onsdag 27. september 2017

ቀነኒሳ ሰው ገደለ

ቀነኒሳ ሰው ገደለ

ሟች አቶ አበራ የቀነኒሳ የረዥም ጊዜ ተንከባካቢ ነበሩ። እንደወትሮው የቀነኒሳን መኖሪያ ለማፀዳዳት ሲገቡ ሳይዘጋ የተረሳው ሌላኛው ክፍል የነበረው በመውጣጥ አቶ አበራን ገሏቸዋል ።
ስለምን እንደማወራ ገብቷቹሃል ? ቦታው 6ኪሎ አካባቢ የሚገኘው የአንበሳ ጊቢ ፓርክ ነው።እየነገርኳቹ ያለሁት ስለ ጀግናው አትሌት ቀነኒሳ ሳይሆን ስለ የዱር ጀግናው «አንበሳ» ነው። አቶ አበራም ( ነብስ ይማር ) በዚሁ ጊቢ ውስጥ የሚሰሩ ሲሆን የአንበሳውን ክፍል ለማፅዳት ቀነኒሳን ወደ ሌላኛው ክፍል አስገብተው ሳይዘጋ መዘንጋቱን በመጠቀም ወዳሉበት ክፍል በመግባት ሊገላቸው በቅቷል።  ነብሳቸውን ለማዳን በተደረገው ተኩስ አለቅ በማለቱ የማደንዘዣ ባለሙያ በስልክ ተጠርቶ ሙከራ ቢደረግም ሊሳካ አልቻለም።
ነብስ ይማር ለቤተሰቦቹ መፅናናትን እመኛለሁ :(

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar