torsdag 7. november 2013

ከአባይ ግድብ ቅርብ ርቀት የተቀበረ ቦንድ ፈነዳ


 ትላንት ስለሽብርተኞች እና አሸባሪዎች አዋጅ አይሉት መግለጫ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲተላለፍ ነበር። በንጋታው ህዝቡ በዚህ ጉዳይ ሲነጋገር፤ “ኢህአዴግ ሰው ሊያስር ወይም ራሱ ቦንብ ማፈንዳት ሲፈልግ ነው ህዝቡን እንዲህ የሚያሸብረው።” እየተባለ ከተማ ውስጥ ሲወራ ቆየ። ይኸው ወሬ ሳያልቅ፤ እንደተፈራው በምዕራብ ኢትዮጵያ፤ ለአባይ ግድብ ከሚቀርበ ሸርቆሌ ከተማ፤ የመሬት ውስጥ የተቀበረ ፈንጂ ፈንድቶ አራት ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው እንግዲህ የኢዜአ ሰዎች፤ ድርጊቱ በአሸባሪዎች መፈጸሙንና የሟቾቹንም ቁጥ ቀንሰው ሶስት ሰዎች መሞታቸውን የነገሩን። ለማንኝውም ዜናውን አርመን ከዚህ በታች አቅርበነዋል።
bomb blast
በሸርቆሌ ከተማ አቅራቢያ የተቀበረ ፈንጂ ፈንድቶ በደረሰዉ አደጋ ሶስት ሰዎች ሲሞቱ በዘጠኝ ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ
አሶሳ ጥቅምት 27/2006 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሸርቆሌ ከተማ አቅራቢያ በመንገድ ላይ የተቀበረ ፈንጂ ፈንድቶ ባደረሰዉ አደጋ ሶስት ሰዎች ሲሞቱ በዘጠኝ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ ። በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት የስራ ሂደት ባለቤት ኮማንደር ታከለ ማሞ ዛሬ እንዳስታወቁት አደጋው የደረሰው ከሸርቆሌ ወደ አሶሳ አቅጣጫ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒ ባስ በመንገድ ላይ የተቀበረ ፈንጂ ላይ በመዉጣቱ ነዉ። በዋናው የመኪና መንገድ በተለምዶው ሰኞ ገበያ በጉንሳ ጎጥ በተባለው አካባቢ ትናንት ከቀኑ አምስት ሰዓት ላይ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 ቤጉ 00203 የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ለጊዜዉ ማንነታቸዉ ባልታወቀ በተቀበረ ፈንጂ ላይ በመዉጣቱ በሰዉ ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ። በሚኒባሷ ውስጥ ከተሳፈሩት 12 መንገደኞች መካከል የሶስቱ ህይወት ወዲያዉኑ ሲያልፍ በአምስቱ ላይ ከባድ ፣በአራቱ ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱንና ተጎጂዎቹ በአሶሳ ሆስፒታልና ሸርቆሌ ጤና ጣቢያ ህክምና እየተደረገላቸዉ መሆኑን ኮማንደር ታከለ ገልጠዋል ። በአደጋው ህይወታቸው ካጡት ሰዎች መካከል እድሜው ከአስር ዓመት በታች የሆነ አንድ ህፃንና አንዲት ሴት እንደሚገኙበት ኮማንደሩ አስረድተዋል ። አደጋውን ያደረሰው ማንነት እስካሁን በውል ያልታወቀ ቢሆንም የጸረ ሰላም ቡድኖች ድርገት ሳይሆን እንደማይቀር አንዳንድ ጠቋሚ መረጃዎች እንደሚያመላክቱ ኮማንደሩ ተናግረዋል ።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar