mandag 7. juli 2014

የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተላልፈው መሰጠታቸውን ተከትሎ ግንቦት 7 የክተት አዋጅ አወጀ

ድርጅቱ ፣ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓም ባወጣው መግለጫ ፣ “የየመን መንግሥት በህገወጥ መንገድ ያገተብንን የንቅናቀዓችንን አመራር በአስቸኳይ እንዲፈታ በተለያዩ መንገዶች ላለፈው አንድ ሣምንት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም ” ብሎአል።
“የአገሩን የረዥም ጊዜ ጥቅም ማየት የተሳነው የየመን መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ይልቅ አምባገኑን ወያኔ መርጦ መሪያችንን ለእርድ አሳልፎ ሰጥቶብናል ፣በዚህም ሳቢያ የየመን መንግሥት ይቅርታ የማያሰጥ ፤ ዘመን የማይሽረው ታሪካዊ ስህተት ፈጽሟል” ሲል ግንቦት 7 አስታውቋል።
” የኢትዮጵያ ሕዝብ ለወዳጅ ጎረቤት ትሁትና ቀና ቢሆንም ጥቃት በሚያደርስበት የቅርብም ሆነ የሩቅ ጎረቤት ላይ ግን ቁጣውን የሚመጥን የአፀፋ እርምጃ መውሰድ ያውቅበታል።” በማለት የሚዘረዝረው የግንቦት 7 መግለጫ፣ “የወያኔ ፋሽስቶች አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በማሰቃየት ትግላችንን ማቀዝቀዝ እንደማይችሉ ልናረጋግጥላቸው እንወዳለን ።”ብሎአል።
“ወያኔ ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በውንብድና ጠልፎ መውሰዱ የትግሉን ሜዳ አስፍቶታል ፤ የትግሉንም ዓይነት አብዝቶታል ። ይህ ደግሞ የወያኔ ፋሽስቶችን ከፍ ያለ ዋጋ ያስከፍላቸዋል ።” በማለት ድርጅቱ አጸፋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቋል።
“የፓለቲካ ልዩነት አጥር ሆኖ ሳይከልላችሁ ከገናችን ለቆማችሁት የሲቪክ ማኅበራትና ዜጎች ሁሉ በወገናዊ
ተግባራችሁ ልባችን ተነክቷ ልያለው ግንቦት 7 ፣ ከዚህ በላይ ደግሞ ለቀጣዩ ወሳኝ ፍልሚያም እንደምንቆም እና የወያኔን እድሜ እንደምናሳጥር እምነታችን አጠንክሮልናል” ሲል አክሎአል።
መግለጫው ” ከዛሬ ጀምሮ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንዳርጋቸውጽጌን ሆኗል” ካለ በሁዋላ፣በአቶ
አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ለደረሰውና ለሚደርሰው ጥቃት እያንዳንዱ የወያኔ ሹም በግል ዋጋ እንደሚከፍል ፣ ሕዝብ ለሚወስደው እርምጃ ተጠያቂው ራሱ ወያኔ መሆኑን እንዲሁም በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እስር የክተት አዋጅ መታወጁን በመጥቀስ” ህዝቡ ለጥሪው መልስ እንዲሰጥ ጠይቋል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar