tirsdag 30. september 2014

ኢሕአዴግ የሰሞኑ የመምህራን ስልጠና እንዳይሳካ እንቅፋት ሆነዋል ያላቸውን 12 ወጣት መምህራን አባረረ (ዝርዝራቸውን ይዘናል)

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ድምጽ ይሰማ ለዘ-ሐበሻ በላከው ዜና መምህራንን ከስራ ቦታችው ማፍናቀል ተጀምሯል አለ። እንደ መምህራኑ ድምጽ ዘገባ 12 ወጣት መምህራን ከሥራቸው ተፈናቅለዋል።

(ፎቶ ፋይል)
ከሰሞኑ በተካሄደው ስልጠና እና ተያያዥ ጉዳዮች ከመምህራን ጋር መስማማት ያልቻልው ገዢው ፓርቲ በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተማዎቸ በመምህርነት ሙያ እያገለገሉ የሚገኙ የተለያዩ ወጣት መምህራንን ስልጠናው በተሳካ ምክንያት እንዳይካሄድ እንቅፋት በመሆን እንዲሁም በትምህርት ቤቶቸ ውስጥ ድብቅ አጀንዳ ይዛችሁ ስትንቅሳቅሱ ተገኝታችኋል በሚል ምክንያት የተነሳ ህወሀት መራሹ መንግስት የሚከተሉትን መምህራን ከሚሰሩበት ትምህርት ቤት ያለፍላጎታችው ተነስተው ወደ ገጠራማ ስፍራዎች እንዲመደቡ ተደርገዋል፡፡ እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ ባገኘው መረጃ መሰረት በግዴታ ዝውውር የተሰጣቸው መምህራን የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. መ/ር ይማም ሐሰን
2. መ/ር ሙለታ ዲንቃ
3. መ/ር ኤርሚያስ ተገኝ
4. መ/ር ሐይለ አምላክ ይገዙ
5. መ/ር ደምስ ግዛቸው
6. መ/ር አንዳርጋቸው ምህረቴ
7. መ/ር አንተነህ ንጉሱ
8. መ/ር ይስሀቅ ጉደታ
9. መ/ር መላኩ አበበ
10. መ/ር ዮሐንስ ካሳሁን
11. መ/ር ዳዊት የሺጥላ
12. መ/ር ዘሪሁን አላምረው ሲሆኑ ከትላንትናው እለት ማለትም 19/01/2007 ዓ.ም ጀምሮ ከስራ ገበታቸው ያለፍቃዳቸው መነሳታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በ2004 ዓ.ም የደመወዝ ጭማሪን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ በተመሳሳይ መንገድ በርካታ መምህራን ከስራ የመባረር እና ራቅ ወዳሉ ስፍራዎች መመደባቸው ይታወሳል።

ኢትዮጵያውያኑ ላይ የተኮሰው የኤምባሲው ታጣቂ ታሰረ! የዋሽግተኑን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተመለከተ – የጉዳያችን አጭር ዘገባ

”መሣርያውን ወደሚከራከሩት ሰዎች ደገነ እና ተኮሰ” ”He points the weapon at others who argue with him and fires” ሮይተርስ ከዋሽግተን ዲሲ ዛሬ የዘገበው።
ዛሬ መስከረም 19፣2007 ዓም ዋሽግተን ዲሲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተቃዋሚ ኢትዮጵያውያን ቁጥጥር ስር ውሎ ባለ ኮከቡ ሰንደቅ ዓላማ በነፃው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ተቀይሯል። ተቃውሞውን አስመልክቶ ኢሳት ዘግይቶ በለቀቀው ተጨማሪ ዘገባ ተቃዋሚዎቹ በኢምባሲው ውስጥ ዘልቀው የአቶ አንዳርጋቸውን እና የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ይዘው ”ነፃነት! ነፃነት!” ሲሉ አሳይቷል።
ቀደም ብሎ አምባሳደር ግርማ ብሩ በሸሚዝ እንደሆኑ ከሌሎቹ የኢምባሲው ሰራተኞች ጋር ቆመው ሲመለክቱም ሌላው የታየው ትዕይንት ነበር።ተቃውሞውን ተከትሎ የዓለም ስመጥር የዜና አገልግሎት ድርጅቶች ሮይተርስ እና የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ኤ ኤፍ ፒን ጨምሮ የቪድዮ ምንጫቸው ኢሳት የኢትዮጵያውያን ቴሌቭዥን መሆኑን ከመጥቀሳቸውም በላይ የኢሳትን ሰበር ዜና የያዘ ቪድዮ በቀጥታ ለጥፈው ታይተዋል።በመሆኑም በዛሬው እለት ኢሳት በመላው ዓለም የዜና አውታሮች የመወሳቱን ያህል ከእዚህ በፊት በእዚህ አይነት ስፋት በመላው ዓለም በሚገኙ ታላላቅ የዜና አውታሮች የተጠቀሰ አይመስለኝም።
በሌላ በኩል በአሜሪካን ሕግ ሽጉጥ ተኩሶ ማስፈራራት አይደለም በአንደበቱ ለማስፈራራት የሞከረ የሚደርስበት ቅጣት ከፍተኛ እንደሆነ ይታወቃል።ሆኖም ግን የኢምባሲው ሰራተኛ በተኮሰው ጥይት አካባቢውን በማሸበር እና በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ባሰሙ ዜጎችን በማስፈራራት ሕግ መጣሱን ለማወቅ ተችሏል።በአሁኑ ሰዓት ግን ግለሰቡ በቁጥጥር ስር መሆኑን በርካታ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች እየጠቀሱ ይገኛሉ።ሆኖም ግን ግለሰቡ የዲፕሎማቲክ ከለላ ካለው አሜሪካ በአጭር ጊዜ ከሀገር እንዲወጣ ልታደርግ ትችላለች።በመሆኑም NBC የዜና አገልግሎት የተኮሰው የኢምባሲ ሰራተኛ መታሰሩን ገልጧል።ዜናውን ይህንን በመጫን ማንበብ ይችላሉ።
ጉዳዩን ተከትሎ በነገው እለት ከኢትዮጵያ የሚወጣው መግለጫ ይዘት ከወዲሁ መገመት አያስቸግርም። ሆኖም ግን ምንም አይነት መግለጫ እና ማብራርያ ቢሰጥ በአሜሪካውያንም ሆነ በምዕራቡ ዓለም ፅንሰ ሃሳብ አንፃር ከጠቅላላ ጉዳዩ ውስጥ የኢምባሲ ሰራተኛው ምንም አይነት የጦር መሳርያ ባልያዙ በባዶ እጃቸው ተቃውሞ ባሰሙ ኢትዮጵያውያን ላይ የጦር መሳርያ በመደገን የማስፈራራቱ እና በኃላም የመተኮሱን ያህል የጎላ እና አናዳጅ ነገር ነጥሮ አይወጣም። በመሰረቱ ዜጎች የሀገራቸውን ኢምባሲ ሲቃወሙ ይህ አዲስ አይደለም።እራሷ አሜሪካ የእራሷ ዜጎች ባልሆኑ ግን በሌሎች ሀገሮች ዜጎች ኤምባሲዋ ተውሯል።
በዲፕሎማሲው ዓለም ደግሞ አንድ ኢምባሲ በራሱ ሀገር ተወላጆች በተቃውሞ ቢናጥ ጉዳዩ የዓለም ዓቀፉን የቬና ስምምነት ከመመልከት ይልቅ የአንዲት ሀገር የውስጥ ጉዳይ ገንፍሎ የመውጣት አይነተኛ አመላካች ጉዳይ ከመሆን አያልፍም።ከእዚህ በዘለለ ኢምባሲው ጉዳዩን ለፖሊስ ደውሎ እርዳታ ከመጠየቅ ይልቅ አራት ኪሎ ያለ ይመስል ዋሽግተንን በተኩስ መናጡ ነው አሜሪካኖችን የሚያናድደው።
በመጨረሻም አንድ ነገር ማንሳት ይቻላል።ባራክ ኦባማ ከአቶ ኃይለማርያም እና ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ቁጭ ብለው ካወሩ ገና ሳምንት ሊሆነው ነው።የዛሬው በመዲናቸው ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተቃውሞ ያሰሙ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ለኦባማም ጭምር የሚያስደነግጥ ነው። የኦባማ የአፍሪካ ፖሊሲ ዕውን በጥናት ላይ የተመሰረተ ነው? ላለመሆኑ ማሳያው የዛሬው ጠንካራ ተቃውሞ ነዋ! United States Secret Service police stand in front of the Ethiopian Embassy in Washington September 29, 2014.          REUTERS/Gary Cameron

የዋሺንግተን ዲሲው ተኩስ፤ ራስን ለመከላከል ወይስ ሰው ለመግደል? (አጭር ትንታኔ)

በዋሺንግተን ዲሲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ለተወሰኑ ጊዜያት በተቃዋሚዎች ቁጥጥር ስር ውሎ ነበር። በዚህ ወቅት ሰለሞን የተባለ የኢምባሲው ባልደረባ በሰልፈኞች ላይ ተኩስ ፈጽሟል። ግለሰቡ ‘የኢምባሲው ጠባቂ ነው’ ከሚል ዜና ውጪ በርግጥ የግቢው ሴኩሪቲ ለመሆኑ ተጣርቶ የታወቀ ነገር የለም። ምናልባት ይህ ግለሰብ የግቢው ዘብ መሆኑን ብንቀበል እንኳን፤ ተኩሱን የከፈተው “ራስን ለመከላከል ወይስ ሰውን ለመግደል?” የሚለውን ጉዳይ በቅርብ ተከታትሎ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ነው። እስካሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ተኩሱን በሰልፈኞች ላይ ከፍቶ የነበረው ግለሰብ ለጊዜው በፖሊስ ታስሮ መፈታቱን እዚህ ላይ ጠቅሰን እናልፋለን። 
በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተቃውሟቸውን የሚያሰሙት ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ድምጻቸውን እያሰሙ ነበር። አሁንም እንደገና ወደ ተኩሱ ጉዳይ እንመለስ። በቪዲዮው ላይ በግለጽ እንደሚታየው ሁለት ግዜ በሰልፈኞቹ ላይ ተተኩሷል። ሶስተኝውን የተኩስ ሙከራ ግን ልብ ብለው ይመልከቱ። ሰላማዊ ሰልፈኛው ላይ በቅርብ ርቀት ለመተኮስ ሲሞክር፤ ጥይቱ ከሽፎበታል። ይህ ጥይት ባይከሽፍ ኖሮ በርግጥም የሰው ህይወት ሊጠፋ እንደሚችል መገመት ይቻላል። ግለሰቡ ወደ ውስጥ የገባውም ሽጉጡ መተኮስ ስላቆመ እንጂ፤ በተለይም የመጨረሻዋ ጥይት ስለከሸፈችበት ነው የሚመስለው። በመጨረሻ በዋሺንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ግርማ ብሩ ወደ ውጭ በመውጣት የተኮሰው ግለሰብ ወደ ውስጥ እንዲገባ ሲያደርጉት ታይቷል።
በዚህ ተኩስ ምክንያት የጠፋ ህይወት ባይኖርም፤ የአንዲት ሴት መኪና የፊት መስታወት ተሰባብሯል። በዚህ ምክንያት ተኩሱን የፈጸመው ግለሰብ የሚጠየቅበት ጥፋት ይጨምራል። አሁንም ቢሆን በዋሺንግተን ዲሲ የሚገኙ አክቲቪስቶች ጉዳዩን ችላ ማለት አይገባቸውም። ኢምባሲው ክስ ሊመሰርት ይችላል የሚለውን ታሳቢ በማድረግ፤ ሳይቀደሙ መቅደም ብልህነት ነው። በመሆኑም በመጀመሪያ ደረጃ ተኩሱን የፈጸመውን ግለሰብ ማንነት አጣርቶ ማወቅ ይጠበቅባቸዋል። በኢምባሲው እና በግለሰቡ ላይ ክስ መመስረትም ሌላኛው አማራጭ ነው። በክሱ ወቅት በርግጥ ተኩስ የከፈተው ግለሰብ የስራ ቅጥር እና ድርሻው ወይም የወር ደሞዝተኛነቱ ሽጉጥ ታጥቆ ኢምባሲውን መጠበቅ መሆን እና አለመሆኑን አጣርቶ ማወቅ ያስፈልጋል። ከሁለቱ ተኩሶች በተጨማሪ የከሸፈችው ሶስተኛ ጥይት፤ ከቅርብ ርቀት ላይ ስለተተኮሰ የሰው ህይወት ሊቀጥፍ ይችል እንደነበር ታሳቢ ማድረግ አስፈላጊ ነው።
ከላይ የገለጽነው ጉዳይ እንዳለ ሆኖ፤ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ወደ ኢምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ገብተው ባለኮከቡን ባንዲራ አውርደው የኢትዮጵያን ባንዲራ መስቀላቸው የሚያኮራ ነው። ከምንም በላይ ግን ሃይል ሳይጠቀሙ በጨዋነት ሃሳብ እና ብሶታቸውን ማሰማታቸው ይበልጥ ደስ ያሰኛል። እንዲህ በሰላማዊ መንገድ በወጡ ሰልፈኞች ላይ በእብሪት ተኩስ መክፈት ግን በርግጥም ትክክል አይመስልም። በርግጥ ሰልፈኞቹ ‘ህገ ወጥ ናቸው’ ከተባለ ወይም ወደ ኢምባሲው ቅጥር ግቢ መግባታቸው ‘ትክክል አልነበረም’ ቢባል እንኳን፤ ጉዳዩን ለከተማው ፖሊስ ማሳወቅ እንጂ ተኩስ መክፈቱ ‘የመግደል ሙከራ ማድረግ’ በሚል የወንጀል አንቀጽ ስር ነው የሚወድቀው።
ወደፊት ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያያዥ ዜናዎች ካሉ፤ ይዘንላችሁ የምንቀርብ መሆኑን በማሳወቅ የዛሬውን አጭር ትንታኔ እዚህ ላይ እናበቃለን።

mandag 29. september 2014

የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ አዘጋጆች መስቀልን ከህሊና እስረኞች ጋር አሳለፉ

የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ የዝግጅት ክፍል ባልደረባ መስከረም 18/2007 ዓ.ም (መስቀልን) ቃሊቲ ከሚገኙ ታሳሪዎች ጋር አሳልፈዋል፡፡ በወቅቱም አቶ በቀለ ገርባን፣ አቶ ኦልባና ሌሊሳን፣ አዛውንቱን ሲሳይ ብርሌን፣ አቶ ጉታ ዋቆንና ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን አግኝተዋል፡፡ ነገረ ኢትዮጵያ ከታሰሪዎቹ መካከል የተወሰኑትን መልዕክት እንደሚከተለው አቅርባለች፡፡
‹‹ህብረ ብሄር ፓርቲዎች ተጠናክረው የብሄር ፓርቲዎችን ማጥፋት አለባቸው›› አቶ በቀለ ገርባ
ከዝዋይ ወደ ቃሊቲ ከመጣሁ 11 ወራት ሆኖኛል፡፡ በህዳር ወር 2006 ዓ.ም ነው ወደ ቃሊቲ የመጣሁት፡፡ በአሞክሮዬ መሰረት ጥር 11 ቀን 2006 ዓ.ም መፈታት ቢገባኝም አሁንም ድረስ እስር ቤት ውስጥ እገኛለሁ፡፡ በወቅቱ በአሞክሮዬ መሰረት መፈታት እንዳለብኝ ለእስር ቤቱ ኃላፊዎች ደብዳቤ ጽፌ ነበር፡፡ ሊፉቱ ሲፈልጉ አስጠርተው ያነጋግሩሃል፡፡ ካልፈለጉ ደግሞ ዝም ይሉሃል፡፡ እኔ ደብዳቤ ብጽፍም አልተጠራሁም፡፡ ምክንያታቸውን ባላውቅም ሊፈቱኝ አልፈለጉም ማለት ነው፡፡ ግን በአሞክሮዬ ባለመፈታቴ አልተጎዳሁም፡፡ በርካታ ነገሮችን ተምሬበታለሁ፡፡ እንዲያውም የሚጎዱት እነሱው ራሳቸው ናቸው፡፡ በርካታ ታሳሪዎች አሳሪዎቹ ለቃላቸውም ሆነ በህጉ ተገዥ እንዳልሆኑ በእኔ ጉዳይ ተምረዋል፡፡ አሁን በመጋቢት ወር ዋናውን ፍርድ ጨርሼ እፈታለሁ ብዬ እጠብቃለሁ፡፡
እኔ የማምነው በባለሙያነቴ ነው፡፡ ፖለቲከኛ ነኝ ብዬ አላምንም፡፡ እንደዛም ሆኖ ግን እንደ ግለሰብ ፍትህን እሻለሁ፡፡ ስልጣን ላይ ማንም ይምጣ ማን ፍትህን የሚሰጥ ከሆነ ችግር የለብኝም፡፡ በሙያተኝነቴ ነው መቀጠል የምፈልገው፡፡ ነገር ግን ክፍቶች አሉ፡፡ ወደ ፖለቲካው የገባሁትም ክፍተቶችን በማየቴ ነው፡፡
ህብረ ብሄራዊ የሚባሉ ፓርቲዎች ለአብዛኛው ህዝብ ተደራሽ አይደሉም፡፡ የህብረ ብሄር ፓርቲዎች ድክመት ደግሞ የብሄር ፓርቲዎች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኗል፡፡ በእነሱ መዳከም ነው የብሄር ፓርቲዎች በየ ቦታው ለመመስረት እድል የሚያገኙት፡፡ ህብረ ብሄር ፓርቲዎች የአንድን ማህበረሰብ ችግር ለመፍታት አቅም የላቸውም ብሎ ያሰበ አካል/ሰው እወክለዋለሁ በሚለው ማህበረሰብ ስም ፓርቲ ያቋቁማል፡፡ እኔም በዚህ ክፍተት ነው ወደ ፖለቲካው የገባሁት፡፡ ይህ ችግር ባይኖር ማህበረሰብን ከፋፍሎ ‹‹ይህኛው ፓርቲ የዚህ፣ ያንኛው ደግሞ የዚህኛው ማህበረሰብ ፓርቲ ነው›› ተብሎ እንዲከፋፈል ፍላጎት የለኝም፡፡
ህብረ ብሄራዊ ፓርቲዎች ቢጠናከሩ በአንድነት መታገልን የመሰለ ነገር የለም፡፡ ከአንዱ ዓለም አራጌ ጋር በታሰርንበት ወቅት ‹‹እናንተ ከተጠናከራችሁ እኛ እንጠፋለን፡፡ እናንተ ተጠናክራችሁ በብሄር የተደራጀነውን ማጥፋት አለባችሁ፡፡ ተጠናከሩና እኛን አጥፉን፡፡ ያኔ ሁላችንም በአንድነት እንታገላለን፡፡ ችግሮችም ይፈታሉ›› እለው ነበር፡፡ የህብረ ብሄራዊ ፓርቲዎች አለመጠናከር እንጅ ለዚህኛው አሊያም ለዛኛው ህዝብ ብዬ መስራት አልፈልግም፡፡ በአንድነት መስራትን የመሰለ ነገር የለም፡፡
ህብረ ብሄር ፓርቲዎች በአንድ በኩል በመረጃ እጥረት፣ በሌላ በኩል በስህተት፣ አሊያም አይቶ በማለፍ የአንድን ማህበረሰብ ችግር ችላ ይሉታል፡፡ ይህ ነው ተነጣጥሎ ለመታገል፣ ለብሄር ፓርቲዎች መበራከት ምክንያት የሆነው፡፡ ህዝብ መብቱ እስከተከበረለት ድረስ ማን መጣ ማን ትኩረት አይሰጥም፡፡ ህብረ ብሄር ፓርቲዎች መዳከም ግን የብሄር ፓርቲዎች ተደማጭነት እንዲያገኙ ምክንያት ሆኗል፡፡ አሜሪካን ለምሳሌ ብንወስድ ህዝቡ መብቱ እስከተከበረለት ድረስ ጥቁር መራ ነጭ ችግር የለበትም፡፡ የእኛ አገርም ጉዳይ ተመሳሳይ መሆን ይችላል፡፡ በዚህ ላይ እኛ ወንድማማቾች ነኝ፡፡
እኔ ህብረ ብሄር ፓርቲዎችን እወቅሳለሁ፡፡ እነሱ ከተጠናከሩ በየቦታው በተናጠል የሚደረገው ትግል ወደ አንድ ጠንካራ ትግል ይመጣል፡፡ እነሱ ከተጠናከሩ በተናጠል የሚደረገው ጭቆና ይቀንሳል፡፡ ክፍተት ባይኖርና ህብረ ብሄር ፓርቲዎች ለሁሉም ህዝብ መድረስ ቢችሉ እኔ በሙያዬ በቀጠልኩ ነበር፡፡ እንዲህ የምንታሰረውም እኩ ከድክመታችን የተነሳ ነው፡፡ ጠንካራ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ ቢኖረን እኮ እኛም አንተሰርም ነበር፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የአገራችንን ችግር መፍታት አንችልም፡፡ በተናጠል ለጭቆና እንዳረጋለን፡፡ በተናጠል እንታሰራለን፡፡ በሂደት ጭቆናውን እየለመድነው እንሄዳለን፡፡ በዚህ ሁኔታ ለውጥ ማምጣት አንችልም፡፡
‹‹ኢትዮጵያ ጭንቅ ላይ እንዳለች እርጉዝ ሴት ነች›› አቶ ሲሳይ ብርሌ
የተፈረደብኝ 13 አመት ነው፡፡ ከታሰርኩ አራት አመት ሆኖኗል፡፡ እድሜየ 65 ደርሷል፡፡ እስር ቤት ውስጥ ችግር አለ፡፡ የእስር ቤቱን ኃላፊዎች የምናገኛቸው ህክምና ስንፈልግ ነው፡፡ ነገር ግን የህክምናው ጉዳይ ባይወራ ይሻላል፡፡ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ በእርግጥ ውጭ ያለው ህዝብም በሰፊው እስር ቤት ውስጥ እንዳለ ነው የሚቆጠረው፡፡ ልዩነቱ የተሻለ ነፋስ ስለምታገኙ፣ ስለምትዘዋወሩና የፈለጋችሁትን ሰውም ስለምታገኙ ነው፡፡
እኛ እያረጀን ነው፡፡ ከእድሜያችን አንጻር በትግሉ ሂደት ብዙም የምንጨምረው ነገር ላይኖር ይችላል፡፡ እናንተ ወጣቶች ናችሁ፡፡ ለትግሉ መሰረት የምትጥሉበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ወጣትነት ለትግል ወሳኝ ጊዜ ነው፡፡ አባት ያላወረሰውን ልጅ ሊያስቀጥል አይችልም፡፡ እናንተ አሁን ለራሳችሁ ብቻ ሳይሆን ለልጆቻችሁም ጭምር ነው የምትታገሉት፡፡ እናንተ በርትታችሁ ካልታገላችሁ ልጆቻችሁ ምንም የሚወርሱት ነገር አይኖርም፡፡ አባት ያላወረሰውን ደግሞ ልጅ ምንም ነገር ሊያስቀጥል አይችልም፡፡ በመሆኑም እናንተ ከአሁኑ ለእውነት በመቆም ልጆቻችሁ የሚያስቀጥሉት ነገር መስራት አለባችሁ፡፡
ጭቆና እስካለ ድረስ እኔም ሆንኩ እናንተ ባንታገልም ጭቆናውን ለማስወገድ የሚነሳ ሰው አይጠፋም፡፡ እናንተን እድለኛ የሚያደርጋችሁ ጭቆናውን ለመግታት ፈልጋችሁ፣ በራሳችሁ ተነሳሸነት በመጀመራችሁ ነው፡፡
ጭንቅ ላይ ያለች እርጉዝ ሴት ካላማጠች አትገላገልም፡፡ ለእኔ ኢትዮጵያ ጭንቅ ላይ እንዳለች እርጉዝ ሴት ነች፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ከሚደርስባት ስቃይ ለመገላገል ማማጥ አለባት፡፡ ያኔ ትገላገለዋለች፡፡ ለዚህ ደግሞ ትግል ያስፈልጋል፡፡ ወጣቶች መታገል አለባችሁ፡፡ ትግሉ ጥንካሬን ይጠይቃል፡፡ መጠንከር አለባችሁ፡፡
‹‹ተቃዋሚዎች በምርጫው ካላመኑበት ሁላችንም አንገባም ማለት አለባቸው›› አቶ ኦልባና ሌሊሳ
የፖለቲካ ፓርቲዎች ስለ ምርጫው ቀድመው መስራት አለባቸው፡፡ ምርጫ ስለመግባት አለመግባት ከመወሰናቸው በፊት ጠንክረው መስራት ይገባቸዋል፡፡ ውሳኔውን ከመወሰናቸው በፊት ውሳኔውን ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን ነገር ማሰብ አለባቸው፡፡ ይህ ጉዳይ ጥናት ያስፈልገዋል፡፡ ለውሳኔያቸው ደግሞ ተገዥዎች መሆን አለባቸው፡፡ አንዴ ከተወሰነ በኋላ ጠንካራ አቋም መያዝ አለበት፡፡ በህዝቡ አመኔታ ለማግኘት በውሳኔያቸው መጽናት አለባቸው፡፡ መወላወል አይገባም፡፡ ጊዜው እስኪደርስ ጠንክረው መስራት አለባቸው፡፡ በአንድ ወቅት 33 የሚባል ስብስብ ነበር፡፡ አሁንም ተባብሮ መስራት ያስፈልጋል፡፡ ለምርጫው በጋራ መስራት ያስፈልጋል፡፡
ተቃዋሚዎች በምርጫው መሳተፍ ለህዝብ የማይጠቅም መሆኑን ካመኑ እና መግባት የማያስፈልጋቸው ከሆነ በአንድነት ኃይልን አሰባስቦ ከምርጫው መውጣት ይቻላል፡፡ በምርጫው ካላመኑበት ሁላችንም አንገባም ነው ማለት ያለባቸው፡፡ በተናጠል ከምርጫው ራስን ማግለል ጥቅም አይኖረውም፡፡ በእርግጥ ይህ መወሰን ያለበት ጊዜው ሲደርስ ነው፡፡ እስከዛ ግን ጠንክረው መስራት አለባቸው፡፡
መጥታችሁ ስለጠየቃችሁን በጣም እናመሰግናለን፡፡ ውጭ ያለውን የቤት ስራችሁንም ጠንክራችሁ መስራት አለባችሁ፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ በቀጣይ ጊዜያትም እስር ቤት ውስጥ የሚገኙትን ሌሎች ኢትዮጵያውያን መልዕክት ለማቅረብ ትጥራለች፡:

‹‹ሁሉም እስረኞች መብት አላቸው፡፡ አንዳንድ እስረኞች ግን ከሌሎቹ የተለየ መብት አላቸው፡፡›› ጌታቸው ሽፈራው (ቃሊቲን እንደቃኘው)

‹, እስረኞች መብት አላቸው፡፡ አንዳንድ እስረኞች ግን ከሌሎቹ የተለየ መብት አላቸው፡፡ አንዳንዶቹ ምንም መብት የላቸውም››
ዛሬ ወደቃሊቲ አቅንተን ነበር፡፡ የእነ አቶ በቀለ ገርባ፣ የአዛውንቱ ሲሳይ ብርሌ፣ የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ምክር፣ ትንታኔና ተስፋ አንዳች ጥንካሬ ይሰጣል፡፡ የእነዚህ ታሳዎች ጥንካሬ ቃሊቲ እስር ቤት መሆኑን ሁሉ ያስረሳል፡፡
መጀመሪያ እነ በቀለ ገርባን ጠይቀን ነው ወደ ጋዜጠኛው ያቀናነው፡፡ ውብሸትን ለመጠየቅ ስናቀና የገቢዎችና ጉምሩክ ምክትል የነበረው ገብረወሃድ እስረኞች ከሚጠየቁበት ውጭ አንድ ጥግ ላይ ከቤተሰቦቹ ጋር ሰብሰብ ብሎ አየነው፡፡ እስረኞች ወደሚጠየቁበት ስናመራ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዳይሬክተር የነበረው መላኩ ፋንታና ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ለመጠየቂያነት የተከለለው ቦታ ላይ ጎን ለጎን ቆመው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እያወሩ ደረስን፡፡
ከውብሸት ጋር ለተወሰኑ ደቂቃዎች ካወራን በኋላ ይበቃል ተባለ፡፡ ገና ወደ ውብሸት ስንመጣ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የነበሩት መላኩ ፋንታ አሁንም ከቤተሰቦቻቸው ጋር እያወሩ ነው፡፡ ገብረ ወሃድም እንደዛው፡፡ እንግዲህ በእስረኞች መካከል የሚፈቀደው የሰዓት ገደብም ይለያያል ማለት ነው፡፡ ለ‹‹አሸባሪ›› ጋዜጠኛ 10ና 20 ደቂቃ፣ ለ‹‹ኪራይ ሰብሳቢ›› ባለስልጣን ደግሞ የፈለገውን ያህል ጊዜ ይሰጣል፡፡
ያቆሰለኝ ግን ይህ አይደለም፡፡ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ከእናትና አባቷ ውጭ በማንም አትጠየቅም፡፡ እህቷ እስከዳርና እጮኛዋ ጋዜጠኛ ስለሽ ሀጎስ ርዕዮትን መጠየቅ ይቅርና ወደ ግቢው እንዳይገቡ ተከልክለዋል፡፡ ውብሸትን ጠይቀን ስንወጣ ለመረዳት እንደቻልኩት እስረኞች ከሚጠየቁበት ውጭ አንድ ጥግ ይዞ ከቤተሰቦቹ ጋር ሰብሰብ ብሎ (ወንበርና ጠባብ ጠረጴዛ ነገር ቀርቦላቸዋል) በዓል እያከበረ የነበረውን ገብረወሃድ ብቻ አልነበረም፡፡ በእጮኛዋና በእህቷ እንዳትጠየቅ ከተደረገችው ርዕዮት ዓለሙ ጋር ታስራ የምትገኘው የገብረ ወሃድ ባለቤት ኮሎኔል ኃይማኖት ከባለቤቷና ከቤተሰቦቿ ጋር ሆና በዓል እንድታከብር ተፈቅዶላታል፡፡
የእኔ ጥያቄ ለምን እነ ገብረወሃድ ተፈቀደላቸው አይደለም፡፡ ነገር ግን ርዕዮት በእጮኛዋና በእህቷ እንዳትጠየቅ በተደረገችበት ወቅት እነ ገብረወሃድና ከርዕዮት ጋር ታስራ የምትገኘው ባለቤቱ ያለ ምንም የሰዓት ገደብ እንዲያውም እስረኞች ከሚጠየቁበት ክልል ውጭ በዓል እንዲያከብሩ መደረጉ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ‹‹እስረኞች መብት አላቸው፡፡ ነገር ግን አንዳንድ እስረኞች ከሌሎቹ የተለየ መብት አላቸው፡፡ አንዳንዶቹ ምንም መብት የላቸውም›› የሚል ያልተጻፈ ህግ እንዳለ ያሳያል፡፡ ህግ በእንሰሳዊ ስልት ለሌቦች አድልታ ስለ እውነት ለቆመችው፣ በብዕሯ ለህዝብ ለማሳወቅ ለጣረችው ወጣት ፊቷን ስታዞር አበቃላት፡፡ ይህ ርዕዮት ላይ ሆኗል፡፡ በቃሊቲ፣ በኢትዮጵያ ፍትህ እንዲህ አብቅቶላታል፡፡

onsdag 24. september 2014

በመላ ሃገሪቱ የተነደፈው የተቀናጀ የጐልማሶች ትምህርት ስኬታማ አይደለም ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሺፈራው ሽጉጤ ተናገሩ፡፡

በመላ አገሪቱ ከ40 ሚሊዮን በላይ መጻፍና ማንበብ የማይችሉ ወጣት እና ጎልማሶች አሉ ያሉት አቶ ሺፈራው ፤  ይህንን የትምህርት እድል ያለገኙ ወጣቶች እና ጎልማሶች አማራጭ
ትምህርት እንዲያገኙ የተደረገው ሙከራ አፈፃጸሙ ከዜሮ በታች ነው ብለዋል። በኢህአዴግ የእቅድ ትውውቅ መድረክ ላይ እንደቀረበው በጎልማሶች የትምህርት አቀራረብ  አማራ 0.9፣ ኦሮምያ ፣ 0.71 ፣ደቡብ 0.63 ፣ትግራይ 2.9
በመቶ ፈጽመዋል።
ኢህአዴግ ደርግን ባመሰገነበት የምክር ቤት ውይይት ፤ “ለምን ህዝቡን በዘመቻ አናስተምርም?” ተብሎ ለተነሳው ጥያቄ ፤ “ኢህአዴግ የተፈጠረው ከዘመቻ ነው፡፡ ወጣቱ ሌላ የትጥቅ ትግል እንዲያደራጅ  መሳሪያ አንሳ ብለን አንልክም”
የሚል መልስ ተሰጥቷል። “በገጠር መሬት አልባ የሆነው ወጣት ፤ በከተማ ስራ አጥ የሆነው የተማረው ሃይል በአንድነት ተገናኝቶ ሊፈጥረው የሚችለው አደጋ ሰፊ ነው፤ ይህ ስጋት ሳይሆን ሃቅ ነው” ሲሉ አቶ በረከት እና አቶ አበይ ፅሃየ
በመደጋገፍ እየተናገሩ ጎልማሶችን በዘመቻ ለማስተማር የቀረበውን ሃሳብ ውድቅ አድርገዋል፡፡ አቶ በረከት እንዲህ አይነቱን አስተያየት የሚያቀርቡት በትጥቅ ትግሉ ወቅት ያልነበሩ አመራሮች ናቸው በሚል አዳዲስ የኢህአዴግን አመራሮች
መወረፋቸው ከኢህአዴግ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

tirsdag 23. september 2014

ሰኞን በቃሊቲ (በኤልያስ ገብሩ ጎዳና)

****ሰኞን በቃሊቲ ****
‹‹መጽሐፉ በመውጣቱ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡
‹‹መጽሐፌን በውጭ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ወገኖቼም ቢያነቡት ደስ ይለኛል››
ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ
————–




ዛሬ ረፋድ ላይ ከወዳጄ አቤል አለማየሁ ጋር ቃሊቲ ሄደን የቀድሞ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ባልደረባችን የነበረውን ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን ለመጠየቅ ተቀጣጥረን ነበር፡፡ አቤል፣ ከቀጠሯችን 20 ደቂቃ ያህል ዘግይቶ መስቀል አደባባይ ደረሰና ደወሎ ተገናኘኝ፡፡ ሁለታችንም በ2007 ዓ.ም በአካል የተገናኘነው ዛሬ ነበር፡፡ ‹‹በ2007 ም ቀጠሮ አታከብርም?›› ብዬ ቀለድኩበት፡፡ ….
ሚኒባስ ታክሲ ተሳፍረን ቃሊቲ ደረስን፡፡ የተለመደ ፍተሻውም ታለፈ፡፡ ነገር ግን፣ እስከዛሬ አጋጥሞኝ የማያውቀው አዲስ ፍተሻ መኖሩን አቤል ነገረኝ፡፡ በዘመናዊ ኤሌክትሮኒክስ ማሽን ጫማ እና ቀበቶን አውልቆ በድጋሚ መፈተሽ ግድ ነበር፡፡ ይህም ታለፈና ‹‹ሸራተን›› ተብሎ ወደሚጠራው የቃሊቲ እስር ቤት አመራን፡፡ ይህንንም የእስረኛ መጠየቂያ ቦታ ስመለከተው ለመጀመሪያ ጊዜ በመሆኑ በማያቸውን ነገሮች ላይ ትኩረት መስጠቴ አልቀረም፡፡
አንድ ጥግ ላይ፣ በአጭር ርዝመት በእንጨት የተሰራች መጠየቂያ ጋር ደርሰን ቆምን፡፡ ለአንዱ ጥበቃ ፖሊስ ውብሸትን እንዲያሥጠራልን ነገርነው፡፡ ውብሸትም ከደቂቃዎች በኋላ ወደእኛ መጣ፡፡ ፊቱ በፈገግታ ተሞልቶ ነበር፡፡ ብርቱካናማ ቲ-ሸርት አድርጓል፡፡ በቅድሚያ ያገኘሁት እኔ ነበርኩ፡፡ ተቃቅፈን ሰላምታ እየተለዋዋጥን እያለ ከለበሰው ልብስ አኳያ ‹‹የቀለም አብዮት ልትጀምር ነው እንዴ?›› አልኩትና ትንሽ ተሳሳቅን፡፡
ከአቤልም ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ የጋራ ወጋችንን ቀጠልን፡፡ ብዙ ሃሳቦች የተወያየነው በቅርቡ ለንባብ ስላበቃው ‹‹የነጻነት ድምጾች›› የሚል ርዕሥ ስላለው የመጽሐፍ ሁኔታ ነበር፡፡ በመጽሐፉ መውጣት በጣም ደስ ብሎታል፤ ይህም ፊቱ ላይ በግልጽ ይነበባል፡፡ ብዙ መከራን አሳልፎ ይህንን ማየት መቻሉ በጨለማ ውስጥ እንዳለች ሻማ ይቆጠራል፡፡ ለረዥም ወራት በኩላሊት ህመም እየተሰቃየ ከዝዋይ ወደቃሊቲ ለሕክምና መጥቶ እንኳን የረባ ሕክምና ሳይደረግለት ውሃ ጠጣ ነበር የተባለው፡፡ ልብ አድርጉ፣ የዝዋይ ውሃ ጠጠር ያለበት መሆኑ እየታወቀ ወደ ዝዋይ እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ የወላጅ አባቱን የሞት መርዶ የሰማው በዘዋይ እስር ቤት ነው፡፡ ሌሎች አስቸጋሪ ነገሮች በውብሸት ሕይወት ውስጥ አልፈዋል፡፡ የሚቀየር ነገር ከሌለ ደግሞ 11 የእስር ዓመታቶች ከፊቱ ይጠብቁታል፡፡ ይህ ሁሉ ታልፎ ይህቺን የተስፋ ብርሃን እንኳ በእስር ቤት ማየቱ ከምር ደስ ይላል – ለሞራሉ!
…ይህህ መጽሐፉን ሙሉ በሙሉ አንብቦ የጨረሰው ዓቤል፣ አንዳንድ ጥያቄዎችን ከመጽሐፉ በመነሳት ሲያቀርብለት እሱም ሲያስረዳ እና ሲመልስለት እያለ ወዳጃችን ሰለሞን ሞገስ አጠገባችን ደረሠ፡፡ የውብሸት ጠያቂዎችም ሶስት ሆንን፡፡ …
‹‹አሁን ከማን ጋር ነው የታሰርከው?›› ስል ጥያቄዬን አቀረብኩለት፡፡ ከገብረዋድ (የቀድሞ የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለሥልጣን መ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር እና በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ጉዳቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኝ) እና ከአንድ ሌላ ልጅ ጋር አንድ ክፍል ውስጥ ነኝ›› አለን፡፡ ገረመኝ፤ አብረው ይሆናሉ ብዬ አልገመትኩም ነበር፡፡
‹‹ለአቶ ገብረዋድ አንድ ጥያቄ ጠይቅልኝ?›› አልኩት ለውብሸት፡፡
‹‹ምን?››
‹‹ከሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ለፍርድ ቤቱ አንድ አቤቱታ አቅርበው ነበር፡፡ በወቅቱ እኔም በችሎት ነበርኩ፡፡ ‹በማዕከላዊ ሰብዓዊ መብታቸው መጣሱን ሲናገሩ ገርሞኝ ነበር ያዳመጥኩት፡፡ በእርግጥ ማንም ሰው በእስር ላይ እያለ ሰብዓዊ መብቱ መጣስ የለበትም፡፡ ነገር ግን፣ አቶ ገብረዋድ የመንግሥት ከፍተኛ ሹመኛ በነበሩበት ጊዜ የተቃውሞ ፓርቲ አመራሮች፣አባላት፣ ጋዜጠኞችና በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ የሚገኙ ዜጎች በተለያየ ምክንያት ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ሲቀርቡ፣ በማዕከላዊ የምርመራ እስር ቤት ሰብዓዊ መብታቸው መጣሱን ለፍርድ ቤት አቤቱታ በተደጋጋሚ ሲያቀርቡ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መስማታቸው አይርቀም፡፡ ያኔ ዝም ብለው አሁን በራሳቸው ላይ ሲደርስ ስለመብት ጥሰት መናገራቸው ተገቢ ነበር ወይ? የመብት ጥሰት በራስ ላይ ሲደርስ ብቻ ነው ወይ ድምጽን ማሰማት የሚገባው?!›› አልኩት፡፡
ጥያቄዬን አድምጦ እጠይቅልሃለሁ አለኝ፡፡
የተለያዩ ነገሮችን እየተወያየን እያለ አንዲት ወጣት ልጅ ምግብ እና አነስተኛ ጥራቱን የጠበቀ ፍራሽ ይዛ በአቅራቢያችን መጣች፡፡ አቤል ‹‹ገብረዋድ ጋር ነች›› አለ፡፡ ወዲያው አቶ ገብረዋድ መጣ፡፡ ምቾት እና ነጻነት ባልተሰማው መንገድ ‹‹ሰላም ናችሁ›› የሚል ቃል ከአንደበቱ ወጣና ከውብሸት ጀርባ አልፎ ከምትጠይቀው ልጅ ጋር በትግርኛ ቋንቋ መነጋገራቸውን ቀጠሉ፡፡ ጠይቀን እንደተረዳነው ከሆነ ልጁ ነች፡፡ እኔም ጥያቄዬን ለአቶ ገብረዋድ ላቀርብለት አስቤ ከውስጤ ጋር አውርቼ ነበር፡፡ ነገር ግን፣ ከነበርንበት ቦታ አኳያ አመቺ ስላልነበረ ተውኩት፡፡ አቶ ገብረዋድም፣ ቀድሞን ወጣና ፍራሽ እና ምግቡን ይዞ ቻው ብሎን ሄደ፡፡ …
ውብሸትም መጽሐፉን አስመልክቶ እንዲህ አለን፡- ‹‹መጽሐፉ በመውጣቱ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ መጽሐፉን ሁሉም ሰው ቢያነበውም ደስ ይለኛል፡፡ ስለሀገራችን የእስር ቤት አስቸጋሪ ሁኔታ እና ስለሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች መጠነኛ መረጃ ያገኛል፡፡ መጽሐፌን በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ወገኖቼም ቢያነቡት ደስ ይለኛል፡፡›› ካለ በኋላ የዳያስፖራ ማኅበረሰብን በተመለከተ ይህቺን ሃሳብ አከለ፡፡
‹‹ዳያስፖራዎች ስለሀገራችን ሁኔታ ያገባናል ስለሚሉ ነው በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ድምጻቸውን በማሰማት ሰልፍ የሚወጡት፡፡ ይህን ባያስቡ ኖሮ በየካፌው ቡና እየተጠጣ ዝም ማለት ይቻላል፡፡ ከታሰርኩ በኋላ ‹‹ፍኖተ ነጻነት›› ጋዜጣን የማንበብ ዕድሉን አግኝቼ ነበር፡፡ አንዲት ሴት የእኔን ፎቶግራፍ ደረቷ ላይ አድርጋ [የታሰሩ ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች ይፈቱ! የሚል] የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ድምጻን ያሰማችበትን ምስል ተመለከትኩና፡፡ ሴትየዋ እኔን አታውቀኝም፡፡ ግን የእኔን የእስር ጉዳት ለመቃወም አደባባይ ወጥታለች፡፡ ይህ ለሀገር ከመቆርቆር የሚመነጭ ነው››
…ባለኝ መረጃ መሰረት የውብሸት መጽሐፍ ጥሩ እየተሸጠ ይገኛል፡፡ ሁለተኛ ዕትምም በቅርቡ ይገባል፡፡
…ከእኛ ራቅ ብሎ የሚገኘው ፖሊስ ከሌሎች ፖሊሶች ጋር ተነጋገረና ‹‹ሰዓት ሞልቷን፤ በቃችሁ›› አለን፡፡
እኛም ውቤን ‹‹አይዞን!›› በማለት አቀፈን የስንበት ሰላምታ ሰጥተነው ተለየነው፡፡ ‹‹አቶ ገብረዋድን ጠይቅልኝ ያልኩህን እንዳትረሳ›› በማለትም በድጋሚ አስታወስኩት፡፡
***FJ 2007****

mandag 22. september 2014

የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ ለብድር ዕዳ አደጋዎች የመጋለጥ ዕድሏ እየሰፋ ነው አለ

ሰሞኑን ለሦስት ቀናት ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩት የዓለም ባንክ ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የኦፕሬሽን ዋና ኃላፊ ስሪ ሙሊያኒ ኢንድራዋቲ፣ እያደገ የመጣው የብድር ዕዳ መጠን በኢትዮጵያ ላይ አደጋዎችን ሊያስከትል እንደሚችል ገለጹ፡፡
ኢንድራዋቲ ባለፈው ረቡዕ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ምንም እንኳን የአገሪቱ የብድር ዕዳ መጠን ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት አኳያ ያለው ድርሻ አነስተኛ ቢሆንም፣ የዕዳውን መጠን በግልጽነት ለማስተዳደር የሚችልና ግልጽነት የሰፈነበት አስተዳደር ማስፈን የመንግሥት ግዴታ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ አገሪቱ ያለባት ጠቅላላ የብድር መጠን 20 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡ ከዚህ ውስጥ 12 ቢሊዮን ዶላር ከውጭ ምንጮች የተገኙ ብድሮችን የሚሸፍን የዕዳ መጠን ነው፡፡ በዚህ መሠረት ከጠቅላላ አገር ውስጥ ምርት አኳያ የዕዳው ድርሻ 44 ከመቶ መድረሱን ይጠቁማል፡፡
ኢንድራዋቲ እንደሚገልጹት፣ ይህ አኃዝ ዝቅተኛ በሚባለው የዕዳ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ነገር ግን የመንግሥት የኢንቨስትመንት ወጪዎች እየተበራከቱ በመምጣታቸው ምክንያት የዕዳ መጠኑን በዚያው ልክ እያደገ በመሆኑ፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን በሚመለከት ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ከሚመለከታቸው ሚኒስትሮች ጋር መነጋገራቸውን አስረድተዋል፡፡ ከውይይቶቹ መካከልም በመንግሥት አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርሞች ላይ ያተኮረው አንዱ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ በዚህም መንግሥት በአስተዳደራዊ መዋቅሮቹ ላይ ማሻሻያ በማድረግ፣ ግልጽነትና ኢኮኖሚውን በብቃት የማስተዳደር ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የኢንቨስትመንት ወጪን መነሻ በማድረግ፣ በኢትዮጵያ እየጨመረ የሚገኘውን የብድር ዕዳ መጠንና ሊከሰት የሚችለውን አደጋ ለመቋቋም የሚያስችል አሠራር ማምጣት እንደሚገባቸው መክረዋል፡፡
‹‹ይህንን ለማከናወን አስተማማኝ የፋናይናንስ ሪፖርት ያስፈልጋል፡፡ ግልጽነትና ወጥነት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ተዓማኒነት ያለው መረጃ መኖሩ ግድ ይላል፡፡ አሁን እየታየ ያለው የብድር ሁኔታ በኢትዮጵያ ላይ ተጨማሪ የተጋላጭነት አደጋ ማስከተሉ በእርግጠኝነት የማይቀር ነው፤›› ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ የብድር ዕዳዋን ለማቃለል የወጪ ንግድ ሚዛኗ ወሳኝ መሆኑን ኢንድራዋቲ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ባለፉት ሦስት ዓመታት በወጪ ንግድ መስክ አገሪቱ ዝቅተኛ ውጤት ስታዝመገዘብ መቆየቷ ለብድር ዕዳ ያላትን ተጋላጭነት አስፍቶታል ይባላል፡፡
አገሪቱ ስታዝመግብ የቆየችው የኢኮኖሚ ዕድገት መልካም የሚባል መሆኑን የጠቀሱት ኢንድራዋቲ፣ ይህም ሆኖ ኢኮኖሚው መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት ብዙ እንደሚቀረው ገልጸዋል፡፡ የኢኮኖሚው ዕድገት በርካታ የሥራ መስኮችን ሊፈጥሩ የሚችሉ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለማምጣት ብዙ መንገድ ይቀረዋል ያሉት ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ፣ ባንኩ የኢንዲስትሪ ዞኖች ግንባታን ፋይናንስ እያደረገ እንደሚገኝም አስታውሰዋል፡፡ በአዲስ አበባ ቦሌ ለሚ ሁለተኛ ምዕራፍና በአቃቂ ቃሊቲ ቂልንጦ አካባቢ ለሚገነቡ ሁለት የኢንዱስትሪ ዞኖች የሚውል የ250 ሚሊዮን ዶላር ብድር መፍቀዱን፣ በኢትዮጵያ የባንኩ ዳይሬክተር ጉዋንግ ዚ ቼን ገልጸዋል፡፡
ባንኩ ለመሠረተ ልማት ከሚሰጠው ድጋፍ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ለመሠረታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራምም ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ተዘዋውረው በጎበኟቸው የሴፍቲኔት ጣቢያዎች ጥሩ ውጤት እንዳዩ ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ ተናግረው፣ እየጨመረ በመጣው የከተሞች የምግብ እጥረት ተጋላጭነት ሳቢያ በድምሩ አሥር ሚሊዮን ሰዎች በሴፍቲኔት ፕሮግራም ይታቀፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ይፋ አድርገዋል፡፡
ስሪ ሙልያኒ ኢንድራዋቲ የዓለም ባንክን ከመቀላቀላቸው አስቀድሞ የኢንዶኔዥያ የፋይናንስ ሚኒስትር በመሆን አገልግለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የኢኮኖሚ ጉዳዮች አስተባባሪ ሚኒስትር በመሆንም ሠርተዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2010 የዓለም ባንክን የተቀላቀሉት ኢንድራዋቲ፣ በምክትል ፕሬዚዳንትነት ደረጃ የሚመሯቸው በርካታ መስኮች አሉ፡፡ በማኔጂንግ ዳይሬክተርነት ሥልጣናቸው የባንኩን የአካባቢያዊ ሥራዎች በጠቅላላ የመምራት ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል፡፡

søndag 21. september 2014

የኢህአዴግ አምባሳደር በስዊዲን ወየንሽት ታደሰ የእንቁላል ድብደባ በከፍተኛ ሁኔታ ደረሰባት።

በስዊዲን የሚገኙ ኢትዮጵያኖች ከዚህ በሆላ እንደድሮው በውጪ እየወጡ መዝናናት የለም በማለት አምባሳደሯን እንቁላል በመወርወር ከፍተኛ የሆነ ውርደት እንድተከናነብ አድርገዋል። አብረዋት የነበሩ የወያኔ ጠባቂዎችም ራሳቸውን ከድብድባው ለማምለጥ ሲሉ ጥለዋት ሄደዋል። የስዊድን ፖሊሶች በርካታ የፖሊስ መኪናዎችን በማምጣት ጸጥታውን ለመቆጣጠር የቻሉ ሲሆን ከረጅም እግታ በሆላ በፖሊሶች እርዳታ ከመኪናዋ ወጥታ ለመሄደ ችላለች።
የኢህአዴግ አምባሳደር በስዊዲን ወይንሽት ታደሰ የእንቁላል ድብደባ በከፍተኛ ሁኔታ ደረሰባት።
እንቁላል አትጨርሱ ዛሬ የባንዳዎች እና የነነዋይ ውርደት በእንቁላል ቢጫ እናድረጋቸዋለን እና እሶ ላይ ብቻ አትጨርሱ፣ መኪናው የእንቁላል ጌጥ በዛበት የሚል አስቂኝ ክስተቶችም ነበሩበት።
በውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያኖች በተጠናከረ መልኩ የወያኔን ባለስልጣናት በሄዱበት የማዋረድና እጃቸው ደም የተበከለ መሆኑን በተደጋጋሚ እየተነገራቸው ሲሆን በቅርቡ በተመሳሳይ ሬድዋን ሁሴን በዋሽንግተን ዲዲ የደረሰበት ውርደት ይታወሳል።
በአሁኑ ሰአት በርካታ የወያኔ ባለስልጣኖች ወደ ውጪ መጓዝን እንደማይመርጡ የደረሰን ሪፖርት ያመላክታል።
በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳና እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ

ሕዝቡና ተማሪው በአገር ጉዳይ ከኢህአዴግ ጋር መግባባት አልቻልንም በማለት ስልጠናው እንዲቋረጥ ጠየቀ።



የጎንደር ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ብሶታቸውን በከፍተኛ ቁጣ ገልጸዋል።
- ለወያኔ ባለስልጣናት የቀረበው ሪፖርት እንደሚያሳየው ስልጠናው ምንም የስኬት ፍንጭ አላሳየም።
- የሃምሳ አመት እቅድ ለምን አስፈለገ የስልጣን ጥመኝነትን ያሳያል።
- ለሶስተኛ ዙር ስልጠና ምዝገባ እየተካሄደ ነው።
- በኢሕአዴግ ውስጥ ያሉ አመራሮችም ይሁኑ አባላቶቹ የአስተዳደር ብቃት የላቸውም።
- ኢትዮጵያውያን በህግ ፊት እኩል የሚሆኑት እና ፍትህ የሚነግሰው ቀን እንናፍቃለን።
- በቫት ስም መንግስት ዘረፋ ይዟል በህጉ ቫት አይከፈልበትም የተባለው የጤና ዘርፍ ሳይቀር ቫት እየቆረጠ ነው።
በየአከባቢው እየተካሂደ ያለው ልማታዊነትን ሽፋን አድርጎ የስልጣን ማስረዘሚያ ሰበካ (ስልጠና) እንደቀጠለ ቢሆንም በህዝቡ እና በአሰልጣኞች መካክል ከፍተኛ የሆነ አለመግባባት ከመከሰቱም በላይ ህዝቡና ተማሪው በአገራችን ጉዳይ ከኢህአዴግ ጋር ልንግባባ አልቻልንም ስለዚህ አበል ይቅርብን እና ስልጠናውን አቋርጡልን በማለት እየጠይቀ መሆኑን ዘገባዎች አመልክተዋል። ሰልጣኞች እንደሚሉት እየተካሄደ ያለው ስልጠና ሳይሆን የፖለቲካ ሰበካ ነው ይህ ደሞ የተለያየ አስተሳሰብ ያላቸውን ህዝቦች ለማደናቆር ካልሆነ በስተቀር ተቀባይነት የለውም። ስለዚህ የያዛችሁን ስልት ቀይራችሁ ህዝብ መሃል ግቡና አናግሩን እንጂ በ አበል እና በቀበሌ ጥቅማጥቅም አታስገድዱን፡ አያዋጣችሁም ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለአዲስ አበባ የኢሕአዲግ ጽ/ቤት ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደጠቆሙት እስከዛሬ በተሰጡ ስልጠናዎች የተሰብሰቡ ሪፖርቶች እንደሚይመለክቱት ሕዝቡም ይሁን ተማሪው በተጻራሪነት እንደቆሙ እና በድርጅቱ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ እና ማንጓጠጥ ያሳዩ መሆኑን የጠቆመ ሲሆን ስልጠናው ምንም የስኬት ፍንጭ አላሳየም ብሏል።
በጎንደር ዩንቨርስቲ ለየት የሚያደርግው ተማሪው ብሶቱን በከፍተኛ ቁጣ መግለጹ ነው።
በጎንደር ዩንቨርስቲ ተማሪው በዩንቨርስቲው ትምህርት ላይየና በመምህራን ጉዳይ ከፍተና ቁጣ በማሰማት ላይ ሲሆን ዩንቨርስቲው በመልካም አስተዳደር እጦት እና በሙስና እየታመሰ መሆኑን ተነግሯል በአንድ ምት ጊዜ ውጽት ብቻ 3 ፕሮፌሰሮች 3 ዶክተሮች 14 ሁለተኛ ዲግሬ ያላቸው ምሁራን ልምድ ያላቸው መምህርን ጎንደር ዩንቨርስቲን ለቀዋል።ለዚህ ምክንያቱ ደሞ የዩንቨርስቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር መንገሻ አምባገነንነት እና ፈላጭ ቆራጭነት መሆኑን ተማሪዎቹ አስምረውበታል።
የዩንቨርስቲው አመራር እና ቦርዱ አምባገነን ናቸው ያሉት ተማሪዎች በሙስና እና በወገንተኝነት የተዘፈቁ ስለሆኑ በዩንቨርስቲው ከ20 አመት በላይ ያገለገሉ ምሁራን እንዲለቁ ምክንያት ህነዋል።በ2007 ይነሳሉ ተብለው የነበሩት እና በጣም አስቸጋሪ ባህሪ እንዳላቸው የሚነግርላቸው የዩንቨርስቲው ፕረዚደንት ፕሮ.መንገሻ በኢሕ አዴግ ብባለስታን ድ/ር ስንታየው ትእዛዝ እንዲቀጥሉ መደረጉን ተማሪውን አስቆጥቷል።
ህዝቡና ተማሪው ዛሬ በጠዋቱ እነዚህን ሲናገሩ አርፍደዋል።
1 ኢሕአዲግ የሃምሳ አመት እቅድ አውጥቷል መጀመሪያ ደረጃ የ50 አመት እቅድ በማን ማንዴት ነው የሚያውጣው ሃምሳ አመት ከህዝብ ፍቃድ ውጪ የመግዛት እቅድ ኢሕአዴግ አለው ማለት ነው ይህንን አንቀበልም ሃገሪቷን ሌላ አደጋ ውስጥ ለመክተት ካልሆነ በቀር ማንም መንግስት እንዲህ አያቅድም።
2 ኒኦሌቤራሊዝምን እና ሶሻሊዝምን እየጠላችሁ ልማታዊ ዲሞክራሲ ትሉናላችሁ ከየትኛው የትናው እንደሚሻል እንኳን ግንዛቤ የላችሁም በውቀት ያልጠገባ አመራር እና አባል ታቅፋችሁ ሃገር እንዲት እንደምትመሩ በፍጹም አቅቷቹሃል እና አስቡበት
3 የትምህርት ጥራት አውርዶ የዩንቨርስቲዎችን ቁጥር ማብዛቱ፡ተቀሜታው ምንድነው ? በጎንደር ዩንቨርስቲ ዋና ነጥብ የሆነው በዩንቨርስቲው ውስጥ ያለው ትምህርትን የመግደል አምባገነናዊ አስተዳደር በስፋት ተነስቶ እንደነበር ሰልጣኖች ጠቁመዋል።
4. የከተሞችን እድገት በተመለከተ አንጻራዊነት አይታይም የይስሙላ ልማት ፕሮፓጋንዳ እንጂ እድገት የለም መንግስት ባወጣው ህግ በጤናው መስክ ፋርማሲዎች ቫት አያስከፍሉም ይባላል በተዘዋዋሪ ግን የቫት ማሽን አስገብተው እያስከፈሉ ነው ይህ የመንግስትን በዝባዥነት ያሳያል ።ብነጻ ገበያ ሰበብ መንግስት እጁን በገብያ ውስጥ እየከተተ የህዝቡን ንሮ እያደፈረሰ ነው ።ጎን ለጎን የጉምሩክ ቀረጥ የሚጠየቀው ከ እቃው በላይ ነው ይህ ደሞ የከብያውን ትራንዛክሽን እየጎዳው ነው የሚሰራው ለህገር ነው ወይንስ ለዘረፋ ህዝቡ ተማሯል መፍትሄ እንጅ ስልጠና አንፈልግም።
5 መንግስት ሙስኛ ባለስልጣናት ተንሰራፍተዋል እያለ ነው ራሳችሁ ያመናችሁበትን እርምጃ ክመውሰድ ይልቅ እናንተ እርምጃ የምትወስዱባችው ከኢህአዲግ ፖለቲካ ጋር ሲኳረፉ ነው ይህ አግባብ አይደለም ሁሉም ስው በህግ ፊት እኩል መሆኑ ማረጋገጥ የተሳነው መንግስት እንዴት ስልጠና ይሰጣል።

onsdag 17. september 2014

በሶማሊ ክልል የተፈጸመው ኢሰብአዊ ድርጊት ” ገዢው ፓርቲ ለህዝብ ያለውን ንቀት ያሳያል” ተባለ

የቀድሞው የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት የህዝብ ግንኙነት ስራ አማካሪ እና የክልሉ የወጣቶች ሊቀመንበር በመሆን ካገለገለ በሁዋላ የተለያዩ
የቪዲዮ ማስረጃዎችን በመያዝ ከአገር የወጣው ወጣት አብዱላሂ ሁሴን ፣ “ኦ ኦጋዴን” በሚል  ያስተላለፈው አጭር የዶክመንታሪ ፊልም፣ በስልጣን ላይ ያሉት ገዢዎች ለሶማሊ፣
ለኢትዮጵያና በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ያላቸውን ንቀት ያሳያል ብሎአል።
ዘገባውን ከተመለከተ በሁዋላ ህመም እንደተሰማው የገለጸው አብዱላሂ፣ አስከሬን እንዲለቅሙ ሲገደዱ የነበሩት ሲቪሎች ሁኔታ በእጅጉ እንደረበሸው ገልጿል አንዳንድ የመንግስት ደጋፊዎች
ኦብነግ አካባቢውን ለመገንጠል የሚንቀሳቀስ በመሆኑ፣ በአባለቱና በደጋፊዎቹ ላይ የተወሰደው እርምጃ ትክክል ነው በማለት በማህበራዊ ድረገጾች ላይ ሲጽፉ ተመልክተናል፣ ለዚህ ምን አስተያየት
አለህ የተባለው አብዱላሂ፣ ” ይህን የሚሉ ሰዎች ማፈር አለባቸው በማለት መልሷል ወጣት አብደዱላሂ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ልዩነታቸውን አስወግደው በአንድነት በመነሳት
በስልጣን ላይ ያለውን ሃይል ማስወገድ እንደሚገባቸውም አብዱላሂ መልእክት አስተላልፏል።
የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር /ኦብነግ የአማርኛ ክፍል ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ሃሰን አብዱላሂ በበኩላቸው፣ በክልሉ የሚፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት የቆየ መሆኑን ገልጸው፣ ድርጅታቸው
በደቡብ አፍሪካ፣ በሄግ፣ በስዊድንና በጄኔቫ ጉዳዩ ተጣርቶ ተጠያቂ የሚሆኑት ባለስልጣኖች በህግ እንዲጠየቁ አቤቱታ ማቅረባቸውን ገልጸዋል።
መንግስት የተገደሉት የኦብነግ አባላት እንጅ ሲቪሎች አይደሉም በሚል ለማስተባበል ቢሞክር የእናንተ ምላሽ ምን ይሆናል ተብለው የተጠየቁት አቶ ሃሰን፣ መንግስት በራሱ የሚተማመን ከሆነ
አካባቢውን የጦር ቀጠና ማድረጉን ትቶ ለውጭ ጋዜጠኞችና የሰአብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ክፍት በማድረግ አለበት በማለት፣ በክልሉ የሚፈጸመው ጥቃት በህዝቡ ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ተናግረዋል።

tirsdag 16. september 2014

አቶ የሽዋስ አሰፋ የርሃብ አድማ አደረገ

በማዕከላዊ ምርመራ ታስሮ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ  አቶ የሽዋስ አሰፋ የአራት ቀን የርሃብ አድማ
ማድረጉን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። አቶ የሸዋስ ከጳጉሜ 4 ጀምሮ አዲሱን አመት በርሃብ አድማ ያሳለፈ ሲሆን ቅዳሜ መስከረም 3/2007 ዓ.ም ምግብ እንደቀመሰ ባለቤቱ ወይዘሮ
ሙሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡
አቶ የሽዋስ የርሃብ አድማ ያደረገው ከታሰረበት ሐምሌ 1/2006 ዓ.ም ጀምሮ ከጠበቃው ጋር ከአንድ ጊዜ በላይ መገናኘት ባለመቻሉና ዘመድ እንዲሁም የኃይማኖት አባት
እንዳይጎበኘው በመከልከሉ ነው፡፡
የሽዋስ አሰፋ በባለቤቱ ብቻ በሳምንት አንድ ቀን እንዲጎበኝ የተፈቀደለት ሲሆን የርሃብ አድማ ባደረገባቸው ቀናት ባለቤቱ  ምግብ ስታስገባ ለየሸዋስ ምግቡ እንደደረሰው ተደርጎ ባዶ
ሳህን ሲደርሳት መቆየቱን፣  ባለቤቱ የበዓል ቀን ልትጎበኘው በሄደችበት ወቅት ‹‹ወጥቷል›› ተብላ መመለሷን፣  በማግስቱ ልጆቹን ይዛ ልትጠይቅ ስትሄድም ‹‹ስብሰባ ላይ ናቸው!››
በሚል እንዳታገኘው በመደረጓ ለ15 ቀናት ሳትጠይቀው መቆየቷን ጋዜጣው ዘግቧል።
በሌላ በኩል ጠበቃው ተማም አባ ቡልጉ አቶ የሽዋስን ለማግኘት በተደጋጋሚ  ወደ ማዕከላዊ ቢያቀኑም ሳያገኙት እንደቀሩ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።

fredag 12. september 2014

የዩክሬይን ክራሚያና የሩስያ ጉዳይ ስለኢትዮጵያና ኤርትራ ያልተዘጋ አጀንዳ ምን ያሰተምረናል?

(አክሊሉ ወንድአፈረው – የግል አስተያየት)
መስከረም 2, 2007 (ስፕተምበር 12 2014  )

ukrባለፉት ጥቂት ወራት በዩክሬንና ክራሚያ ውስጥ የተቀሰቀሰው ሁኔታ እና አሁን የደረሰበት ደረጃ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር አንጻር ብዙ ዕድምታዎች አሉት፡፡ እነዚህን ዕድምታዎች መመርመር  በሀገራችን ውስጥ ያለፉና የወደፊት ጉዞ ላይ የተከሰቱ፤ እና ሊከሰቱም የሚችሉ ጉዳዮችን  ከወዲሁ በግምት ውስጥ በማስገባት  ሀገራዊ ራዕያችንን ፣ የትግል አቅጣጫችንን አና አጋርና ተቀናቃኝ ሊሆኑ የሚችሉትን ሃይሎች ለይቶ ለማወቅ ያግዛል ብዩ አሰባለሁ።  ይህን ማወቁ ደግሞ በሀገራችን እና በብሑራዊ  ጥቅማችን ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ከሚችሉ ተግባሮች እንድንቆጠብ ዕድል ይሰጠናል። የዚሀ ጽሁፍ ዓላማም በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት ለመጫር ነው።

ለመንደርደሪያ ያህል፦ ለመሆኑ በታሪክ ክራሚያ ዩክሬን ወይስ ሩሲያ ነበረች?
ጠቅለል ባለ ሁኔታ የክራሚያን ያለፉት 200 ዓመታት ታሪክ ስንመለከት በዋናነት የሩሲያ አካል ሆና መቆየቷን እናያለን። በሌኒን የሚመራው የሶሻሊስት አብዮት ከተቀጣጠለ ከ 1917 በሁዋላም ቢሆን ክራሚያ በሶቭየት ህብረት ዕቅፍ ውስጥ አንድ ራስ-ገዝ አስተዳደር ሆና ቆይታለች።

ክሬሚያ የዩክሬን አካል የሆነችው ባውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1954 በወቅቱ የራሽያ ኮሚኒስት ፓርቲና ያገሪቱ መሪ በነበሩት በኒኪታ ክሩስቼቭ ሲሆን፤ እኘህም ሰው የትውልድ ቦታቸውና የፖለቲካ አጋራቸው ለሆነችው ዩክሬን በስጦታ መልክ ከሰጡ በሁዋላ ነበር፡፡ በወቅቱ ይህ ጉዳይ ለሶቭየት ፖለቲካ መሪዎችም ሆነ ለክራሚያ ነዋሪዎች አስጨናቂ ጉዳይ አልነበረም፡ ለምን ቢሉ ዩክሬን የሶቭየት ህብረት አንድ ክፍለ ሀገር (ሪፐብሊክ) የነበረች ሲሆን የክራሚያ ዩክሬን ውስጥ መግባት ለአስተዳደር አመቺነት ካልሆነ በስተቀር በጊዜው ሌላ ሰፊ የፖለቲካ እንደምታ አልነበረውምና ነው። ከዚያም አልፎ በተለይ በምስራቅ አውሮፓ ይገኙ የነበሩት ሁሉም ሶሻሊሰት ሀገሮች  በሶቭዬት ሶሻሊስት ሪፐብሊክ የበላይነት ጥላ ስር  እንዳንድ ሀገር ሆነው  (በሶሻሊስት ዓለማቀፋዊነት መርህ) ይመሩ ስለነበርም እንኳንስ በአንድ ሀገር ስር ያሉ ያስተዳደር ክልሎች በተለያዩ ሶሻሊስት ሀገሮችም መካከል ቢሆን ድንበርና ድንበርተኘነት ታላቅ ቁምነገር ያለው ተደርጎም ይወሰድ እንዳልነበር ማሰታወስ ያስፈልጋል።

የክራሚያ ነዋሪዎች በማንነት አንጻር ራሳቸውን እንዴት ይመለከታሉ?
ይህ ጉዳይ አጅግ አወዛጋቢና በዪከሬን ግጭት ውስጥ ተፋላሚ የሆኑ ክፍሎችም የግል አቌማቸውን የብዙሃኑን ፍላጎት እንደሚንጸባርቅ አድርገው የሚሟገቱበት ዕውነታ ነው::

በዩክሬይን ስልጣኑን የጨበጡት ክፍሎች እና ደጋፊዎቻቸው “የክራሚያ ነዋሪዎች ራሳቸውን የሚያዩት ከሁሉም በላይ  ከራሽያ የተለዩና ዩከሬንያዊ አድርገው ነው የሚቆጥሩት”  የሚለውን አመለካከት ሁሉም ስው እንዲቀበለው ይፈልጋሉ:: ክራሚያ የዩክሬን አካል ሆና የቆየችበትን ጊዜ በማጣቀሰም በተለይም አዲሱ ትውልድ የተማረውም፤ ያደገውም ስለዩክሬን እየተነገረው ስለሆነ ስለ ራሽያዊነት የሚሰማውም የሚያውቀውም  ቅንጣት ያህል ነገር እንደሌለና ይህም በመሆኑ  ከራሽያ ጋር  የሚያገናኝው ስንሰለት እንደተበጣጠስ ደጋግመው ሲናገሩ ይደመጣሉ::

በክራሚያ ውስጥ የሚታየውና የሚጨበጠው  እውነታ ግን ሌላ ነው:: ከ 60 ዓመታት የዩክሬን አካልነት እና ከ23 አመታት ሙሉ ለሙሉ መለያየት በሁዏላም የከሬሜያም ሆነ ሌላው የምሥራቅና ደቡብ ምሥራቅ ዩክሬን ነዋሪዎች የሚሰማችው ስሜት ግን ከሩሲያ ጋር ያላችው የቀደመ ትስስር አንጅ የዩክሬን አካልነት ሆኖ አልተገኘም:::

ከዚህ በታቸ የሚታየውና በቅርቡ የተካሄደ  አንድ ጥናት  እንደሚያሳየው  ከ 70%  (ሰባ ከመቶ) የማያንሱ ክራሚያዎች ራሳቸውን የሚቆጥሩት ብቻ ሳይሆን ትስስርንም ቢሆን የሚሹት ከሩሲያ ጋር እንደሆነ ያመለክታል::

Data: Razumkov Center; Figure: Grigore Pop-Eleches and Graeme Robertson/The Monkey Cage

ይሀ ሁኔታ የሚያሳየው ከአቅመቢሷ ዩክሬን ጋር ከመዳበል ይልቅ ሰፋና ጠንከር ካለችው ሩሲያ ጋር መሆኑ ምን ያህል ጠቀሜታ እንዳለው መገንዘብን ብቻ ሳይሆን የረጅሙ ጊዜ ትስስር የፈጠረውን ማንነትንም በቀላሉ መበጣጠስም  እንደማይቻል ነው::

በዚህም ምክንያት ይመስላል ክራሚያዎች በተለያየ ሁኔታ በዩክሬን ውስጥ ማንነታቸውን ሊያሰከብሩ ሲጥሩ ቆይተውና ሳይሳካላቸው ባሉበት ሁኔታ ዩክሬን ጓዟን ጠቅልላ በአውሮፓ ማህበረሰብ ዕቅፍ ስር ለመግባት ርምጃ መውሰድ ስትጀምር ሁኔታው ስላልጣማቸው ከገቡበት ፈተናና አጣብቂኝ እንድትታደጋቸው ሩሲያን የተማጸኑት።
ቀደም ሲል በምዕራቡ ዓለም ፖለቲካ ተንታኞች  ክራሚያወች ወደ ራሽያ መዋሀድን አይፈልጉም፤  ፍላጎታቸው ከሌላው አውሮፓ ጋር ይበልጥ መተሳሰር ነው በማለት ደግመው ደጋግመው ይናገሩ ወይም ያስተጋቡ እንጂ በማርች 2014  ሬፈረንደም ሲካሄድ ግን  97%  የሆነው ህዝብ ነበር ዩክሬንን ትቶ ወደ ራሽያ መቀላቀልን የመረጠው። ይህ ሁኔታ የክራሚያ ተወላጆች ከሩሲያ ጋር  ለረጅም ዘመናት ከነበራቸው የታሪክ፣ የፖለቲካ፤ የቤተሰብ፣ የባህል፣ የስነ ልቦናና፣የማሕበራዊ ግንኙነት   ሙሉ በሙሉ  መለያየት ችለናል፤  በራሸያና በክራሚያወች  መካከል የነበረውን የአንድነትና የትስስር ስሜት አጥፍተነዋል፤  ብለው ሲያስቡ ለነበሩ ሁሉ መርዶና የራስ ምታት ነው የሆነባቸው::
ክራሚያውያን ከሩስያ ጋር መልሶ ለመቀላቀል ከ 90 በመቶ በላያ በሆነ ድምጽ  ፍላጎታቸውን ገልጸው ደስታቸውን ሲገልጹ )  Mike Collett-White and Ronald Popeski SIMFEROPOL/KIEV Sun Mar 16, 2014 SIMFEROPOL/KIEV (Reuters) – Russian)
ባሁኑ ሰአት በክሬሚያ የሚታየው ሁኔታ በሻቢያ ስር የወደቀውን ህዝብ የማንነት ጥያቄ በተመለከተ ብዙ ጉዳዮችን እንድናገናዝብ ያስገድዳል። ላለፉት 23 አመታት “የኛ ሀገር ነች; የማንነታችን  መግለጫ ነች”; ብለው ከሚመለከቷት እና ከሚወዷት ኢትዮጰያ ተነጥለውና በኤርትራ ውስጥ ከነመሬታቸው ተገደው ከሚገዙት የአፋር፤ ኩናማ፤ ኢሮብ፤ የሀማሴን፣አካለጉዛይ እና ሌሎችም ወገኖቻችን ሁኔታ ጋር እጅግ ይመሳሰላል። ታላቁ የአፋር ተወላጅ የተከበሩት ቢትወደድ ዓሊ ሚራህ፣ “እንኳንስ ህዝቡ ግመሎቻችንም ቢሆኑ የኢትዮጵያን ባንዲራ ያውቃሉ” ሲሉ የተናገሩት ታላቅ መሪ ቃል  ስለአፋር ህዝብ የማይናጋ ጥልቅ ኢትዮጽያዊነት በቂ ማስረጃ ነው። ከዚህም ሌላ ቅድመ ሻቢያ/ወያኔ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ ምንም አናውቅም ብለው ስለቆሙ በሻቢያ ሰራዊት በተደጋጋሚ የተደበደቡት የኩናማ፤ የሳሆ ወዘተ ወገኖች ታሪክ  ኢትዮጰያዊነትንና የትዮጵያዊነትን ስሜት ከነዚህ ህዝቦች መለየት እንደማይቻል ወይም እጅግ ረጅም ጊዜ እንደሚወስድ ያመላክታል።
በመሀል ብዙ ቅሬታ እንደተከሰተ አጠያያቂ ባይሆንም ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር ለማሰተሳሰር ስለታገሉትና ስለወደቁት አርበኞች፣በልጆቻችውና በልጅ ልጆቻቸው አዕምሮ ውስጥ በአሁኑ ሰአት ምን አይነት ስሜት እንደሚመላለስ  የክራሚያ ተመክሮ ፍንጭ ሊሰጥ ይችላል:: በተለይም ደግሞ የክሬሚያ አዲስ ትውልድ አሁንም ከአማሪጮች ሁሉ ወደ ራሸያ ማዘንበሉን እንደመረጠ ስንመለከት አበረታች ሁኔታ ቢፈጠር በሻቢያ ስር በምትገኘው ኤርትራ ውስጥ ሊከሰት የሚችለውን ዕውነታ መገመት አይከብድም::

የክራሚያን ሁኔታና ዕውነታ ስንመለከት፤ የህወሀት መሪወች ሲሰብኩት የቆየውና አሁን ደግሞ ባንዳንድ  ተቃዋሚወች ውስጥም እየሰረጸ ያለው “የኤርትራ ጉዳይ ያለቀለት ጉዳይ ነው” የሚለው  አመለካከት የህዝብን ሰነልቦናዊ ጥንካሬ ወደሚቦረቡር እና ብሄራዊ ጥቅምንም ወደሚጎዳ ተግባር እንዳያነጉደን ያሰጋል። የሀገር ጥቅም የሚጠበቀው ጽናት እና ጥራት ባለው ራዕይ ላይ በተመሰረተ ትግል እንጂ  ጊዚያዊ ጥቅምን ለማሳደድ ሳያላምጡ በመዋጥ ወይም ደግሞ መሰረታዊ የሀገር ጥቅምን “እሱን አሁን እርሱት”  በሚል  ራእይ የለሽ አካሄድ ከቶውንም ሊሆን አይችልም::

ሩሲያ ስለ ክራሚያ ምን ያስጨንቃታል?
ሩሲያ በኢኮኖሚም ሆን በወታደራዊ ሃይል በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊነትና ተደማጭነት ያላት ታላቅ ሀገር እንደመሆኑዋ በቆዳ ስፋቱዋም ቢሆን አሁንም ባንደኘነት ደረጃ ላይ ትገኛለችል። ባንጻሩ ደግሞ ክራምያ በህዝብ ቁጥርም ሆነ በኢኮኖሚ ለሩስያ እዚህ ግባ የማይባል አስተዋጽኦ ነው የሚኖራት። በኢኮኖሚ አንጻር ብቻ ካየነው በዋናነት ተጠቃሚዋ ከራሚያ እንጂ ሩሲያ አትሆንም፡፡ ሆኖም ግን የዘር ሓረግና ታሪክን የሚገዛው ገንዘብ ብቻ አደለምና  ክራሚያ በሩስያ  (ሩስያም በክሬምያ) በታሪክም ሆነ በህዝቡ ሥነ-ልቦና ላይ እጅግ ቁልፍ ቦታ አላቸው፡፡ይህ ሁኔታ ምን ያህል መሰረት ያለው እንደሆነ ለመገንዘብ የሚቀጥሉትን ታሪካዊ ሁኔታዎች እንመልከት፡

  • በጊዜው በመዳከም ላይ የነበረው የኦቶማን ኢምፓየር እና ራሸያ በኦክቶበር 1853 ውጊያ ውስጥ የገቡት በክሬምያ ጉዳይ ነበር፡፡ ውጊያው የተቀሰቀሰው ሩሲያ በክራሚያ የነበሩ የኦርቶዶክስ ክርስትና ተከታዮችን ከጥቃት ለማዳን በወሰደችው እርምጃ ነው ።
  • ይህን ተከትሎ ከ 1853–1856 ባንድ በኩል በራሸያ በሌላ በኩል ደግሞ በፈረንሳይና እንግሊዝ ጥምር ጦር መሀል የተካሄደው ጦርነት በክሬምያ ውስጥ ነበር፡፡
  • የቦልሽቪኮችን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ ነጩ ሰራዊት ( the white army) እየተባለ የሚጠራውና ሶሻሊዝምን በሚቃወሙ የምዕራብ ሃይሎች ይደገፍ የነበረው የተቃዋሚዎች ሀይል በ1920 የመጨረሻውንና ወሳኙን ውጊያ ያካሄዱትም በዚሁ በክሬሚያ ነበር።
  • በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከፍተኛ ደም የፈሰሰበት ጦርነት ከተካሄደባቸው ቦታዎች ውስጥ ክራሚያ አንዷና በዋናነት የምትጠቀስ ነች።
  • የጀርመን ናዚዎች ክራሚያን ለመያዝ ባደረጉት ወረራ ከ 170 ሽህ በላይ የሶቭየት ጦር የተሰዋ ሲሆን በወቅቱ ፋሽስቶችን እስከመጨረሻ የመከተችው ኣና የጀግኖች ከተማ በመባል ልዩ ሽልማት የተሰጣት የክራሚያ ዋና መናገሻ የሆነችው ሴቫስቶፖል ነበረች። በወቅቱ ምዕራብ ዩክሬን የፋሽስቱ ሂትለር ተባባሪ በመሆን በሽዎች የሚቆጠሩትን ጸረ-ፋሽስት ሃይሎች እንደገደሉና እንዲሰደዱ እንዳደረጉ ታሪክ መዝግቦታል።
  • በሁለተኛው ያለም ጦርነት ማጠቃለያ በሦስቱ ተባባሪ ሐያላን ሀገሮች (Allied Forces) መሪዎች ያሜሪካው ፍራንክሊን ሩዝቬልት፣ የሩሲያው ጆሴፍ ስታሊን እና የኢንግሊዙ ዊንስተን ቸርችል መካከል የተደረገው ስብሰባ የተካሄደው በያልታ ፣ ክራሚያ ውስጥ ነበር።

ይህ ሁሉ በራሽያውያንና ክራሚያ መካከል ያለውን ከፍተኛ የታሪክና  የሰነልቦና ትሰሰር  አንዱ ሌላውን ለምን እንደሚፈልግ ያሳያል::

ይህ ብቻ ሳይሆን ክራሚያ ለሩሲያ የምታስገኘው  ጂኦ-ፖለቲካዊና ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታም እጅግ ትልቅ ነው። ክራሚያ ቀደም ሲል የሶቭየት ህብረት በሁዋላም የሩሲያ ፌዴሬሽን ባህር ሀይል የሆነው ብላክ ሲ ፍሊት የጦር ሠፈር ነች። በዩክሬን ውስጥ የራሽያ ፍቅር የሌለው መንግስት ሥልጣን ቢይዝ የሩሲያን ደህንነት ዛሬም ባይሆን ነገና ከነገ ወዲያ አደጋ ላይ ሊጥለው እንደሚችል ራሸያ ጠንቅቃ ታውቃለች። ይህ አደጋም አፍንጫዋ ስር ሲከሰት እጅ አጣጥፎና ምንም እንዳልተፈጠረ በማስመሰል ማለፍን የራሸያ መሪወችም አልፈለጉም። ስለዚህም ቀልጠፍና ፈርጠም  ያለ እርምጃ መውስድን አስፈላጊ ሆኖ አግኝተውታል። የራሽያው ፕሬዚደንት ፑትን በቅርቡ ለሀገሪቱ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር ክራሚያ ለሩሲያ ምን ያህል ስትራተጂያዊ አስፈላጊነት እንዳላት ሲገልጹ “ ወደ ሜዴትራንያንና ወደ ጥቁር ባህር መሽጋገሪያችን የሆነችው ሶቫስቶፖል በባዕዳን ቁጥጥር ስር ሆና ማየት ከቶውንመ ተቀባይነት የለውም “ ነበር ያሉት።

ከላይ ስንደረደርበት የቆየሁት አመለካከት ወዳገራችን ሁኔታ ሲመለስ፤ ኢትዮጵያሰ ስለ ኤርትራ ምን ያስጨንቃታል የሚለውን ጥያቄ ማጫሩ አይቀሬ ነው። ከዚህ አኳያ እያንዳንዱ ሰው የየራሱን ምርምር አድርጎ መደምደሚያ ላይ እንዲደርስ ያስፈልጋል ብዬ አስባለሁ። ሆኖም ግን ኢትዮጵያ በታሪክ፣ በኢኮኖሚ፣ በሀገር ደህንነት ወዘተ አንጻር እጅግ ብዙ ጉዳት እንደደረሰባት  እና ወደፊትም መገመት የሚከብድ አደጋ እንደተጋረጠባት ብዙወች በመረጃ አስደግፈው ጽፈውበታል። በኢኮኖሚ አንፃር ብቻ ሲታይ እንኴ የራሷን ወደብ እንድታጣ የሆነችው ኢትዮጵያ ለጂቡቲ መንግስት ለወደብ ኪራይ የምትክፍለው ገንዘብ በየቀኑ በሚሊዮኖች የሚቆጠር እንደሆነ ይታወቃል:: ይሀ ገንዘብ ለሀገር ልማት ቢውል ኖሮ የምን ያክል ህጻናትን ህይወት ማዳን እንደሚቻል ምን ያህል ተጨማሪ ትምርት ቤት ጤና ጣቢያ ማቌቌም እና ህይወት ማዳን እንደሚቻል ስናስብ የሁኔታውን አንገብጋቢነት ለመገንዘብ ይረዳል::

አሁን ካለው አሀዝ ስንነሳ ኢትዮጵያ የራሷን ወደብ አጥታ ለጅቢቲ የምትከፍለው ወጪ  በያመቱ ለአንዳንዱ ወረዳ በሚሊዮኞች የሚቆጠር ተጨማሪ በጀት ለመመደብ የሚያሰችል ነው። ይህ ታዲያ ድህነትን ለመቀነስ፣ ለልማት ወዘተ ምን ያህል አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ማንናውም ጤነኛ አእምሮ የሚገነዘበው ነው።

በዚህ አንጻር ሰፋ ያለ ግንዛቤ ለማግኘት ለሚፈልግ ሁሉ የዶ/ር ያዕቆብ ሐይለማርያም “አሰብ የማን ናት”፤ የአምባሳደር ዘውዴ ረታን “የኤርትራ ጉዳይ”፤ ባዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የታተመውን “የአክሊሉ ማስታወሻ” ጥሩ ግንዛቤና መረጃ ሊሰጡ የሚችሉ መጻህፍት መሆናቸውን መጥቀስ እወዳለሁ።

የሶቭየት ህብረት መፈራረስ ክራሚያና ኤርትራ
የሲቭየት ህብረት መፈራረስን ተከትሎ በነበረው ያልተረጋጋ ወቅት ክራሚያም በግርግር ከዩክሬን ጋር ተደባልቃ ከራሸያ ተገንጥላ እንድትሄድ አድርገዋል የሚባሉት እንኳንስ ለሀገር ለራሳቸውም ማሰብ ይሳናቸው ነበር እየተባለ የሚነገርላቸው ፕሬዚደንት ቦሪስ ዬልሰን ናቸው:: ግለሰቡ የዚሀ አይነት ውሳኔ ሲወስኑ የክሬሚያን ታሪክ፣ ስትራተጂክ ጠቀሜታ ወዘተ ከቁብ አላስገቡትም፣ የህዝቡንም ስሜት ቦታ አልሰጡትም ነበር። የሳቸው ሩጫ ከምን እንደመነጨ በግልጽ በማይታወቅ መልኩ ጎርባቾቭ የቀደዱትን የለውጥ መንገድ በመለጠጥ ሶቭየት ህብረትን በማፈራረስ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ ክራሚያን በተመለከተም የሶቭየት ህብረት ታላቅ የባህር ሀይል የሆነው ብላክ ሲ ፍሊት ንብረት ሽያጭና ገንዘብ መሰብሰብ ላይ ነበር ትኩረታቸው። ያም ሆኖ  በንግድ አንጻር እንኳ እዚህ ግባ የሚባል ገንዘብ አላገኙበትም።

የክራምያን ጉዳይ መደምደሚያ ለመስጠት የተሞከረው በሶቭይት ሕብረት ባጠቃላይ እንዲሁም በራሽያና በተቀሩት  ሶሻሊስት ሀገሮች ታይቶ የማይታወቅ ቀውስ እና አለመረጋጋት በሰፈነበት ወቅት ነበር። በዚያ የቀውስ ወቅት በቂ የሆነ አማራጭና ረጋ ብሎ ለማሰብ ጊዜ ሳይኖር ሬፈረንደም ተካሄደና 58% የሚሆን ህዝብ ደገፈው በማለት ክራሚያ ከሩሲያ ተለይታ የዩክሬን ግዛት ሆና እንድትሄድ ተወሰነ።

ይህ ጉዳይ ግን በብዙ ዜጎች ልብ ውስጥ ቁርሾ አስከተለ፤ ጠባሳም ጣለ። የጊዜው ሁኔታ ባይመችና በወቅቱ ማድረግ ስለሚገባቸው ነገር ግራ ቢጋቡም፤ እጅግ ብዙ የክራሚያ ኑዋሪዎች ልባቸው መሸፈቱ አልቀረም፡፡ በዘሩም በታሪኩም ራሽያዊ ነኝ ብሎ የሚያምነው የክሬምያ ሀዝብ የለም ዩክሬናዊ ነህ ሲባል ጥርሱን ነከሰ። ሆኖም ግን በወቅቱ የሚያዳምጠው አላገኝም። ያ ታምቆ የቆየ  ቅሬታ  አሁን በቅርቡ አመጽ ወልዶ እነሆ እየሆነ ያለውንና የሆነውን ዓለም እየመሠከረ ነው።

የኤርትራ ከኢትዮጵያ የመገንጠል ዕውነታ ከሶቭየት ህብረት መፈራረስ እና ከቀዝቃዛው ጦርነት “መገባደድ” ጋር በቅርብ የተቆራኘ ነበር፡ “ህዝበ ውሳኔ” (ሬፈራንደም ) የተባለው ሂደትም በሀሪቱ በከፍተኛ ቀውስ ውስጥ በነበረችበት፣ ገና ቋሚ መንግስት እንኳን ሳይኖራት ነበር። በ“ህዝበ ውሳኔ” ሂደት ውስጥም የኢዮጵያዊነት አማራጭ በታፈነበት ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምነውና የሆነውን የአፋርና ኩናማ፣ የሳሆ፤ ወ.ዘ.ተ ህዝብንም ፍላጎት ለማክበር ምንም ጥረት ሳይደረግና ውጤቱም ሳይታይ በግድ ያልሆነውንና ያላመነበትን ማንነት  ተቀበል ተብሎ የተጠናቀቀ የግርግር ሁኔታ ነው። ይህ ስለሆነም እነሆ እስካሁን የቀጠለው ቅሬታ የመሳሪያ ግጭትን ወልዶ ካንድ ቀውስ ወደሌላ በመሽጋገር ላይ ይገኛል።

የሚገርመው ከስልሳ አመት በሓላ ሩሲያ በክሩስቼቭ ጊዜ የተጀመረውን ያስተዳደር ክልል ማሸጋሸግ እና በቦረስ ዬልሲን ዘመን የተወሰደውን የረጅም ጊዜ ዕይታ የጎደለውን የፖለቲካ ርምጃ ለማረም የተዘጋጀ ድርጅትና መሪ አግኝታለች። ኢትዮጵያችን ግን በሁሉም መልኩ ሀላፊነት የጎደለውን የመለስ ዜናዊ ለሀገር ደንታ ቢስ የሆነ ውሳኔ ለማረም እና ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ጥቅም በድፍረት የቆመ የመንግስት መሪ ገና አልታደለችም። ያም በመሆኑ መከራውም ቀጥሏል መፍትሄውም እየተወሳሰበ መሄዱ አይቀሬ ሆኗል።

የተባበሩት መንግሥታት “የዩክሬንን ሀገራዊ አንድነት ስለማሰከበር” ያካሄደው የድምጽ አሰጣጥ
የክሬሚያ ነዋሪወች በዩክሬን ስር መተዳደርን አንፈልግም ብለው ማጉረምረም ሲጀምሩ ነው ታላላቆቹ የምእራብ መንግስታት ሁኔታውን ለማዳፈን መሯሯጥ የጀመሩት። የክሬምያን ህዝብ ታሪክ፣ ፍላጎትና ማንነት ጠንቅቀው የሚያውቁት ምዕራባውያን ጭንቀታቸው ያነጣጠረው በክሬምያ ላይ ሳይሆን ሩሲያ እንደገና ተጠናክራ በመውጣት ጉዳይ ላይ ስለሆነ ይህንን ለማከሽፍ፣ ባለፈው የካቲት መጨረሻ ገደማ ዩክሬን ውስጥ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠው መንግስት ባመጽ ሲፈነቀል ቃል ያልተነፈሱት ምዕራባውያን፤ በክራሚያ የተደረገውን ሬፈረንደም ተከትሎ ዩክሬን ተወረረ፣ ወዘተ፤ የሚለውን ከበሮ መደለቅ ጀመሩ። ከሁካታው በስተጀርባ ግን አሁን ባለው ሁኔታ ምዕራባውያኑም ሆኑ ራሱ የዩክሬይን መንግስት የክራሚያ ጉዳይ ያለቀለት እንደሆነ የተቀበሉት ይመስላል። ሩጫው ሊፈጠር የሚችለውን ሌላም ምስቅልቅል ሁኔታ ለመቀነስ ምናልባትም ራሱ የዩክሬን እንደሀገር የመቀጠል ጉዳይ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ የመጨነቅ፣ ሰፋ ያለ የርስ በርስ ጦርነት ባውሮፓ ውስጥ እንዳይቀሰቀስ የመፍራት ጉዳይ እንጂ ክራሚያን የማስመለስ ፍላጎት አይመስልም።

የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ጥበቃው ምከር ቤት (ድምጽን በድምጽ ሽሮ ጥርስ-አልባ የሆነው) እና ጠቅላላ ጉባኤውም በዚህ ጉዳይ ያስተላለፈውና ከፍተኛ ክፍፍል የነበረበት ውሳኔ “ይህን ብለን ነበር “ ከማለት የማያልፍ ነው። ጠንከር ያለ የማዕቀብ እርምጃ ወሰዱ የተባሉት አሜሪካና የአውሮፓ ማህበረሰብም ቢሆኑ ርምጃቸው ጥቂት ባለስልጣኖችን የሚነካ ከመሆን አላለፈም።

ቀረብ ብሎ ሲታይ ደግሞ ያፍሪካ መንግስታት በተለይም የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግስታት የወሰዱት አቋም ትኩረትን የሚስብ ነው፡፡ የሁለቱም ወኪሎች  በተባበሩት መንግስታት ውሳኔ አሰጣጥ ላይ የክሬምያን ከዩክሬን መገንጠል ሳያወግዙም ሳይደግፉም ድምጽ ተአቅቦ (አብስቴን) በማድረግ ማለፉቸውን እንገነዘባላን።

ይህ የድምጽ አሰጣጥ ከብዙሀኑ ያፍሪካ ሀገሮች የተለየ አይደለም፤ በተባበሩት መንግሰታት ምክር ቤት ”የዩክሬንን ሀገራዊ አንድነት ማሰከበር “ በሚል ርእስ የክራሚያን መገንጠል ለመቃወም የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ የደገፉ ያፍሪካ ሀገሮች 19 ብቻ ሲሆኑ የተቃውሞ ድምጽ ያሰሙ ሁለት (ሱዳንና ዚምባብዌ ) ድምጸ ተአቅቦ ያደረጉ ደግሞ ወደ 22 ያፍሪካ ሀገሮች ነበሩ። ከነዚህም ውስጥ ኢትዮጰያና ኤርትራ ይገኙበታል። ይህ በሶሰት ቦታ የተከፈለ የድምጵ አሰጣጥ  የሚያሳየው የተባበሩት መንግሥታትም ሆነ ያፍሪካ አንድነት ማህበር በተመሳሳይ ሁኔታዎች ላይ የሚወስዷቸው አቋሞች ከሀገራቸው ፖለቲካ፣ እና ከሚያስገኝላቸው ጥቅም አንጻር እንጂ ከቋሚ መተክልና ዕምነት በመነሳት እንዳልሆነ ነው፡፡

ከዚህ ሁኔታ መገንዘብ እንደሚቻለው ለተመሳሳይ ሁኔታወች እያንዳንዱ ሀገር ስለሚወስደው እርምጃ ወሳኙ ጉዳይ “የተባበሩት መንግስታት ወይም ያፍሪካ አንድነት ህግ” ሳይሆን እያንዳንዱ ሀገር የሚያገኘው ጥቅማ ጥቅም እንደሆነ ነው። ባጭሩ የሀይል አሰላለፉን  የሚገዛው መተክል (ፐሪንስፕል) ሳይሆን በጊዜው ሀገራት የሚያገኙት ጥቅም እና የሀይል ሚዛን ይመስላል።