tirsdag 13. august 2013

ኦህዴድ ኢሳትን ለማስቆም እንደሚሰራ አስታወቀ

ሰሞኑን የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በነቀምት ባደረጉት ስብሰባ ህዝቡ ኢሳትን እንዳይመለከት ካድሬዎች ከፍተኛ ስራ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
አመራሮቹ ኢሳት የአሸባሪ ድርጅቶች ንብረት በመሆኑ፣ ህብረተሰቡ ኢሳትን መመልከቱን እንዲያቆም ባለስልጣኖቹ ወትውተዋል።
በስብሰባው ወቅት ለካድሬዎች ከተነገራቸው ነገር መካከል አንዱ ኢሳትን በሚመለከት ህግ ሊወጣ ነው መባሉ ነው። ምን አይነት ህግ እንደሚወጣ ግን ባለስልጣኖቹ ከማብራራት ተቆጥበዋል።
ኢሳት በናይልሳት የሚያሰራጨው ስርጭቱ በአፈና እንዲቋረጥ ከተደረገ በሁዋላ ላለፉት 7ወራት  በኤስ ኢ ኤስ 5 እና በአሞስ ላይ የቴሌቪዥን ስርጭቱን እንዲሁም በተለያዩ የሬዲዮ ሞገዶች የኢትዮጰን ህዝብ እያገለገለ ይገኛል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar