tirsdag 2. september 2014

ተማሪዎች ዘንድሮም ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በግዴታ እንዲከፍሉ ታዘዙ

መጪውን የትምህርት ዘመን ለመጀመር የሚያስችል ምዝገባ ለማካሄድ በትምህርት ቤቶች የተገኙ
ተማሪዎች ለአባይ ግድብ ገንዘብ የማያዋጡ ከሆነ እንደማይመዘገቡ ተገልጸላቸዋል።
ተማሪዎቹ በነፍስ ወከፍ 120 ብር የማይከፍሉ ከሆነ ምዝገባ እንደማያካሂዱ እንደተነገራቸው ለኢሳት እንደተነገራቸው ገልጸዋል።
ሁለት እና ከዚያ በላይ  ልጆች ያላቸው ወላጆች በቤተሰብ ደረጃ ሳይሆን በእያንዳንዱ ልጅ ስም የመክፈል ግዴታ ተጥሎባቸዋል።
አንዳንድ ተማሪዎች በእያመቱ ለአባይ ግድብ እየተባለ የምንከፍለው ክፍያ አግባብ አይደለም በማለት አስተያየታቸውን ለኢሳት ዘጋቢ ገልጸዋል።
መንግስት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ከህዝብ እስበስበዋለሁ ብሎ ያሰበው እቅዱ አልተሳካለትም። በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝና በአቶ በረከት ስምኦን
የሚመራው የገንዘብ አሰባሳቢ ኮሚቴም እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ አይታይም። በውጭ አገር ለግድቡ ማሰሪያ ይደረጉ የነበሩ ዝግጀቶችም በውጭ
አገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሚደርሰው ተቃውሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቆመዋል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar