tirsdag 1. desember 2015

የባሌ መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሲቃወሙ አመሹ * በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ የፌደራል ፖሊስ የፈጸመውን ግድያ አወገዙ

የአዲስ አበባን አዲሱን ማስተር ፕላን በመቃወም የተነሳው የሕዝብ ቁጣ ወደ ተለያዩ ከተሞች እየተዛመተ ሲሆን የመንግስት ሚድያዎች በበኩላቸው ምንም እንዳልተፈጠረ መረጃዎቹን በማፈን ስለ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እያወሩ ይገኛሉ:: በሃሮማያ ዪኒቨርሲቲ የተማሪዎቹን ሰላማዊ ጥያቄ ፖሊስ በኃይል ለመበተን ባደረገው ጥረት ሰዎች መሞታቸውና መቁሰላቸውን ዘ-ሐበሻ ቀደም ብላ መዘገቧ የሚታወስ ሲሆን ይህን ተከትሎም በባሌ መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ አመሻሹ ላይ ተማሪዎች ቁጣቸውን መግለጻቸው ተሰምቷል:: በመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ቁጣቸውን ከገለጹ በኋላ ወደ መኝታቸው እንደሄዱ የገለጹት ምንጮቻችን በተለይ በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ በመንግስት ኃይሎች የተወሰደውን እርምጃ ተቃውመዋል:: መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደሚገኝ የሚገልጹት ምንጮች አካባቢው በፖሊስ መወረሩም ተዘግቧል::


Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar