søndag 20. juli 2014

ልዕልት ሂሩት በ84 አመታቸው አረፉ

የልዕልት ተናኘወርቅ ኃይለስላሴ እና የራስ ደስታ ዳምጠው ልጅ የነበሩት ሂሩት ደስታ ዳምጠው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። የቤጌምድር አስተዳዳሪ የነበሩት ባለቤታቸው ጄነራል ነጋ ተገኝ የዛሬ አስር አመት በሞት የተለዩ ሲሆን፤ ልዕልት ሂሩት በደርግ ዘመን ከሌሎች ንጉሣዊ ቤተሰቦች ጋር ለ14 አመታት ከታሰሩ በኋላ እንደኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1980 ከእስር መፈታታቸው የሚታወስ ነው። ከ እስር ከተፈቱ በኋላ ነዋሪነታቸውን በለንደን አድርገው ይኖሩ የነበሩት ልዕልት ሂሩት ምንም ልጅ አልነበራቸውም።
ቀዳማዊ ኃይለስላሴ እ.አ.አ አሜሪካን ሲጎበኙ የልጅ ልጃቸው ልዕልት ሂሩትም አብረው መጥተው ነበር። ከጃኩሊን ኬኔዲ ጎን ቆመው የሚታዩት እኚሁ ልዕልት ሂሩት ናቸው።
ቀዳማዊ ኃይለስላሴ እ.አ.አ አሜሪካን ሲጎበኙ የልጅ ልጃቸው ልዕልት ሂሩትም አብረው መጥተው ነበር። ከጃኩሊን ኬኔዲ ጎን ቆመው የሚታዩት እኚሁ ልዕልት ሂሩት ናቸው።
በደርግ ዘመን ከተረሸኑት 60ዎቹ ሰዎች መካከል የልዕልት ሂሩት ወንድም እና የባህር ኃይል አዛዥ የነበረው እስክንድር ደስታ አንዱ እንደነበር ይታወሳል። የልዕልት ሂሩት የቀብር ስነ ስርአት ባለፈው ሳምንት በቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን፤ በተለይ ለንጉሣውያን ቤተሰቦች በተዘጋጀው ከቤተ ክርስቲያኑ ምድር ቤት በክብር አርፏል።

1 kommentar:

  1. ethiofeteh blogger, the same news has been published on EMF. You just deleted the word (ኢ.ኤም.ኤፍ) and posted as yours... this is plagiarism. And of course, it's shameless action. Check the original news on http://ethioforum.org/amharic/%E1%88%8D%E1%8B%95%E1%88%8D%E1%89%B5-%E1%88%82%E1%88%A9%E1%89%B5-%E1%89%A084-%E1%8A%A0%E1%88%98%E1%89%B3%E1%89%B8%E1%8B%8D-%E1%8A%A0%E1%88%A8%E1%8D%89/

    SvarSlett