mandag 16. september 2013

ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ አስታወቀ

አዲስ ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ምንም እንኳ የአዲስ አበባ መስተዳደር ለሰልፉ  በ12 ሰአታት ውስጥ መልስ የመስጠት ሀላፊነት የነበረበት ቢሆንም ይህን አላዳረገም።  ፓርቲው የሚጠበቅበትን ሁሉ ለሚመለከተዉ አካል የማሳወቅ ግዴታ በአግባቡ ስለተወጣና ለሰልፉም የሚያስፈልጉ ስራዎች እየተከናወኑ በመሆኑ መስከረም 12 ቀን 2006 ዓ.ም በታቀደው መሰረት ሰልፉ ይካሄዳል ብሎአል፡፡
በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ የምናነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሲቪክ ማሕበራትና ዜጎች በአጠቃላይ በሰልፉ ላይ በመሳተፍ የዜግነት ድርሻቸውን እንዲወጡ ፓርቲ ጥሪውን አቅርቦ ፣ ሰላማዊ ሰልፉን በመቆጣጠርና የሕዝብን ሰላምና ፀጥታ የሚያውክን ሁኔታ በማስወገድ የሰላማዊ ሰልፈኞች መብቶችን ለመጠበቅ የፖሊስና የፀጥታ ኃይሎች የተሰጣቸውን ኃላፊነትና ተግባር በአግባቡ እንዲያከናውኑ ጠይቋል።
አንድነት ፓርቲ ለመስከረም 19 የተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱና ፈቃድ ማግኘቱ ይታወቃል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar