fredag 14. august 2015

ፍርድ ቤቱ ለሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የሰጠው ዋስት በፖሊስ ታገደ

ነገረ ኢትዮጵያ


nከምርጫው ማግስት ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በፖሊስ ተይዘው ነሃሴ 6/2007 ዓ.ም እያንዳንዳቸው በ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ተጠይቀው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ዋስትናቸው በአቃቤ ህግና በፖሊስ መታገዱን የፓርቲው የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ፖሊስ በአመራሮቹ ላይ ላቀረበው ክስ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ነሃሴ 6/2007 ዓ.ም ከምርጫው ማግስት እየታደኑ የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ 8 የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን እያንዳንዳቸው የ15 ሺህ ብር ዋስ አቅርበው እንዲፈቱ የወሰነ ሲሆን ሁለቱ ወዲያውኑ ወጥተዋል፡፡ ይሁንና የዋስትናው ገንዘብ እስኪሞላላቸው እስር ቤት የቆዩት 6ቱ አመራሮች ትናንት ነሃሴ 7/2007 ዓ.ም የክልሉ አቃቤ ህግና ፖሊስ ለማረሚያ ቤቱ ባቀረቡት ጥያቄ ዋስትናቸው መታገዱ ታውቋል፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ዋስትናቸው የታገደው ገንዘቡን ካስያዙ በኋላ መሆኑም ታውቋል፡፡ እንዲከፍሉ የተጠየቁትን ገንዘብ ካስያዙ በኋላ ዋስትና የተከለከሉት አመራሮች፡-
1. ልዑልሰገድ እምባቆም
2. ፋንታሁን ብዙአየሁ
3. መንግስቴ ታዴ
4. አዳነ አለሙ
5. ስማቸው ምንይችል
6. አበባው አያሌው ናቸው

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar