onsdag 20. februar 2013

ጄነራል ሳሞራ የኑስ በ80 ሚሊዮን ብር ህንጻ አሰርተው እያከራዩ ነው

Samora house 1Samora house 4ኢታማጆር ሹሙ ጄኔራል ሳሞራ የኑስ በቄራ መብራት ሀይል አካባቢ በ80 ሚሊዮን ብር ዘመናዊ ህንጻ ማሰራታቸውን በፎቶ ግራፍ አስደግፈው ውስጥ አዋቂዎች ለኢሳት ላኩት መረጃ ያመለክታል።
የጄኔራል ሳሞራ ህንጻ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክን ጨምሮ ሌሎች ድርጅቶችም መከራየታቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
ጄኔራል ሳሞራ መከላከያ ሚኒስቴር በወር 10 ሺ ዶላር የሚከፍልበት በልዩ የደህንነት መሳሪያዎች በየሚጠበቅ መኖሪያ ቤት ውስጥ ይኖራሉ። አብዛኞቹ የህወሀት ጄኔራሎች በቦሌ ክፍለ ከተማ የሚያሰሩዋቸውን ህንጻዎች በፎቶግራፍ በማስደገፍ መዘገባችን ይታወሳል።
ጄኔራል ሳሞራ በፎቶ ግራፍ ከሚታየው ህንጻዎች በተጨማሪ ሌሎች ህንጻዎች እንዳሉዋቸውም ለማወቅ ተችሎአል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar