fredag 23. august 2013

በአማራ ክልል በአንድ ሰምንት ጊዜ ውስጥ በጎርፍ ከ45 ሰዎች በላይ ሞቱ


 በአካባቢው በሚጥለው ከባድ ዝናም የተነሳ በክልሉ በሚገኘው ኦሮሚያ ዞን ባለፈው ሳምንት ከ30 ያላነሱ ሰዎች የተገደሉበትን ክስተት ጨምሮ ፣ በደቡብ ወሎ ዞን በአንባሰል ወረዳ አንዲት ሚኒ ባስ በጎርፍ በመወሰዷ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል። በጎርፍ የተወሰዱ ሰዎችን አስከሬን ለማግኘት በተደረገ ጥረት የ14 ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል። የአካባቢውን ፖሊስ አዛዥ ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።
በክልሉ እየጣለ ያለው ሀይለኛ ዝናብ ከፍተኛ ጉዳት እያመጣ መሆኑን ከክልሉ የሚደረሱን ዘገባዎች ያመለክታሉ። በአንዳንድ አካባቢዎች ትራንስፎርመሮች በመቃጠላቸው መብራት ለሳምንታት መቋረጡም ታውቋል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar