fredag 6. september 2013

ኢትዮጵያ ከሚሊዮን በላይ በልመና የሚተዳደሩ ሰዎች አሉ ተባለ

የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ኑሮ ጠንቆች ሲል ባስጠናው እና በዓመቱ መጠናቀቂያ በወርሐ ጳጉሜ ይፋ በሚያደርገው መረጃ እዳመለከተው የልመና ተዳዳሪነት በሐገሪቱ ላይ ጥቁር ጥላውን እያጠላበት ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ የቱሪስቶች የደህንነት ስጋት ከመሆን ባለፈ ለዜጎችም መትረፋቸውን ገልጿል።
በመገባደድ ላይ ባለው በ2005 ዓ.ም ብቻ በአማራ ክልል ከሶስት መቶ ሺ ፣ በትግራይ ከሁለት መቶ ሺ በላይ ዜጎች  በየቤተ ክርስቲያኑ እና በየቤተ እምነቱ ተጠልለው ሲለምኑ፤ ደቡብ እና ሐረሬም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ለማኞች ይገኛሉ። በአዲስ አበባም በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ለማኞች በከተማዋ እንደሚገኙ ይታወቃል።
በኢትዮጵያ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ሲኖሩ  8 ሚሊዮን የሚጠጉት ደግሞ በሴፍትኔት ወይም ምግብ ለስራ ታቅፈዋል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar