mandag 26. mai 2014

የኦሮሚያ ፖሊስ አስራት አብርሃን ሰወረ

የአራት ፓርቲዎች መድረክ የሆነው መድረክ ትናንት በአዲስ አበባ ላደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቀደም ብለው የቅስቀሳ ስራ ሲሰሩ የነበሩ አስራ ሁለት ሰዎች በቡራዩ ከተማ በፖሊስ መታሰራቸውን የሰሙት የአረና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ሐብታይ ገብረ ሩፋኤልና በቅርቡ አንድነት ፓርቲን የተቀላቀለው ደራሲና ፖለቲከኛ አስራት አብርሃ እስረኞቹን ሊጠይቁ በሄዱበት በወረዳው ከታሰሩ በኋላ ፖሊስ አቶ ሐብታይን ሲለቅ አቶ አስራትን በወረዳው አሳድሯቸው ነበር፡፡
Asrat Abraha
Asrat Abraha

ዛሬ ማለዳ አቶ አስራትንና የመድረክ አባላትን ለመጠየቅ ወደ ቡራዩ ያመሩት የአቶ አስራት ባለቤትና የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች አቶ አስራት በፖሊስ ጣብያው አለመታሰራቸው ተነግሯቸዋል፡፡አቶ ሐብታይ በስፍራው በመገኘት ‹‹አስራት ከእኔ ጋር ታስሮ ነበር››ቢሉም የኦሮሚያ ፖሊስ ‹‹የምትሉትን ሰው እኔ አላሰርኩትም›› የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
በቡራዩ ከተማ ሶስት ፖሊስ ጣብያዎች በመኖራቸው አስራትን ፍለጋ ወደ ፖሊስ ጣብያዎቹ ያመሩት የአንድነት አመራሮች ተመሳሳይ ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar