onsdag 12. november 2014

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሰነዘረዉ ክስ

የኢትዮጵያ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) መንግሥት በፓርቲዉ አመራርና አባላት ላይ የሚሰነዝረዉን ማዋከብ ከምንጊዜዉም በላይ አጠናክሮ ቀጥሎአል ሲል ከሰሰ።

  የፓርቲዉ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል እና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዘካርያስ የማነ ብርሃን እንደገለፁት በሀገሪቱ ሊደረግ የታቀደዉን ብሔራዊ ምርጫ አስመልክቶ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ የሚሰነዘረዉ ወከባ መንግስት የፖለቲካ እንቅስቃሴዉን ለመቆጣጠር ሆነ ብሎ እያደረገ ያለዉ ተግባር ነዉ።
እንደ ሁልጊዜዉ ሁሉ አሁንም የፓርቲዉ አባላት ላይ እስራት፤ እንግልትና ወከባ ይፈፀምባቸዋል፤ ያሉት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባልና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዘካርያስ የማነ ብርሃን ለሀገሪቱ ዘርፈ ብዙ ፖለቲካዊ ችግሮች እስርና ወከባ መፍትሄ አይሆንም የሚል መግለጫ ፓርቲያቸዉ ማዉጣቱን ገልፀዋል። ይህ ደግሞ በመጪዉ ግንቦት በሚደረገዉ ብሄራዊ ምርጫ ላይ ፓርቲዉ እንዳይሳተፍ የተወሰደ ርምጃ ነዉ ያሉት አቶ ዘካርያስ የማነ ብርሃን።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar