fredag 12. september 2014

በሽብርተኝነት የተከሰሱት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ወደ ማዕከላዊ ተዛወሩ

በሽብርተኝነት ተከሰው አርባምንጭ ታስረው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞ ጎፋ ዞን አመራሮች ከነበሩበት የአርባ ምንጭ እስር ቤት አዲስ አበባ ወደሚገኘው የፌደራል ወንጀል ምርመራ መዘዋወራቸው ታወቀ፡፡
news
ከዞኑ አመራሮች መካከል የአርባ ምንጭ ምክትል ሰብሰቢ አቶ በፍቃዱ አበበ እና ደርጅት ጉዳይ ኃላፊው ኢንጅነር ጌታሁን በየነ ጱግሜ 5 ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ ወደ ማዕከላዊ የተዘዋወሩ ሲሆን ቀሪዎቹ አሁንም አርባምንጭ ውስጥ ታስረው ይገኛሉ፡፡
ወደ ማዕከላዊ የተዘዋዋሩትን የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞጎፋ አመራሮች ምግብና ልብስ ከማቀበል ውጭ መጠየቅ እንደማይቻል የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar