፍ ያሉት ምንጮች እንደገለጹት በ1ለ5  አደራጃጀት መሰረት ህዝቡ በሰልፉ ላይ እንዳይገኝ መመሪያ ለሚመለከታቸው ወገኖች ተላልፏል።

  የፖሊስ አባላት ሰልፎችን በመበተን የድርሻቸውን እንዲወጡ የተሰጣቸው መመሪያ በመካከላቸው ክፍፍል እንዲፈጠር እንዳደረገ  ምንጮች ገልጸዋል፡፡

  ፖሊሶቹ በስራ አጥነት እና በኑሮ ውድነት የተማረረውን ህዝብ ለማቆም አንችልም በማለት ሲናገሩ ተስምተዋል።


ነሀሴ 26 በደብረማርቆስ ከተማ የሚካሄደውን ህዝባዊ ስብሰባ ለመገደብ እና በ1 ለ 5 አደረጃጀት የተቀየሰውን የማገቻ ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን እና ምክትላቸው አቶ ገዱ አንደርጋቸው የስልጠናና የማሳሰቢያ ስራዎችን ለመስራት ወደ ደብረማርቆስ  እየተመላለሱ ነው።


 ሐምሌ 28 በባህርዳር የተጠራውን ህዝባዊ ሰልፍ ለማስቆም በየደረጃው ያሉ አመራሮች ሁሉንም መንገዶች እንዲከተሉ፣ የብአዴን ድርጅት ጉዳይ ጽ/ቤት ሃላፊዎች እና ሁሉም የመንግስት አመራሮች በንቃት እንዲሳተፉ ለማድረግ  ተወስኖ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡

 በባህር ዳር፣ ሐዋሳ፣ መቀሌና የአዳማ ተመሳሳይ ስራዎችን እንዲያከናውኑ በሚኒስትር ደረጃ የተወከሉ አመራሮች ወደ ስፍራው አምርተዋል፡፡


ከኢህአዴግ ዜና ሳንወጣ  ለመለስ ፋውንዴሺን እርዳታ ከህዝቡ የገንዘብ ልመና ጥያቄ መቅረቡን ለማወቅ ተችሎአል።


የመለስ ፋውንዴሺን አመራሮች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነሐሴ 14 በደመቀ ሁኔታ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሙት አመት በሻማ ማብራት ስነ ስርዓት እንዲከበር መታቀዱን ተናግራዋል፡፡


በእለቱም ለፋውንዴሺኑ የተቋም ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ ይጣላል ተብሎአል፡፡


በቀጣይም ለፋውንዴሺኑ እርዳታ  የሚሆን ገንዘብ ከዝቅተኛው የህብረተሰብ ክፍል ለመሰብሰብ ታስቦ የባንክ አካውንት ለባለሃብቶች ፤


ለድሃው ደግም በሞባይል ቁጥር በቴሌ በሚቆረጥ  ከ2 ብር ጀምሮ 100 ብር የሚደርስ የገንዘብ መክፈያ መዘጋጀቱን ወ/ሮ አዜብ መስፍን ገልጸዋል።

søndag 21. juli 2013

በአማራ ክልል ከ2001- 2004 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ብቻ 67 በገንዘብ የማይተመኑ ቅርሶች ተዘረፉ ፡፡



የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አጠናቅሮ ለክልሉ ባለስልጣናት ባቀረበው ሪፖርት ላይ እንተመለከተው የክልሉ ቅርስ ጥበቃ ቢሮ ታሪካዊ ቦታዎችን በመንከባከብና የቅርስ ዘረፋ እንዳይካሄድ በመከላከል በኩል በቂ ጥረት አላደረገም።


በክልሉ ከ3000 በላይ የቅርስ መገኛ ተቋማት ቢኖሩም  ሙዝየም በማሰራት ቅርሶቻቸውን በጥንቃቄ ለእይታ የቀረቡት 13 ብቻ መሆናቸውን የኦዲት ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡


lørdag 20. juli 2013

አንድነት ፓርቲ ተቃውሞ የሚካሄድባቸውን ቦታዎች ይፋ አደረገ


ፓርቲው ባወጣው የህዝባዊ ንቅናቄ እቅድ መሰረት ባህርዳር፣ ጅንካ፣ አርባምንጭ፣ አዳማ፣ ባሌ፣ ወሊሶ፣ ፍቼ፣ ጋምቤላ፣ አሶሳ እና አዲስ አበባ ለህዝባዊ ሰልፎች ሲመረጡ፣ መቀሌ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ አምቦ፣ ደብረማርቆስና አዲስ አበባ በድጋሜ ለህዝባዊ ስብሰባዎች ተመርጠዋል።

 ሀምሌ 21 እና 28 በአዲስ አበባ 2 ቦታዎች እንዲሁም ሀምሌ 28 በወላይታ ሶዶና በመቀሌ ህዝባዊ ስብሰባዎች ሲደረጉ፣ በተመሳሳይ ቀን ሀምሌ 28 በባህርዳር፣ ጅንካና አርባምንጭ የተቃውሞ ሰልፎች ይደረጋሉ።

ነሃሴ 12 ደግሞ አዳማ፣ ባሌ፣ ወሊሶ እና ፍቼ የተቃውሞ ሰልፎችን ሲያስተናግዱ ነሃሴ 26 ደግሞ ጋምቤላና አሶሳ ያስተናግዳሉ።

 ድሬዳዋ አዋሳ፣ አምቦና ደብረማርቆስ ከተሞች ደግሞ ነሀሴ 26 ህዝባዊ ስብሰባዎችን ያደርጋሉ። መስከረም 5፣ 2006 ዓም  ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አንዱአለም አራጌ የታሰሩበትን 2ኛ አመት ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የማጠቃለያ የተቃውሞ ሰልፍ ይደረጋል።

ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ከደሴና ጎንደር የተቃውሞ ሰልፎች በሁዋላ ድርጅቱን የሚቀላቀሉ ሰዎች ጨምረዋል።

fredag 19. juli 2013

በወልድያ 2 ወር ያልሞላትን አራስ ጨምሮ ከ10 ያላነሱ ሙስሊሞች ታሰሩ


ዘወትር አርብ የሚደረገውን ስግደት ተከትሎ ተቃውሞ ሊያስነሱ ይችላሉ ተብለው የተጠረጠሩ ከ10 ያላነሱ የወለድያ ከተማ ነዋሪዎች ታስረው ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል።


ከታሰሩት መካከል ኢብራሂም ገበየሁ፣ ከድር ሙሀመድ፣ ወ/ሮ ሀያት ይማም፣ ወ/ሮ ነሲሳ አህመድ፣ ወ/ሮ ሀያት አህመድ ይገኙበታል። ወ/ሮ ሀያት አህመድ ሁለት ወር ያልሞላት አራስ ስትሆን፣ ወደ እስር ቤት የተወሰደችውም አዲስ ከተወለደው ህጻኗ ተለይታ ነው።


በፖሊስ ጣቢያው አካባቢ የተሰባሰበው ህዝብ ” ቤተሰቦቻችንን ፍቱልን” በማለት ከሰአት በሁዋላ በፖሊስ ጣቢያ አካባቢ በመሰባሰብ ጥያቄ ቢያቀርብም፣ በፖሊስ ተባረዋል።


የአካባቢው ሙስሊሞች “መሄጃ አጣን” በማለት ግራ መጋባታቸውን ተናግረዋል።

አንድነት የተቃውሞ ፊርማ የማሰባሰብ ሂደቱ በደህንነቶችና በፖሊስ ጥምረት እየተደናቀፈ ነው አለ




ፓርቲው  በህገ ወጥ የዘመቻ እስር የሚሊዮኖች ድምፅ አይታጠፍም” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ በአዲስ አበባ ከተማ የጸረ ሽብር አዋጁ በህገ መንግስቱ እውቅና የተቸራቸውን መብቶችን የሚጨፈልቅና ከህገ መንግስቱ ድንጋጌዎች ጋር የሚጋጭ በመሆኑ መሰረዝ ይገባዋል የሚሉ ዜጎች ወደ ዋናው የፓርቲው በጽ/ቤት በመምጣት የተቃውሞ ፊርማቸውን እንዲያኖሩ የሚጠይቅ ‹‹ከሚሊዮኖች ለምን አንዱ አይሆኑም›› የሚል በራሪ ወረቀት በሁሉም የአዲስ አበባ ወረዳዎች ለማሰራጨት የተጀመረውን እንቅስቃሴ መታወቂያቸውን ለማሳየት በማይፈቅዱ ደህንነቶች ነን ባዮችና በፖሊስ ጥምረት በሕገወጥነት መንግድ እየተደናቀፈ መገኘቱ ” አሳዝኖኛል ብሎአል።


“ፖሊስ የአንድ ፓርቲ ወገንተኛ ሳይሆን ህዝብን ማገልገልና ሁሉንም በህግ መነጽር መመልከት የሚገባው አካል ቢሆንም ሚዛናዊነትን ባልጠበቀ ሁኔታ ህገ መንገስታዊ መብታችንን በመጠየቅ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የምናቀርበውን አቤቱታ ለማደናቀፍ መሞከሩና አባላቶቻችንን እግር በእግር እየተከታተለ ለእስር መዳረጉን በቸልታ ለመመልከት አንፈቅድም” አንፈቅድም ሲል ፓርቲው አክሎአል።


በራሪ ወረቀቶችን መበተን ከጀመርንበት ደቂቃ ጀምሮ አባሎቻችን እየታሰሩና ፍርድ ቤት እየቀረቡ ይገኛሉ ያለው አንድነት፣ ፖሊስ ፍርድ ቤት ባቀረባቸው ወጣቶች ላይም አንድነት የሚባል ፓርቲ መኖሩን አጣርቼ እስክመጣ የ10 ቀን ጊዜ ይሰጠኝ ማለቱና ፍርድ ቤቱም የተጠየቀውን መፍቀዱ የምንገኝበት ሰዓት ምን ያህል ፈታኝ እንደሆነ እንድንገነዘብ አድርጎናል ብሎአል።


አንድነት በአባላቶቹና በእንቅስቃሴው ላይ የተከፈተውን ህገ ወጥ የፖሊስ ዘመቻ ለማስቆምና በደል ፈጻሚዎቹም በታሪክ፣ በህዝብና በህሊና ዳኝነት ይጠየቁ ዘንድ ወደ ፍርድ ቤት እንደሚያመራም አስታውቆ ፤ የጸረ ሽብር አዋጁ እንዲሰረዝ እያሰባሰበ በሚገኘው የህዝብ ድምጽ እንደሚገፋበትም ግልጽ አድርጎአል።

torsdag 18. juli 2013

የአውሮፓ የፓርላማ ልኡካን በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች እና የሲቪክ ማህበረሰቡ መሪዎች እንዲፈቱ ጠየቁ



በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝነት በማድረግ ላይ ያለው የልኡካን ቡድኑ መሪ ባርባራ ሎክብሂለር ጋዜጠኞች እና የሲቪክ ማህበረሰብ መሪዎች ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የማምለክና የመሰብሰብ መብታቸውን በመጠቀማቸው መታሰራቸው ተገቢ ባለመሆኑ ሊፈቱ ይገባል ብለዋል።


በኢትዮጵያ በስራ ላይ ያለው የጸረ ሽብርተኝነት ህጉ የፖለቲካ ልዩነትን ለማፈን እየዋለ መሆኑን የገለጸው የልኡካን ቡድኑ፣  የአገሪቱ ህገመንግስት ጥሩ ቢሆንም የፍትህ ስርአቱ አድሎአዊ መሆኑን ለመመልከት ችለናል ብሏል።


የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ አገሪቱ ያሰረቻቸው ፖለቲካ እስረኞች የሌሉ በመሆኑ ፣ እነሱ ስላሉ የሚፈቱበት ሁኔታ የለም በማለት የህብረቱ ልኡክ ለሰጠው መግለጫ ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል።


አቶ ጌታቸው አክለውም በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞችና እና የሲቪክ ማህበር መሪዎች የታሰሩት የሽብር ወንጀል ሲፈጽሙ በመገኘታቸው በመሆኑ ሊፈቱ የሚችሉትም የእስር ጊዜያቸውን ሲፈጽሙ ወይም መልካም ስነምግባር ካሳዩ በገደብ ነው ብለዋል።


የአውሮፓ ህብረት የሰጠው መግለጫ ለህብረቱ እና ለኢትዮጵያ ግንኙነት የሚጠቅም አይደለም በማለትም አቶ ጌታቸው አክለዋል።


የአውሮፓ ህብረት የልኡካን ቡድን እስረኞችን ለመጠየቅ ወደ ቃሊቲ ቢያመራም  የእስር ቤቱ ሀላፊ ” ከእናንተ ጋር ለመስራት ጊዜ የለኝም” በሚል እንደሸናቸው ጆርጅ ሊችትፊልድ የተባሉ  የልኡካን ቡድኑ አባል ተናግረዋል። ሁሉም የልኡካን ቡድኑ አባላት የእስር ቤቱ ሀላፊ በሰጡት መልስ መደናገጣቸውን የገለጸው አሶሼትድ ፕሬስ፣ ኢትዮጵያ እስር ቤቱን ለማሻሻል ጥያቄ በማቅረቡዋ እስር ቤቱን በአካል ተገኝቶ ለመጎብኘት አንደሄዱ መናገራቸውንም ዘግቧል።


የአውሮፓ  ህብረት ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ልገሳ እንደሚያደርግ ይታወቃል።

onsdag 17. juli 2013

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ከናይጀሪያ ለቀቁ




የአፍሪካ ህብረት በጤና ጉዳይ ላይ ለመመካከር በናይጀሪያ ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ የተገኙት የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ሰብሰባቸውን ሳይጨርሱ ወደ አገራቸው የተመለሱት ፣ አለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የናይጀሪያ መንግስት ይዞ እንዲያስራቸው አቤቱታውን ለፍርድ ቤት ካቀረበ በሁዋላ ነው።

ፕሬዚዳንቱ ሰኞ እለት ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ሲጠበቅ፣ በድንገት አገሪቱን ለቀው መውጣታቸው ታውቋል።

ፕሬዚዳንት በሽር ናይጀሪያ ሲገቡ የናይጀሪያ መንግስት የክብር አቀባበል አድርጎላቸው ነበር።  የናይጀሪያ አለማቀፍ የወንጀለኞች ፍርድቤት ጥምረት ፕሬዚዳንቱ ታስረው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ለአገሪቱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ክስ መስርቶ እንደነበር ዘገባዎች አመልክተዋል።

በአማራ ክልል በ12 ወረዳዎች ባለፉት 10 አመታት 13 ሺ 64 ሰዎች ከነፍስ ግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ ተገድለዋል



የክልሉ አሰተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ባካሄደው  የዳሰሳ ጥናት በ10 አመታት ውስጥ ከነፍስ ግድያ ጋር በተያያዘ 13 ሺ 64 ሰዎች ሲገደሉ ፣ 11 ሺ 93 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።

 በጥናቱ ውስጥ እንደተመለከተው ድብደባ መፈጸም ቀዳሚነቱን ሲይዝ  አካል ማጉደል እና ነፍስ ማጥፋት ወንጀሎች  ተከታታዮችን ደረጃዎች ይዘዋል።


የክልሉ ኗሪዎች በወንጀሎች መበራከት ለእስር ፤ለመበታተን፤ለሽፍትነት ፤ለመሰደድ፤ ለድህነት ፤ለጦም አዳሪነት፣  ለማህበራዊ ፤ኢኮኖሚያው ምስቅልቅሎች መዳረገቸው በጥናቱ ተመልክቷል፡፡


በ2004 ዓ.ም በክልሉ ማረሚያ ቤቶች በነፍስ ግድያ ወንጅል ተጠርጥረው ለገቡ  22 ሺ 26 ታራሚዎች  ሌሎች ወጭዎችን ሳያካትት ለምግብ አገልግሎት ብቻ 73 ሚሊዩን 130 ሺ 40 ብር ወጭ መደረጉም በጥናቱ ተጠቅሷል።


እያንዳንዱ ታራሚ  በትንሹ አምስት አመት ቢታሰር  በ 5 አመት 365 ሚሊየን 650 ሺ 200 ብር ወጪ ይደረጋል።


ጥናቱ በአማራ ክልል ካሉ 11 ዞኖች ውስጥ በተመረጡ 6 ዞኖች 12 ወረዳዎች ብቻ የተካሄደው ነው፡፡

tirsdag 16. juli 2013

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች አመጽ እንደቀጠለ ነው።









በአዲስ አበባ የአንድነት ፓርቲ አባሎች እየታሰሩ ነው








ፓርቲው በደሴና እና በጎንደር የተሳኩ የተቃውሞ ሰልፎችን ባካሄደ ማግስት ከ30 በላይ አባሎቹ በዋና ከተማዋ የተቃውሞ ፊርማ ሲያሰባስቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

ባለፉት ሳምንታትትም በተመሳሳይ መንገድ የታሰሩ እና የፍርድ ቤት ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ያሉ አባላት አሉ።

አንድነት ፓርቲ ለ3 ወራት በሚቆየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ  በዋና ዋና ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎችን ከማካሄድ ባሻገር ቤት ውስጥ ስብሰባዎችንና እና 1 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ፊርማ ያሰባስባል።

ፓርቲው በደሴና በጎንደር ያደረገው ተቃውሞ ለፓርቲው አባላት ከፍተኛ መነቃቃት እንደፈጠረ አንዳንድ አባላቱ ተናግረዋል።



mandag 15. juli 2013

As the Ramadan fasting season befalls, Ethiopian Muslims heap on protests



Ethiopian Muslims have heaped on their peaceful Friday protests in different parts of the Country.

 The protesters in Addis Abeba have echoed the following slogans “Is there no government?,
 The murder of Sheikh Nur Imam is a drama, the Drama should stop, free our leaders, illiterates


cannot lead us, the government itself kills and charges, the terrorist is the government, criminals of the government should appear before court, we are not terrorists, ETV is a liar, Abuki Ambassador,

 Kamil Shemsu Ambassador, Bedru Hussien Ambassador and we will die for our Din”.

Some protesters told ESAT that this Friday’s protest was the biggest of its kind.  Similar protests were held in Woldiya, Nazareth/Adama, Assasa and Shashemane. Observers said that the

søndag 14. juli 2013

ታዋቂው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሆኖ በገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ሊመረጥ እንደሚችል ተጠቆመ


ሻለቃ ኃይሌ ፕሬዚዳንት የመሆን ፍላጎት እንዳለው ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን መግለጹን ተከትሎ ኢህአዴግ መራሹ
ራዲዮ ፋና ባልተለመደ መልክ ዜናውን ደጋግሞ እንዳራገበው አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ጠቅሰው ፣ ሀይሌ የሰጠውም መግለጫ ሆነ የሬዲዮ  ፋና ዘገባ በድንገት የሆነ ሳይሆን ታቅዶበት የተደረገእንደሚሆን ግምታቸውን አስቀምጠል፡፡

በአሁኑ ወቅት በስልጣን ላይ የሚገኙት መቶ አለቃ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ሁለተኛውን የሥልጣን ዘመናቸውን ከአንድ ወር በኋላ
የሚያጠናቅቁ ሲሆን በመስከረም ወር 2006 መጨረሻ አዲስ ፕሬዚዳንት በፓርላማው አብላጫ ወንበር ያለው ገዥው
ፓርቲ ኢህአዴግ ዕጩ አቅርቦ ያስመርጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በፓርላማ የግል ተመራጭ የሆኑት የጥርስ ሐኪም ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ፕሬዚዳንት ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ሰፊ ግምት ተሰጥቷቸው የቆዩ ሲሆን እሳቸውም ለኢህአዴግ ያላቸውን ታማኝነት በየአጋጣሚው ሲያሳዩና ሲገልጹ መክረማቸው የሚታወስ ነው፡፡

ኃይሌ ሰሞኑን ፕሬዚዳንት እንደሚሆን መግለጫ የሰጠው ምናልባት ከኢህአዴግ ታጭቶና እሱም ዕጩነቱን ተቀብሎ ሊሆን
እንደሚችልና ይህም ወሬውን አስቀድሞ ሕዝብ ውስጥ በማስገባት የልብ ትርታውን የማዳመጥ ጉዳይ ሊሆን እንደሚችል ጠንካራ
ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

fredag 12. juli 2013

በሮመዳን ጾም ጅማሮ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጠንካራ ተቃውሞ አሰሙ


በአዲስ አበባ በአንዋር መስጊድ ከፍተኛ ህዝብ በተገኘበት ተቃውሞ ተካሂዷል። መንግስት የለም ወይ፣ የሼክ ኑር ኢማም ግድያ ድራማ ነው፣ ድራማው ይብቃ፣      መሪዎቻችን ይፈቱ፣ መሀይም አይመራንም፣ በፍትህ እጦት ድፍን አንድ አመት መንግስት ራሱ ገዳይ ራሱ ከሳሽ፣ ።
አሸባሪው  መንግስት ነው፣  ፍትሕ ማዳን።
ፍትህ እያሉ ቃሊቲ ገቡ ገደሉት ብለው ድራማ ሰሩ።
የመንግስት ወንጀለኞች ለፍርድይቅረቡ።
አሸባሪአይደለንም።
ኢቲቪ ውሸታም ሌባ።
የገደለው መንግሥት ነው።
ኮሚቴው ይፈታ።
አቡኪ አምባሳደር።
ካሚል ሸምሱ አምባሳደር ።
በድሩ ሁሴን አምባሳደር ።
ለዲናችን እንሞታለን።የሚሉና ሌሎችም ተቃውሞዎች ለ45 ደቂቃዎች ያክል ተስተጋብተዋል።
ኢሳት ያነጋገራቸው ሙስሊሞች እንደገለጹት በአንዋር መስጊድ የተካሄደው ተቃውሞ እስከዛሬ ከታዩት ሁሉ የሚልቅ ነው።
በተመሳሳይ ዜናም በወልድያ ከተማ የሚገኙ ሙስሊሞች ‘ መንግስት ድምጻችን ይስማ፣  በመሀይሞች መመራት በቃን፣ መድረሳችን ይመለስ” የሚሉ መፈክሮችን በማሰማት ተቃውሞአቸውን ሲያሰሙ ውለዋል።  በናዝሬት/አዳማ፣ በአሰሳ እና ሻሸመኔም ተመሳሳይ ተቃውሞች ተካሂደዋል።
መንግስት በደሴ በሼክ ኑር ኢማም ግድያ ላይ የሰጠው ትኩረት ብዙ ሙስሊሞችን ማበሳጨቱንና ለዛሬው ከፍተኛ ተቃውሞ መንስኤ መሆኑን ጉዳዩን በቅርብ የታዘቡ ወገኖች ይገልጻሉ።

ገዢው ፓርቲ በደሴና ጎንደር የሚካሄዱትን ሰላማዊ ሰልፎች ለማደናቀፍ እየሞከረ ነው የፓርቲው ሰዎች በአቋማቸው ጸንተዋል


ሀምሌ 7፣ 2005 ዓ/ም በደሴና ጎንደር ከተሞች አንድነት ፓርቲ የጠራቸው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች በታቀደላቸው ጊዜ እንደሚካሄዱ ከመንግስት እውቅና የተሰጣቸው ቢሆንም፣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና ባለስልጣናት የቅስቀሳ ወረቀቶችን የሚበትኑትን ሰዎች ከማሰር እና ከማስፈራራት አልፈው ፣ ከአዲስ አበባ የሄዱ የፓርቲው አመራሮች አልጋ እንዳያገኙ የሆቴል ባለንብረቶችን እስከ ማስፈራራት መድረሳቸውን የፓርቲው አመራሮች ለኢሳት ገልጸዋል።
የአንድነት ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካሪያስ የማነብርሀን ፣ የደሴ ከንቲባ ፣ አፈ ጉባኤውና 7 የምክር ቤት አባሎች በተገኙበት ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የደሴ ከንቲባ አቶ አለባቸው ፓርቲው ሰላማዊ ሰልፉን ከረመዳን ጾም በሁዋላ እንዲያካሂድ ጥያቄ አቅርበዋል።
ከንቲባው ካቀረቡዋቸው ምክንያቶች መካከል “ወሩ የረመዳን ጾም የተጀመረበት በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ ጸጥ ብሎ እንዲጾም እና እንዳይረበሽ፣ በቅርቡ በደሴ ከተማ ተገደሉት ሼክ ሟች ቤተሰቦች ብስጭት ላይ ስለሆኑ በሰልፉ ላይ አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ፣ ገዳዮችን ለማፈላለግ የጸጥታ ሀይሎችን ስላሰማራን ሀይል ባለመኖሩ” የሚሉት ይገኝበታል። ፓርቲው ” በቅዱስ ረመዳን ወቅት ጽዱስ ስራ መስራት ተገቢ ነው” በማለት በከንቲባው የቀረቡትን ምክንያቶች ውድቅ አድርጓል፡፡
ፓርቲው በጸጥታ ሀይሎች እየደረሱ ናቸው ያላቸውን ችግሮች ዘርዝሮ ለከንቲባው አቅርቧል። ከንቲባውም ስራችሁን ቀጥሉ ችግሮች ካሉ እንነጋገራለን ማለታቸውን አቶ ዛካሪያስ አስታውሳው ይሁን እንጅ ቅስቀሳ ለማድረግ የወጡ ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ መታሳራቸውን ገልጸዋል።  የጸጥታ ሀይሎች በአንድነት አመራሮች ላይ የሚደርሱትን እንግልት የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ” ለምን?’ በማለት ሲቃወሙ መታየታቸውንም አቶ ዘካሪያስ ገልጸዋል:: በከተማዋ የሚገኙ አንዳንድ ነዋሪዎች በመጪው እሁድ በሚደረገው ሰልፍ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል
በጎንደር ከተማ ደግሞ ከአዲስ አበባ የሄዱ ፓርቲው አመራሮች አልጋ እንዳያገኙ እስከመከልከል የደረሰ እርምጃ መሰዱን የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ጎንደር ዞን ተወካይ አቶ እእምሮ አወቀ ገልጸዋል ። በነገው እለት ከአዲስ አበባ ከሄዱት አባሎች ጋር በመሆን  ወረቀት ማሰራጨት እና በመኪና ላይ ቅስቀሳ እንደሚያደርጉ አቶ አእምሮ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የሰላማዊ ሰልፍለማድረግ ያቀረበው ጥያቄ በአዲስ አበባ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ።

መስተዳድሩ-ለፓርቲው በጻፈው ደብዳቤ- መድረክ ለእሁድ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓመተ ምህረት ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6 ፡00 ሰዓት የሚቆይና ከስድስት ኪሎ ተነስቶ በአራት ኪሎ፣ በፒያሳና በቸርችል ጎዳና በማድረግ  መዳረሻው ድላችን ሐውልት የሚያደርግ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ያቀረበውን ጥያቄ እንደተመለከተው በመጥቀስ፤ሰላማዊ ሰልፉ የሚደረግበት የጉዞ መስመር  በአሁኑ ጊዜ እየተዘረጋ ባለው የባቡር መስመር የትራፊክ መስመር እየተጨናነቀ ስለሆነ ለሰልፉ እውቅና እንዳልሰጠ ገልጿል።
በደብዳቤው ከምኒልክ አደባባይ እስከ አትክልት ተራ ድረስ ያለው  መንገድ በባቡር መንገድ ሥራ በመዘጋቱ አሁን ያለው ብቸኛ መንገድ የፒያሳና የቸርችል ጎዳና ነው ያለው መስተዳድሩ፤እንዲሁም ከመገናኛ ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ በመዘጋቱና ለሰልፉ የተመረጠው መንገድ ማስተንፈሻ በመሆኑ ፤ከዚህም በላይ በአካባቢው የመንግስት ተቋማትና ሆስፒታሎች ስለሚገኙና እነዚህም ስፍራዎች በአዋጁ የተከለከሉ በመሆናቸው ለሰላማዊ ሰልፉ እውቅና ለመስጠት አንችልም ብሏል።
የመድረክ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ መንግስት ሰላማዊ ሰልፉን መከልከሉን አረጋግጠዋል

torsdag 11. juli 2013

በኢትዮጵያ የ35 ሀገራት አምባሳደሮች የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርን ጠርተው አነጋገሩ

በአሜሪካን ኤምባሲ በተካሄደው የአምባሳደሮቹ ስብሰባ ላይ በቅርቡ የተመሰረተውንና በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች የተገኙበትን ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ የቻለውን ሰማያዊ ፓርቲን ብቻ ጠርተው አነጋግረዋል።
በተለምዶ ‘‘የኢትዮጵያ ለጋሾች ቡድን’’ የሚል መጠሪያ ያለውና የአሜሪካንን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች በአባልነት የሚገኙበት የለጋሾች ቡድን በተለያዩ ጊዜያት በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ ከፍተኛ የተቃዋሚ አመራሮች ጋር በሀገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የሚያወያዩ ሲሆን  የአምባሳደሮቹ ቡድን ትናንት በአሜሪካ ኤምባሲ ባካሄደው ስብሰባ ላይ ሰማያዊ ፓርቲ
በተለየ ሁኔታ መጋበዙን የፓርቲው  ሊቀመንበር  ገልፀዋል።
ኢንጂነር ይልቃል በፓርቲው የፖለቲካ መርሀ ግብሮች እና በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለ1 ሰአት ከ30 ደቂቃ  ያክል ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል

አንድነት ፓርቲ በደሴና በጎንደር በመጪው እሁድ ለሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳውን ቀጥሎአል

በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ የኑሮ ውድነት እና የፍትህ እጦት ለመቃወም ፓርቲው በጎንደርና በደሴ የጀመረውን ቅስቀሳ ወረቀቶችን በመበተን፣ እና በመኪና ላይ በመሆን በየሰፈሩ በመዘዋወር በድምጽ ማጉያ የትግል ጥሪ እያስተላለፈ ነው።
በደሴ ከተማ በማስተባበር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሃንና የፍኖት ነጻነት ጋዜጠኛ የሆነዉ አቶ ወንደወሰን ክንፈ ታግተው መለቀቃቸውን ከፓርቲው ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የደሴ ከንቲባ በመጪው እሁድ ምንም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይደረግ ቢከለክልም አቶ ዘካርያስ የማነብርሃን ግን ተቃውሞውን ከማድረግ የሚከለክላቸው ነገር እንደሌለ ገልጸዋል
በተመሳሳይ ዜናም በአዲስ አበባ ቄራ አካባቢ የፓርቲውን  ወረቀቶች በትነዋል የተባሉ አቶ ዳንኤል ፈይሳ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮልና አቶ አበበ ቁምላቸው ተይዘው ከታሰሩ በሁዋላ  ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ፖሊስ “አንድነት የሚባል ፓርቲ መኖሩን እስከማረጋገጥ ድረስ የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ” በማለት ፍርድ ቤቱን የጠየቀ ሲሆን፣ ፍርድቤቱም የፖሊስን ጥያቄ ተቀብሎ የ10 ቀናትየጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል።  እስረኞቹም ወደ ማረሚያ ቤት ተልከዋል።
በየካ ክ/ከተማ ደግሞ አቶ ብሩክ አሻግሬ እና አቶ ወንድይፍራው ተክሌ የተባሉ የፓርቲው አመራሮች ታስረው በዋስ መለቀቃቸው ታውቋል።

onsdag 10. juli 2013

በቁጫ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የታሰሩ ሰዎች ቁጥር ከ450 በላይ መድረሱ ታወቀ

ምንጮች እንደገለጡት ካለፈው አርብ ጀምሮ ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ተቃውሞ ከ470 ያላናሱ ሰዎች እስከ ትናንት ድረስ ተይዘው የታሰሩ ሲሆን፣ ተቃውሞውን አስተባብረዋል ከተባሉት መካከል በዋና ከተማዋ ሰላም በር የሚኖሩ ከ13 በላይ የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች ተመርጠው ወደ አርባ ምንጭ እስር ቤት መወሰዳቸው ታውቋል።
ወደ  አርባምንጭ እስር ቤት ከተላኩት መካከል አቶ አማኑኤል ጎቶሮ ፣ ደፋሩ ዶሬ ፣  እዮብ ጦና፣  ሻምበል ሻዋ፣ አልመሳ አርባ፣ አቶ ባንቲርጉ ሄባና፣ ወ/ሮ ጊፍታነህ ፈርአ፣ ባሻ ፋንታሁን ታደሰ፣ አቶ አበራ ገ/መስቀል፣ መ/ር ዶለቦ ቦንጃ ፣ መምህር መሸሻ ማላ፣ አቶ ጴጥሮስ ሀላላ እና አቶ ቲንኮ አሻንጎ ይገኙበታል።
የወረዳው ፖሊስ በዛሬው እለት 15 የሚሆኑ ወጣቶችን ከእስር ለመልቀቅ መፈለጉን ቢያስታውቅም፣ “እስረኞቹ ግን መጀመሪያውኑ ለምን አሰራችሁን አሁንስ በምን ምክንያት ትለቁናላችሁ” የሚል ጥያቄ በማቅረባቸው እስካሁን እንዳልተለቀቁ ታውቋል።
በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው በከተማዋ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ተወካይ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እንደተናገሩት ፖሊስ ምግብ ከሚያቀብሉ ሴቶች እና ልጆች  በስተቀር ሌሎች ነዋሪዎች ወደ አካባቢው እንዳይጠጉ በመከልከሉ የእስረኞችን ቁጥር በትክክል ለማወቅ እንዳልተቻለ ተናግረዋል። ይሁን እንጅ ከ470 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን መረጃ እንደደረሳቸው ገልጸዋል።
ኢሳት ከ86  በላይ የታሰሩ ሰዎች ስም ዝርዝር ደርሶታል።  ከእስረኞች መካከል የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው በሙያቸው ረዥም ዓመታትን ያገለገሉ  ከ22 የማያንሱት ደግሞ የኢህአዴግ አመራር አባላት የነበሩ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ ደግሞ ነጋዴዎች፣ ተማሪዎች፣ ሥራ አጦች፣ የዩንቨርሲቲና የኮሌጅ ሌክቼሬሮች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፤ የከተማ ነዋሪዎች ናቸው፡፡
አካባቢው ዛሬም በመከላከያ እና በልዩ ፖሊስ አባላት እየተጠበቀ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል
እሁድ ሰኔ 30፣ 2005 ዓም በደቡብ ክልል በጋሞ ጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ በሰላም በር ከተማና አካባቢዋ የሚኖሩ ከ7 ሺ በላይ ነዋሪዎች፣ የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው የታሰሩ መሪዎቻችን ይፈቱትልን የሚል ጥያቄያቸውን በወረዳ ጽህፈት ቤት ተገኝተው ለማቅረብ በተጓዙበት ወቅት የዞንና የወረዳ ፖሊሶች በነዋሪዎቹ ላይ ድበደባ መፈጸማቸውን እና በመቶዎች የሚቆጠሩትን ማሰራቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

fredag 5. juli 2013

በግብጽ ፕሬዚዳንት ሙርሲ በህዝብ እና በወታደራዊ ግፊት ስልጣናቸውን ካጡ በሁዋላ አገሪቱ መስቀለኛ መንገድ ላይ እንደምትገኝ እየተነገረ ነው


ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሙርሲ ፍትሀዊ እና ግልጽ በሆነ ምርጫ ተመርጠው ለአንድ አመት ያክል በስልጣን ላይ ከቆዩ በሁዋላ በህዝብ ተቃውሞና በወታደራዊ ግፊት ከስልጣን እንዲወርዱ ተደርጓል።

ፕሬዚዳንቱ በአንድ አመት የስልጣን ጊዜያቸው ፣ እርሳቸውን ለስልጣን ያበቃውን የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ አባላትን ከመጥቀም ባለፈ የፈየዱት ነገር የለም በሚል ተደጋጋሚ ተቃውሞ ሲቀርብባቸው ቆይቷል። በአገሪቱ ውስጥ እየተስፋፋ የመጣውን ስራ አጥነት፣ የኑሮ ውድነት እና የጸጥታ ችግር ተከትሎ በርካታ የግብጽ አብዮታዊ ወጣቶች ” ለዚህ ነበር የታገልነው” በማለት ቅሬታቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል።

ፕሬዚዳንቱ አንደኛ አመት የስልጣን ጊዜያቸውን ለማክበር ሽር ጉድ በሚሉበት ጊዜ “ታማሮድ” ወይም አመጸኞች በማለት ራሳቸውን ሰየሙ የግብጽ ወጣቶች ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን እንዲነሱ የሚጠይቁ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ፊርማዎችን ከመላው አገሪቱ አሰባሰቡ። ከፊርማ ባለፈ ተቃውሞአቸውን በአደባባይ ማሰማት ጀመሩ። ሺዎች ወደ አደባባይ ጎረፉ።

 የህዝቡን ስሜት የተረዱ የሚመስሉት ወታደራዊው አዛዥ ጄኔራል አብዱል ፋታህ አል ሲሲ ፕሬዚዳንቱ የተቃዋሚዎችን ድምጽ እንዲሰሙ ጠየቁ። ፕሬዚዳንቱ በመጀመሪያ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነቱን እንዳልወደዱት ቢገልጹም፣ በሁዋላ ሁኔታው እየገፋ መሄዱ ስላሰጋቸው ጥምር መንግስት የማቋቋም ሀሳብ አቀረቡ። ተቃዋሚዎች ግን የሚቀበሉት ሆኖ አልተገኘም።

በኢትዮጵያ ፓርላማ ብቸኛ የመድረክ/አንድነት ተመራጭ የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ የብሮድካስት ባለሥልጣን በጀቱ እንዲቀነስና እንዲፈርስ ላቀረቡት ሞሽን (የውሳኔ ኃሳብ) ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ በቂ ምላሽ ሳይሰጡ ቀሩ፡፡


onsdag 3. juli 2013

ሩሲያ ተዋጊ ጄቶችን ለኢትዮጵያ ለመሸጥ እየተደራደረች ነው


አር አይ ኤ የተባለው የዜና ማሰራጫ የሮስቦሮን ኤክስፖርት አርምስ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑትን አሌክሳንደር ሚካሄቨን ጠቅሶ እንደዘገበው ሩሲያ 18 ኤስ ዩ 30 ከ የተባሉ የጦር ጄቶችን ለኢትዮጵያ ለመሸጥ በድርድር ላይ ናት።

ጄቶችን ለመሸጥ ከኢትዮጵያ ጋር እየተነገጋገርን ነው። የጄቶችን ቴክኒካዊና ታክቲካዊ ብቃት ከፍ ለማድረግ እንዲሁም ከአየር ወደ ምድር የሚወነጨፉ ሚሳኤሎችን እንዲሸከሙ ለማድረግ ሀሳብ አቅርበናል። ብለዋል ምክትል ዳይሬክተሩ።

የኢትዮጵያ መንግስት ስምምነት ላይ ከደረሰ ዘመናዊ ጄቶችን በሚቀጥሉት 4 ወይም 6 ወራት ውስጥ እንደሚያቀርቡ ባለስልጣኑ ገልጸዋል።

ዘገባው የጄቶቹን ዋጋ አላስቀመጠም።

tirsdag 2. juli 2013

መንግስት በእስራኤል አገር የሰለጠኑ የደህንነት ሀይሎችን አሰማራ



የኢትዮጵያ የብሄራዊ ጸጥታና  ደህንነት መስሪያ ቤት በእስራኤል አገር በታል አራድ ኔጊቭ ማሰልጠኛ ጣቢያ ያሰለጠናቸው  987 የደህንነት ሰራተኞች በመላ አገሪቱ በሚገኙ 572 ታላላቅ መስጊዶች እና በቴሌኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት ማሰማራቱን ከደህንነት መስሪያ ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል ፡፡

ከሰልጣኞች መካከል 11 ዱ ብቻ የእስልምና እምነት ተከታዮች ሲሆኑ ቀሪዎቹ አረብኛ  አቀላጥፈው የሚናገሩ ፣ ቁራንን በስርዓት የተማሩ እና እስልምናን ስርዓቶች ሙሉ በሙሉ የሚፈጽሙ ናቸው፡፡

ቀሪዎቹ ሰልጣኞች በቴሌ ኮሚኒኬሸን መስሪያ ቤት የተመደቡ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ በስልክ ጠለፋ  ስራ ላይ ይሰማራሉ፡፡

ከሰልጣኞች መካከል 631 ዱ የትግራይ ብሄር ተወላጆች ሲሆኑ፣ በትምህርት ደረጃም የ2002 ምሩቃን በብዛት ይገኙበታል።
በቴሌ የተቀጠሩት አዲሶቹ የደህንነት ሰራተኞች መንግስት ከፈቀደላቸው ውጭ ሌላ የስልክ ግንኙነት የተጠቀሙትን ሚኒስትሮች በድምጽ እንዲለዩ በተሰጣቸው ፈተና መሰረት የተወሰኑ ሚኒስትሮችን ስም ዘርዝረው አቅርበዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ከሰተ ብርሃን አድማሱ፣ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር አቶ ሙክታር ከድር፣ የንግድ ሚኒስትርነት አቶ ከበደ ጫኔ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደርና ሪፎርም ዘርፍ (ክላስተር) አስተባባሪ  አቶ ሙክታር ከድር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታው አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ፣እንዲሁም  የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል መንግስት ከፈቀደላቸው የስልክ ግንኙነት ውጭ በራሳቸው መንገድ ስልክ ሲያወሩ ተገኝተዋል ።

ባለስልጣኖቹ በእነዚህ ስልኮች ተጠቅመው የተናገሩት በ ዶ/ር ደብረ ጽዩን አማካኝነት ወደ መረጃ እና ደህንነት ቢሮ መተላለፉ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ኢሳት መንግስት በእስራኤል አገር ልኮ ያሰለጠናቸውን የደህንነት ሰራተኞች እውነተኛ ስም እና ዝርዝር ታሪክ አስፈላጊ ነው ብሎ በሚያምንበት ጊዜ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ለማስታወቅ ይወዳል፡፡