onsdag 25. september 2013

ዜና ከአዲስ አበባ – 15 የሚሆኑ የአንድነት ፓርቲ አባለት ዛሬ ህገወጥ እስር ተፈፀመባቸው፤ የአራት ኪሎን ህዝብ እናመሰግናለን – ፍኖተ ነጻነት


አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ መስከረም 19 ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ የመኪና ላይ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ 15 አባላቱ ህገወጥ እስር ተፈፀመባቸው፡፡ አባላቱ ከስድስት ኪሎ ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው ጎዳና በመኪና ላይ እየቀሰቀሱ ባለበት ወቅት ሚኒሊክ ት/ቤት ፊትለፊት የፖሊስና የደህንነት ኃይሎች የሚተላለፈውን መኪና መንገድ በመዝጋት ቅስቀሳውን አደናቅፈዋል፡፡
በስፍራው የነበሩ በርካታ ሰዎች “ቀስቃሾቹ ህጋዊ ወረቀት ይዘዋል፤ልቀቋቸው” በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል ከአንድነት ፓርቲ ጎን እንደሚቆሙም ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ 15 የሚሆኑትን የቅስቀሳ ቡድን አባላት ወደ ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወስደዋቸዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች አባላቱ ወደ ታሰሩበት 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ረ/ኢ መንግስቱ ለማ የተባሉት

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar