torsdag 14. mai 2015

በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሮሮ

ሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ፓስፖርታቸውን ለማሳደስ ወይም በሌላ ለመቀየር ረጅም ጊዜ በመውሰዱ መቸገራቸውን ገለጹ። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ሳዑዲ አረቢያ በተለይም ጂዳ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ቆስላ አሮጌ ፓስፖርታቸዉን ሰብስቦ አዲሱን ግን ለረጅም ጊዜ አልሰጣቸዉም።
Australische Einreisestempel in einem deutschen Pass
በዚሕም ምክንያት የመኖሪያ ፍቃዳቸዉ ጊዜ ማለፉን ወይም ሊያልፍ መቃረቡን ይናገራሉ። እንደሚሉትም ፓስፖርታቸውን እንዲታደስ ወይም እንዲቀየር ሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የጠየቃቸውን ገንዘብ ቢከፍሉም፤ የታደሰዉን ፓስፖርት ለማግኘት ከአምስት ወራት በላይ ጠብቀዋል። እስካሁን አላገኙትም።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar