lørdag 11. oktober 2014

በአፋር ክልል ለትምህርት ወደ ውጭ አገር ሊሄዱ የነበሩ ተማሪዎች ከጉዞ ታገዱ

አኩ ኢብን ከአፋር  እንደዘገበው ወደ ተለያዩ የአውሮፓ ማለትም ወደ ስዊድን፣ ጀርመን፣ ቤልጂየም የመሳሰሉ አገራት ለትምህርት ሊሄዱ ተዘጋጅተው የነበሩ ተማሪዎች ባልጠበቁት ምክንያት እንዲቀሩ ታዘዋል።
news
የአፋር ክልልን እየመራ ያለው የአብዴፓ ፓርቲ እነዚህ ወጣት ምሁራን እንዳይሄዱ የከለከለበት ምክንያት «”ወደ አውሮፓ ከወጡ በዛው ይቀሩብኛል” የሚል ፍራቻ ሳይሆን አይቀርም» የሚሉ ብዙ አስተያየት ሰጭዎች አሉ። እነዚህ ተማሪዎችን ከትምህርት ያስቀሩት ወይም እንዳይሄዱ ያዘዙት የአብዴፓ ፓርቲ አባል የሆኑት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አቶ አሚን አብዱልቃድር መሆናቸውም ተሰምቷል።
የሕወሓት አባላት የሆኑ ተማሪዎች በስኮላርሺፕ የትም ሃገር ለመሄድ እንደማይከለከሉ የማይከለከሉ ከመሆኑም በላይ የውጭ እድል እንደሚመቻችላቸው የሚገልጹ አስተያየት ሰጪዎች የአፋር ክልል ይህን ማድረጉ አስገርሟቸዋል። ይልቁንም በነዚህ ተማሪዎች ስም ሌሎች እንዳይሄዱበት ስጋት እንዳላቸው አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።                                                                                                                                                                                                                                                              

ተዛማጅ ፅሁፎች::

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar