mandag 25. mai 2015

ሳይጀመር የተጠናቀቀው

 
_ሳይጀመር የተጠናቀቀው፡ ድምጽ ከመሰጠቱ በፊት ውጤቱ የታወቀው፡ ቀኑ ሳይደርስ አሸናፊው የተረጋገጠለት፡ መራጩ፡ አስመራጩ፡ ተመራጩ፡ ዓለም ዓቀፉ ማህብረሰብም ሁሉም ቀድመው ውጤቱን ያወቁለት ምርጫ 2007። ትላንት የተካሄደው ምርጫ የህዝብ ስሜት የተቀዛቀዘበት፡ በሊግ፡ በፎረም፡ በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት፡ በኮብል ስቶን ስራ የተደራጁ፡ ወጣቶች፡ እናቶች፡ ምርጫ ጣቢያዎችን ሞልተው የዋሉበት ዕለት ሆኖ አልፏል።
- የትላንቱ ምርጫ በአብዛኛው በወከባ ተጀምሮ በወከባ የተጠናቀቀ፡ ኮሮጆዎች ሌሊቱን ሲሞሉ ያደሩበት፡ የተቃዋሚ ታዛቢዎች የተገፉበት፡ በሰራዊት የተጥለቀለቀ፡ እንደነበር ከየአቅጣጫው የሚደርሱን ሪፖርቶች ያመለክታሉ::
_የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ደጋፊ መገናኛ ብዙሃን የአንዳንድ አከባቢዎችን ውጤቶች እየገለጹ ናቸው። በአዲስ አበባና በጎንደር ገዢው ስርዓት ሙሉ በሙሉ አሸንፏል እያሉ ናቸው። ዶክተር መረራ ጉዲናና ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን በተወዳደሩባቸው ቦታዎች አሸነፍኳቸው ብሏል ህወሀት።
_በተለያዩ የጎንደር አከባቢዎች መጠነ ሰፊ አፈናና አፈሳ እየተካሄደ ነው። በቀበሌ 18 ባህረ ሰላም ሆቴል ውስጥ ትላንት 4 ወጣቶች የመከላከያ ሰራዊት ትጥቅ በለበሱ ሰዎች ታፍነው ተወስደዋል። በደምቢያም 20 ኢትዮጵያውያን በፌደራል ፖሊስ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። ከመሃላቸው በ4ቱ ላይ በተፈጸመ ከፍተኛ ድብደባ ለህይወታቸው አስጊ በሆነ አደጋ ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል።
_በምርጫው ግርግር ይፈጠራል በሚል የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ መንግስት ባለስልጣናት ቤተሰቦቻቸውን ወደ ውጭ ሀገራት እየላኩ መሆናቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመለከተ። በቦሌ በኩል እየተሸኙ ያሉት የባለስልጣናት ቤተሰቦች ወደ አሜሪካና አውሮፓ የሚያመሩ እንደሆነም ተገልጿል። ባለስልጣናቱ ግን እንዳይወጡ በህወሀት ቁንጮ መሪዎች እንደታገዱም ከምንጮች መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
ሌሎችም
(http://ethsat.com/esat-radio-special-election-2007-report-…/)

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar