torsdag 30. januar 2014

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ጎንደር ላይ ታሰሩ

ከድንበር ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መንግስታት መካከል ያለው ንግግር ለህዝብ ግልጽ እንዲሆን ለመጠየቅ በመጪው እሁድ በጎንደር ከተማ ለማካሄድ የታቀደውን ሰልፍ ለማስተባበር ወደ ጎንደር ያቀኑት የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ሌሊት ከተማዋ ደርሰው በማግስቱ የቅስቀሳ ስራ ሲጀምሩ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
አመራሮቹ ሲታሰሩ የተመለከተ አንድ ታዛቢ ከኢሳት ጋር ባደረገው አጭር ቆይታ እንደገለጸው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ፣   ዮናታን ተስፋየ፣ ወይንሸት ሞላ፣ አቤል ኤፍሬምና ጌታነህ ባልቻ ታስረዋል።
ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የቅስቀሳ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል። ሰሜን ጎንደር ፖሊስ አዛዥን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
ባለፈው አርብ በትግራይ አዲግራት ከተማ ከህዝብ ጋር ለመወያየት ለቅስቀሳ ስራ ሄደው የነበሩት አቶ አስገደ ገብረስላሴ፣ መምህር አብርሃ ደስታና አቶ አምዶም ገብረስላሴ መደብደባቸው ይታወቃል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar