tirsdag 27. mai 2014

በሃረር ታስረው ክሚገኙት ነጋዴዎች መካከል የተወሰኑት ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

በቅርቡ በሃረር የደረሰውን የእሳት ቃጠሎ ተከትሎ ንብረታቸው የወደመባቸው  ነጋዴዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሳቸው ከሽብረተኝነት ወደ ባንዲራ ማቃጠል፣ ንብረት ማውደም እና አመጽ ማስነሳት መለወጡ ተነግሯቸዋል።
ከእሰረኞቹ መካከል 2ቱ በመታወቂያ ዋስ እንዲፈቱ ሲደረጉ፣ 20 ዎቹ እስረኞች ደግሞ ባንዲራ አውርዶ በማቃጠል፣ 500 ሰዎችን አስተባብረው አመጽ በማስነሳት፣ የመንግስትን ስራ በማስተጓጎልና የግለሰብና የመንግስት ንብረት በማውደም ክስ ቀርቦባቸዋል። የእያንዳንዱ ክስ የቅጣት ጣራ ከ15 አመታት በላይ የሚያሳስር በመሆኑ እስረኞቹ የዋስ መብት እንደሌላቸውና ጉዳያቸውን በእስር ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ውስኗል።
በዛሬው ፍርድ ቢኒያም ጌታቸው፣ ለይላ አሊ አህመድና ዙቤር አህመድ የተባሉት የክስ ቻርጅ የደረሰቻው ሲሆን ሌሎች 17ቱ ግን የክሱ ዝርዝር አልደረሳቸውም። ለይላ አህመድ የተባለችው ነጋዴ በእስር ቤት ማህጸኗ ላይ ባደረሱባት ድብደባ በህመም እየተሰቃየች እንደምትገኝ መዘገባችን ይታወሳል።
ቢኒያም ጌታቸው የተባለው ወጣት ደግሞ የኮምፒዩተር ጥገና ባለሙያ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም የሃረር ፖሊስ ጽህፈት ቤትን ኮምፒይተሮች በመጠገን፣ ያልተከፈለው 12 ሺ ብር እንዳለና ምናልባትም የእስሩ ምክንያት ከዚሁ ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል። ቢኒያምን በምንም አይነት ወንጀል መጠርጠር እንደማይችል የሚናገሩት ጉዳዩን የሚከታተሉ ምንጮች፣ ፖሊስ ኮሚሽን የራሱን ችግር ለመሸፋፈን ሲል እንዳሰረው አስተያየት ይሰጣሉ።
ድብደባ የተፈጸመባትና ዋስትና የተከለከለችው ለይላ ደግሞ  የመንግስትን ባለስልጣናት “እናንተ ናችሁ ቃጠሎውን ያስነሳችሁት ፣ ሌቦች” ብላ በመሳደቡዋ መታሰሩዋን ምንጮች ገልጸዋል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar