mandag 22. april 2013

የትም ይኑር የትም ነው እኮ ህጋዊ

የትም ይኑር የትም  ነው እኮ ህጋዊ


አንዱ ሁሉም ቦታ ሁሉም በ አንድ ቦታ
ተወስኖ እንዲኖር አልፈቀደም  በ አንድ ጌታ።
ይገደብ ሚለው ቃል ለ አባይ መስሎኝ ነበር
እንደምን ተርጉመው አረጉት ለብሔር።
በ አ የሚጀምር ሁሉ ይገደብ ሲል
አባይን ጀምሮ አማራ ሲከተል
እኔስ ልቤ ፈራ በ አፋር እንዳይቀጥል
ትናንት ከደቡቡ ዛሬ ከ ቤንሻንጉል
እያነጣጠሩ አንድን ብሔር ማግለል
መፍትሔውን ሳይሆን ውድቀቱን ያመጣል።
ይሄ መፈናቅል በእስር ቤት ከሰራ
አሣምነው ጽጌ እንዲሁም ተፈራ
ዝዋይ ሆነላቸው ክልሉ የ አማራ።
ተብሎ ተጠርቶ እንኳን ኢትዮጵያዊ
ሌላም ስም ቢሰጠው ገላጭ ለምድራዊ
በፈቃድ ከገባ ሆኖ ሰላማዊ
የትም ይኑር የትም  ነው እኮ ህጋዊ
የትም ይኑር የትም  ነው እኮ ህጋዊ።



 

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar