mandag 8. juli 2013

አንድነት ፓርቲ በጎንደር የጠራውን ሰልፍ በመንግስት ጥያቄ ማራዘሙን ገለጸ



ፓርቲው በላከው መግለጫ   ቀኑ እንዲራዘም የተደረገው የከተማው ከንቲባ በእለቱ የተማሪዎች የምረቃ በአል ፣ የመንገድ ምርቃና የፖሊስ ሀይሉ በስልጠና ላይ በመሆኑ በቂ ሀይል የለም በሚል ፓርቲውን በጠየቀው መሰረት ነው።

ፓርቲው በከንቲባው የቀረበውን ጥያቄ ተገቢ ሆኖ ስላገኘነው በጎንደር የሚደረገውን ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ከሰኔ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ወደ እሁድ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም ማራዘሙን አስታውቋል።

በሰሜን ጎንደር ዞን በምዕራብ አርማጭሆ አብርሃ ጅራ ከተማ አቶ አለልኝ አባይ፣ አቶ እንግዳው ዋኘው፣ አቶ አብርሃም ልጃለምና አቶ አንጋው ተገኝ የፓርቲውን የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ወረቀቶች ለምን በተናችሁ ተብለው ከሰኔ 22 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ  እንደሚገኙ ፓርቲው ገልጿል።

በጎንደር ከተማ አቶ ማሩ አሻገረ ከሰኔ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ፣ አቶ አምደማሪያም እዝራ እና አቶ ስማቸው ዝምቤ ከሰኔ 25 ቀን 2005ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኙ የገለጸው አንድነት  በወገራ አቶ ጀጃው ቡላዴ ሰኔ 25 ቀን 2005 ዓ.ም ታስሮ ተለቋል፡፡

አቶ ጋሻው ዘውዱ በተባሉት ላይ  ጥይት በመተኮስ የመግደል ሙከራ ቢደረግበትም ሮጦ ለማምለጥ መቻሉን፣ በአለፋ ጣቁሳ ወረዳ መምህር አዋጁ ስዩም ከሰኔ26 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በእስር እንደሚገኙ ፓርቲው በላከው መገለቻ አብራርታል።

በህገወጥ መንግድ የታሰሩ አባላት የርሀብ አድማ ላይ እንደሚገኙም ፓርቲው ገልጿል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar