torsdag 23. januar 2014

በመንግስት ተቋማት ላይ ሙስና መስፋፋቱ ተነገረ

ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከለጋሽ አገሮች ባገኘው ድጋፍ ተመስርቶ የውጭ ባለሀብቶችን በማሳተፍ ባስደረገው ጥናት የመንግስት ግዢዎችና ኮንትራቶች ግልጽነት የጎደላቸው መሆናቸውን አረጋግጧል። የውጭ ባለሀብቶች አራት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ሙሰኞች ብለው እንደፈረጁዋቸው ሪፖርተር ዘግቧል።
71 በመቶ የሚሆኑ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ቢዝነስ ለማቀላጠፍ አስቸጋሪ ነው ይላሉ። ባለሀብቶቹ በዋናነት ያነሱትም ሙስና ተስፋፍቷል የሚል ነው። ውስብስብ የሆነው የግዢ ሂደትም ችግር መፍጠሩን ይናገራሉ።
ከ67 በመቶ በላይ የውጭ አገር ባለሀብቶች ጉዳያቸውን ለማስፈጸም ለመንግስት ባለስልጣናት እና ሰራተኞች ጉቦ እንደሚሰጡ ገልጸዋል። የተወሰኑ ባለሀብቶች ጉቦ ከመስጠት ሌላ አማራጭ በማጣታቸው ጉቦ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።
ጉምሩክ፣ ትራንስፖርት፣ የመሬት አስተዳደርና መብራት ሃይል ከፍተኛ ጉቦ የሚበላባቸው መስሪያ ቤቶች ናቸው ተብሎአል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar