fredag 20. september 2013

የኢትዮጵያ አየር ሀይል መዳከሙን ካፒቴን አክሊሉ ተናገሩ




የኢትዮጵያ አየር ሃይል በመተው ሰሞኑን ግንቦት 7ትን  ከተቀላቀሉት አብራሪዎች እና የበረራ አስተማሪዎች መካከል የተዋጊ ሄሊኮፕተር ተዋጊና አዛዥ የሆኑት ካፒቴን አክሊሉ መዘነ ዛሬ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ በአንድ ወቅት በገናናነቱ የሚታወቀው የኢትዮጵያ አየር ሐይል አሁን ያለበት ደረጃ የሚያሳፍር መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ ሰፍኖ አየር ሀይሉ ተመልሶ የሚገነባበት ጊዜ እንደሚመጣ የገለጹት ካፒቴን አክሊሉ፣ እስከ ዛሬ አገራቸውን በጀግንነት ማገልገላቸውና አሁን ደግሞ ለህዝብ ለመስራት የነጻነት ታጋዮችን መቀላቀላቸውን ተናግረዋል።
“ወያኔዎችን እናውቃቸዋለን” በማለትም አሸንፈው እንደሚወጡ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar