fredag 19. juli 2013

በወልድያ 2 ወር ያልሞላትን አራስ ጨምሮ ከ10 ያላነሱ ሙስሊሞች ታሰሩ


ዘወትር አርብ የሚደረገውን ስግደት ተከትሎ ተቃውሞ ሊያስነሱ ይችላሉ ተብለው የተጠረጠሩ ከ10 ያላነሱ የወለድያ ከተማ ነዋሪዎች ታስረው ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል።


ከታሰሩት መካከል ኢብራሂም ገበየሁ፣ ከድር ሙሀመድ፣ ወ/ሮ ሀያት ይማም፣ ወ/ሮ ነሲሳ አህመድ፣ ወ/ሮ ሀያት አህመድ ይገኙበታል። ወ/ሮ ሀያት አህመድ ሁለት ወር ያልሞላት አራስ ስትሆን፣ ወደ እስር ቤት የተወሰደችውም አዲስ ከተወለደው ህጻኗ ተለይታ ነው።


በፖሊስ ጣቢያው አካባቢ የተሰባሰበው ህዝብ ” ቤተሰቦቻችንን ፍቱልን” በማለት ከሰአት በሁዋላ በፖሊስ ጣቢያ አካባቢ በመሰባሰብ ጥያቄ ቢያቀርብም፣ በፖሊስ ተባረዋል።


የአካባቢው ሙስሊሞች “መሄጃ አጣን” በማለት ግራ መጋባታቸውን ተናግረዋል።


በጉዳዩ ዙሪያ የወልድያን ፖሊስ ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar