torsdag 28. november 2013

በሳውድ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እንደቀጠለ ነው

ኢሳት ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን እንደገለጹት ስትርሀ እየተባሉ በሚጠሩ የማጎሪያ ካምፖች ውስጥ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛሉ።
በውሀ እና በምግብ እጥረት የሚሰቃዩ እርጉዝ ሴቶች፣ ህጻናትና እናቶች አሁንም የድረሱልን ጥሪያቸውን እያሰሙ ነው። በማጎሪያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊን ምግብ እና ውሀ ለመግዛት ወጣ ሲሉ እንደሚገደሉ ጓደኞቻቸው የተገደሉባቸው ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል
የኢሳት የአዲስ አበባው ዘጋቢ እንደገለጸው ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት በአይ ኦ ኤም ወጪ ህክምና እየተሰጣቸው ሲሆን ብዙዎች ከአካል ጉዳት በተጨማሪ ለስነልቦና ቀውስ መዳረጋቸው ታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሳውዲ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጽመውን ግፍ ለመቃወም የሚደረጉ ሰልፎች ቀጥለዋል። በስዊድን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ረቡእ እለት በኢትዮጵያ ኢምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ የሳውዲን ንጉስ ፎቶ ግራፍ አቃጥለዋል። ሀሙስ እለት ደግሞ በስፔን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ማድሪድ በሚገኘው የሳወዲ ኢምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። ኢትዮጵያውያኑ አቤቱታቸውን ለሳውዲ ኢምባሲ ተወካይ ማቅረባቸውም ታውቋል;፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar