fredag 13. september 2013

ቻይና ለመለስ ፋውንዴሽን ማስገንቢያ ገንዘብ ለገሰች

የአቶ መለስን ፋውንዴሽን ለመገንባት መንግስትና የመለስ ፋውንዴሽን በጋራ በመንቀሳቀስ ላይ ባሉበት በዚህ ጊዜ፣ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ልኡካን ለፋውንዴሽኑ ግንባታ የሚውል 50 ሺ ዶላር ለመለገስ ቃል መግባቱዋን የልኡካን ቡድኑ መሪ ሚስተር ዛሆ ገልጸዋል።
አቶ መለስ በቻይናና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት እንዲጠናከር በማድረጋቸው  ልኢካኑ አመስግነዋቸዋል። ቻይና የኢትዮጵያን የአምስት አመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ እንደምትደግፍም እኚሁ ባለስልጣን ገልጸዋል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar