tirsdag 3. september 2013

ላለፉት 2 አመታት ስርአቱን በሀይል ለመፈታተን ከሞከሩት ሁሉ የሀይማኖት እንቅስቃሴዎች ዋነኞቹ እንደነበሩ ኢህአዴግ አስታወቀ


ፓርቲው አዲስ ራእይ በሚባለው ልሳኑ ” ፣ በሀይማኖት ሽፋን የሚካሄዱ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች እየተዳከሙና እየተጋለጡ መሄዳቸው ባይቀርም ባለፉት ሁለት አመታት ልማታዊና ዲሞክራሲያዊ ስርአቱን በሐይል ለመፈታተን ከመከሩት የሁከት ሀይሎች ዋነኞቹ ነበሩ ማለት ይቻላል” ብሎአል።
ኢህአዴግ ከአክራሪዎች ጎን በመቆም አመጽ ለማነሳሳት ሞክረዋል ካላቸው ድርጅቶች መካከል ድምጻችን ይሰማ፣ ግንቦት 7 አሜሪካ ድምጽ ሬዲዮና ቢላል ሬዲዮ በዋናነት ተጠቅሰዋል።
በውስጡ ያሉ አንዳንድ የኢህአዴግ አመራሮችም እንዲሁ በሀማኖት ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ ችግሩን እያባባሱ በመሆኑ፣ እነዚሁ ባለስልጣናት የመንግስትን ስልጣን አስረክበው ወደ ሰባኪነታቸው እንዲያመሩ እንመክራለን ብሎአል።
መጽሄቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በክርስትና እና በእስልምና ሀይማኖቶች ውስጥ እየታየ ያለውን የአክራሪነት አዝማሚያና ይህን ተጠቅሞ የሚካሄደውን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለመግታት መንግስት በየትምህርት ተቋማት ትምህርቶችን መስጠት፣ ለወጣቶች ተገቢውን ስራ በመስጠትና አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደላበት ጠቁሟል።

ኢህአዴግ አሁን የሚታየው የሙ

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar