tirsdag 15. april 2014

‘ድምፃችን ይሰማ’ - የተቃውሞ ድምፅ አሰማ

በሽብር ወንጀል ተከስሰው በክርክር ላይ የሚገኙት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና ሌሎችም ተከሣሾች ለፍርድ ቤት ሲሰጡ የቆዩትን ቃል ዛሬ አጠቃልለዋል።
‘ድምፃችን ይሰማ’ - የተቃውሞ ድምፅ አሰማ /ፎቶ አል-ጃዚራ/

ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት

በሽብር ወንጀል ተከስሰው በክርክር ላይ የሚገኙት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና ሌሎችም ተከሣሾች ለፍርድ ቤት ሲሰጡ የቆዩትን ቃል ዛሬ አጠቃልለዋል።

የመከላከያ ምሥክሮችን ለመስማት ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ሰላማዊ ትግል የሚመራ ”የድምፃችን ይሰማ ንቅናቄ” ዛሬ በአዲስ አበባው የአንዋር መስጅድና በሌሎችም ከተሞች የመፍትሔ አፈላላጊውን ኮሚቴ የፍርድ ሂደት በማስመልከት ”ፍትህ ተነፍገን ትግላችን አይቆምም” የሚል መፈክር በማንገብ ሰላማዊ ተቃውሞ ማካሄዱን ገልጿል።

በኢትዮጵያ ሙስሊሞች በሣምንቱ በየመስጅዶች ይካሄድ የነበረው ተቃውሞ ረዘም ላለ ጊዜ ቆሞ እንደነበር ይታወቃል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar