mandag 22. januar 2018

ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ ኦስሎ በደማቅ ተከናወነ

የዲሞክራሲያዊ ስርዓት  ምስረታን በሀገራችን እውን ለማድረግ በሚደረገው ርብርብ ትግሉ የሚፈልጋቸውን የድጋፍ ዘርፎች እያጠና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ላይ ያለው እና መቀመጫ ዋና ፅህፈት ቤት በኦስሎ ኖርዌይ  በማድረግ  እየሰራ የሚገኝው  የድሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጭ ድርጅት በኖርወይ  በትናትናው ዕለት ማለትም በ19.01.2018 እኤአ የጠራው ሰላማዊ በደማቅ ሁኔታ ተከናዉኗል።
በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሶስት መሰረታዊ ነጥቦችን በማንሳት መልእክት ተላልፏል ፡
  1. የሃገራችን ህዝብ ለነፃነቱ እና የዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲኖረው ከዘረኛው አገዛዝ ጋር የሞት ሽረት ትንቅንቅ ላይ ባለበት በዚህ ወቅት የኖርዌይ መንግሥት ከኢትዮጵያ አምባ ገነን ገዥዎች ጋር እያደረገ ያለው የዲፕሎማቲክ ግንኙነት እና የገንዘብ ድጋፍ በማቆም ከህዝብ ጎን እንዲቆም ለማሳሰብ :
  2. በሊቢያ እና በመካከለኛዉ ምስራቅ ሃገራት የሚደረገውን የባሪያ ንግድ ለማስቆም የኖርዌይ  መንግስት የበኩሉን ስራ እየስራ ያለመሆኑን ለመቃወም ;
  3. በኖርዌይ የምገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የሚደረገውን የማዋከብ እና ያለ ምንም የመጉዋጉዋዣ ሰነድ እና ፍቃደኝነት የሚደረገውን ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ  ተግባር አጥብቆ ለመቃወም ሲሆን ::
ሰልፉም ከመሃላ ከተማ ያረባነቶርጌት ተጀምሮ  የኖርዌይ ፓርላማ ፊትለፊት ተሰላፊው ድምፁን በማሰማት ወደ ውጭ ጉዳይ ቢሮ በማምራት በዚያ ተቃውሞን በከፍተኛ ድምፅ ካሰማ በሁኋላ የተዘጋጀውን  ደብዳቤ በድርጅታችን ፅሃፊ ወይዘሪት ኤልሳቤጥ ግርማ አማካኝነት  በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  የአፍሪካ ቀንድ  እና ምእራብ  አፍሪካ ከፍተኛ አማካሪ  ማራታ ዲሩድ ተረክበዋል።  ተወካይዋ ጉዳያችንን በጥልቀት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  በኩል እደሚመልከቱት እና መልሳቸውን በደብዳቤ እንደሚያሳውቁን ገልፅውልናል ::
በሰልፉ መዝጊያ የሰልፉ አስተባብስሪ አቶ ፍቅሬ አሰፋ ለታዳሚው ባደረጉት ንግግር በሃገራችን እና በመላው አለም በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለው መከራ እና በደል ምንጩ  በሃገራችን የሚገኝው አገዛዝ ሲሆን ይንን ጠባብ ገዥ መደብ በውስጥም በውጭም በሚደረግ ትግል አዳክሞ ማፍረስ እና በሁሉም የሁሉ የሆነ የዲሞክራሲያዊ ስርዓት በመስረት ዛሬ ነጌ የማይባልበት ጉዳይ በመሆኑ ተናግረዋል :: ድርጅታቸው ለዝሁ ኢትዮጵያን የመታደግ አላም ከሚታገሉ ሃይላት ጋር በትብብር  በፅናት እየሰራ መሆኑንም አክለው ተናግረዋል ::
አቶ ፍቅሬ  በተጨማሪ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ ቀጥታ ወደ ኦስሎ መብረር  መጀመሩን ተከትሎ የኖርዌይ መንግስት ኢትዮጵያ ካለው አገዛዝ ጋር ከአለም አቀፍ ህግ ጋር በተቃረነ መልኩ የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቁ ኢትዮጵያውያንን ያለ ፓስፖርት እና ከስደተኞቹ እውቅና ውጭ በሌሊት እያፈኑ አውሮፕላን ውስጥ በማስገባት ቦሌ አየር ማረፊያ  እየወሰዱ መጣል መጀመራቸው እንደ ኢትዮጵያዊ በጣም የሚያሳዝን ተግባር ነው ብለዋል :: ይህ  ተግባር የኢትዮጵያን ክብር የሚነካ ውርደትም ነው ብለዋል።  በዚያች ሃገር ማንነቱ እንኩዋን ሳይጠየቅ የተላከ መረጃ ሳይኖራቸው ጭምር የወያኔ ደህንነቶች ጋር ተመሳጥረው በራሳችን አየር መንገድ መታፈን አሳዛኝ ተግባር ስለሆነ  በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ በቀጣይነት በአለም አቅፍ ደርጃ የሚሰሩ ስራዎች  እንደሚኖሩ ተናግረዋል ::
በመጨረሻም ታዳሚው ያለውን ከፍተኛ የኖርዌይ ቅዝቃዜ ተቋቁሞ  በሃገሬ ጉዳይ ያገባኛል  በማለት ስለተገኘ በዲሞክራስያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጭ ድርጅት በኖርዌይ ስም አመስግነው ሰልፉ በተሳካ መልኩ ተፈጽፏል።

ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar