fredag 6. september 2013

የአርበኞች ግንባር አባላት ናቸው የተባሉ ሰዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

በሰሜን ጎንደር ዞን ነዋሪ የሆኑት ጸጋው አለሙ፤ ዋስይሁን ንጉሱ፤ ጎዳዳው ፈረደ፤ ማማይ ታከለ እና ተገኝ ሲሳይ የተባሉት ሰዎች በኤርትራ ስልጠና ካገኙ በሁዋላ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ በትግራይ ክልል ማካይዳ ከተማ መያዛቸውን ፋና ዘግቧል።
ተከሳሾች  ኤርትራ እና አውሮፓ ከሚገኙ የአሸባሪው ድርጅት የተለያዩ አመራሮች ጋር ግንኙነት በመፍጠር አባላትን እየመለመሉ ወደ ኤርትራ መላካቸውን ገልጾ ፣ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት ተረኛ ችሎት ከጸረ ሽብር ህጉ አንጻር የዋስትና ጥያቄያቸውን ውድቅ በማድረግ ክሱን ለማሰማት ለጥቅምት 7 2006 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ዜጎች ከአርበኞች ግንባር፣ ከግንቦት 7፣ ኦነግና ኦብነግ ጋር በተያያዘ በቃሊቲና በሌሎችም እስር ቤቶች በመሰቃየት ላይ ይገኛሉ። መንግስት እነዚህን ድርጅቶች በአሸባሪነት መፈረጁ ይታወቃል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar