tirsdag 16. september 2014

አቶ የሽዋስ አሰፋ የርሃብ አድማ አደረገ

በማዕከላዊ ምርመራ ታስሮ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ  አቶ የሽዋስ አሰፋ የአራት ቀን የርሃብ አድማ
ማድረጉን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። አቶ የሸዋስ ከጳጉሜ 4 ጀምሮ አዲሱን አመት በርሃብ አድማ ያሳለፈ ሲሆን ቅዳሜ መስከረም 3/2007 ዓ.ም ምግብ እንደቀመሰ ባለቤቱ ወይዘሮ
ሙሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡
አቶ የሽዋስ የርሃብ አድማ ያደረገው ከታሰረበት ሐምሌ 1/2006 ዓ.ም ጀምሮ ከጠበቃው ጋር ከአንድ ጊዜ በላይ መገናኘት ባለመቻሉና ዘመድ እንዲሁም የኃይማኖት አባት
እንዳይጎበኘው በመከልከሉ ነው፡፡
የሽዋስ አሰፋ በባለቤቱ ብቻ በሳምንት አንድ ቀን እንዲጎበኝ የተፈቀደለት ሲሆን የርሃብ አድማ ባደረገባቸው ቀናት ባለቤቱ  ምግብ ስታስገባ ለየሸዋስ ምግቡ እንደደረሰው ተደርጎ ባዶ
ሳህን ሲደርሳት መቆየቱን፣  ባለቤቱ የበዓል ቀን ልትጎበኘው በሄደችበት ወቅት ‹‹ወጥቷል›› ተብላ መመለሷን፣  በማግስቱ ልጆቹን ይዛ ልትጠይቅ ስትሄድም ‹‹ስብሰባ ላይ ናቸው!››
በሚል እንዳታገኘው በመደረጓ ለ15 ቀናት ሳትጠይቀው መቆየቷን ጋዜጣው ዘግቧል።
በሌላ በኩል ጠበቃው ተማም አባ ቡልጉ አቶ የሽዋስን ለማግኘት በተደጋጋሚ  ወደ ማዕከላዊ ቢያቀኑም ሳያገኙት እንደቀሩ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar