mandag 11. desember 2017

የአማራ የኦሮሞ እና ወላጆች የልጆቻቸውን አስከሬን እስከመቼ ይቀበሉ?

አዲሡ ሥራ አሥፈፃአሚ ተግባራዊ ሥራውን ጀመረ የ አማራና ኦሮሞ ተማሪዎችን በማሥጨፍጨፍ
በዩኒቨርስቲ ውስጥ እኛም አልፈናል። የብሔር ግጭትን ጨምሮ አልፎ አልፎ በግቢዎች ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ ይነሳል። ግጭቶችን ለማብረድ የመንግሥት ፀጥታ አካላት በግቢዎች ውስጥ ትጥቃቸውን አንዠርገው ከመዟዟር ጀምሮ በሌሊቱ መሬት አስቀምጠውን በቆፈን እንድንጠበስ ያደርጉናል። ከብዙ ዛቻ እና ስድብ አለፍ ካለ አስካርባ እና ግፍተራ ነበሩ ቅጣቶች። በዚህ ሁሉ ጊዜ ግን የአካባቢው ማኅበረሰብ እንደወላጅ ከመንሰፍሰፍ ባለፈ እህል ውኃ በማቅረብ እንዲሁም በተማሪዎች እና በፀጥታ አካሉ/የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር መካከል አስታራቂ ሆኖ በመቅረብ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲቀጥል በማድረግ ረገድ አይነተኛ ሚና ይጫወት ነበር። በቅርብ ጊዜ እንኳን በመቱ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ወደ ቀያችን እንመለሳለን ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች በተለይም አባ ገዳዎች እና የኃይማኖት አባቶች በመሐል ገብተው አግባብተው ወደ ግቢ መልሰዋቸዋል። ይህ ከጨዋ ማኅበረሰብ የሚጠበቅ ቅዱስ ማኅበራዊ ኃላፊነት ነው።
*****
“#በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጎበዝና ታታሪው የምዕራብ #ጎጃም የፈረስ ቤት ተወላጁና በፅንፈኛ #ትግሬዎች በግፋ የተገደለው ወንድማችን #ሀብታሙ #ያለው ይህ ነው።
ለቤተሰቦቹ መፅናናትን እንመኛለን
ይህ ፈቶ የተለቀቀው ቤተሰቦቹ ስለሰሙ ነው
አዲግራት ውስጥ የምንሰማው ጉድ ከላይ ካነሳነው ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ነው። በአዲግራት ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ከሌላ አካባቢ በተለይም ከአማራ ክልል የመጡ ተማሪዎችን የከተማው ወጣቶች ከማዋከብና ማስፈራራትም አልፈው ሕይወት እስከመጥፋት የደረሰ አደጋ አድርሰውባቸዋል። (አቶ ንጉሱ ጥላሁንና አቶ ዳንኤል ብርሃነ በፌስቡክ ገፃቸው የሞቱን ዜና አረጋግጠዋል።) አዲግራት ዩኒቨርስቲ በከተማው በመኖሩ ቁጥር አንድ ተጠቃሚዎች የአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው። ይህን በመዘንጋት ይሁን ተማሪዎችን የማዋከብ እና ትምህርታቸውን ተረጋግተው እንዳይከታተሉ ወጣቶቻቸው በሕይወት የመኖር ዋስትናቸውን ሳይቀር አደጋ ላይ ጥለውታል። ይህ በምንም መመዘኛ አሣፋሪ እና ለአካባቢው ማኅበረሰብ መልካም ስምም የማይመጥን ርካሽ ተግባር ነው።
*****
አማራነታቸው እንደወንጀለኛ አስቆጥሯቸው የመስዕዋት በግ የሆኑ ተማሪዎች ከሚመለከተው አካል የደህንነት ዋስትና ካላገኙ እዚያው መቆየታቸው ተገቢ ነው ብዬ አላምንም። የትምህርት ሚኒስቴር እነዚህ ተማሪዎች ከትግራይ ክልል ውጭ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመድባቸውና ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ ሊደረግ ይገባል። የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትም እነዚህ ተማሪዎች እንዳዲስ እስኪመደቡ ድረስ በሰላም ወደ ቀያቸው የሚመለሱበትን መንገድ ሊያመቻች ይገባል። የአማራ ወላጆች የልጆቻቸውን አስከሬን እስከመቼ ድረስ እንዲቀበሉ ይፈረድባቸው?

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar