mandag 6. oktober 2014

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር አንድ ባለስልጣን መግደሉን አስታወቀ

ግንባሩ ለኢሳት በላከው መግለጫ  ማክሰኞ መስከረም 22 ቀን 2007 ዓ/ም በመተማ ወረዳ  ገንዳ-ውሃ ከተማ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ  በወሰደው እርምጃ የወረዳው ፖሊስ ኢንስፔክተር ዮሃንስ ይግዛው ሲገደል፣
ኮንስታብል ሻንበል አበበ በጥይት ተመቶ ክፉኛ ቆስሏል ብሎአል። ህዝብን እየበደሉ ባሉ የስርዓቱ ታጣቂዎች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወስድ ግንባሩ አስጠንቅቋል። ኢሳት የመተማ ገንዳውሃ ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።
አርበኞች ግንባር በቅርቡ በሰሜን ጎንደር አካባቢዎች ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እየሰነዘረ ነው።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar