torsdag 1. august 2013

ከ2 ቢሊዩን ብር በላይ በሆነ ወጭ የተገነቡ የውሃ ተቌማት ላይ ጉዳት ደረሰ

በአማራ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ዞንና ወረዳዎች በበጎ አድራጊዎች ድጋፍና በህብረተሰቡ የተገነቡ ከ110 በላይ  የውሃ ተቌማት ላይ የእጅ ፓምፕ ዝርፊያ በመፈጸሙ በውሀ አቅርቦቱ ላይ ችግር ተፈጥሯል።
ዝርፊያውን ተከትሎ የወረዳ አመራሮች ለህዝቡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ናቸው እያሉ ፤ ፓርቲዎችን የማሰጠላት ዘመቻ እያከናወኑ ነው፡፡
በተለያዩ  አካባቢዎች እየተከሰተ ባለው የውሃ ተቋማት ዝርፊያ እስካሁን ወደ 250 የሚጠጉ ሰዎች  ከ2 ወር እስከ 12 ዓመት በእስራት እንዲቀጡ ተደርጓል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ በደቡብና ሰሜን ጎንደር ፤ደቡብና ሰሜን ወሎ የእጅ ውሃ ማውጫ ፓምፖች ተሰርቀው ከጥቅም ውጭ ሁነዋል፡፡
የጉዳቱን መጠንና ችግሩን በተመለከተ የክልሉ ውሃ ሃብት ቢሮው ይፋ ያላወጣው ሪፖርት እንደሚያመለክተው የችግሩ መጠን መባባሱን ያሳያል፡፡ በዚህ ሂደት ተሳታፊ ናቸው የተባሉ ወገኖች ላይ እርምጃ ለመውሰድ የተሞከረ ቢሆንም እስካሁን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ማዋል አልተቻለም፡፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar