onsdag 30. april 2014

አንድነት – የአንድነት መግለጫ የዞን ዘጠኝ እስረኞችን በተመለከተ


1zone9
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
———————————————————–
የኢህአዴግ መንግስት በሚቃወሙትና በሚተቹት ላይ እየወሰደ ያለውን አፈና እና እስር የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲታገለው ጥሪ እናቀርባለን!!!
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
ፓርቲያችን አንድነት አበክሮ በተደጋጋሚ እንደገለፀው ኢህአዴግ ያነበረው አምባገን እና ክፉ ስርዓት ዜጎች በተለያየ ጊዜ የሚያነሱትን የሰብዓዊ መብት፣ የዴሞክራሲና የፍትህ ጥያቄ የሚቀለብሰው ወታደራዊ አቅሙን በመጠቀም ነው፡፡ በዚህ ህገ-ወጥ አካሄዱም ስርዓቱን ይቀናቀናሉ የሚላቸውን ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ሰዎችና በግለሰብ ደረጃ ተቃውሞ የሚያሰሙ ዜጎችን የተለያየ ስም እየሰጠ ወደ እስር ቤት አውርዷል፡፡ እያወረደም ይገኛል፡፡ በርካታ ዜጎች የአስከፊው ስርዓት ሰለባ ሆነዋል፣ እየሆኑም ነው፡፡ ሀገራችን በመነጋገርና በመደማመጥ ችግራችንን የምንፈታባት እንዳትሆን ሆን ተብሎ ለዘላለም መንገስ በሚፈልጉ ባለጊዜዎች የፊጥኝ ታስራ፤ ዜጎቿ እንደቀደመው ስርኣት ሁሉ በእስር እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡
እንደዜጋም በታላቋ ሀገራችን በሰቆቃ እንድንኖር ተፈርዶብናል፡፡ ኢህአዴግ ዛሬም ከመንገድ አፍሶ መውሰዱን ቀጥሏል፡፡ ማሰቃየቱንና ማንከራተቱን ገፍቶበታል፡፡ ከጊዜና ሁኔታዎች እንደመማር ዛሬም ለስርዓቱ አደጋ ናቸው የተባሉ ወጣቶች ሰበብ እየተፈጠረ ወደ ማሰቃያ ስፍራ እየተጋዙ ነው፡፡ የገዥው ፓርቲ አፈ-ቀላጤ በሆኑ ሚዲያዎች የታሰሩት ክስና ወደፊት የሚታሰሩት እነማን እንደሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡ ወጣት አመራሮቻችንና አባላትን የማሸማቀቅ ስራ እየተሰራም ነው-ስራ ከሆነ፡፡
የኢህአዴግ መንግስት ሰሞኑንም በግል ተነሳሽነታቸው ለሀገራቸው አስተዋፅኦ ለማድረግ ወስነው በብዕራቸው የሰብኣዊ መብት እንዲከበርና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲረጋገጥ በሚወተውቱ የነበሩ የዞን ዘጠኝ አባላትና ጋዜጠኞች ላይ የወሰደው የእስር ርምጃ የሚያመለክተው በቀጣዩ አመት የሚካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ የተወሰደ የማሸማቀቅና የወጣቶችን ጥያቄ ለመቀልበስ የሚፈልገው የአምባገነኑ ስርዓት ተግባር ነው፡፡
ፓርቲያችን ሚያዝያ 17 ቀን 2006 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ዞን 9 በተሰኘ ድረ ገጽ (ብሎግ) ላይ በሳል ፖለቲካዊና ማህበራዊ ትችቶችን በማቅረብ ከሚታወቁትን ወጣት ጋዜጠኞች ማህሌት ፋንታሁን፣ በፍቃዱ ሀይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ዘላለም አጥናፍ ብርሀን፣ አቤል ዋበላ እንዲሁም ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣ ጋዜጠኛ አስማመው ኃ/ጊዎርጊስ እና ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የሚሸረሽር እንደሆነ እናምናለን፡፡ አፈናው ግን ሌሎችን በሺዎች የሚቆጠሩ ብሎገሮችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን እንደሚፈጥር አንጠራጠርም፡፡
የኢህአዴግ መንግስት የከፈተው የእስር ርምጃ በአስቸኳይ እንዲያቆምና የታሰሩትም ታሰሩ ከተባለበት ሰዓትና ደቂቃ ጀምሮ የሚገኙበትን አጠቃላይ ሁኔታ እንዲጣራ፤ መንግስት ያሰረበትን ተጨባጭ ማስረጃ ካለ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ፤ ያ ካልሆነ ግን እስረኞቹን በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ እናሳስባለን፡፡ ፓርቲያችን ዘላቂው መፍትሄ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመፍጠር የሚደረገውን ትግል አፋፍሞ መቀጠልና በሰላማዊ ትግል አምባገነኑን ስርኣት ማስወገድ ብቻ እንደሆነ ያምናል፡፡
ድል የህዝብ ነው!!!

tirsdag 29. april 2014

በገንዳሆ ከተማ በህዝቡና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት 4 ሰዎች ተገደሉ

በሰሜን ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ በገንዳሆ ከተማ አንድ በጉምሩክ በኩል ውክልና ያለው የፌደራል ፖሊስ አንዱን የባጃጅ ሹፌር ” ኮንትሮባንድ ጨርቅ ጭነሃልና ጉቦ ሰጥተኸኝ እለፍ” በማለቱና ሾፌሩም “ለዚህ ለማይረባ ጨርቅ ጉቦ አልከፍልህም” የሚል መልስ በመስጠቱ ፖሊሱ ሾፌሩን ተኩሶ መግደሉን የአካባቢው ነዋሪዎች  ገልጸዋል።
በድርጊቱ የተበሳጨው የገንዳውሃ ህዝብ ወደ ወረዳው ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ  ገዳዩ ለፍርድ እንዲቀርብ ጠይቋል።  የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤትም “ጉዳዩ እኛን አይመለከትም ወደ ፌደራል ፖሊስ ሄዳችሁ ጠይቁ” የሚል መልስ መስጠቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ህዝቡ ወደ ፌደራል ፖሊስ ጽ/ቤት በሚሄድበት ጊዜ ፣ ፖሊሶች በከፈቱት ተኩስ 3 ሰዎች ወዲያውኑ ሲገደሉ፣ 3 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ቆስለው ወደ ጎንደር ሆስፒታል ተወስደዋል።
ውጥረቱ አሁንም እንዳለ ሲሆን፣ የአካባቢው  ህዝብ በነገው እለት ተቃውሞ ለማድረግ እየተዘጋጀ መሆኑን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል
በጉዳዩ ዙሪያ የወረዳውን ፖሊስ ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

በዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና በጋዜጠኞች ላይ የተወሰደው የእስር እርምጃ እንዳሣሰበው ሲ.ፒ.ጄ ገለጸ።

                                        
ዓለማቀፉ የጋሴጠኞች ተንከባካቢ ድርጅት(ሲፒጄ)  ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ሰሞኑን በ9 ጸሀፍያን ላይ የወሰደው የእስር እርምጃ፤ ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ ከተቃጡ የከፉ እርምጃዎች አንዱ ነው ብሏል።
“የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በሰላማዊ መንገድ ሀሳብን መግለጽን እንደወንጀል እየቆጠሩት ነው” በማለት ነው -የሲፒጄ የምስራቅ አፍሪቃ ወኪል-ቶም ሩድስ-እርምጃውን የኮነኑት።
እሁድ ዕለት የመንግስት አቃቤ ህግ በ አዲስ ጉዳይ ዋና አዘጋጅ በ አስማማው ሀይለጊዮርጊስ፣ በፍሪላንስ ጋዜጠኞቹ በተስፋለም ወልደየስ እና በ ኤዶም ካሣዬ፣ እንዲሁም በጦማርያኑ በ አቤል ዋቤላ፣በ አጥናፍ ብርሀኔ፣በማህሌት ፋንታሁን፣ በዘላለም ክብረት እና በበፈቃዱ ሀይሉ ላይ  ከውጪ ድርጅቶች ጋር ይሠራሉ፣ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀምም በሀገሪቱ አለመረጋጋት እንዲፈጠር ይንቀሳቀሳሉ.. የሚል ክስ እንደመሰረተባቸው ሲፒጄ አውስቷል።
ተስፋለም፣አስማማውና ዘላለም ለፊታችን ሚያዚያ 28 ቀሪዎቹ ደግሞ ለሚያዚያ 29 እንደተቀጠሩ ከሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች የደረሰውን መረጃ ዋቢ አድርጎ የጠቀሰው ሲፒጄ፤ በታሳሪዎቹ ላይ እስካሁን መደበኛ ክስ እንዳልተመሰረተ ጠቁሟል።
ሲፒጄ በመግለጫው-ፀሀፊዎቹ ዞን ዘጠኝ ተብሎ የሚጠራ የገለልተኛ አክቲቪስቶች ስብስብ አባል ሆነው የተለያዩ ዜናዎችንና ጽሑፎችን ይጽፉ እንደነበር  አመልክቷል።
“ዞን ሰጠኝ የተሰኘው ስያሜ ከቃሊቲ የተገኘ  መሆኑና  የጸሐፊዎቹ  መሪ ቃል፦”ስለሚያገባን እንጦምራለን” የሚል  መሆኑ በሲፒጄ መግለጫ ተመልክቷል።
ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ የታሰሩት ከደህንነቶች በሚደርስባቸው ወከባ ምክንያት ላለፉት ሰባት ወራት ዘግተውት የቆዩትን የፌስቡክ ገፃቸውን ዳግም በከፈቱ ማግስት መሆኑን እንደተረዳም የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ተቋሙ ገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት ጌታቸው ረዳ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ፦”የታሰሩት ጋዜጠኞች አይደሉም፤ እስሩ ከጋዜጠኝነት ሥራቸው ጋር የተገናኘ አይደለም። ከከባድ ወንጀል ጋር የተገናኘ ነው” ማለታቸውን ሲ.ፒ.ጄ ጠቁሟል።
“በጋዜጠኝነት ወይም ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት ላይ የቃጣነው በትር የለም። ሆኖም ማንም ቢሆን ሙያውን ሽፋን በማድረግ ወንጀል ለመፈፀም ሲሞክር በህግ ይጠየቃል” ሲሉም አክለዋል-አቶ ጌታቸው ረዳ።
“የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ወደለየለት ፈላጪ ቆራጭ አገዛዝ  ማዘንበላቸውን እንዲገቱና በሀገሪቱ  ነፃ ሀሳቦች ይንሸራሸሩ ዘንድ እንዲፈቅዱ ጥሪ እናቀርባለን” ብለዋል-ሚስተር ቶም ሩድስ።
የታሰሩት 9ኙም ጸሀፊዎች በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል። ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቋም ሂውማን ራይትስ ዎችና ሌሎች ድርጅቶችም የ ኢትዮጵያ ባለስልጣናት በጦማርያኑ እና በጋዜጠኞቹ ላይ የወሰዱትን እርምጃ በማውገዝ ፤ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ዛሬ አዲስ አበባ የሚገቡት የ አሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ  እስረኞቹን እንዲፈታ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቋል።
የተለያዩ ዓለማቀፍ የሚዲያ ተቋማትም ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስት በ9ኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላይ የወሰደውን የማሰር እርምጃ ሽፋን ሰጥተውታል።
ከሚዲያ ተቋማቱ መካከል ኤ.ቢ.ሲ ኒውስ፣ ሲ ኤን.ኤን፣ ዋሽንግተን ፖስት፣ ሬውተርስ፣ እና አልጀዚራ ይገኙበታል።
እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በጉብኝታቸው ስለታሰሩት ጦማርያን እና ጋዜጠኞች አጠንክረው እንደተናገሩ  የኒውዮርክ ታይምሱ ታዋቂ አምደኛ  ኒኮላስ ክሪስቶች ለሰጣቸው አስተያዬት፤ “ በጣም  ጠቃሚ ጉዳይ ነው። ዩናይትድስቴትስ  በመላው ዓለም ላይ የፕሬስ ነፃነትን በመደገፍና ከጥቃት በመከላከል ባላት ጠንካራ አቋም ትቆያለች” በማለት ምላሽ ሰጥተውታል።

mandag 28. april 2014

ኢትዮጵያ የታሰሩ ጋዜጠኞችና ጸሃፊዎችን እንድትፈታ ሂውማን ራይትስ ወች ጠየቀ


መንግስት ተጨባጭ ማስረጃ እስካላመጣ ድረስ ከ3 ቀናት በፊት ያሰራቸውን 3 ጋዜጠኞች እና 6 ጸሃፊዎችን በአስቸኳይ እንዲፈታ የሰብአዊ መብት ድርጅቱ አሳስቧል፡፡
ኢትዮጵያን የሚጎበኙት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጆን ኬሪ ፍትሃዊ ባልሆነ ዳኝነት በእስር የሚሰቃዩ ጋዜጠኞች እንዲሁም ያለበቂ ማስረጃ የሚታሰሩት ጋዜጠኞች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እንዲፈቱ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲያሳድሩ ሂውማን ራይትስ ወች ጠይቋል።
የሂውማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ዳይሬክተር ሌስሌ ሌፍኮ “የ9ኙ ሰዎች መታሰር መንግስትን የሚተቹ ሁሉ አፋቸውን እንዲዘጉ እንደሚደረጉ ማሳያ ነው” ብለዋል።
ዞን 9 እየተባለ የሚጠራ የፌስ ቡክ አካውንት በመክፈት ጽሁፎችን ሲጽፉ ከነበሩት ወጣቶች መካከል በፈቃዱ ሃይሉ፣ አጥናፍ ብርሃኔ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ዘላለም ክብረት እና አቤል ዋቤላ ከስራ ቦታቸውና ከመንገድ ላይ ታፍሰው መታሰራቸውን፣ ጋዜጠኛ ተስፋ አለም እና ኤዶም ካሳየም እንዲሁ ፖሊስ ወደ ማእከላዊ እስር ቤት ተወስደው መታሰራቸውን ድርጅቱ ገልጿል። የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ዋና አዘጋጅ አስማማው ሃይለ ጊዮርጊስም እንዲሁ ወጣቶቹ በታሰሩ ማግስት መታሰራቸውን በመግለጫው ጠቅሷል።
በእስር ላይ የሚገኙት ወጣቶች ከማንም ጋር እንዳይገናኙ ተደርጎ የታሰሩ በመሆኑ ለጥየቃ የሄዱ ቤተሰቦች ሳያገኙዋቸው ቀርቷል።
ዞን 9 እየተባሉ የሚጠሩ ወጣቶች ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ የሆነ ማስፈራሪያ ሲደርስባቸው ነበር።
ሂውማን ራይትስ ወች የኦባማ አስተዳደር በኢትዮጵያ ስለሚታየው የሰብአዊ መብት ጥሰት ምንም አለማለቱን ወቅሷል።
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ) ባወጣው መግለጫ ደግሞ መድረኩ እስካሁን በሰበሰበዉ መረጃ መሰረት ወጣቶቹን ለእስር የሚያበቃ ምን ም አይነት ማስረጃ ለማግኘት አለመቻሉን ገልጿል።
ለእስር ከመዳረጋቸው በፊት ከመንግስት ሲርስባቸዉ በነበረዉ ህገወጥ ድርጊቶች ምክንያት ለረጅም ጊዜ ስራቸዉን ካቋረጡ በኋላ በቅርቡ ወደ ስራ መመለሳቸዉን ይፋ አድርገው እንደነበር ከድረገጻቸው ላይ ለመረዳት መቻሉን ኢጋመ ጠቅሷል።
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ መንግስት ታሳሪዎቹን ለማሰር ያበቃዉ ተጨባጭ ማስረጃ ካለ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ፤ ያ ካልሆነ ግን እስረኞቹን በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ ጥያቄ አቅርቧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለገዢው ፓርቲ ቅርበት አለው የሚባለው ዛሚ ኤፍኤም 90.7 ከዞን 9 ጋር በተያያዘ የታሰሩ ጸሃፊዎችና ጋዜጠኞች ላይ የተጀመረው እስር በሌሎችም ላይ እንደሚቀጥል የሚያረጋግጥ ዘገባ አቅርቧል፡፡
ሬዲዮው ከፖሊስ ታማኝ ምንጮቼ አገኘሁት ባለው መረጃ መሠረት ከዞን 9 ጋር በተያያዘ የታሰሩ ብሎገሮችና ጋዜጠኞች በህቡዕ ተደራጅተው መንግስትን በአመጽ ለመጣል ማሴራቸውን፣ እንዲሁም ማናቸውንም ዓይነት ሰላማዊ ሰልፎች እንዲካሄዱና በሰልፎቹ ላይ መንግስትን ለመቃወም ስልጠናዎችን በውጪና በአገር ውስጥ መውሰዳቸውን አትቷል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ ጤናን የሚመለከት ሰልፍም ቢሆን እንዴት ወደተቃውሞ መቀየር እንደሚቻል ተጠርጣሪዎቹ ስልጠና መውሰዳቸውን ተናግራል፡፡
ሬዲዮው ከታሰሩት በተጨማሪ በሕጋዊ መንገድ በመመስረት ሒደት ላይ የሚገኘው ኢትዮጽያ የጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ) በተመሳሳይ መንገድ በውጪ አገር ከሚንቀሳቀሱ ተቁዋማት ጋር ግንኙነት እንዳለው ከፖሊስ መረጃ አግኝቻለሁ ከማለቱም በተጨማሪም በማህበሩ ላይ ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡ ይህ ሁኔታ በቀጣይ ማህበሩ ላይ ትኩረት መደረጉን እንደሚያሳይ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ጠቁመዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሚያዝያ 17 እና 18 ቀን በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩ ሦስት ጋዜጠኞችና ስድስት ጦማርያን በትላንትናው ዕለት እሑድ ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. በሶስት መዝገብ ፖሊስ ፍርድ ቤት አቅርቦአቸው የጊዜ ቀጠሮ እንደጠየቀባቸው ሪፖርተራችን ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት የላከችው ዘገባ ያስረዳል፡፡
ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት፣ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል መርማሪ ፖሊስ ያቀረባቸው በፍቃዱ ኃይሉ፣ ማህሌት ፋንታሁን አቤል ዋበላ በአንድ መዝገብ፤ ዘለዓለም ክብረት፣ ተስፋዓለም ወልደየስና አስማማው ኃይለጊዮርጊስ በሌላ መዝገብ እንዲሁም አጥናፉ ብርሃኔ፣ ናትናኤል ፈለቀና ኤዶም ካሳዬ አንድ ላይ፣ ዘጠኙም ተጠርጣሪዎች ሦስት ሦስት ሆነው ቀርበዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነን ከሚሉ የውጭ ኃይሎች ጋር በሙሉ ሐሳብና በገንዘብ በመስማማት፣ ሕዝብን የሚያተራምስና አገርና መንግሥትን የሚያፈርስ ዘገባ በኢንተርኔትና በማኅበራዊ ድረ ገጾች ያልሆነ መረጃ ማስተላለፋቸውን ፖሊስ ለፍ/ቤቱ ገልጾአል፡፡ ፖሊስ ምርመራውን ባለመጠናቀቁም የ15 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቢጠይቅም የተፈቀደለት የ10 እና 11 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ነው፡፡ እስካሁን መንግስት በተጠርጣሪዎቹ ጉዳይ በይፋ የሰጠው መግለጫ የለም፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለገዢው ፓርቲ ቅርበት አለው የሚባለው ዛሚ ኤፍኤም 90.7 ከዞን 9 ጋር በተያያዘ የታሰሩ ጸሃፊዎችና ጋዜጠኞች ላይ የተጀመረው እስር በሌሎችም ላይ እንደሚቀጥል የሚያረጋግጥ ዘገባ አቅርቧል፡፡
ሬዲዮው ከፖሊስ ታማኝ ምንጮቼ አገኘሁት ባለችው መረጃ መሠረት ከዞን 9 ጋር በተያያዘ የታሰሩ ብሎገሮችና ጋዜጠኞች በህቡዕ ተደራጅተው መንግስትን በአመጽ ለመጣል ማሴራቸውን፣ እንዲሁም ማናቸውንም ዓይነት ሰላማዊ ሰልፎች እንዲካሄዱና በሰልፎቹ ላይ መንግስትን ለመቃወም ስልጠናዎችን በውጪና በአገር ውስጥ መውሰዳቸውን አትታለች፡፡
እንደዘገባው ከሆነ ጤናን የሚመለከት ሰልፍም ቢሆን እንዴት ወደተቃውሞ መቀየር እንደሚቻል ተጠርጣሪዎቹ ስልጠና መውሰዳቸውን ተናግራለች፡፡
ሬዲዮው ከታሰሩት በተጨማሪ በሕጋዊ መንገድ በመመስረት ሒደት ላይ የሚገኘው ኢትዮጽያ የጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ) በተመሳሳይ መንገድ በውጪ አገር ከሚንቀሳቀሱ ተቁዋማት ጋር ግንኙነት እንዳለው ከፖሊስ መረጃ አግኝቻለሁ ከማለቷም በተጨማሪም በማህበሩ ላይ ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጻለች፡፡ ይህ ሁኔታ በቀጣይ ማህበሩ ላይ ትኩረት መደረጉን እንደሚያሳይ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ጠቁመዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሚያዝያ 17 እና 18 ቀን በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩ ሦስት ጋዜጠኞችና ስድስት ጦማርያን በትላንትናው ዕለት እሑድ ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. በሶስት መዝገብ ፖሊስ ፍርድ ቤት አቅርቦአቸው የጊዜ ቀጠሮ እንደጠየቀባቸው ሪፖርተራችን ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት የላከችው ዘገባ ያስረዳል፡፡
ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት፣ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል መርማሪ ፖሊስ ያቀረባቸው በፍቃዱ ኃይሉ፣ ማህሌት ፋንታሁን አቤል ዋበላ በአንድ መዝገብ፤ ዘለዓለም ክብረት፣ ተስፋዓለም ወልደየስና አስማማው ኃይለጊዮርጊስ በሌላ መዝገብ እንዲሁም አጥናፉ ብርሃኔ፣ ናትናኤል ፈለቀና ኤዶም ካሳዬ አንድ ላይ፣ ዘጠኙም ተጠርጣሪዎች ሦስት ሦስት ሆነው ቀርበዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነን ከሚሉ የውጭ ኃይሎች ጋር በሙሉ ሐሳብና በገንዘብ በመስማማት፣ ሕዝብን የሚያተራምስና አገርና መንግሥትን የሚያፈርስ ዘገባ በኢንተርኔትና በማኅበራዊ ድረ ገጾች ያልሆነ መረጃ ማስተላለፋቸውን ፖሊስ ለፍ/ቤቱ ገልጾአል፡፡ ፖሊስ ምርመራውን ባለመጠናቀቁም የ15 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቢጠይቅም የተፈቀደለት የ10 እና 11 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ነው፡፡ እስካሁን መንግስት በተጠርጣሪዎቹ ጉዳይ በይፋ የሰጠው መግለጫ የለም

lørdag 26. april 2014

Urgent action: Opposition leaders denied medical treatment (AI)


AI – Olbana Lelisa and Bekele Gerba are being denied medical treatment. The two men, political opposition leaders and prisoners of conscience, are reported to be ill in Kaliti prison, Ethiopia. Olbana Lelisa’s friends believe his condition may be life-threatening.
Several months ago Olbana Lelisa and Bekele Gerba were moved from Ziway prison south of Addis Ababa, to Kaliti prison on the outskirts of the capital city, reportedly after a doctor in Ziway referred the two men for hospital treatment.
However, since the transfer, the men have been denied access to a hospital. It is not clear what is wrong with the wo men as they have not access to a full diagnosis. Continue reading –>

fredag 25. april 2014

የአዲስ አበባ ፖሊሶች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችንና ደጋፊዎችን ለማስፈራራት ሙከራ እያደረጉ ነው



ወጣት ብርሃኑ እንዳለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር በሰልፉ ላይ አንድም ነገር ቢከሰት እንዲሁም ከተሰጣችሁ ጊዜ አንድ ማይክሮ ሰከንድ ብታልፉ ሰልፉን እንበትናለን በማለት ለማስፈራራት ሞክረዋል።
ማስፈራሪያውን የሰጡት የፖሊስ አዛዡ በስም ይታወቁ እንዲሆን ጥያቄ የቀረበለት ወጣት ብርሃኑ፣ ኮሚሽነሩ ማንነቱን የሚገልጽ መረጃ በጠረጴዛው ላይ ባለማስቀመጡ ስሙን ለማወቅ እንዳልተቻለ፣ ነገር ግን ቢሮው ውስጥ አብረው የነበሩትን ኮሚሽነር እንደሚያውቃቸው ገልጿል
ቅስቀሳው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ና የህዝቡም ማበረታቻ ጥሩ መሆኑን  የገለጸው ወጣት ብርሃኑ ፣ ነገር ግን  በቅስቀሳ ላይ የነበሩ 25 አባሎቻቸው ታስረው እስካሁን አለመፈታታቸውን ገልጿል።
ወጣት ብርሃኑ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ግብ ሳይሆን ወደ ቀጣዩ ትግል መሸጋገሪያ መሆኑን ገልጾ ፣ የአዲስ አበባ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ድምጹን ያሰማል ብሎ እንደሚያምን ተናግሯል።
ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት በደረሰን ዜና ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የሆኑት ሊቀመንበሩ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ ምክትሉ አቶ ስለሺ ፈይሳ እና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው አቶ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በፖሊስ ተይዘው ወደ እስር ቤት ተጉዘዋል። ወደ እስር ቤት እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ኢንጂነር ይልቃልን አነጋግረነው ነበር።

torsdag 24. april 2014

የካሽ ሬጅስትራር እቅድ አለመሳካቱ ተገለጸ

የገቢዎችናጉምሩክባለስልጣንነጋዴዎችየሸያጭመመዝገቢያማሽኖችን (ካሽሬጂስተር) እንዲጠቀሙናበዚሁመሠረትየሚፈለግባቸውንግብርናታክስእንዲከፍሉበማሰብከተሸጡትመሳሪያዎችመካከልየሸያጭመረጃንወደመረጃቋትየሚልኩት 12 በመቶብቻመሆናቸውንዋናኦዲተርሰሞኑንለፓርላማውባቀረበውየ2005 የኦዲትሪፖርትአስታውቋል፡፡
የሸያጭመመዝገቢያመሳሪያዎችአገልግሎትላይመዋልከጀመሩበትከ2000 እስከ 2005 ዓ.ምባሉትጊዜያትለግብርከፋዩሕብረተሰብ 82 ሺ141 የሸያጭመመዝገቢያመሳሪያዎችየተሸጡሲሆንከዚህውስጥአገልግሎትላይየዋሉት 72 ሺ964 ወይንም 89 በመቶያህሉብቻናቸው፡፡
አገልግሎትላይከዋሉትመሳሪያዎችመካከል 8ሺ755 ወይንም 12 በመቶመረጃንወደ መረጃቋትየሚያስተላልፉሲሆንየተቀሩት 64 ሺ 209 ወይንም 88 በመቶመረጃን ወደ መረጃቋትየማያስተላልፉናቸውብሎአል፡፡ በተጨማሪም 5ሺ 888 ወይንም 12 በመቶያህልየሽያጭመመዝገቢያ መሳሪያዎችከሲስተሙጋርጨርሶያልተያያዙመሆናቸውንአስቀምጦአል፡፡
ባለስልጣኑበሸያጭመመዝገቢያመሳሪያየተመዘገቡየሽያጭመረጃዎችወደመረጃመረብቋትመተላለፍናአለመተላለፋቸውን ለማወቅ በየታክስማዕከሉምሆነበዋናውመ/ቤትደረጃክትትልናቁጥጥርማድረግየሚችልበትሥርዓትአለመዘርጋቱንዋናውኦዲተርአጋልጦአል፡፡
በተጨማሪምግብርከፋዩከሸያጭመመዝገቢያመሳሪያአቅራቢዎችገዝቶከሚጠቀምባቸውመሳሪዎችበአማካይበኣመት 15 ሺ 670 የሚሆኑትበብልሽትምክንያትለጥገናየሚገቡሲሆንከዚህውስጥ 46 በመቶውበ48 ሰዓታትእንደሚጠገኑ፣የተቀሩት ግን ሳይጠገኑ እንደሚከርሙየዋናውኦዲተርሪፖርትይጠቅሳል፡፡
የሽያጭመመዝገቢያመሳሪያዎቹበየኣመቱ መታደስየሚኖርባቸውሲሆንበዚሁመሠረትከአንድኣመትበላይየሆናቸው 72 ሺ 964 ማሽኖችዓመታዊምርመራ በተሟላሁኔታእንደማይደረግላቸውናይህንንግዴታያልተወጡአቅራቢዎችየሚጠይቃቸውእንደሌለም አመልክቷል፡፡
በአገርአቀፍደረጃየሸያጭመመዝገቢያመሳሪያአቅርቦትንናአጠቃቀምንለማስፋትበተያዘውዕቅድመሰረትለ14የሸያጭመመዝገቢያመሳሪያአቅራቢዎችእናለ 7 የፊስካልፕሪንተርሶፍትዌርአቅራቢዎችየፈቃድዕውቅናመሰጠቱንከባለሰልጣኑየተገኘመረጃይጠቁማል፡፡
አንድአነስተኛየሽያጭመመዝገቢያማሽንከ8ሺእስከ 15 ሺ ብርየሚሸጥሲሆንበተለይገናበመቋቋምላይያሉታዳጊነጋዴዎችይህንንለማሟላትከፍተኛችግር እንደሚገጥማቸውየሚታወቅነው፡፡

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የመንግስታቸውን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቀረቡ

የመንግሥታቸውንየ2006 በጀትዓመትየዘጠኝወራትዕቅድአፈጻጸምበዛሬውዕለትለፓርላማያቀረቡትጠ/ሚኒስትርኃይለማርያምደሳለኝ፤የቀድሞጠ/ሚኒስትርአቶመለስዜናዊ “መሰዋት” ለኢኮኖሚዕድገቱፈታኝነበርብለዋል፡፡
ጠ/ሚኒስትሩበ2005 በጀትዓመት 11 በመቶዕድገትታስቦ 9.7 በመቶዕድገትመገኘቱንጠቅሰውዕድገቱ ከዕቅዱያነሰቢሆንምከሰሃራበታችያሉአገራትካስመዘገቡትየ5.4 በመቶዕድገትጋርሲነጻጸርእጅግከፍተኛነበርሲሉአወድሰዋል፡፡
በ2005 በጀትዓመትመጀመሪያየቀድሞጠ/ሚኒስትርአቶመለስዜናዊመሰዋትንተከትሎየነበረውየመቀዛቀዝሥጋትበዕድገቱላይአሉታዊተጽዕኖሊያሳድርየሚችልፈታኝሁኔታየነበረመሆኑይታወሳልብለዋል፡፡
ጠ/ሚኒስትሩበተለይየአቶመለስንተፈጥሮአዊሞትመሰዋዕትነትበማድረግየማቅረባቸውና  ሞታችውበአገርኢኮኖሚዕድገትላይአሉታዊተጽዕኖማሳረፉንመናገራቸው፣ሪፓርቱን በተከታተሉት የመዲናዋ ነዌረዎች ዘንድ ግንባሩየነበረውአንድሰውብቻነበርወይ?የሚልጥያቄ መፍጠን ዘጋብያችን አመልክቷል፡፡
በተጨማሪም 2005 ዓ.ምበዓለምገበያየቡናናየወርቅዋጋበከፍተኛደረጃያሽቆለቆለበትዓመትእንደነበርበሌላመልኩአገሪቱከውጪየምታስገባውየነዳጅምርቶችዋጋመጨመርአስቸጋሪ ሁኔታ ፈጥሮ እንደነበርጠቁመዋል፡፡
ከ2003 ዓ.ምጀምሮየተከሰተውንየዋጋንረትለማረጋጋትየተወሰዱእርምጃዎችአሉታዊተጽዕኖንእንዳያስከትሉበ2005 ዓ.ምከፍተኛጥንቃቄመደረጉንያስታወሱትጠ/ሚኃይለማርያምሆኖምጥንቃቄውስላመጣውውጤትሳይጠቅሱአልፈዋል፡፡
በተጨማሪምየትራንስፖርትናሎጀስቲክአገልግሎትንይበልጥቀልጣፋናውጤታማለማድረግሲባልሥራላይየዋለውየመልቲሞዳልሥርዓትበአቅምማነስምክንያትበወጪናበገቢንግድእናበኢኮኖሚእንቅስቃሴላይአሉታዊተጽዕኖፈጥሮየነበረመሆኑንምአምነዋል፡፡በ2006 በጀትዓመትዘጠኝወራትከወጪንግድየተገኘውየቡናኤክስፖርትበ25 በመቶቅናሽማሳየቱንአቶኃይለማርያምጠቅሰውበጠቅላላውየዘጠኝወራቱአፈጻጸምከዕቅዱአንጻርሲመዘንአፈጻጸሙ 63 በመቶያህልብቻመሆኑንአስታውቀዋል፡፡
አቶ ሃይለማርያም ከ5 አመቱ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ የተወሰኑትን ቀደም ብለው መሳካታቸውን አብዛኞቹን በቀሪው አንድ አመት ውስጥ ተንጠራርተው ሊደርሱባቸው እንደሚችሉና ጥቂቶች ላይ ደግሞ በተቀመጠላቸው  ግብ መሰረት ሊሳኩ  እንደማይችሉ ገልጸዋል። አቶ ሃይለማርያም በ4 አመታት ውስጥ ላማሳካት ያልቻሉዋቸውን አብዛኞቹን እቅዶች እንዴት በአንድ አመት ውስጥ እንደሚያሳኩዋቸው አልተናገሩም።
ብቸኛው የተቃዋሚ የፓርላማ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ አይሳኩም የተባሉት ጥቂቶች ፕሮጀክቶች ለምን በዝርዝር አይቀርቡም ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል። አቶ ግርማ ጥሩ እቅድ አቅዶ የአፈጻጸም ድክመት ማሳየት አያስጠይቅም ወይ ሲሉም ጠይቀዋል።
አቶ ሃይለማርያም ኢትዮጵያ ስንዴ ከመለመን ወጥታ በብዙ ቢሊዮኖች ብር እያወጣች ግንባታ የምታካሂድ አገር መሆኑዋን በመጥቀስ፣ እቅዳችን የተሳካ ነው ብለን እናምናለን ብለዋል። አቶ ሃይለማርያም ይህን ይበሉ እንጅ ኢትዮጵያ አሁንም ለ11 ሚሊዮን ህዝብ ስንዴ ከውጭ አገር በሴፍትኔት ስም ትቀበላለች።
የፓርላማ አባሉዋ ወ/ሮ አልማዝ አርአያ የመቀሌ፣ የሽሬ እና የአክሱም የውሃ ችግሮች ከክልሉ አቅም በላይ መሆኑን ገልጸዋል። የቦንጋ የውሃ እጥረትም እንዲሁ ለአመታት ጥያቄ ቢቀርብበትም መልስ አለማግኘቱ ተገልጿል።

onsdag 23. april 2014

የእውቅና ፎርም ከሞላ በኋላ፣ ሰማያዊ ለሚያዚያ 19 ሰልፍ ወደ ተግባር መሄድ እንደሚችል አስተዳደሩ ገለጸ

የአዲስ አበባ አስተዳደር ሚያዚያ 15 ቀን ለሰማያዊ ፓርቲ በጻፈው ደብዳቤ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን ሊያደርግ ላሰበው ሰላማዊ ሰልፍ፣ በአስተዳደሩ ሕጋዊ አሰራር መሰረት፣ የሚገባዉን የእውቅና ፎርሞ እንዲሞላና ወደ ቅስቀሳ እንዲሰማራ ጠየቀ። 
addis-ababa-semayawi-party
«የእወቅና ጥያቄ ፎርም ሳትሞሉ ሕጉን በመጣስ ወደ ተለያዩ የተግባር እንቅስቃሴ የገባችሁ ስለሆነ ከዚሁ ተግባራችሁ ታቅባችሁ ወደ ህጋዊ አሰራር በመግባት ማሟላት የሚገባችሁን አማልታችሁ የ ወቅና ፎርም በመሙላት ወደ ተግባር እንድትገቡ እናሳሰባለን» ሲል የገልጸው አስተዳደሩ፣ መሞላት ያለበት ፎርም ከተሞላ ሰማያዊ በሚያዚያ 19 ቀን ሰልፍ ማድረግና ለሰልፍ የሚያስፈልጉትን ተግባራት መፈጸም እንደ ሚችል ለምገልጽ ሞክሯል።
አስተዳደሩ ያለፈው ሳምንት፣ ለሰማያዊ ፓርቲ በጻፈው ደብዳቤ፣ በሚያዚያ 19 ቀን ሰልፍ ማድረግ እንደማይቻል መግለጹ ይታወቃል።
ከአዲስ አበባ አስተዳደር አካባቢ ካሉ፣ ምንጮቻችንም በደረሰን ዘገባ መሰረት፣ አስተዳደሩ ከደህንነት ሃላፊዎች በቀጥታ በደረሰዉ ትእዛዝና መመሪያ፣ ለአንድነት ፓርቲ የከለከለዉን፣ ሰማያዊ ፓርቲ ግን ሚያዚያ 19 ቀን ሰልፍ እንዲያደርግ ሊፈቅድ እንደሚችል መዘገባችን ይታወቃል።

tirsdag 22. april 2014

በአፋር የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ 8 ሰዎች በፌደራል ፖሊሶች ተገደሉ

ቁርቁራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በአፋር እና በሶማሊ ጎሳ አባላት መካከል የተነሳውን ውዝግብ ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ 8 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ሰዎች እና የአፋር ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ሲገልጽ ፣ አፋር ህዝብ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ደግሞ የሟቾቹን ቁጥር 12 አድርሶታል።
የፌደራል ፖሊስ የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ በአዋሽ ሰባት ኪሎ አካባቢ ህዝቡ ወደ ወደ አውራ ጎዳናዎች በመውጣት ወደ ጅቡቲ የሚሄዱትን መኪኖች ለ12 ሰአታት ያክል አግዷል። የአፋር ክልል ባለስልጣኖች ወደ አካባቢው በመሄድ ህዝቡን ለማነጋገር ቢኖክሩም፣ ህዝቡ ግን አትወክሉንም የሚል መለስ እንደሰጣቸው ታውቋል። 3የመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች በ10 ቀናት ውስጥ ችግሩ እንደሚፈታ ቃል ገብተው የመኪና እገታው እንደተጠናቀቀ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
አንድ ስሟ እንዳይገለጽ የፈለገች የአፋር ተወላጅ  የ85 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ 8 ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ማየቷን ከኢሳት ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ ገልጻለች አንዲት እርጉዝ ሴትም እንዲሁ ልጇን ሲገድሉባት በልጇ ላይ ስትወድቅ በእርሷም ላይ በተፈጸመ ድብደባ የእርሷም ህይወት አደጋ ላይ ወድቋል። መንግስት ሶማሊያ ገብቶ የሌሎችን ጸጥታና ሰላም ለማስከበር ሲሞክር ፣ እኛን ዜጎቹን ግን ረስቶናል በማለት አክላለች ።
የአፋር ሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪ ድርጅት ሊ/መንበር የሆኑት አቶ ገአስ አህመድ የሟቾች ስም ዝርዝር እንደደረሳቸው ገልጸው፣ ህዝቡ መንገድ ለመዝጋት የተገደደው በማቾች በመበሳጨታቸው መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ ገአስ የሁለቱን ድንበሮች ለማካለል በድሬዳዋ ስብሰባ እየተካሄ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ገአስ የአፋር ህዝብ የራሱን መብት ለማስከበር እንዲህ አይነት እምቢተኝነት አስፈላጊ በመሆኑ የ አፋር ህዝብ ትግሉን እንዲቀጥል እንዲሁም ሁሉም ፓርቲዎችና አለማቀፍ ሰብአዊ መብት ድርጅቶች ከጎናቸው ሆነው ድርጊቱን እንዲያወግዙ ጠይቀዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ሙከራ አልተሰካም።

lørdag 19. april 2014

በሱሉልታ ከተማ የአማራ ተወላጆች ናችሁ የተባሉ ተደበደቡ

ስት ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው በአዲስ አበባ የተለያዩ ሆስፒታሎች ገብተዋል
"ረብሻውን ያነሱት ህዝብን የማይወክሉ ወሮበሎች ናቸው" የከተማው ኮሙዩኒኬሽን
"ባህርዳር በተካሄደው የስፖርት ውድድር ላይ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ አድልዎ ተፈጽሟል" በማለት የተቧደኑ ወጣቶች, ባለፈው ሐሙስ የሱሉልታ ከተማ ነዋሪ የሆኑ በርካታ የአማራ ተወላጆች ላይ ድብደባ ፈፀሙ.
በድብደባ በርካታ ሰዎች ከመጐዳታቸውም በተጨማሪ; ቤት ንብረት ላይም ጥፋት እንደደረሰ የተናገሩት ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች ጉዳዩን ሕገወጥ ነው ሲሉ አውግዘውታል. የከተማዋ ኮሙኒኬሽን ጽ / ቤት ሃላፊ; የስፖርት ውድድርን ሰበብ በማድረግ ረብሻ የቀሰቀሱ ሰዎች ህዝብን የማይወክሉ ወሮበሎች ናቸው ብለዋል.
ረብሻውን ቀስቅሰዋል ተብለው ከተጠረጠሩት ውስጥ አራቱን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለም ገልፀዋል ሃላፊው. "የቤቴ በርና መስኮት እንዳልነበር ሆኗል; አጥር ተገነጣጥሏል; መስኮቶች ዱቄት ሆነዋል" ያሉት አንድ የከተማዋ የረጅም ጊዜ ነዋሪ; ከ 30 በላይ ቤቶች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል. የስድስት ልጆች እናት እንደሆኑ የገለፁልን ሌላዋ ነዋሪ; በቤታቸውና በንብረታቸው ላይ አደጋ መድረሱን ጠቅሰው; እንደሌሎች ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ባያጋጥማቸውም በእጃቸው ላይ በደረሰባቸው ጉዳት በከተማዋ አንድ ክሊኒክ ህክምና እንደተደረገላቸው ተናግረዋል.
"ይህ ህዝቡ በሰላም አብሮ እንዳይኖርና እንዳይግባባ ሆን ተብሎ የሚጫር የነገር እሳት ነው" ያሉት የ 56 አመት አዛውንት በበኩላቸው; መንግስት መፍትሔ ከላበጀለት በቀር በአሁኑ ወቅት ከየአቅጣጫው የምንሰማው በዘር ተቧድኖ ግጭት የመፍጠር ጉዳይ አስጊ ነው ብለዋል.
የከተማው አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ጽ / ቤት ሃላፊ አቶ መሳይ ከበደ; ከከተማ አስተዳደር በደረሳቸው ሪፖርት ተዘዋውረው እንደተመለከቱ ገልፀው, የተወራውን ያህል ባይሆንም የስምንት ቤቶች የበርና የመስኮት መስታወቶች ተሰባብረዋል; የቆርቆሮ አጥሮች ተገነጣጥለዋል ብለዋል. ሰዎች አራት እንደተጐዱና የሶስቱ ሰዎች ጉዳት ከፍተኛ ስለሆነ በአዲስ አበባ የተለያዩ ሆስፒታሎች ውስጥ በክህምና ላይ መሆናቸውን አቶ መሳይ ጠቅሰው; አንዲት እናት በእጃቸው ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸው በከተማው ጤና ጣቢያ ታክመው ተመልሰዋል ብለዋል.
"የረብሻው መንስኤ በቅርቡ ባህርዳር የተካሄደው የመላው ኢትዮጵያ ጫዋታዎች ውድድር ላይ በኦሮሞ ተወላጆች ላይ አድልዎና ተፅእኖ ተደርጓል የሚል ሰበብ ነው" ብለዋል አቶ መሳይ.
"በረብሻው ዙሪያ ህዝቡንና የከተማ ነዋሪውን በመሰብሰብ ረብሻውን ያስነሱት ሰዎች ህዝብን የማይወክሉ እና ህዝብን ለማጋጨት ፍላጎት ያላቸው የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች መሆናቸውን ተወያተናል" ያሉት የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊው, ህዝቡ እንዲህ ዓይነት ቡድኖችም ሆኑ ግለሰቦችን አሳልፎ እንዲሰጥ ተግባብተናል ብለዋል. ረብሻው ወዲያውኑ በፖሊሶችና ከጫንጮ በመጡ የፀጥታ ኃይሎች መቆሙን ተናግረዋል - ሃላፊው.