lørdag 3. mai 2014

ጋዜጠኛ ነብዩ ልዩ ምርመራ ተደረገበት

በካዛንቺስ አካባቢ የቅስቀሳ ስራ ይሰሩ የነበሩ አባላት የሚሰሩትን ለመዘገብ ከቀስቃሽ ቡድኑ ጋር የነበረው የፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ነብዩ ሐይሉ በታሰረበት የስድስተኛ ፖሊስ ጣብያ ከተያዘበትና በፍርድ ቤት ከቀረበበት ክስ ጋር በማይገናኝ ጉዳይ ሲቪል በለበሱ ደህንነቶች ምርመራ እንደተደረገበት ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡
የአዲስ አበባ መስተዳድር እውቅና ለሰጠው ሰላማዊ ሰልፍ የቅስቀሳ ስራ ለመስራት ወደ አራት ኪሎና ካዛንቺስ አቅንተው የነበሩት ሁለት የአንድነት አመራሮችና ጋዜጠኛ ነብዩ ሐይሉ ከትናንት ወዲያ ፍርድ ቤት ቀርበው የአስራ አንድ ቀን ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ወደ ፖሊስ ጣብያው እንዲመለሱ መደረጋቸው ይታወቃል፡፡
ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን በያዘበት ጉዳይ ምርመራ ማድረግ የሚችል ቢሆንም ነብዩን የመረመሩት ሲቪል ለባሾች ከክሱ ጋር ባልተያያዘ መንገድ‹‹ጋዜጠኛ መሆንህን እናውቃለን፡፡ከዞን ዘጠኝ አባላት ጋር ያላችሁን ግኑኝነትም ደርሰንበታል፡፡አዲሱ የጋዜጠኞች ማህበር ከውጪ ድርጅቶች ጋር እንደሚሰራ እናውቃለን››በማለት ማስፈራሪያ አዘል ምርመራ እንዳደረጉበት ምንጮቻችን አጋልጠዋል፡
10312367_628946547190283_7908140656346366611_n

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar