onsdag 23. april 2014

የእውቅና ፎርም ከሞላ በኋላ፣ ሰማያዊ ለሚያዚያ 19 ሰልፍ ወደ ተግባር መሄድ እንደሚችል አስተዳደሩ ገለጸ

የአዲስ አበባ አስተዳደር ሚያዚያ 15 ቀን ለሰማያዊ ፓርቲ በጻፈው ደብዳቤ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን ሊያደርግ ላሰበው ሰላማዊ ሰልፍ፣ በአስተዳደሩ ሕጋዊ አሰራር መሰረት፣ የሚገባዉን የእውቅና ፎርሞ እንዲሞላና ወደ ቅስቀሳ እንዲሰማራ ጠየቀ። 
addis-ababa-semayawi-party
«የእወቅና ጥያቄ ፎርም ሳትሞሉ ሕጉን በመጣስ ወደ ተለያዩ የተግባር እንቅስቃሴ የገባችሁ ስለሆነ ከዚሁ ተግባራችሁ ታቅባችሁ ወደ ህጋዊ አሰራር በመግባት ማሟላት የሚገባችሁን አማልታችሁ የ ወቅና ፎርም በመሙላት ወደ ተግባር እንድትገቡ እናሳሰባለን» ሲል የገልጸው አስተዳደሩ፣ መሞላት ያለበት ፎርም ከተሞላ ሰማያዊ በሚያዚያ 19 ቀን ሰልፍ ማድረግና ለሰልፍ የሚያስፈልጉትን ተግባራት መፈጸም እንደ ሚችል ለምገልጽ ሞክሯል።
አስተዳደሩ ያለፈው ሳምንት፣ ለሰማያዊ ፓርቲ በጻፈው ደብዳቤ፣ በሚያዚያ 19 ቀን ሰልፍ ማድረግ እንደማይቻል መግለጹ ይታወቃል።
ከአዲስ አበባ አስተዳደር አካባቢ ካሉ፣ ምንጮቻችንም በደረሰን ዘገባ መሰረት፣ አስተዳደሩ ከደህንነት ሃላፊዎች በቀጥታ በደረሰዉ ትእዛዝና መመሪያ፣ ለአንድነት ፓርቲ የከለከለዉን፣ ሰማያዊ ፓርቲ ግን ሚያዚያ 19 ቀን ሰልፍ እንዲያደርግ ሊፈቅድ እንደሚችል መዘገባችን ይታወቃል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar