tirsdag 8. juli 2014

የሰማያዊ ፓርቲው አቶ የሽዋስ አሰፋ በመኖሪያ ቤቱ ታገተ


ኢ.ኤም.ኤፍ) የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የአቶ የሽዋስ አሰፋ መኖሪያ ቤት በፖሊሶች ተከቦ ብርበራ እየተደረገበት መሆኑ ታወቀ። አቶ የሽዋስም በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ እንደታገቱ ናቸው። ዮናታን አያሌው ከስፍራው እንደገለጸው ከሆነ፤ የሽዋስ አሰፋ በቤቱ እንዳለ ብዛት ያላቸው የፌደራል ፖሊሶች አከባቢዉን በመክበብ ጎረቤቶቹን ካራቁ በኋላ እሱን ብቻውን ቤቱ ውስጥ በማፈን እስካሁን ድረስ ቤቱን እየበረበሩ መሆኑን ባለቤቱ አሳውቃለች፡፡
Yeshwas Assefaባለቤቱ ከስራ በጓረቤቶቻቸው ተደውሎላት ወደ ቤቷ ሄደች ቢሆንም ወደ አካባቢው እንዳትቀርብ ታዛለች፡፡ በአሁኑ ሰዓት አካባቢው ላይ በርካታ ፌደራል ፖሊሶችና ደህንነቶች ውጥረት አንግሰውበታል፡፡ 

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar