tirsdag 13. august 2013

በአማራ ክልል የመልካም አስተዳደር ችግር ስር የሰደደ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ተናገሩ

የመልካም አስተዳደር ኮማንድ ፖስት እየተባለ የሚጠራው መስሪያ ቤት በክልሉ ባሉ የአስተዳደር ቢሮዎች ባካሄደው ቅኝት የመልካም  አስተደዳር ችግር በክልሉ ተባብሶ መቀጠሉን ገልጿል፡፡
በተለይም በፍትህ ፤ በፖሊስ ፤ በማረሚያ ቤቶች ፤ በመሬት ፤ኢንቨስትመንት፤ መብራት እና ውሃ ደግሞ የችግሩ መለያ ቦታዎች መሆናቸውን ለክልሉ ካቢኔ የቀረበው ሪፖርት የቅሬታ ምንጭ መሆናቸውን ያወሳል፡፡
በክልሉም ከጊዜ ወደ ጊዜ የቅሬታዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የሚያወሱት የኮማንድ ፖስት መሪው አቶ አምባቸው ከ115 ሺ በላይ ቅሬታዎች በመልካም አስተዳደር ዙሪያ በዚህ አመት ቀርበዋል፡፡እነዚህ ቅሬታዎች እድል አግኝተው ከክልሉ ርዕሰ መዲና ባህርዳር የደረሱ ናቸው፡፡ በመሬት ዙሪያ ደግሞ ከ 46 ሺ የአካባቢ ጥበቃ መስሪያ ቤቶች ከ 60ሺ በላይ ቅሬታዎች ተሰተናግድዋል፡፡
የመናሃሪያና የፍትህ አካላት፤የትራንስፖርት ችግር የህገወጥ መሳሪያዎች ዝውውር መበራከት ባለበት እንደቀጠለ ነው፡፡
ያለው ኮማንድ ፖስት በፌደራል ወይም በማእከላዊ መንግስት የሚተዳደሩ ተቋማት የችግሩ መንስኤ መሆናቸውን የክልሉ ኮሚንኒኬሺን ጉዳይ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ይናገራሉ፡፡
የከልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ በበኩላቸው ባለፈው ስድስት ወራት መልካም አሰተዳደርን ለማስፈን የተደረገው ጥረት ውጤት አልባ ሆኗል ብለዋል፡፡
ከክልሉ ዜና ሳንወጣ በህዳር ወር 2005 ዓ.ም በባህርዳር ከተዘጋጀው 7ኛው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ጋር በተያያዘ የተሠራችው “ህብር” የተሠኘች ጀልባ በቴክኒክ ችግር ምክንያት አገልግሎት መስጠት አለመቻሏ ተገለጸ፡፡
ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ወጥቶባት በእርግብ ቅርጽ የተሰራችው እና እስካሁን ካሉት ጀልባዎች በውስጣዊ ይዘቷ ትለያለች የተባለችው ይህቺው ጀልባ ህዳር 29 በጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ከተመረቀች በኃላ በቴክኒክ ችግር ምክንያት አገልግሎት መስጠት ባለመቻሏ ያለስራ ለመቆም መገደድዋን ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
የጣና ሐይቅ ትራንስፖርት ድርጅት የመከላከያ ንብረት ከሆነው ከብረታብረት ኢንጂነሪንግ ድርጅት እና ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የክልሉ መንግስት በመደበው ገንዘብ የሠራት ህብር የተሰነችው ይህቺ ጀልባ የቴክኒክ ችግሯ መቀረፍ ባለመቻሉ ምክንያት እዚያው በቆመችበት የስብሰባ አዳራሹን ወደሲኒማ ቤት ለመቀየር ሃሳብ መኖሩ ታውቋል፡፡
በዘመነ ደርግ የተሰራችው ንጋት በመባል የምትታወቀው ጀልባ በሆላንድ ባለሙያዎች ጭምር አሰራርዋ አድናቆት ያገኘና እስካሁንም አገልግሎት እየሰጠች ነው፡፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar